4.
ኢየሱስ ክርስቶስ ይረዳችኋል
መዝሙር 147፥3
ኢየሱስ ክርስቶስ ጉልበታችሁ ነው። በዚህ ህይወት እና ለዘለአለም ደስታ እንዲኖራችሁ አስፈላጊውን ሁሉ አድርጓል። እርሱን እና ወንጌሉን በመምረጥ፣ ዘላለማዊ ደስታን እየመረጡ ነው።
ጥሩ ምርጫ ለማድረግ የተቻላችሁን ለማድረግ ስትሞክሩ እንኳን፣ አንዳንድ ጊዜ ስህተትን ትሰራላችሁ። ባላደረኩት ብላችሁ የምትመኙትን ነገር ልታደርጉ ትችላላችሁ። ሁሉም ሰው እንዲህ ሊያደርግ ይችላል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ፣ ተስፋ መቁረጥ ወይም መቼም በቂ ዕልሆንም ብሎ ማሰብ ቀላል ነው። ነገር ግን መልካም ዜና አለ—አስደናቂ እና ተስፋ ሰጪ ዜና! እግዚአብሔር ስለሚወዳችሁ፣ ንስሐ እንድትገቡ፣ ይቅር እንድትባሉ እና እድገታችሁን እንድትቀጥሉ ኃጢአታችሁን በራሱ ላይ የወሰደውን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኳል።
ዘለአለማዊ እውነቶች
ኢየሱስ ክርስቶስ ያበረታችኋል። ፍላጎታችሁን፣ ሃሳባችሁን እና ተግባራችሁን እንድትቀይሩ ሊረዳችሁ ይችላል። ስትጨነቁ፣ ስትፈሩ ወይም በማንኛውም መንገድ ስትቸገሩ እርሱ ያጽናናችኋል። በሁሉም የሕይወታችሁ ዘርፍ ይረዳችኋል። በእርሱ ላይ እምነትን መጣል ትችላላችሁ።
ንስሐ መግባት የኃጢአት ቅጣት አይደለም፤ አዳኙ እኛን ከኃጢአት ነፃ የሚያወጣበት መንገድ ነው። ንሰሃ መግባት ማለት መለወጥ ማለት ነው—ከሃጥያት መራቅ እና ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። መሻሻል እና ይቅርታን ማግኘት ማለት ነው። የዚህ አይነት ለውጥ የአንድ ጊዜ ክስተት አይደለም፤ ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው።
ግብዣዎች
ኢየሱስ ክርስቶስን የህይወታችሁ ትኩረት አድርጉ፡፡ በምታደርጉት ነገር ሁሉ እርዳታውን ፈልጉ።
ንስሀ ግቡ። ለመሻሻል ባለ ፍላጎት ወደ ጌታ ተመለሱ። የሆነ ስህተት ከሰራችሁ በሐቀኝነት በእግዚአብሔር ፊት እና እንደ አስፈላጊነቱ ለኤጲስ ቆጶሳችሁ እና ለጎዳችሁት ማንኛውም ሰው ስህተታችሁን አሳውቁ። ነገሮችን ለማስተካከል የተቻላችሁን አድርጉ።
ይበልጥ የተሻለ ለማድረግ እና ለመሆን በተሰጠው ስጦታ ተደሰቱ። ቀላል ባይሆንም እና ከምትፈልጉት በላይ ረዘም ያለ ጊዜ በሚወስድበት ጊዜም እንኳ መሞከራችሁን አታቋርጡ። መሥራታችሁን እና በጌታ መታመናችሁን ቀጥሉ። እርሱ በእያንዳንዱ መንገዳችሁ ይረዳችኋል።
ቃል የተገቡ በረከቶች
የሰማይ አባት ንስሐ ስትገቡ ይቅር ይላችኋል እንዲሁም ይፈውሳችኋል። የጥፋተኝነት ስሜታችሁን በሰላምና በደስታ ይተካል። ኃጢአታችሁንም ከእንግዲህ ወዲህ አያስብም። ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይላችሁ ነው፤ በኃይሉም ትእዛዛቱን የመጠበቅ ፍላጎታችሁን ይጨምራል።
እርሱም ህይወታችሁን እና ልባችሁን ይቀይራል። ቀስ በቀስ፣ ታድጋላችሁ እንዲሁም እንደእርሱ መሆን ትጀምራላችሁ።
ጥያቄዎች እና መልሶች
እግዚአብሔር ይቅር እንዳለኝ እንዴት አውቃለሁ? እግዚአብሔር ንስሐ የገቡትን ይቅር እንደሚላቸው ቃል ገብቷል። የመንፈስ ቅዱስ ማጽናናት ሲሰማችሁ የአዳኙ የሃጢያት ክፍያ ሃይል በህይወታችሁ እየሰራ እንደሆነ ማወቅ ትችላላችሁ።
ንስሃ ለመግባት የኤጲስ ቆጶስ እርዳታ የሚያስፈልገኝ መቼ ነው? ንስሐ እንድትገቡ ለመርዳት ኤጲስ ቆጶስ የክህነት ቁልፎችን እና መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይዟል። በማንኛውም ጊዜ የእርሱን እርዳታ እና ምክር መጠየቅ ትችላላችሁ። ለምሳሌ የንፅህና ህግን መጣስን የመሰሉ ከባድ ስህተቶችን ሰርታችሁ ከሆነ፣ከኤጲስ ቆጶሳችሁ ጋር ተገናኙ። እሱ አይኮንናችሁም። የኢየሱስ ክርስቶስ ተወካይ ስለሆነ እንዴት ሙሉ በሙሉ ንስሀ መግባት እና የአዳኙን የፈውስ እና የብርታት ሀይልን እንዴት መቀበል እንደምትችሉ ለማወቅ ይረዳችኋል።
ንስሀ ለመግባት እየሞከርኩ ነው፣ ነገር ግን ተመሳሳይ ስህተቶችን እሰራለሁ። ምን ማድረግ ይገባኛል? ተስፋ አትቁረጡ። ወደ ክርስቶስ ተመለሱ፣ እና በእርሱ ላይ እምነትዎን ያድርጉ። ጸጋው በቂ ነው። በድጋሚ ሞክሩ። ለማደግ በምታደርጉት ጥረት ውስጥ ብቻችሁን አይደላችሁም። ኢየሱስ ክርስቶስ ሁልጊዜም ከእናንተ ጋር ነው።
ሄኖስ 1፥6 (ጥፋተኝነት ሊወገድ ይችላል)፤ ሞዛያ 4፥3 (በመንፈስ ቅዱስ በኩል፣ እግዚአብሔር ይቅር እንዳላችሁ ያሳውቃችኋል)፤ 26፥30 (ንስሐ በገባን ቁጥር አዳኙ ይቅር ይላል)፤ ኤተር 12፥27 (የአዳኙ ጸጋ ደካማ ነገሮችን ሊያጠናክር ይችላል)፤ ሞሮኒ 6፥8 (ንስሃ የገቡ ይቅር ተባሉ)፤ 10፥32 (በክርስቶስ ፍጹማን ሁኑ)፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥32 (ጌታ ንስሐ የገቡትን ይቅር ይላል)፤ 58፥42–43 (ንስሐ ኃጢአትን መናዘዝንና መተውን ይጨምራል) ተመልከቱ።
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ጥያቄዎች
-
ስለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና እንደ አዳኝ እና ቤዛነት ስላለው ሚና ምስክርነት አለህ/አለሽ?
-
እንደ ንስሐ አካል በመሆን የክህነት ሥልጣን ባላቸው ሊፈቱ የሚገባቸው ከባድ ኃጥያቶች በህይወትህ/ሽ ውስጥ አሉ?