ወጣቶች
1 የእግዚአብሔር እቅድ ለእናንተ ነው


ክርስቶስ በሜዳ ውስጥ እየተራመደ

1

የእግዚአብሔር እቅድ ለእናንተ ነው

አልማ 22፥13

ወደ ምድር ከመምጣታችሁ በፊት ከሰማይ ወላጆቻችሁ ጋር ትኖሩ ነበር። እናንተ የምትወደዱ ልጆች ናችሁ። በሰማይ እያላችሁ ስለ እግዚአብሔር ቤተሰብ ዕቅድ ተማራችሁ። ይህን እቅድ በደስታ ተቀብላቹሃል ምክንያቱም ሥጋዊ አካልን በመቀበል፣ የምድራዊ ቤተሰብ አካል በመሆን እና በምድር ላይ ህይወትን በመለማመድ እንደ እግዚአብሔር እንድትመስሉ ስለሚረዳችሁ ነው። ከእነዚህ ልምዶች ውስጥ አንዳንዶቹ አስቸጋሪ ይሆናሉ። አባታችን ይህንን ያውቅ ነበር፣ ስለዚህ እንደ እቅዱ አካል አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲረዳችሁ ላከ። ይህንን የመዳን እቅድ ወይም የደስታ እቅድ ብለን እንጠራዋለን።

ዘለአለማዊ እውነቶች

የሰማይ አባት የዕቅዱ ደራሲ ነው። እርሱ የመንፈሳችሁ አባት ነው፤ እርሱም ይወዳችኋል። ትልቁን በረከቱን ሊሰጣችሁ ይፈልጋል— ከእርሱ ጋር የዘላለም ሕይወት። በሌላ አነጋገር፣ እርሱን እንድትመስሉ እና እርሱ የሚኖረውን አስደሳች፣ የከበረ ህይወት እንድትኖሩ ይፈልጋል። እርሱ ሁሉን ቻይ እናም ሁሉንም ነገር ዐዋቂ ነው። ሕይወት ከባድ ቢሆንም እንኳ በእርሱ ላይ እምነት መጣል ትችላላችሁ።

ኢየሱስ ክርስቶስ እቅዱን ተግባራዊ አድርጎታል። ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የሰማይ አባት አዳኛችሁ እንዲሆን መረጠው። በሰማያት ወዳለው አባታችሁ ሊመልሳችሁ የሚችለው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ለዚህም ነው እርሱን ለመከተል የመረጥነው። ሁሉም ነገር በዚያ ምርጫ ላይ የተመሰረተ ነው!

ጋብቻ እና ቤተሰብ ለእግዚአብሔር ዕቅድ አስፈላጊ ናቸው። እናንተ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካል ናችሁ፣ እና ሁሉም መንፈሳዊ ልጆቹ በእናትና በአባት በኩል ወደ ምድር ይመጣሉ። እግዚአብሔር ሴቶች ልጆቹና ወንዶች ልጆቹ አብረው ወደ ዘላለማዊ ፍጹምነት እንዲያድጉ ይፈልጋል። ወንዶችና ሴቶች እያንዳንዳቸው ለፍቅር እና ለአንድነት ጋብቻ እኩል አስተዋፅዖ ያደርጋሉ። እዚህ በምድር ላይ ያለው የቤተሰብ ሕይወት—ምንም እንኳን ጉድለቶቹ ቢኖሩም—ታላቅ ደስታን ሊያመጣ ይችላል። ከእግዚአብሔር ጋር የዘላለም ሕይወትን ለመኖር ለመዘጋጀት እንዲረዳችሁ የታሰበ ነው።

ግብዣዎች

ዘለአለማዊ እይታ ይኑራችሁ። ፈተናዎች፣ ችግሮች፣ ተስፋ መቁረጥ ወይም አስቸጋሪ ምርጫዎች ባጋጠማቹ ቁጥር የእግዚአብሔርን እቅድ አስታውሱ። . ስለ እቅዱ የምታውቁትን ዘላለማዊ እውነቶች ተግዳሮታችሁን በተለየ መንገድ እንድትመለከቱ እንዴት እንደሚረዳችሁ ተመልከቱ። .

በሕይወታችሁ ውስጥ የእግዚአብሔርን እጅ ፈልጉ። እግዚአብሔር የሚባርካችሁን መንገዶች አስተውሉ። . የአንድ ሰው ደግነት ድርጊት፣ የሰላም ጊዜ ወይም የጸሎት መልስ ሊሆን ይችላል። .

የእግዚአብሔርን ዕቅድ ለመከተል ምረጥ። የሰማይ አባታችሁ እንድታደርጉ የሚፈልገውን ነገር ተማሩ። ቅዱሳት መጻሕፍትን፣ የሕያዋን ነቢያትን ቃላት፣ የቤተሰብ አዋጅ እና የፓትሪያርክ በረከታችሁን ስታጠኑ መመሪያውን ፈልጉ። ይህ እንደ ሚስዮናዊ እና ሕይወታችሁን በሙሉ ጌታን ለማገልገል እንድዘጋጁ ይረዳቹሃል። ጌታን ማገልገል፣ ዘላለማዊ ጋብቻና ልጆችን ማሳደግ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር እድርጉ። የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርቶች በመከተል ደስተኛ ቤተሰብ እንዲኖራችሁ የበኩላችሁን አድርጉ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሣር ባለበት ሜዳ ላይ እየተራመደ ብርሃን ከእርሱ ላይ እየበራ

ቃል የተገቡ በረከቶች

በክርስቶስ በድፍረት እና በተስፋ የሕይወትን ፈተናዎች መጋፈጥ ትችላላችሁ። ስለ እግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ስለምታውቁ በአስቸጋሪ ጊዜያት ሊረዳችሁ የሚችል ጠቃሚ መሳሪያ አላችሁ። በልደት እና በሞት መካከል ከሚሆነው በላይ በሕይወት ውስጥ ብዙ ነገር እንዳለ ታውቃላችሁ ። ማን እንደሆናችሁ፣ አላማችሁ ምን እንደሆነ እና በአዳኙ እርዳታ ማን መሆን እንደምትችሉ ታውቃላችሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ጉልበታችሁ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስን ስትከተሉ የዘላለምን ሕይወት ማግኘት ትችላላችሁ። እርሱን እንድትመስሉ፣ ወደ ሰማያዊ ወላጆቻችሁ እንድትመለሱ እና ከምትወዷቸው ሰዎች ጋር ለዘላለም በደስታ እንድትኖሩ ኃይል ይሰጣቹሃል። በኢየሱስ ክርስቶስም እመኑ።

ጥያቄዎች እና መልሶች

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት በጣም ከባድ የሚሆነው ለምንድነው? ጥንካሬን እንዴት ማግኘት እችላለሁ? በዚህ ህይወት ውስጥ ያላችሁ ልምዶች—በጣም አስቸጋሪዎቹም እካን ቢሆኑ—ለእናንተ ጥቅም ሊሆኑ ይችላሉ። ወደ አዳኙ ስትዞሩ እንድታድጉ እና እድገትን እንድታሳዩ ሊረዱችሁ ይችላሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢያት ክፍያ መሥዋዕቱ ምክንያት ያልተረዳው የሚያጋጥማችሁ ምንም ነገር የለም። እንዴት እንደሚረዳችሁ በትክክል ያውቃል። ሕይወታችሁን በእርሱ ላይ አተኩሩ እርሱም ከፍርሃትና ከጥርጣሬ ሁሉ በላይ ያነሣቹሃል።

አንዳንድ ጊዜ በቤተሰብ እና በትዳር ውስጥ የደስታ ሀሳብ በጣም ሩቅ ይመስላል። በራስ መተማመንን እንዴት ማግኘት እችላለሁ? ሁኔታችሁ ምንም ይሁን ምን፣ በሰማይ አባት እቅድ ተስፋ አትቁረጡ። እርሱ በእናንተ ተስፋ አይቆርጥም። ለአዳኝና ለቃል ኪዳኖቻችሁ ታማኝ ከሆናችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ውስጥ መልስ ታገኛላችሁ። ያጋጠማችሁን ሁሉ ይረዳል። በእርሱ አማካኝነት የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመታዘዝ እና እርሱ የገባውን ቃል ኪዳን ለመቀበል ብርታት ታገኛላችሁ። በእርሱ እና በወንጌሉ እመኑ።

2 ኔፊ 9፥13 (የአምላካችን እቅድ ምንኛ ታላቅ ነው!)፤ ሞዛያ 2፥41 (ትእዛዛቱን የሚጠብቁ ማለቂያ በሌለው ደስታ ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖሩ ይችላሉ)፤ አልማ 12፥28–34 (እግዚአብሔር የመቤዠት እቅድን ለልጆቹ አሳወቀ)፤ አብርሃም 3፥22–26 (የእግዚአብሔር እቅድ ትእዛዛቱን እንድንከተል ለራሳችን የምንመርጥበት ወደ ምድር መላክን ያካትታል) ተመልከቱ።

የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ወረቀት ለማግኘት የሚጠየቅ ጥያቄ

  • በዘለአለም አባት እግዚአብሔር፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ እምነት እና ምስክርነት አለህ/አለሽ?