የቀዳሚ አመራር መልዕክት
ውድ ወጣት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን
እንወዳችኋለን፣ እንዲሁም በእናንተ እንተማመናለን። እናንተ በእውነት በዚህ ጊዜ አስፈላጊ ነገሮችን ለማድረግ ወደ ምድር ከተላኩ የሰማይ አባት ምርጥ መንፈሶች መካከል ናችሁ።
ከምታስቡት በላይ ጠንካራና የበለጠ ችሎታ አላችሁ። በአዳኙ በምትተማመኑበት ጊዜም ጉልበታችሁ እየጨመረ ይሄዳል። እርሱ “የወጣቶች ጥንካሬ” ነው።
ይህ መመሪያ ወደ ዘላለም ሕይወት በሚወስደው መንገድ ላይ ለመቆየት ምርጫ ለማድረግ ጠንካራ መሠረት እንድትጥሉ ያግዛችኋል። ይህም በቤተመቅደስ ውስጥ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ለመግባት ለማዘጋጀት፣ ምስዮን ለማገልገል ለመዘጋጀት እና ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተል በህይወታችሁ ሁሉ ደስታን ለማግኘት ይረዳችኋል። በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ አላችሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ዓላማውን እንድታሳኩ ይረዳችኋል
እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ እናውቃለን። ከእግዚአብሔር ጋር የተቀደሰ ቃል ኪዳኖችን በማድረግ እና በመጠበቅ መንገድ ላይ በፅናት እንድትቆዩ ጸሎታችን ነው። በሰማያት ወዳለው አባታችሁ የሚወስደው መንገድ ይህ ነው። ይህን በምታደርጉበት ጊዜ፣ ወንጌልን በደስታ በማካፈል፣ የእግዚአብሔርን ልጆች በመሰብሰብ እና ዓለምን ለአዳኙ ዳግም ምጽአት በማዘጋጀት በጎ ተጽእኖ ታሳድራላችሁ። አስታውሱ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ጉልበታችሁ ነው!
ቀዳሚ አመራር