ኑ፣ ተከተሉኝ
ነሐሴ 24–30(እ.አ.አ)። “ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ”፦ መዝሙረ ዳዊት 49፥51፤ 61–66፤ 69–72፤ 77–78፤ 85–86


“ነሐሴ 24–30(እ.አ.አ) ‘ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ’፦ መዝሙረ ዳዊት 49-51፤ 61፤ 69-72፤ -78፤ 85 ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026 እ.አ.አ)

“ነሐሴ 24–30(እ.አ.አ) “ለነፍሴ ያደረገላትን እናገራለሁ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ በለሊት ፋኖስ ይዞ

የጠፋውን ለማዳን፣ በማይክል ቲ. ማልም

ነሐሴ 24–30፣ “ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ”

መዝሙረ ዳዊት 49–5161–6669–7277–7885–86

የመዝሙር ጸሐፊዎች በግጥማቸው ጥልቅ ግላዊ ስሜቶቻቸውን አካፈሉ። ስለተስፋ መቁረጥ፣ ፍራቻ፣ እና ፀፀት ስሜት ፃፉ። አንዳንድ ጊዜ፣ በእግዚአብሔር እንደተረሱ ተሰምቷቸው ነበር፣ እና ጥቂቶቹ መዝሙሮች የብስጭት ወይም የተስፋ መቁረጥ ስሜት አላቸው። እንደዚህ አይነት ስሜት ከተሰምቷችሁ መዝሙረ ዳዊትን ማንበብ እናንተ ብቻ እንዳልሆችሁ እንድታውቁ ይረዳችኋል። ነገር ግን እንደዚያ አይነት ስሜቶች ሲኖሯችሁ ሊያበረታቷችህ የሚችሉ መዝሙራትም ታገኛላችሁ፣ ምክንያቱም መዝሙረኞቹ ስለ መልካምነቱ ጌታን አመስግነዋል፣ በኃይሉ ተደንቀዋል፣ እና በምህረቱ ተደስተዋል። እኛ ክፋትና ኃጢአትን እንደተሸከምን ያውቁ ነበር ነገር ግን ጌታ “መልካም እና ይቅር ለማለት ዝግጁ አንደሆነ” ያውቁ ነበር (መዝሙረ ዳዊት 86፥5)። በጌታ ላይ እምነት መኖር በጭንቀት፣ በኃጢያት፣ ወይም በፍራቻ በፍጹም ትግል አይኖርም ማለት እንዳልሆነ ገብቷቸው ነበር። ይህም ወደ ማን እንደምትዞሩ ታቃላችሁ ማለት ነው።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

መዝሙረ ዳዊት 4962፥5–12

ቤዛነት የሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።

መዝሙረ ዳዊት 49 ለ“ዝቅተኞችና ከፍተኞች፣ ባለጠጎችና ድሆች” (ቁጥር 2) መልእክት አለው። ይህ መልዕክት ምንድነው ብላችሁ ታስባላችሁ? በመልክቱ ላይ መዝሙረ ዳዊት 62፥5–12 ምን እንደሚጨምር ይሰማችኋል?

እነዚህን መዝሙሮች ማንበብ መዳን ለማግኘት ከእግዚአብሔር በቀር በሌላ ነገር ለመታመን በምንፈተንባቸው መንገዶች ላይ እንድታሰላስል ሊያነሳሳህ ይችላል (መዝሙረ ዳዊት 49፥6–7ን ተመልከቱ)። “እግዚአብሔር [ነፍሳችሁን] ከሲኦል እጅ ይቤዣታል” የሚለው ምስክርነታችሁ በህይወታችሁ ላይ እንዴት ነው ተጽእኖ የሚያደርገው? (መዝሙረ ዳዊት 49፥15)።

መዝሙረ ዳዊት 5185–86

የሴሚናሪ ምልክት
በአዳኙ ምህረት ምክንያት፣ ከኃጢያቶቼ ይቅር ልባል እችላለሁ።

ንጉሥ ዳዊት መዝሙረ ዳዊት 51ን የጻፈው የኃጢአት ይቅርታ እንደሚያስፈልገው ከተገነዘበ በኋላ ነው። የነበራችሁን ስሜት የሚገልጹት ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው? በዚህ መዝሙር ውስጥ ይቅርታ ለማግኘት የሚያስችል ተስፋ የሚሰጥህ ነገር ምን ታገኛለህ?

በተጨማሪም ንስሐ መግባት ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ መዝሙረ ዳዊት 51ን መመርመር ትችላለህ። ላገኛችሁት ነገር ዝርዝር አዘጋጁ። የፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰንን መልእክት “የተሻለ ማድረግ እንችላለን እንዲሁም የተሻልን መሆን እንችላለን፣” የሚለውን በመፈለግ ወደ ዝርዝራችሁ ለመጨመር ትችሉ አንደሆን (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 67–69) ተመልከቱ።

በክርስቶስ ኣማካኝነት ይቅርታ ማግኘት ምን ስሜት አንደሚፈጥር አንዴት ትገልፁታላችሁ? ስሜታችሁን ለመግለጽ እርዳታ ከፈለጋችሁ በመዝሙረ ዳዊት 51፥1-2፣ 7-1285፥2-9 ላይ ያለውን ሃሳብ ማንበብ ትችላላችሁ። አንዳንድ ሰዎች ስሜታቸውን ለመግለጽ ስዕሎችን መሳል ወይም ስዕሎችን መፈለግ ይወዳሉ፤ አናንተም እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ። ስለ አዳኙ መዝሙር ለመዘመር ወይም ማዳመጥም ይችላሉ፣ ለምሳሌ “I Stand All Amazed [ተደንቄ ቆሚያለሁ]” (መዝሙር፣ ቁጥር 193)።

ንስሐ ለመግባት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያነጻን እንደሚችል ብቻ ሳይሆን እንደሚያነጻንም እምነት ሊኖረን ይገባል። በመዝሙረ ዳዊት 86፥5፣ 13፣ 15 ላይ አዳኙ ይቅር ለማለት ፈቃደኛና ችሎታ ያለው መሆኑን እንድታውቁ የሚረዳችሁ ምንድን ነው?

በተጨማሪም አልማ 36፤ ፒተር ኤፍ ሜርስ፣ “He Could Heal Me!፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023፣ 39-41 ተመልከት።

መዝሙረ ዳዊት 51፥13–1566፥5–2071፥15–24

በኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝ ምስክርነት ሌሎች ወደ እርሱ እንዲመጡ ሊረዳ ይችላል።

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ኃጢያት ክፍያው እንዴት ምስክርነትን እንዳገኛችሁ አሰላስሉ። ከዚያም፣ መዝሙረ ዳዊት 51፥13–1566፥5–2071፥15–24ን ስታነቡ፣ እንዴት ሌሎችን “ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ” ብላችሁ ለመጋበዝ እንደምትችሉ አስቡ (መዝሙረ ዳዊት 66፥5)። መዝሙረ ዳዊት 66፥16 “አምላክ ለነፍሳችሁ ያረገውን ሁሉ ብትናገሩ” ምን ትናገሩ ነበር?

ይህ ለእናንተ “አንደበቴ ደግሞ ሁልጊዜ ጽድቅህን ይናገራል” ማለት ምን ማለት ነው (መዝሙረ ዳዊት 71፥24)።

በተጨማሪም አልማ 26 ተመልከቱ።

መጣት ወንድ ቅዱሳት መፃህፍትን ለሌሎች በማካፈል ላይ

“ኑ፥ ስሙኝ፤ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።” (መዝሙረ ዳዊት 66፥16)።

መዝሙረ ዳዊት 6369; 77–78

በአጣዳፊ ችግሬ ጊዜ ጌታ ይረዳኛል።

በርካታ መዝሙሮች ከእግዚአብሔር ርቆ መኖር ምን እንደሚመስል እና የእርሱን እርዳታ ሲፈልገን ምን እንደሚሰማን ይገልጻሉ (መዝሙረ ዳዊት 63፥1፣ 869፥1–8፣ 18–2177፥1–9ተመልከቱ)። በመዝሙረ ዳዊት 636977–78 ውስጥ ለእነዚህ መዝሙረኞች ማረጋገጫ የሰጣቸው ምን እንደሆነ አገኛችሁን?

በተጨነቃችሁ ጊዜ፣ “የእግዚአብሔርን ሥራ ማስታወስ” እና የእርሱን “የቀደመውን ተአምራትን” ማስታወስ እንዴት ነው የሚረዳችሁ? (መዝሙረ ዳዊት 77፥11)። ጥቂቶቹ ተአምራቶች በመዝሙረ ዳዊት 78 ውስጥ ተብራርተዋል። ሰለ እነርሱ ስታነቡ፣ “ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ” ምን እንደሚረዳ አሰላስሉ (ቁጥር 7)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ይህ እሁድ የወሩ አምስተኛ ሰንበት ስለሆነ የልጆች ክፍል አስተማሪዎች የመማሪያ አክቲቪቲዎችን በ“Appendix B: Preparing Children for a Lifetime on God’s Covenant Path” እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ።

መዝሙረ ዳዊት 5186፥5፣ 13፣15

የተሳሳተ ምርጫን ስመርጥ ኢየሱስ እንድለወጥ ይረዳኛል።

  • ልጆቻችሁን በመዝሙረ ዳዊት 51፣ ላይ ስለ ንስሐ የሚገልጹትን እውነቶች እንዲገነዘቡ ለመርዳት ትልቅ ልብ መሳል ትችላላችሁ። በልቡ ውስጥ ልጆቻችሁን ሰይጣን እንድናደርግ የሚፈልገውን መጥፎ ነገሮች እንዲጽፉ ለመርዳት ትችላላችሁ። እነዚህን ነገሮች ከልባችን እንዴት እናስወግዳለን? ልጆቻችሁን በመዝሙር 51፥10፣ 17 ላይ የሚገኘውን “ልብ” የሚለውን ቃል እንዲያገኙ ጠይቋቸው። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ንስሃ ምን እንደሚያስተምሩን ጠይቋቸው? ልጆቻችሁን በልቡ ውስጥ ያሉትን ቃላት እንዲሰርዙ እና ንስሐ ስንገባ ኢየሱስ እኛን ሊለውጠን የሚችለውን መንገድ የሚገልጹ አዳዲስ ቃላትን እንዲጽፉ አድርጉ።

  • ልጆቻችሁን “የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲያውቁ መርዳት ትፈልጉ ይሆናል (መዝሙረ ዳዊት 51፥17)። እንደ እንቁላል ወይም ኦቾሎኒ ያሉ ጠንካራ ቅርፊት ያላቸውን ነገሮች በየተራ እየሰበሩ መክፈት ይችላሉ። ቅርፊቶቹን የሰማይ አባትን ፍቅር እንዳይሰማን ከሚያደርጉ ነገሮች ጋር እንዲያነጻጽሩት ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ልባችንን ለጌታ እንዴት ልንከፍት እንችላለን?

  • በተጨማሪም የአዳኙን ስዕል አብራችሁ በመመልከት ልጆቻችሁን እርሱን ለመግለጽ ምን ቃላትን እንደሚጠቀሙ መጠየቅ ትችላላችሁ። መዝሙረ ዳዊት 86፥5፣ 13፣ 15 ላይ ስለሱ የሚገልጹትን ቃላት እንዲያብራሩ ጋብዟቸው። ስለሱ እነዚህን ነገሮችን ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

መዝሙረ ዳዊት 61፥2–3

ኢየሱስ ክርስቶስ አለቴ ነው።

  • ልጆቻችሁ የመዝሙረ ዳዊት 61፥2–3 ታሪኮች ስዕል መሳል ሊያስደስታቸው ይችላሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ታላቅ “አለት” (ቁጥር 2)፣ “መጠለያ፣” እና “ጽኑ ግንብ” የሆነው እንዴት ነው? (ቁጥር 3)።

ከድንጋይ የተሰራ ማማ

“ጽኑ ግንብ፣ እና መጠለያ ሆነኸኛል” መዝሙረ ዳዊት 61፥3

መዝሙረ ዳዊት 66፥1677፥1178፥6–7

“የእግዚአብሔርን ሥራ አስታወስሁ።”

  • ልጆቻችሁ የሚወዷቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኰች እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው (Gospel Art Book [የወንጌል ስዕል መጽሐፍ] ስዕሎች ሊረዷችሁ ይችላሉ)። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ጌታ ምን ያስተምሩናል? መዝሙረ ዳዊት 66፥16ን በጋራ ማንበብ ትችላላችሁ፣ ከዛ “ጌታ ለነፍሴ ምን አደረገልኝ”? ለሚለው ጥያቄ በየተራ መመለስ ትችላላችሁ።

  • መዝሙረ ዳዊት 77፥1178፥6–7 በጋራ ስታነቡ፣ “የእግዚአብሔርን ሥራ አስብ” (መዝሙረ ዳዊት77፥11)፣ በሕይወትህ ውስጥ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ጨምሮ እንዴት ጥረት እንደምታደርግ እርስ በርስ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። ቅዱስ ቁርባን “ሁል ጊዜ እንድናስታውስ” የሚረዳን እንዴት ነው? (ሞሮኒ 4፥35፥2)።

መዝሙር 71፥8

ስለ ኢየሱስ ለሌሎች መንገር እችላለሁ

  • መዝሙረ ዳዊት 71፥8ን ከልጆቻችሁ ጋር ካነበባችሁ በኋላ ተለቅ ያለ አፍ እንዲስሉ ጋብዟቸው ። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሌሎች ልንነግራቸው የምንችላቸውን ነገሮች በሚወክሉ ስዕሎች ወይም ቃላት አፉን “ለመሙላት” እንዲረዷችሁ ጠይቋቸው።

  • የኢየሱስ ክርስቶስን ሥዕል ማስተላለፍ ትችላላችሁ። ሥዕሉን የያዘው ሰው ስለ ስለሱ አንድ ነገር መናገር ይችላል። ስለ እንዚህ ነገሮች ሌሎች እንዲያውቁ ልንረዳቸው እንችላለን?

ልጆች ብዙ የሚያካፍሉት ነገር አላቸው ልጆች አዲስ ነገሮችን ሲማሩ፣ በተፈጥሮ ለሌሎች ለማካፈል ይፈልጋሉ። ልጆች የወንጌል መርሆዎችን አንዳቸው ላንዳቸው፣ ለቤተሰብ አባሎች እና ለጓደኛቸው እንዲያስተምሩ እድሎችን በመስጠት ይህን ፍላጎት አበረታቱ። እንዲሁም ከምታስተምሯቸው መርሆዎች ጋር የሚዛመዱ ሃሳቦቻቸውን፣ ስሜቶቻቸውን እና ልምዶቻቸውን ለእናንት እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው። ቀላል፣ ንፁህ እና ኃይለኛ ሃሳቦች እንዳሏቸው ትገነዘባላችሁ (በአዳኙ መንገድ ማስተማር32)።

መዝሙር 86፥7

የሰማይ አባት ጸሎቴን ይሰማል እንዲሁም ይመልሳል።

  • ብዙዎቹ መዝሙሮች ለእግዚአብሔር እንደሚቀርቡ ጸሎቶች ናቸው። መዝሙሮችን ከልጆቻችሁ ጋር በምታነቡበት ጊዜ እንደ ስልክ ወይም ደብዳቤ ያሉ ሩቅ ካሉ ሰዎች ጋር ለመግባባት ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን ነገሮች ልታሳዩአቸው ትችላላችሁ። ከዛ መዝሙር 86፥7 ተመልከቱ። የሰማይ አባትን ጥያቄዎች የምንጠይቀው እንዴት ነው? እሱ የሚመልስልን እንዴት ነው?

  • ስለ ጸሎት አብራችሁ መዘመር ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ “A Child’s Prayer” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 12–13) በተጨማሪም ሱዛን ኤች ፖርተር፣ “ጸልዩ፣ እርሱ አለ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2024፣ 77-79) ተመልከቱ። ስለ ጸሎት አብራችሁ መዝፈን ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።

የኢየሱስ ምስል

ወደ ክርስቶስ ኑ፣፣ በኬሱይ ቻድስ

ዋና የእንቅስቃሴ ገጽ፦ የተሳሳተ ምርጫን ስመርጥ ኢየሱስ እንድለወጥ ይረዳኛል።