“ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሀሳቦች፦ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ግጥምን ማንበብ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“በብሉይ ኪዳን ግጥምን ማንበብ፣” ፣ ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
በአእምሮ ሊያዝ የሚገቡ ሀሳቦች
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ግጥምን ማንበብ
ከዘፍጥረት እስከ አስቴር ባለው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ በአብዛኛው ታሪኮችን እናገኛለን—ታሪካዊ ክስተቶችን በመንፈሳዊ እይታ የሚገልጹ የትረካ ዘገባዎች። ኖህ መርከብ እንደሠራ፣ ሙሴ እስራኤልን እንዳዳነ፣ ሐና ወንድ ልጅ እንዲኖራት እንደጸለየች እና የመሳሰሉትን። ከኢዮብ ጀምሮ፣ የተለየ የአጻጻፍ ስልት እናገኛለን። በእነዚህ መጻሕፍት ውስጥ፣ የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች በማይረሳ መንገድ ጥልቅ ስሜቶችን ወይም ግዙፍ ትንቢቶችን ለመግለጽ ወደ ግጥማዊ ቋንቋ ዞሩ።
በታሪካዊ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍቶች ውስጥ በሙሉ፣ ጥቂት ግጥማዊ የአጻጻፍ ምሳሌዎችን ጣል ጣል ብለው አይተናል። ከኢዮብ መጽሐፍ ጀምሮ ወደፊት እንደዚያ ያለ ብዙ ተጨማሪ እንመለከታለን። የኢዮብ፣ የመዝሙር እና ምሳሌ መጽሐፍት ሙሉ በሙሉ ግጥሞች ናቸው፣ እንዲሁም የኢሳይያስ፣ ኤርምያስ እና አሞጽ ነቢያት ፅሁፎች ክፍልም እንዲሁ ናቸው። ግጥም ማንበብ ታሪክን ከማንበብ የተለየ ስለሆነ፣ እነዚህን መረዳቱ ብዙውን ጊዜ የተለየ አካሄድ ይጠይቃል። በብሉይ ኪዳን ግጥም ውስጥ የበለጠ ትርጉም እንድታገኙ የሚረዷችሁ አንዳንድ ሃሳቦች እዚህ አሉ።
የዕብራይስጥ ግጥምን ማወቅ
መጀመሪያ፣ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የዕብራይስጥ ግጥም፣ እንደ ሌሎች የግጥም አይነቶች፣ ቤት የሚመታ እንዳልሆነ ማወቁ ሊረዳችሁ ይችላል። ምንም እንኳን ምት፣ የቃላት አጻጻፍ እና ድምፆች መደጋገም የጥንት የዕብራይስጥ ግጥም የተለመዱ ባህሪዎች ቢሆኑም፣ እነዚህ ነገሮች በተለይ በትርጉም ሂደት ውስጥ ጠፍተዋል። ወደፊት የምታስተውሉት አንድ ገጽታ ግን አንዳንድ ጊዜ “ትይዩነት” ተብሎ የሚጠራው የሀሳቦች መደጋገም ነው። የኢሳይያስ ቀላል ምሳሌ ይኸውና፦
ፅዮን ሆይ፣ ሀይልሽን ልበሺ፤
ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ቆንጆ ልብስሽን ልበሺ። (ኢሳይያስ 52፥1)
መዝሙር 29 ብዙ ትይዩ መስመሮች አሉት—ለምሳሌ፦
የእግዚአብሔር ድምፅ ኃያል ነው፤
የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማ ሞገስ የተላበሰ ነው። (መዝሙረ ዳዊት 29፥4)
ሁለተኛው መስመር ከመጀመሪያው ጋር ትይዩ መሆኑን ማወቁ አንቀጹን በቀላሉ የሚረዳበት ምሳሌ እዚህ አለ፡-
በከተማችሁ ሁሉ ጥርስን ማጥራት፥
በየቦታችሁም የእንጀራ እጦት አለ። (አሞጽ 4፥6)
በእነዚህ ምሳሌዎች ውስጥ ገጣሚው ትንሽ ልዩነት ያለውን ሀሳብ ደጋግሞ ገልጿል። ይህ ዘዴ የተደጋገመውን ሀሳብ አፅንዖት ለመስጠት እና ልዩነቶቹን በበለጠ ለመግለጽ ወይም ለማዳበር ሊጠቀምበት ይችላል።
በሌላ ሁኔታዎች፣ ሁለቱ ትይዩ ሃረጎች የተጠናከረ ሃሳቦችን ለማስተላለፍ ተመሳሳይ ቋንቋን ይጠቀማሉ፣ ልክ እንደዚህ ምሳሌ፦
የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች፤
ክፉ ቃል ግን ቁጣን ያነሣሣል። (ምሳሌ 15፥1)
የዚህ ዓይነቱ ትይዩነት በአጋጣሚ የተከሰተ አይደለም። ፀሃፊዎቹ ሆን ብለው ያደረጉት ነው። መንፈሳዊ ስሜቶችን ወይም እውነቶችን በሀይል እና በውበት እንዲገልጹ ረድቷቸዋል። ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ጽሁፎች ውስጥ ትይዩነቶችን ስታስተውሉ፣ የጸሃፊዎቹን መልእክት እንዴት ለመረዳት እንደሚረዳችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ “ጥንካሬን” “በሚያምር ልብስ” እና “ጽዮን”ን ከ“ኢየሩሳሌም” ጋር በማዛመድ ምን ለማለት ሞክሮ ሊሆን ይችላል? (ኢሳይያስ 52፥1)። “የለዘበች መልስ” ለሚለው ሐረግ “ሸካራ ቃል” ተቃራኒው መሆኑን ካወቅን ምን መልእክት ከዚህ ለመውሰድ እንችላለን (ምሳሌ 15፥1)።
He Restoreth My Soul[ነፍሴን መለሳት]፣ በዋልተር ሬን
የዕብራይስጥ ግጥም እንደ አዲስ ጓደኛ
አንዳንድ ሰዎች ግጥም ማንበብን አዲስ ሰውን ከመተዋወቅ ጋር ያወዳድራሉ። እንግዲህ የብሉይ ኪዳንን ግጥም ማንበብ ከሩቅ አገር እና ከባዕድ ባህል የመጣን ከእኛ የተለየ ቋንቋ የሚናገር እና ከሁለት ሺህ ዓመት በላይ ከሆነው ሰው ጋር እንደመተዋወቅ ሊሆን ይችላል። እነዚህ ሰዎች ምናልባት መጀመሪያ ላይ ያልተረዳናቸውን ነገሮች ሊናገር/ልትናገር ይችላል/ትችላለች፣ ነገር ግን ይህ ማለት ምንም ጠቃሚ ነገር የለውም/የላትም ማለት አይደለም። ነገሮችን ከእርሱ/ከእርስዋ አንጻር ለማየት በመሞከር ከእነሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ብቻ ያስፈልገናል። በርግጥ አንዳችን ሌላችንን በደንብ እንደምንረዳ በጥልቀት እንገነዘብ ይሆናል። ትዕግሥትና ርኅራኄ ካሳየን ደግሞ አዲስ የምናውቀው ሰው ውሎ አድሮ ውድ ጓደኛ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ ለምሳሌ ከትንቢተ ኢሳይያስአንድ አንቀጽ ስታነቡ የአዲስ ትውውቅ የመጀመሪያ መግቢያችሁ አድርጋችሁ አስቡት። እራሳችሁን ጠይቁ፣ “ምንድነው መጀመሪያ የተሰማኝ ስሜት?” እያንዳንዱ ቃል ባይገባችሁም እንኳን ምንባብ እንዴት እንዲሰማችሁ ያደርጋል? ከዚያም እንደገና አንብቡት፣ ከተቻለ ብዙ ጊዜያት። ጮክ ብለው ማንበብን አስቡ አንዳንድ ሰዎች በዚያ መንገድ ተጨማሪ ትርጉም ያገኛሉ። የተወሰኑ ኢሳይያስ የመረጣቸውን ቃላትን አስተውሉ፣ በተለይም በአእምሮአችሁ ውስጥ ስዕል የሚስሉ ቃላትን። እነዚህ ምስሎች ምን እንዲሰማችሁ ያደርጋሉ? ስለ ኢሳያስ ስሜት ምን ሐሳብ ይጠቁማሉ? የእነዚህን የብሉይ ኪዳን ፀሃፊዎች ቃላትን በበለጠ ባጠናችሁ ቁጥር፣ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ መልእክት ለመግለጽ ሆን ብለው ቃላቶቻቸውን እና ዘዴዎቻቸውን የመረጡ ሆነው ታገኟቸዋላችሁ።
ግጥሞች ስሜታችን እና ልምዶቻችንን እንድንረዳ ስለሚረዱን ግሩም ጓደኞች ሊሆኑ ይችላሉ። የብሉይ ኪዳን ግጥሞች በጣም ውድ ናቸው ምክንያቱም በጣም አስፈላጊ የሆነውን ስሜታችንን እና ልምዶቻችንን እንድንረዳ - ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ግንኙነት ጋር ይረዱናል።
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ግጥምን ስታጠኑ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመራን በጣም ጠቃሚ እንደሆነ አስታውሱ። በእርሱ ላይ እምነታችሁን የሚገነቡ ምልክቶችን፣ ምስሎችን እና እውነቶችን ፈልጉ። ስታጠኑ የመንፈስ ቅዱስ መነሳሻን አዳምጡ።
የጥበብ ስነ ጽሁፍ
አንዱ የብሉይ ኪዳን ግጥም ምሁራን “የጥበብ ሥነ ጽሑፍ” የሚሉት ነው። ኢዮብ፣ ምሳሌ እና መክብብ በዚህ ውስጥ ይመደባሉ። መዝሙሮች የውዳሴ፣ የሐዘንና የአምልኮ ስሜቶችን ሲገልጹ፣ የጥበብ ሥነ ጽሑፍ ግን ጊዜ የማይሽረው ምክር ወይም ጥልቅ፣ የፍልስፍና ጥያቄዎች ላይ ያተኩራል። መፅሐፈ ኢዮብ፣ ለምሳሌ፣ የእግዚአብሔርን ፍትህ እና በሰዎች ስቃይ ጀርባ ያለውን ምክንያት ይዳስሳል። መጽሐፈ ምሳሌ ከቀደሙት ትውልዶች የተሰበሰቡትን እና ያስተላለፉትን ብልህ አባባሎች ጨምሮ በጥሩ ሁኔታ እንዴት እንደሚኖሩ ምክር ይሰጣል። እናም መክብብ የሕይወትን ዓላማን እንዲጠየቅ ያስደርጋል—ሁሉም ነገር ጊዜ ያለፈበት እና የዘፈቀደ በሚመስልበት ጊዜ እውነተኛ ትርጉም ከየት እናገኛለን? ስለ እግዚአብሔር እና ስለፈጠረው አለም ምልከታዎችን ለመካፈል ከሚፈልጉ ከተመስጦ መካሪዎች ጋር የጥበብ ስነ-ጽሁፍን እንደ ጥንቃቄ የተሞላ ውይይት አድርገው ታስቡ ይሆናል - እና ምናልባት እነዚህን ነገሮች ከበፊቱ ትረዱ ዘንድ የሚረዷችሁም ሊሆኑ ይችላሉ።