“ሐምሌ 27–ነሐሴ 2 “ታላቅ ሥራ እየሠራሁ ነው”፤ ዕዝራ 1፥3–7፤ ነህምያ 2፥ 4–6፤ 8” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ሐምሌ 27–ነሐሴ 2 “ታላቅ ሥራ እየሠራሁ ነው፣” ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
I Have a Great Work to Do [የምሠራው ትልቅ ስራ አለኝ]፣ በታይሰን ስኖው
ሐምሌ 27–ነሐሴ 2 “ታላቅ ሥራ እየሠራሁ ነው”
ዕዝራ 1፤ 3–7፤ ነህምያ 2፤ 4–6፤ 8
የአይሁድ ሕዝብ ለ70 ዓመታት ያህል በባቢሎን በምርኮ ቆይተዋል። ኢየሩሳሌምን እና ቤተመቅደሱን አጥተዋል፣ እና ብዙዎች ለእግዚአብሔር ሕግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ረስተው ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር እነርሱን አልረሳቸውም። በእርግጥም፣ በነቢዩ አማካኝነት እንዲህ አውጇል፣ “እጐበኛችኋለሁ፣ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ” (ኤርምያስ 29፥10)። በዚህ ትንቢት መሰረት፣ ጌታ ህዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ወደ ቃል ኪዳናቸው የሚመለሱበትን መንገድ አዘጋጀ። እናም “ታላቅ ሥራ” የፈጸሙ አገልጋዮችን አስነሳ (ነህምያ 6፥3)፦ ዘሩባቤል የሚባል ገዥ የእግዚአብሔርን ቤት እንደገና መገንባቱን ይቆጣጠር ነበር። ዕዝራ፣ ካህን እና ጸሐፊ፣ ሕዝቡ ልባቸውን ወደ ጌታ ሕግ እንዲመልሱ ረድቷቸዋል። ነህምያም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያሉትን የመከላከያ ግንቦች እንደገና እንዲገነባ መርቷል። ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር፣ ነገር ግን ያልተጠበቁ ምንጮች እርዳታ አግኝተዋል። እኛም ታላቅ ሥራ እየሠራን ስለሆነ፣ የእነርሱ ልምዶች እንድናውቅ እና እንድንነሳሳ ለማድረግ ይችላል። እናም እንደ እነርሱ፣ የእኛ ሥራ ከጌታ ቤት፣ ከጌታ ሕግ እና በእርሱ ውስጥ ካገኘነው መንፈሳዊ ጥበቃ ጋር ብዙ የሚገናኝ ነው።
ስለዕዝራ እና ነህምያ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ዕዝራ“ እና “ነህምያ” የሚሉትን ይመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ዕዝራ 1
ጌታ የእርሱን አላማውን እንዲፈጽሙሰዎችን ያነሳሳል።
ፋርስ ባቢሎንን ድል ካደረገች በኋላ የፋርስ ንጉስ ቂሮስ ቤተመቅደሱን እንደገና ለመገንባት የአይሁድ ቡድን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲልክ ጌታ አነሳስቶታል። ዕዝራ 1ን በምታነቡበት ጊዜ፣ ቂሮስ አይሁዳውያን በዚህ አስፈላጊ ሥራ ለመደገፍ ምን እንዳደረገ ተመልከቱ። የቤተክርስቲያኗ አባል ያልሆኑትን ጨምሮ ጌታ በዙሪያችሁ ባሉ ወንዶች እና ሴቶች በኩል ሲሰራ እንዴት ታዩታላችሁ? ይህ ስለጌታ እና ስለስራው ምን ጥቆማን ይሰጣችኋል?
እንዲሁም ኢሳይያስ 44፥24–28ን ይመልከቱ።
ዕዝራ 3፥8–13፤ 6፥16–22
የጌታ ቤት የደስታ ቦታ ነው።
ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን በወረሩ ጊዜ ቤተመቅደሱን ዘርፈው በእሳት አቃጥለውታል (2ኛ ነገሥት 25፥1–10፤ 2ኛ ዜና 36፥17–19ን ተመልከቱ)። ይህንን ከተመለከቱት አይሁድ መካከል ብትሆኑ ኖሮ ምን ይሰማችሁ የነበረ ይመስላችኋል? (መዝሙረ ዳዊት 137ን ተመልከቱ)። አይሁዶች፣ ከአስርተ ዓመታት በኋላ፣ ተመልሰው መቅደሱን እንደገና እንዲገነቡ በተፈቀደላቸው ጊዜ ምን እንደተሰማቸው ልብ በሉ (ዕዝራ 3፥8–13፤ 6፥16–22ን ተመልከቱ)። ይህ ስለ ጌታ እና ስለ ቤቱ ያላችሁን ስሜት እንድታስላስሉ ሊገፋፋችሁ ይችላል። የቤተመቅደስ መገንባት ለማክበር ምክንያት የሆነው ለምንድነው?
የዘሩባቤል ቤተ መቅደስ፤ ምሳሌ በሳም ላውሎር
ዕዝራ 4–7፤ ነህምያ 2፤ 4፤ 6
እግዚአብሔር እኔ እንድሰራው የሚፈልገው ስራ አለው።
የጌታ ስራ ያለ ተቃዋሚ አይሄድም። በዘሩባቤልና በነህምያ መሪነት ያደረጉት ጥረት ይህ ነበር። ከእነዚህ ታሪኮች እንድትማሩ እና ተቃውሞ ቢያጋጥማችሁም የጌታን ሥራ እንዴት መሥራት እንደምትችሉ ለማገናዘብ የሚያስችል ቀላል አቀራረብ እነዚህ ናቸው፦
የእግዚአብሔር ሥራ ለዘሩባቤል (ዕዝራ 4፥3)፦
የእግዚአብሔር ሥራ ለነህምያ (ነህምያ 2፥17-18)፦
የእግዚአብሔር ሥራ ለእኔ፦
ዘሩባቤል የገጠመው ተቃውሞ (ዕዝራ 4፥ 4–24)፦
ነህምያ የገጠመው ተቃውሞ (ነህምያ 2፥19፤ 4፥ 1-3፣ 7-8፤ 6፥1–13)፦
እኔን የገጠመኝ ተቃውሞ፦
ዘሩባቤል እንዴት ምላሽ ሰጠ (ዕዝራ 5፥ 1-2)፦
ነህምያ እንዴት ምላሽ ሰጠ ነህምያ2፥ 20 ፤ 4፥6-9፤ 6፥ 3–15)፦
እኔ እንዴት ምላሽ መስጠት እችላለሁ፦
የነህምያንን ልምድ ከህይወታችሁ ጋር ለማነጻጸር እርዳታ ለማግኘት የፕሬዘዳንት ዲተር ኤፍ ኡክዶርፍ መልእክት “ታላቅ ስራን እየሰራን ነው እናም ማቆም አንችልም፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 59–62 በተለይም የመጨረሻዎቹ ሁለት ክፍሎችተመልከቱ። እግዚአብሔር የሰጣችሁን ሥራ ስታስቡ፣ “የወጣት ሴቶች ጭብጥ” ወይም “የአሮናዊ ክህነት ቡድን ጭብጥ”ን ልታጠኑ ትችላላችሁ (የወንጌል ላይብረሪ)። ወይም እንደ “As Sisters in Zion [በጽዮን እንዳሉ እህቶች ]” (መዝሙር፣ ቁጥር 309) ወይም “Ye Elders of Israel [እናንተ የእስራኤል ሽማግሌዎች]” (መዝሙር፣ ቁጥር 319) መዝሙሮች መመልከት ትችላላችሁ።
በአዳኙ አገልግሎት ውስጥ “የመሥራት አሳብ” መኖር ምን ማለት ይመስላችኋል? (ነህምያ 4፥6)። ሥራውን በምትሠሩበት ጊዜ “የእግዚአብሔር መልካም እጅ በእናንተ ላይ” መኖር ምን ማለት ሊሆን ይችላል? (ነህምያ 2፥8፤ በተጨማሪም ነህምያ 2፥18፤ ዕዝራ 7፥6፣9፣27-28ተመልከቱ። እሱን ለማገልገል በምታደርጉት ጥረት እጁን ያያችሁት እንዴት ነው?
ነህምያ 8
ቅዱሳት መጻህፍትን ሳጠና እባረካለሁ።
በምርኮ ውስጥ ለነበሩት ትውልዶች፣ አይሁዳውያን “የሙሴን ሕግ መጽሐፍ” የማግኘት ዕድል ውስን ነበር (ነህምያ 8፥1)። በ ነህምያ 8፣ ዕዝራ ሕጉን ለሕዝቡ አነበበ። ዕዝራና ሕዝቡ ስለ አምላክና ስለ ቃሉ ያላቸውን አመለካከት የሚያሳይ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ምን ታገኛላችሁ? (በተለይ ቁጥር 1-12ን ተመልከቱ)። በሕይወታችሁ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ቃሉ ያላችሁን ስሜት የሚያሳየው ምንድን ነው?
በተጨማሪ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንቶች ትምህርቶች፡ ዕዝራ ታፍት ቤንሰን (2014 (እ.አ.አ))፣ 115–24 ተመልከቱ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ዕዝራ 3፥8–13፤ 6፥16–22
የጌታ ቤት የደስታ ቦታ ነው።
-
አይሁዳውያን ቤተ መቅደሳቸው ሲታደስ የተሰማቸውን ደስታ ለልጆቻችሁ ለማስተማር ከታች ያለውን ምሥል ልታሳዩአቸው ትችላላችሁ። እነዚህ ሰዎች በጌታ ቤት በመሆናቸው ደስ የተሠኙትለምን እንደሆነ ተናገሩ። ቤተ መቅደሱ ለእናንተ የደስታ ቦታ የሆነበትን ምክንያት ለልጆቻችሁ መንገር ትችላላችሁ። ቤተመቅደሱ ወደ ሰማይ አባት እና ወደ አዳኙ የመቅረብ ስሜት እንዲሰማችሁ የረዳችሁ እንዴት ነው?
-
ዕዝራ 3፥-10–13ን ከልጆቻችሁ ጋር ስታነቡ አይሁዳውያን ቤተ መቅደሱ እንደገና በሚገነባበት ጊዜ ምን እንደተሰማቸው የሚያሳዩ ቃላትን እንዲያገኙ እርዷቸው። ወደ ቁጥር 13 መጨረሻ ስትደርሱ፣ ምናልባት አብራችሁ በደስታ መጮህ ትችላላችሁ። ጌታ ቤተመቅደሶችን ስለ ሰጠን ልጆቻችሁ ደስተኞች የሚሆኑባቸውን ምክንያቶች እንዲያስቡ እርዷቸው። ይህን ደስታ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
-
እንደ “Welcome Home[እንኳን ደህና መጣችሁ ወደ ቤት]” ሁለተኛ ሥንኝ ያለ ስለ ቤተመቅደስ የሚያወሳ መዝሙርን ከልጆቻችሁ ጋር መዘመርን አስቡ። ከእያንዳንዱ መስመር በኋላ፣ አንድ/አንዲት ልጅ ስለ ቤተመቅደስ የሚወደውን/የምትወደውን ነገር እንዲያካፍል/እንድታካፍል ለመጠየቅ ቆም ማለት ትችላላችሁ። በምትዘምሩብት ጊዜ የቤተ መቅደስ ምሥል ማየትም ትችላላችሁ።
ነህምያ 2፥17–20፤ 6፥1–9
ጌታ “ታላቅ ስራውን” እንድሰራ ይረዳኛል።
-
የነህምያን ታሪክ ለልጆቻችሁ አካፍሉ (ነህምያ 2፥17–20፤ 6፥1–9፤ ወይም “ነህምያ” በOld Testament Stories [የብሉይ ኪዳን ታሪኮች]፣ 173–74 ተመልከቱ። ነህምያ 2፥ 20 ን ስታነቡ እናንተና ልጆቻችሁ “ልትነሱ” እና የኢየሩሳሌምን ግንብ እየሠራችሁ እሆነ ልታስመስሉ ትችላላችሁ። ወይም ልጆቻችሁ በድንጋይ ወይም በሌሎች ነገሮች ግድግዳ መገንባት ያስደስታቸው ይሆናል። እነርሱ በሚገነቡበት ጊዜ፣ የሰማይ አባት እንድንሰራ የሚፈልጋቸውን አስፈላጊ ነገሮች እንዲያስቡ ልትረዷቸው ትችላላችሁ።
1:38Nehemiah
-
ነህምያ 6፥9 ን ስታነቡ “እጆቼን አበርታ” ስትሉ ሲሰሙ ልጆቻችሁ እጃቸውን እንዲያነሱ ጋብዟቸው። እግዚአብሔር ስራውን ለመስራት እጆቻችሁን ሲያበረታ የተሰማችሁን ጊዜ ለልጆቻችሁ ንገሯቸው።
ነህምያ 8፥1–12
ቅዱሳት መጻሕፍት በረከት ናቸው።
-
ዕዝራ ድምፁን ከፍ አድርጎ ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነብ ሕዝቡ ምን እንዳደረገ የሚገልጹ አንዳንድ ሐረጎችን ከ ነህምያ 8፥2–3፣ 5–6፣ 8–9፣ 12 ውስጥ ጮክ ብላችሁ አንብቡ። በምታነቡበት ጊዜ ልጆቻችሁ እነዚህን ሐረጎች መተወን ማድረግ ይችላሉ። ከዚያም ቅዱሳት መጻህፍትን ስታነቡ ወይም ስትሰሙ ምን እንደሚሰማችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ።
-
ነህምያ 8: 8ን አብራችሁ ስታነቡ ልጆቻችሁ ቅዱሳን ጽሑፎችን እንዲረዱ የሚረዳቸው ምን እንደሆነ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያጠኑ እንደ የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያን እና Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች] (ወንጌል ላይብረሪ)ያሉ የቅዱሣት መፃህፍት ማጥኛ መርጃዎችን እንዴት እንደሚጠቀሙ አሳዩቸው። ልጆቻችሁን ከቅዱሳት መጻህፍት ስለ አዳኙ የተማሩትን ነገር እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው።
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ዘላለማዊ እውነትን ፈልጉ። ቅዱሳት መጻህፍት… በወንጌል እውነቶች የተሞሉ ናቸው፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ እነሱን ለማግኘት የታሰበበት ጥረትን ይጠይቃል። ከቅዱሳት መጻህፍት አብራችሁ እየተማራችሁ በመሆኑ ቆም ብላችሁ የምታስተምሯቸው ሰዎች ልብ ስላሏቸው የወንጌል እውነቶች ጠይቋቸው። እነዚህ እውነቶች ከሰማይ አባት የደህንነት ዕቅድ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ እንዲመለከቱ እርዷቸው። አንዳንድ ጊዜ ዘላለማዊ እውነቶች በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ተገልጸዋል፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በምናነባቸው የሰዎች ታሪኮች እና ሕይወቶች ውስጥ ይታያሉ። ስለምታነቧቸው ጥቅሶች ታሪካዊ አመጣጥ እና ትርጉም በጋራ ማሰስ እና ዛሬ ለእኛ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ መፈለግም ሊረዳ ይችላል (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኝ መንገድ ማስተማር]፣ 22)።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።