“ነሐሴ 10-16። ‘እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ’፤ ኢዮብ 1–3፤ 12–14፤ 19፤ 21–24፤ 38–40፤ 42” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ነሐሴ 10-16። ‘እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፣’ ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
የኢዮብ ፍርዶች፣፣ በጆሴፍ ብሪኬይ
ነሐሴ 10-16፤ “እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ”
ኢዮብ 1–3፤ 12–14፤ 19፤ 21–24፤ 38–40፤ 42
መጥፎ ነገሮች ለምን በጥሩ ሰዎች ላይ ይፈጸማሉ —ወይም እንዲሁም፣ ጥሩ ነገሮች ለመጥፎ ሰዎች የሚሆኑላቸው ለምንድን ነውብሎ ማሰቡ ተፈጥሮአዊ ነው። ጻድቅ የሆነው እግዚአብሔር ያንን የሚፈቅደው ለምንድን ነው? መጽሐፈ ኢዮብ እንደእነዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን ይዳስሳል። ኢዮብ ጥሩ ከሆኑ ስዎች ውስጥ ሆኖ መጥፎ ነገሮች ከሚፈጠርባቸው አንድ ነበር። በኢዮብ ፈተናዎች ምክንያት፣ ጓደኞቹ በእውነቱ ጥሩ ሰው ሰለመሆኑ ተጠራጥረው ነበር። ኢዮብ የራሱን ጻድቅነት አረጋግጦ ነበር እና እግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ጻድቅ ስለመሆኑ አሰበ። ነገር ግን ኢዮብ ቢሰቃይ እናቢደነቅም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ጽኑ አቋሙን እና እምነቱን አጥብቆ ቀጠለ። በመፅሐፈ ኢዮብ ውስጥ እምነት ይጠየቃል እና ተፈትኗል ግን በፍፁም ሙሉ በሙሉ አልተተወም። ይህ ሁሉም ጥያቄዎች ተመልሰዋል ማለት አይደለም። በኢዮብ መጽሐፈ ላይ ጥያቄዎች እስኪመለሱ ድረስ ከእምነት ጋር አብረው ይኖራሉ። እስከዚያው የሚከሰትም ምንም ይሁን ምን ስለ ጌታችን እንዲህ ማለት እንችላለን፣ “እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ” (ኢዮብ 13፥15)።
ስለ መጽሐፈ ኢዮብ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት “ኢዮብ” የሚለውን በቅዱሳት መጽሐፍት መመሪያ (ወንጌል ላይብራርይ) ላይ ተመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ኢዮብ 1–3፤ 12–13
በሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ላይ እተማመናለሁ።
የኢዮብ የመክፈቻ ምዕራፎች የሰይጣንን የጠላት ወይም ከሳሽ በመሆን የሚጫወተውን ሚና በግጥም አጽንዖት ይሰጣሉ፣ እንጂ እግዚአብሔር እና ሰይጣን በእውነቱ እንዴት እንደሚገናኙ ለመግለጽ አይደለም። ስለ ኢዮብ የሰይጣንን የይገባኛል ጥያቄዎች በምታነቡበት ጊዜ (ኢዮብ 1፥9–11፤ 2፥4–5 ተመልከቱ)፣ እራሳችሁን “ለምን ለእግዚአብሔር ታማኝ እሆናለሁ? ብላችሁ ጠይቁ። ስይጣን ባቀረበው ምክንያት ብቻ ለጌታ መታዘዝ አስቸጋርይ የሚያደርገው እንዴት ነው?
ኢዮብ በፈተና ውስጥ የስጠው ምላሽ ያስገረማችሁ ምንድነው? ( ኢዮብ 1፥20–22፤ 2፥9–10ተመልከቱ)።
የኢዮብ ጓደኞቹ እግዚአብሔር እየቀጣው እንደነበር ሀሳብ ሰጡ (ኢዮብ 4–5፤ 8፤ 11ን ተመልከቱ)። በዚህ አሳብ ውስጥ ትክክል ያልሆነ ነገር ትመለከታላችሁ? የኢዮብን መልስ በ ምዕራፎች 12-7አንብብ። ኢዮብ በእግዚአብሔር ላይ እንዲተማመን የረዳው እውቀት ምንድ ነው? ፈተናዎቻችሁን እንድትጋፈጡ የሚረዳችሁ ስለእግዚአብሔር ምን ታውቃላችሁ?
ኢዮብ 19
ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዬ ነው።
አንዳንድ ግዜ በችግር ውስጥ ስንሆን አስፈላጊ እና ጠቃሚ እውነታ እንማራለን። በኢዮብ 19፥1–22 ውስጥ ኢዮብ የገለጸውን ፈተናዎች እና በበቁጥር 23–27 ውስጥ ባወጀው እውነት ላይ አሰላስሉ። ቤዛችሁ በህይወት እንደሚኖር እንዴት ታውቃላችሁ? ይህ እውቀት በሕይወታችሁ ውስጥ ምን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል?
ስለእየሱስ ክርስቶስ የተዘመሩ መዝሙሮችን ለመዘመር ወይም ለመስማት አስቡበት፣ እንደ “I Know That My Redeemer Lives [አዳኜ እንደሚኖር አውቃለሁ]” (መዝሙር፣ ቁ. 136)። ከዚህ መዝሙር ውስጥ የትኛው የእናንተን ስሜት የሚገልጽ ቃላት አገኛችሁ?
በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–12፤ 122ን ተመልከቱ።
ኢዮብ 21–24
“ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።”
በ ኢዮብ 21–24፣ በኢዮብ እና ጓደኞቹ መካከል ሰለነበረው ክርክር ማንበብ ትችላላችሁ። በዚህ ክርክር ውስጥ ስዎች የሚጠይቁት ጥይቄ ነበር፤ ለምን ጥሩ ስዎች አንዳንድ ግዜ ይስቃያሉ?
ቢሆንም ዳግም በተመለሰው የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ ለሁሉም መልስ ባናገኝም ፣ ነገር ግን የተወሰኑ እውነታዎች ስለመከራና ስለስቃይ እንድንገነዘብ ሊረዳን ይችላል። ከዚህ በታች የኋለኛው ቀን ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተወስኑ እውነታዎች ይዘዋል። እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ስለሰማያዊ አባት እና ስለእቅዱ ምን ያስተምራችሃል?
እንዲሁም የፕሬዘዳንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምቦል በመከራ ውስጥ ስላለው ችግር ያስተማሩትን ማንበብ ትችላላችሁ በ “Tragedy or Destiny? [አሳዛኝ ወይስ እጣ ፈንታ?]” (የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፦ስፔንሰር ደብሊው ኪምቦል [2011 (እ.አ.አ)])፣ 11–21)።
በተማራችሁት ትምህርት ላይ ተመስርታችሁ፣ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎች ትመልሳላችሁ ”ለምን እግዚአብሔር ጻድቅ በሆኑ ስዎች ላይ መከራን ይፈቅዳል?”
Calm and Stars [የተረጋጋ እና ኮከቦች]፣ በዮንግሳንግ ኪም ምስል ጨዋነት በ havenlight.com
ኢዮብ 38–40፣ 42
የእግዚአብሔር አመለካከት ከእኔ ይበልጣል።
በጓደኞቹ ክስ ተስፋ በመቁረጥ (ኢዮብ 16፥1–5፤ 19፥1–3ን ተመልከቱ)፣ ኢዮብ ስለ ሥቃዩ ማብራሪያ በመፈለግ እግዚአብሔርን ጠየቀ (ኢዮብ 19፥6–7፤ 23፥1–9፤ 31ን ተመልከቱ)። በመጽሐፈ ኢዮብ ላይ ጌታ ግልጽ ምክንያት አልሰጠም። ነገር ግን አስፈላጊ መልእክት በ በምዕራፎች 38–40አስተምራል። ይህን መልዕክት እንዴት ታጠቃልሉታላችሁ? ለምሳሌ፣ ስለጌታ ጥያቄዎች ከ ኢዮብ 38፥ 1-7፣ 18-24ምን ትማራላችሁ?
አስተውሉ ጌታ ከኢዮብ ጋር ስለፍጥረት እና ሌላ አስደናቂ ስራዎቹ ነግሮታል (ኢዮብ 38–39 ተመልከቱ)። አንዳንድ ፍጥረቶችን (ወይም ምስሎቻቸውን) መመልከት ትችላላችሁ። እነዚህ ነገሮች ስለእግዚአብሔር የተለየ አስተሳሰብ እንዲኖራችሁ ያደረገው እንዴት ነው? ስለእናንተ መከራዎች? ይህ የኢዮብን አመለካከት የቀየረው እንዴት ነበር? ( ኢዮብ 42፥1-6፤ በተጨማሪ ሙሴ1፥8–10ተመልከቱ)።
እነዚህ አመለካከታችንን እንድንቀይር ሊረዱ የሚችሉ ሁለት አጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶች እንመልከት፦ ታማራ ደብሊው ሩኒያ፣ “የእግዚአብሔርን ቤተሰብ በአጠቃላይ እይታ ሌንስ ውስጥ መመልከት” (ሊያሆና፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ) 62–69)፤ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ስለ ሰለስቲያል አስቡ!” (ሊያሆና፣፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ)፣ 117–20)። በሁለቱ መልእክት ውስጥ መከራዎቻችሁ አስቸጋርይ ሲመስላችሁ ማስታወስ የምትፈልጉትን መልእክት ፈልጉ። የተማራችሁትን ነገር ለራሳችሁ የምታስታውሱት እንዴት ነው?
አዲስ ነገር ፈጣሪ ሁኑ። ትምህርት ማንበብን፣ ማሰብን እና መናገርን የያዘ ብቻ መሆን የለበትም። አንዳንድ ግዜ የሚታወሱ ትምህርቶች ከአካላዊ እንቅስቃሴ ሊመጡ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ስታነብ ጌታ እንዴት የኢዮብን አመለካከት እንደቀየረ በ ኢዮብ 38–40፣ የጌታን ፍጥረት ከትልቅ እስከ ትንሽ በመንቀሳቀስ እና መመልከት ትችላላችሁ ወይም አንድን ነገር ከተለየ አመለካከት ማየት ከላይ፣ ከታች፣ወደ ላይ፣ ከርቀት እና የመሳሰሉት።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ኢዮብ 1–2፤ 12፤ 19
በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን በአስቸጋሪ ጊዜያት ይረዳኛል።
-
ልጆቻችሁን ስለኢዮብ የሚያውቁትን እንዲንግሯችሁ አበረቷቷቸው። እርዳታ ከፈለጉ፣ ወደዚህ ጠቁሙዎቸው (ኢዮብ 1፥1፣ 13–22፤ 2፥7-10፤ ወይም “ኢዮብ” (በ Old Testament Stories [የብሉይ ኪዳን ታሪኮች]፣ 145-47 ተመልከቱ)። ኢዮብ ለፈተናዎቹ ምን ምላሽ ሰጠ? (ኢዮብ 1፥21፣ 2፥10ተመልከቱ)።
1:55Job
-
ኢዮብ በፈተናዎቹ ውስጥ ታማኝ ነበር ምክንያቱም ስለጌታ የሚያውቀው ነገር ስላለ። እናንተ እና ልጆቻችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ከስዎች ጋር ሲገናኝ የሚያሳይ ምስል ተመልከቱ ( እንደ ከታች እንዳለው ወይም ምስል ከ Gospel Art Bookመመልከት ትችላላችሁ)። ስለእርሱ የምታውቁትን ተንጋገሩ እና ምን እንደሚወድ። እነኚህ የተወሰኑ ምእራፎች የሚያሳዩት ኢዮብ ጌታን እንደሚያውቀው ነው፦ ኢዮብ 12፥10፣ 13 ፣16፤ 19፥25–27። ስለእርሱ እነዚህን ነገሮች ማወቅ ምን ጥቅም አለው?
ሁሉንም ፈወሳቸው፣ በማይክል ማልም
ኢዮብ 14፥14
በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ከሞትኩ በኋላ እንደገና በህይወት እንኖራለሁ።
-
ኢዮብ ጠቃሜ ጥያቄ ጠይቋል በ ኢዮብ 14፥14። ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ በተራ ለኢዮብ መልስ ትሰጣላችሁ። ሀሳቦችን በ አልማ 11፥42–44 በቪዲዮ “In a Coming Day [በሚመጣው ቀን]”(የወንጌል ላይብረሪ)፣ ወይም ስለ ትንሳኤ መዝሙር፣ ለምሳሌ “Did Jesus Really Live Again?”መፈለግ ትችላላችሁ። የልጆች መዝሙር መፅሀፍ 64)።
#BECAUSEofHIM: An Easter Message of Hope and Triumph
ኢዮብ 16፥1–5፤ 22፥5
ጥሩ ጓደኞች ያንሳሳሉ እና እርስ በርስ ይበረታታሉ።
-
የኢዮብ ሲከፋው፣ ጓደኞቹም ከፍቶቸው እግዚአብሔር በሃጢያቱ ምክኛት እየቀጣው እንደነበር ሀሳብ (ኢዮብ 22፥5ተመልከቱ)። እኛ የኢዮብ ጓደኛ ብንሆን እንዴት ልንረዳው እንሞክር ነበር? የእኛ ቃላት ሌሎች ሲከፋቸው እንዴት ሊረዳቸው ይችላሉ? (ኢዮብ 16፥5 ተመልከቱ)። ጥያቂዎቹን በምትወያዩበት ግዜ አንድ ወይም ከዛ በላይ ምስሎችን ማሳየት ትፈልጉ ይሆናል።
-
ልጆቻችሁን የጥሩ ጓደኛ መስፈርቶች ምን እንደሆኑ እንዲዘረዝሩ ጠይቋቸው እና ከዛ ይህን መስፍርት ይሚያሟላ የጓደኛቸውን ስም እንዲዘረዝሩ አድርጉ። የኢየሱስ ክርስቶስ ምስል መመልከት ትችላላችሁ። በምን መንገድ ነው ጌታ ለእያንዳዳችን ጥሩ ጓደኛ የሆነን? ስለአንድ በመከራ ውስጥ ስላለ ስው አስቡ። እንዴት ለጓደኞቻችሁ የክርስቶስ ምሳሌ ለመሆን እቅድ አውጡ።
ኢዮብ 19፥23–27
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኚ ነው።
-
ኢዮብ 19፥23–27ን ካነበባችሁ በኋላ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ እንዴት አዳኛችን እንደሚኖር እንዳወቁ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ምስክርነታችሁን (ወይም የአዳኙን ሥዕሎች) በመጽሐፍ ውስጥ ለማስቀመጥ አብራችሁ ልትሠሩ ትችላላችሁ (ቁጥር 23ን ተመልከቱ)።
-
ስለአዳኝ የሚመሰክሩ መዝሙርን ለመዘመር እንደ “I Know That My Redeemer Lives [አዳኜ ህያው እንደሆነ አውቃለሁ]” (መዝሙር፣ ቁጥር 136) መዘመር ትችላላችሁ። በእርሱ ላይ እምነታችሁን የሚገነባ የመዝሙር ሀረጎች አካፍሉ። ኢየሱስ ክርስቶስን መኖር ጥቅሙ ምንድን ነው?
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።