ኑ፣ ተከተሉኝ
ነሐሴ 17-23 (እ.አ.አ)። “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው”፦ መዝሙር 1-2፤ 8፤ 19–33፤ 40፤ 46


“ነሐሴ 17-23። ‘‘እግዚአብሔር እረኛዬ ነው’፦ መዝሙረ ዳዊት 1–2፤ 8፤ 19–33፤ 40፤ 46” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 17-23። ‘‘እግዚአብሔር እረኛዬ ነው’” ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ በጎችን እየመራ

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፣ በዮንግሱንግ ኪም ምስል ጨዋነት በ havenlight.com

ነሐሴ 17-23፦ “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው”

መዝሙረ ዳዊት 1–2819–334046

መዝሙረ ዳዊትን ማን እንደጻፈ በእርግጠኝነት አናውቅም። ጥቂቶቹ ንጉሥ ዳዊት እንደጻፋቸው ይታመናሉ፣ ነገር ግን አብዛኞቹ ፀሐፊዎች ስማቸው አልተገለጠም። ሆኖም መዝሙሮችን ካነበብን በኋላ፣ ስማቸውን ባናውቅም እንኳ የመዝሙረኞችን ልብ እንደምናውቅ ሆኖ ይሰማን ይሆናል። እኛ የምናውቀው መዝሙሮች በእስራኤላውያን መካከል ትልቅ የአምልኮ ክፍል እንደነበሩ፣ እና አዳኝ ብዙ ጊዜ እንደጠቀሳቸው ነው። በመዝሙሮች ውስጥ፣ ወደ እግዚአብሔር የጥንት ሰዎች ነፍስ ውስጥ የሚያሳይ መስኮትን እናገኛለን። ስለ እግዚአብሔር ምን እንደተሰማቸው፣ ምን እንዳስጨነቃቸው እና እንዴት ሰላም እንዳገኙ እናያለን። ዛሬ አማኞች እንደመሆናችን፣ በመላው ዓለም፣ አሁንም እነዚህን ቃላት ለእግዚአብሔር አምልኮአችን እንጠቀማለን። የመዝሙረ ዳዊት ጸሐፊዎች በእኛ ነፍስ ውስጥ መስኮት ነበራቸው ላለት ይቻላል፣ ምክያቱም ሰለ አምላክ ያለንን ስሜት፣ የምንጨነቅበትን እና ሰላም የምናገኝበትን መንገድ ገልፀውልናል።

ስለ መዝሙረ ዳዊት አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መዝሙረ ዳዊት“ የሚለውን ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

መዝሙረ ዳዊት 12326–2846

“በጌታ ታምኛለሁ ።”

መዝሙረ ዳዊትን ስታነቡ፣ ፀሃፊዎቹ ፍርሃትን፣ ሀዘንን ወይም ጭንቀትን ምን ያህል ጊዜ እንደገለፁ ማስተዋል ትችሉ ይሆናል። ለእምነት ሰዎችም እንኳ፣ እንዲህ ያሉት ስሜቶች የተለመዱ ናቸው። ነገር ግን መዝሙሮችን የሚያነቃቃ የሚያደርጋቸው ቢኖር የሚሰጡዋቸው መፍትሄዎች ናቸው፣ እንዲሁም በጌታ ላይ ሙሉ መታመንን ጨምሮ። እናንተ መዝሙረ ዳዊት 12326–2846ን ስታነቡ፣ ፃፉ፦

  • ጌታን ለመታመን ግብዣ።

  • እርሱን የሚገልጹ ቃላት።

  • እርሱ የሚሰጣቸውን ሰላም፣ ጥንካሬ፣ እና ሌሎች በረከቶች የሚገልጹ ቃላት፤

  • በእርሱ የሚተማመኑትን የሚገልጹ ቃላት።

እንዲሁም ደማቅ ምስሎችን እንዲሁም መዝሙር ሰለ አዳኝ ለማስተማር የሚጠቀምበትን ምልክቶች ተመልከቱ። ለምሳሌ በመዝሙረ ዳዊት 23 ውስጥ እንደ “በለመለመ መስክ ያሳድረኛል” ወይም “በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል” ቁጥር 2 ያሉ ሀረጎች ምን ያስታውሳሉ? አፅናኙ “በትር” እና “ምርኩዝ” (ቁጥር 4) ምንን ያመለክታል? የእኛ “ጽዋ” (ቁጥር 5) መሮጥ ምን ማለት ሊሆን ይችላል?

መዝሙረ ዳዊት 222

ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የተገባው መሲህ ነው።

በርካታ መዝሙሮች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ ሕይወት ያመለክታሉ። በአዲስ ኪዳን ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች እነኚን ግንኙነቶች አይተዋል። የሚቀጥሉትን የመጽሃፍ ቅዱስ ማጣቀሻ ለማንበብ አስቡባቸው። በነዚህ መዝሙሮች ውስጥ ባሉት ቃላት እና በአዳኙ ህይወት መካከል ግንኙነት ተመልከቱ፦

  • መዝሙረ ዳዊት 2፥1-3 እና የሐዋርያት ስራ 4፥24-28

  • መዝሙር 2፥7 እና የሐዋርያት ስራ 13፥30-33

  • መዝሙረ ዳዊት 22፥–1 እና ማቴዎስ 27፥ 45-46

  • መዝሙረ ዳዊት 22፥7–8 እና ማቴዎስ 27፥39–43

  • መዝሙር 22፥16 እና ሉቃስ 23፥32-33

  • መዝሙረ ዳዊት 22፥18 እና ማቴዎስ 27፥ 35

  • መዝሙር 31፥5 እና ሉቃስ 23፥46

ከእነዚህ ዝርዝሮች ምን ትማራላችሁ? የትኞቹ የቅዱሳን መፃህፍት ትንቢቶች እና ቃልኪዳኖች ናቸው እስካሁን ያልተፈፀሙት? በእነዚህ ተስፋዎች ውስጥ ስለ ወደፊቱ ምን ተስፋ የሚሰጥ ነገር አግኝታችኋል?

ወንዝ እና ድንጋዮች

መዝሙረ ዳዊት 81933

“የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች።”

መዝሙረ ዳዊት 81933 ን ማንበብ የጌታን ብዙ ድንቅ ፍጥረቶች እንድታስቡ ሊያነሳሳችሁ ይችላል። ያን ስታደርጉ ለሃሳባችሁ እና ስሜቶቻችሁ ትኩረት ስጡ። ከእነዚህ መዝሙሮች ጋር የሚመሳሰል ዘምሩ ወይም አሰላስሉ፣ እንደ “How Great Thou Art [ምን ያህል ታላቅ ነህ]” (መዝሙር፣ 86)። እንዴት የጌታ ፍጥረቶች ለእናንተ “የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ” (መዝሙረ ዳዊት 19፥1)።

እነዚ በመዝሙረ ዳዊት አነሳሽነት ከተጻፉ መዝሙሮች አንዳንዶቹ ናቸው፥

  • መዝሙረ ዳዊት 23The Lord Is My Shepherd [እግዚአብሔር እረኛዬ ነው]” (መዝሙር፣ ቁጥር 108)

  • መዝሙር 23፥6150Praise to the Lord, the Almighty [ሁሉን ቻይ የሆነው ጌታ ይክበር ይመስገን]” (መዝሙር፣ ቁጥር 72)

  • መዝሙር 26፥8We Love Thy House, O God [አምላክ ሆይ ቤትህን እንወዳለን]” (መዝሙር፣ ቁጥር. 247)

  • መዝሙረ ዳዊት 27፥1The Lord Is My Light [እግዚአብሔር ብርሃኔ ነው]” (መዝሙር፣ ቁጥር 89)

  • መዝሙ 33፥1-695፥1–6For the Beauty of the Earth” (መዝሙር፣ ቁጥር 92)

  • መዝሙር 37:3–9Be Still, My Soul” (Hymns፣ ቁጥር 124)

  • መዝሙር 148፥8All Creatures of Our God and King [የአምላካችንና የንጉሳችን ፍጥረታት ሁሉ]” (መዝሙር፣ ቁጥር. 62)

ሙዚቃን ተጠቀሙ። ፕሬዝዳንት ዳሊን ኤች. ኦክስ እንዲህ አሉ፦ “መዝሙርን መዘመር እራሳችንን ከጌታ መንፈስ ጋር ለማስማማት ከሁሉ የተሻለ መንገድ ነው.… የተቀደሰ ሙዚቃ ለጌታ ያለንን የፍቅር ስሜት የመግለፅ ልዩ ችሎታ አለው። እንደዚ አይነት የሀሳብ ልውውጥ ለአምልኳችን ግሩም እርዳታ ነው። … መዝሙሮቻችን በእውነት እና በግጥም ተፅዕአቸው በቅዱሳን መፃሕፍት ብቻ የሚበልጡ አቻ የለሽ አስተምሮ እና ስብከት ይይዛሉ” (“Worship through Music [በመዝሙር አምልኩ]፣” ኢንዛየን፣ ሕዳር. 1994 (እ.አ.አ) 10 11። በዚህ ሳምንት አምልኳችሁን ለማሳደግ ምን አይነት መዝሙሮችን ማዳመጥ ወይም መዘመር ትችችላላችሁ?

መዝሙረ ዳዊት 19፥7–1129

የጌታ ቃል “ልብን ደስ የሚያሰኝ” ኃይለኛ ነው።

በመዝሙራት ውስጥ እንደ ምስክርነትገጽታትእዛዝ፣ እና ፍርዶች ያሉ ቃላት የጌታን ቃል ሊያመለክቱ ይችላሉ። እናንተ መዝሙረ ዳዊት 19፥7–11ን ስታነቡ ያንን በአእምሮአችሁ ያዙ። እነዚህ ጥቅሶችለእናንተ ስለጌታ ቃል ምን ይጠቁማሉ? መዝሙረ ዳዊት 29 ስለ እርሱ ድምጽ ምን ያስተምራችኋል? በእናንተ ተሞክሮ፣ የጌታ ቃል ወይም ድምጽ ከእነዚህ መግለጫዎች ጋር እንዴት ነው የሚዛመደው?

መዝሙረ ዳዊት 2426–27

የሴሚናሪ ምልክት
ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንድገባ አዳኝ ንፁህ እንድሆን ሊረዳኝ ይችላል።

በኢየሩሳሌም ያለው ቤተመቅደስ የተገነባው በተራራ ላይ ስለሆነ “የእግዚአብሔር ተራራ” (መዝሙረ ዳዊት 24፥3) የሚለው ሐረግ ቤተ መቅደሱን ወይም የእግዚአብሔርን መኖር ሊያመለክት ይችላል። ያም እናንተ በመዝሙረ ዳዊት 24 ያላችሁ መረዳት ላይ ምን ይጨምራል? “እጆቹ የነጹ ፣ ልቡም ንጹሕ የሆነ” ማለት ለእናንተ ምንድን ነው”? (ቁጥር 4)። መዝሙረ ዳዊት 26-27ን፣ ስታነቡ፣ ስለ ጌታ ቤት ምን ተማራችሁ?

አንዳንድ ጊዜ፣ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት ንፁ መሆን እንዳለብን ስንሰማ ተስፋ ልንቆርጥ እንችላለን። ደግሞም፣ ሁላችንም እንታገላለን፣ እና ሁላችንም ፍፁም አይደለንም። በሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር መልዕክት ውስጥ “Clean Hands and a Pure Heart [እጆቹ የነጹ ፣ ልቡም ንጹሕ የሆነ]” ምን ተስፋ ታገኛላችሁ? (ሊያሆና፣ ህዳር 2007 (እ.አ.አ)፣ 80–83)። ፍጹም ለመሆን የተጨነቅን ሰው ለመርዳት ይህን መልዕክት እንዴት መጠቀም ትችላላችሁ? “ንጹህ እጆች እና ንጹህ ልብ” እንዲኖራችሁ በሚያደርጉት ጥረት የአዳኙን እርዳታ እንዴት እንደሚቀበሉ አስቡበት።

በተጨማሪ ብራድሊ አር. ዊልኮክስ፣ “Worthiness Is Not Flawlessness፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 61–67፤ ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

መዝሙረ ዳዊት 2327–283246

ጌታ ተስፋን፣ ሰላምን እና ምሪትን ይሰጠናል።

  • ጌታ …ነው ልጆች እነዚህን አይነት ጥቅሶች ተጠቅመው አረፍተ ነግሩን የሚያጠናቅቁባቸውን መንገዶች እንዲፈልጉ ጋብዟቸው፦ መዝሙረ ዳዊት 23፥127፥128፥128፥732፥746፥1። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ጌታ እንዴት እንደሚረዳን ምን ያስተምሩናል?

  • ጠቦት በጎች ደህንነቱ እንዲጠበቅና ጤናማ እንዲሆን እንዲሆን ምን እንደሚያስፈልገው መወያየት ትችላላችሁ። ከዚያም መዝሙረ ዳዊት 23ን አብራችሁ ስታነቡ ልጆቻችሁ እረናኛ ለጠቦት የሚያደርገውን ኢየሱስ ለእኛ ካደረገው ጋር እንዲያወዳድሩ እርዷቸው። በመንፈሳዊ ደህና እንድንሆንና ጤናማ እንድንሆን ምን ያስፈልገናል? እንደ “I Feel My Savior’s Love” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 74–75 ያለ መዝሙሮችን አብራችሁ መዘመር አሳቦችን ይሰጣችሃል።

ኮንስፕሲኦን ቺሊ ቤተመቅደስ

ኮንስፕሲኦን ቺሊ ቤተመቅደስ

መዝሙረ ዳዊት 24፥3–4

ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት “ንፁህ እጆችና ንፁህ ልብ” ያስፈልገናል።

  • መዝሙረ ዳዊት 24፥3ን በጋራ ስታነቡ፣ ልጆቻችሁ ስለ ቤተ መቅደስ የሚያስታውሳቸውን ቃላት መፈለግ ይችላሉ። እንዲሁም የቤተመቅደስ ምስል መመልከት ይችላሉ። ከዚያም ቁጥር 4ን ወደ ቤተ መቅደስ ማን እንደሚገባ በጋራ አንብቡ። እጅ እንዴት እንደሚቆሽሽ እና እንዴት መፅዳት እንደሚችል ተናገር። በመንፈሳችን እንዴት ነው የምንቆሽሸው? አዳኝ የሚረዳን እንዴት ነው?

መዝሙር 30፥5

ኢየሱስ ክርስቶስ ሀዘንን ወደ ደስታ መቀየር ይችላል።

  • ወጣት ልጆች ካሏችሁ፣ ከመዝሙር 34፥5 ስታነቡ ማልቅስ እንዲያስመስሉ ጋብዟቸው፣ “ማልቀስ ለአንድ ለሊት ሊቆይ ይችላል።” “ግን በማለዳ ደስታ ይመጣል” ይህን በምታነብበት ወቅት ደስተኛ ፊት እንዲያሳዩ ጠይቁቸው። ይህን ሀረግ ለተወሰነ ጊዜ ደጋግሙት

  • የአዳኙን ምስል ለልጆቻችሁ ማሳየትን አስቡ፣ ከዚያም ደስታ የሚያመጣላችሁን ለእናንተ ያደረገላችሁን ለልጆቹ ንገሯቸው። እንዲህም እያንዳንዱን ልጅ ሰእሉን እንዲይዝ ተራ ስጡ እና ኢየሱስ ያደረገላቸውን ደስታ ያመጣላቸውን ነገር እንዲያካፍሉ አድርጉ።

መዝሙር 46፥10

“ዕረፉ እና እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ።”

  • ልጆቹ ከመዝሙር 46፥10 ላይ “ዕረፉ እና እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤” የሚለውን የመጀመሪያ መስመር እንዲሸመድዱ እርዷቸው። ትሁት መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ወይም ጊዜ ወስዳችሁ እነዚህን ጥቅሶች በክፍል ደረጃ በጋራ ልትለማመዷቸው ትችላላችሁ። የመንፈሱ ተጸዕኖ በተሰማችሁ ጊዜ የነበራችሁን ልምድ አንዳችሁ ለአንዳችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። “ዝም ብለው” እያለ ከሰማይ አባት ጋር ቅርብ እንደሆኑ እንዲሰማቸው አግዟቸው።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።

አድኝ መብራትን ይዞ

መልካሙ እረኛ፣ በኢቫ ቲሞቲ

ዋና ተግባር ገጽ፦ “እግዚአብሄር እረኛዬ ነው”