ኑ፣ ተከተሉኝ
ነሐሴ 3–9 (እ.አ.አ)። “ደግሞስ ወደ…የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል”…አስቴር


“ነሐሴ 3–9። ‘ደግሞስ ወደ…የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል’ አስቴር፣” ኑ፥ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 3–9። ‘ደግሞስ ወደ…የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል፣’” ኑ፥ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

አስቴር በንጉሱ ፊት ተንበርክካ

Queen Esther Saves Jehovah’s People [ንግሥት አስቴር የያህዌህን ህዝብ አዳነች፣ በሳም ላውሎር

ነሐሴ 3–9፦ “ደግሞስ ወደ…የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል”

አስቴር

በመፅሐፈ አስቴር ውስጥ ያሉ ብዙ ክስተቶች እንደ ዕድል ወይም የአጋጣሚ ሊመስሉ ይችላሉ። ወላጅ አልባ አይሁዳዊት ሴት ህዝቧን ከመታረድ ለማዳን በትክክለኛው ጊዜ የፋርስ ንግሥት እንደሆነች እንዴት በሌላ መልኩ ልታብራሩ ትችላላችሁ? የአስቴር አጎት ልጅ መርዶክዮስ ንጉሱን ለመግደል የተጠነሰሰውን ሴራ ለመስማት የመቻሉ እድል ምን ያህል ነበር? እነዚህ አጋጣሚዎች ነበሩ፣ ወይስ የመለኮታዊ ዕቅድ አካል ነበሩ? ሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራስባንድ እንደጠቀሱት፥ “ተራ አጋጣሚ ሊመስል የሚችል ነገር፣ በእርግጥም፣ በወዳጅ የሰማይ አባት ቀድመው ታይተዋል። … ጌታ በህይወታችን በእያንዳንዱ ጥቃቅን ዝርዝሮች ውስጥ ነው” (“በመለኮታዊ ንድፍ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ) 56)። በእነዚህ “ጥቃቅን ዝርዝሮች” ውስጥ የጌታን ተጽዕኖ ሁልጊዜ ላናውቅ እንችላለን። ነገር ግን ከአስቴር ተሞክሮ የምንማረው እርሱ በመንገዳችን ሊመራን እንደሚችል እና እኛ የእርሱን አላማ ለሟሟላት በእጆቹ መሳሪያዎች ወደምንሆንበት “እንደዚህ ላለው ጊዜ” (አስቴር 4፥14) እንደሚያዘጋጀን ነው።

ስለመፅሀፈ አስቴር አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “አስቴር፣ መጽሀፈ” የሚለውን ይመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

አስቴር

የሴሚናሪ ምልክት
ጌታ ሌሎችን ለመባርክ በምችልበት ቦታ ያስቀምጠኛል።

ፕሬዘደንት ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዳስተማሩት እያንዳዳችን “በተለየ ቦታ ቆመናል እናም ትልቅ ስራን እኛ ብቻ የምንስራው ተስቶናል… ጌታ ለእናንተ አላፊነት ሲሰጥ በምክንያት ነው። እናንተ ብቻ ልትደርሱባቸው እና ልትነኳዋቸው የምትችሏቸው ሰዎች እና ልቦች ሊኖሩ ይችላሉ። ማንም በተመሳሳይ መልኩ እንደእናንተ ሊያደርጉት አይችልም” (“በቆማችሁበት አንሱ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 56)።

የአስቴርን ታሪክ ስታነቡ፣ ይህ ጽሁፍ እንዴት በእርሷ ተግባራዊ እንደሆነ አሰላስሉ። አይሁድን ለማዳን ጌታ ለእሷ የሚያስችሏትን መንገዶች እንዲገኙ እንዳደረገ ፈልጉ (ለምሳሌ፣ አስቴር 2፥21–233፥10–144፥14–16ን ተመልከቱ)። ከዛም ሌሎችን ለመባረክ እድል እንደሰጣችሁ አሰላስሉ። “እንደዚህ ላለው ጊዜ” የመሯችሁ አንዳንድ ሁኔታዎች ወይም ግንኙነቶች ምንድን ናቸው? (አስቴር 4፥14)። የፓትሪያርክ በረከት ካላችሁ፣ ጌታ እናንተ እንድትሰሩ የሚጠብቀውን ስራ የበለጠ ለማወቅ እሱን ማንበብን አስቡ። ይህንን ስራ ለመስራት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

እንዲሁም “For Such a Time as This [እንደዚህ ላለው ጊዜ]” (ቪዲዮ)፣ ተመልከቱ ChurchofJesusChrist.org።

13:44

For Such a Time as This

ከመስማት ይልቅ በተግባር የበለጠ መማር እንችላለን። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ.ቤድናር አስተማሪዎችን እንዲህ መክረዋል፦ “የእኛ ዓላማ ‘ምን ልንገራቸው’ መሆ የለበትም። ከዚያ ይልቅ፣ እራሳችንን መጠየቅ ያለብን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ነው፣ ‘ምን እንዲያደርጉ ልጋብዛቸው? ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ከሆኑ፣ መንፈስ ቅዱስን ወደ ሕይወታቸው መጋበዝ የሚጀምር ምን ዓይነት የተነሳሳ ጥያቄዎች ልጠይቅ?’” (በ Teaching in the Savior’s Way {በአዳኘ መንገድ ማስተማር]25)። ቤተሰባችሁን ወይም ክፍላችሁን ስለአስቴር እያስተማራችሁ ከሆነ፣ እንዲማሩ ሊረዳቸው የሚችልምን እንዲያደርጉ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ ?

መርዶክዮስ ሃማን በጎዳና ላይ ፈረስ ሲጋልብ እያየ

“ሃማም መርዶክዮስ…እንዳልሰገደለትም ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣ” (አስቴር 3፥5)።

አስቴር 35፥9–147

ኩራት እና ቁጣ ወደ ውድቀት ሊመራ ይችላል።

በመፅሐፈ አስቴር ውስጥ ከአስቴርና ከመርዶክዮስ ታማኝነት እንዲሁም ከሃማ ኩራት እና ቁጣ እንማራለን። እናንተ አስቴር 35፥9–14ን ስታነቡ፣ የሐማን ስሜቶች፣ ቃላቶች፣ እና ድርጊቶች አስተውሉ። ስለእርሱ እና ስለፍላጎቶቹ ምን ይገልጣሉ? እርሱን ምን ውጤቶች አጋጠሙት ? ( አስቴር 7ን ተመልከቱ)። ሰለ ሐማ ማንበብ ስሜቶቻችሁን እና ድርጊቶቻችሁን ምን እንደሚያነሳሳ እንድትመረምሩ ይገፋፋችሁ ይሆናል። ለውጥ ለምድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋልን? ለእርዳታ ወደሰማይ አባት እንዴት ነው ልትዞሩ የምትችሉት?

በተጨማሪ ምሳሌ 16፥32አልማ 5:28ን ተመልከቱ።

አስቴር 3–45፥2–38፥11–12

መፆም በጌታ ላይ ማመኔን እና መተማመኔን ያሳያል።

አስቴር እና የተቀሩት አይሁዳዊያን እንዲጾሙ ያደረጋቸውን ሁኔታዎች አስተውሉ (አስቴር 3፥134፥1–3፣ 10–17ን ተመልከቱ)። ፆም የባረካቸው እንዴት ነው? (አስቴር 5፥2–38፥11–12ን ተመልከቱ)። ጌታ እንድንፆም የሚጠይቀን ለምንድነው ? (ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “ፆም እና የፆም በኩራት፣” ከወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ)። ጾምን በህይወታችሁ ውስጥ እንዴት ትልቅ በረከት ለማድረግ እንደምትችሉ አስቡ።

በተጨማሪም ኢሳይያስ 58፥6–12፤ “Fasting: Young Single Adult Ward, Amanda” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።

2:41

Fasting: Young Single Adult Ward, Amanda

አስቴር 3፥1–114፥10–175፥1–49፥17–19

ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ብዙ ጊዜ ድፍረትን ይጠይቃል።

መርዶክዮስና አስቴር ለሚያምኑት ነገር እና ለህዝባቸው ሲቆሙ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ነበር። ምርጫዎቻችን ከባድ ያልሆኑ መዘዞች ሊኖሯቸው ይችላል፣ ነገር ግን ትክክለኛውን ነገር ማድረግ አሁንም ድፍረትን ይጠይቃል። ከአስቴር 3፥1–44፥10–17 ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ብርቱ ስለመሆን ምን ትማራላችሁ? ድፍረትን ካሳዩ በኋላ መርዶክዮስና አስቴር የደረሰባቸውን የተለያዩ ውጤቶች አስተውሉ (አስቴር 3፥5–75፥1–4 ተመልከቱ)። አስቴርና መርዶክዮስ ያደረጉትን ምርጫ ለማድረግ ስለእግዚአብሔር ምን ማወቅ ያስፈልጋቸው ነበር?

ትክክል ለሆነው ነገር ለመቆም ድፍረት የሚያስፈልግበትን ሁኔታ አስቡ። በጌታ ላይ ድፍረት እንድታገኙ የሚረዳችሁ ከአስቴር እና ከመርዶክዮስ ምን ትማራላችሁ?

የአስቴር ድፍረት ወደ “ደስታ ቀን” አመራ (አስቴር 9፥17–19 የክርስቶስን የመስለ ድፍረት “የደስታ ቀን ” የሠጣችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም፣ “Courage,” “Dare to Stand Alone” (ቪዲዮዎች)፣ የወንጌል ላይብረሪ፤ “True to the Faith [ለእምነት እውነት]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 254 ተመልከቱ።

3:19

Courage

4:20

Dare to Stand Alone

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

አስቴር 2፥5–7

ቤተሰቤን ማገልገል እችላለሁ።

  • መርዶክዮስ ለአስቴር እንዳደረገው ልጆቻችሁን የተቸገሩትን የቤተሰብ አባላትን እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ለማስተማር አስቴር 2፥7 እንድትጠቀሙ ተነሳስታችሁ ይሆናል። ጥቅሱን እብራችሁ ማንበብ ወይም በራሳችሁ ቃላት መጠቅለል ትችላላችሁ። ምናልባት እናንተና ልጆቻችሁ የእናንተን እርዳታ የሚፈልግ የቤተሰብ አባል ልታስቡ ትችላላችሁ። እነርሱን ለመርዳት እቅድ አውጡ።

አስቴር 3፥1–114፤10–17

ጌታ ደፋር እንድሆን ሊረዳኝ ይችላል።

  • የአስቴርና የመርዶክዮስ ምሳሌ ልጆቻችሁ ድፍረት ማለት በሚፈሩበት ጊዜም እንኳ ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ እንደሆነ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። መርዶክዮስ ደፋር ነበር እሱ… እና አስቴርም ደፋር ነበረች እሷ … የሚሉትን ሐረጎች መጻፍን አስቡ። የአስቴርን ታሪክ አብራችሁ ስትማሩ፣ ልጆቻችሁ ዓረፍተ ነገሩን የሚጨርሱበትን መንገድ ሊጠቁሙ ይችላሉ። አስቴር 3፥1–114፥10–17 ወይም “Queen Esthe [ንግስት አስቴር]” (በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 166–70) ማንበብ ወይም ምስሉን ከስዕሎቹ ማየት ትችላላችሁ። ከዚያም ደፋር እንደምሆን በ…፣ እና ልጆቻችሁ የሰማይ አባት እንዲያደርጉ የሚፈልጓቸውን ድፍረት የሚሹ ነገሮችን እንዲዘረዝሩ ጋብዟቸው። ስለደፍረት የተዘመሩ መዝሙሮች እንድ “Dare to Do Right [በትክክል ለመስራት ድፍረት]” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 158) ሊረዳ ይችላል።

    2:45

    Queen Esther

  • እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ደፋር ስለነበረበት ጊዜ መማር ትችላላችሁ—ለምሳሌ፡ በጌቴሴማኒ እና በመስቀል ላይ ስለ ኃጢአታችን ሲሰቃይ (ማቴዎስ 26፥36-3927፥33–35ተመልከቱ)። ልጆቻችሁ ደፋር የሆኑበትን ግዜ እንዲያካፍሉ ጠይቁ፣ እና እናንተም የራሳችሁን ተሞክሮ አካፍሉ።

አስቴር 4፥1–3፤ 10–17

ፆም ከጌታ ዘንድ በረከቶችን ያመጣል።

  • አስቴር 4፥1–3፤ 10–17ን አንብቡ ይህ ለልጆቻችሁ ስለመጾም ለማስተማር ይረዳችሃል። አስቴር እና አይሁዶች የጾሙት ለምንድ ነው? ለምን እንደምትጾሙ ለልጆቻችሁ ንገሩ። እንዲሁም ስለጾሙ ምንም ለማያውቅ ጓደኛቸው እንዴት እንደሚያስረዱ ልትጠይቋቸውም ትችላላችሁ። ጓደኞቻችን ከጾም የሚገኘውን በረከት እንዲገነዘቡ ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት ነው?

  • ልጆቻችሁ የጌታ እርዳታ የሚፈልጉበትንየሆነ ነገር እንዲያስቡ አበረታቷቸው። ያንን የጾማቸውን ክፍል በሚቀጥለው እሁድ የጾም ቀን እንዲያደርጉት ጠቁሙ።

ንግሥት አስቴር ከንጉሡ አጠገብ ቆማ።

አስቴር ደፋር ስለነበረች የጌታን ሕዝብ ማዳን ችላለች።

አስቴር 4፥14

በእግዚአብሄር እጆች ውስጥ መሳሪያ መሆን እችላለሁ።

  • አስቴር በፈራች ጊዜ መርዶክዮስ “እንደዚህ ላለው ጊዜ” ንግሥት እንድትሆን ጌታ እንደረዳት በመግለጽ እንዳበረታታት ልጆቻችሁን እንዲገነዘቡ እርዷቸው” (አስቴር 4፥16)። መርዶክዮስ ይህን ሲል ምን ማለቱ ነበር? አስቴር እንዴት የጌታ መሣሪያ እንደነበረች እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ። ለጌታ መሣሪያዎች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

  • ልጆቻችሁ መሣሪያ ምን እንደሆነ እንዲገነዘቡ እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? ምናልባት አንድ ሰው በመሣሪያ መዝሙር እንዲጫወት ልትጋብዙ ወይም መሣሪያ ሲጠቀም የሚያሳይ ምስል ማሳየት ትችላላችሁ። በእግዚአብሄር እጆች መሳሪያ መሆን ምን ማለት እንደሆነ መነጋገር ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።

ንግስት አስቴር

ንግስት አስቴር፣ በሚኔርቫ ኬ. ቴይቸርት፣ © ዊሊያም እና ቤቲ ስቶክስ

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፡ ጌታ ደፋር እንድሆን ሊረዳኝ ይችላል።