“ሐምሌ 20–26 (እ.አ.አ)። “አይኖቻችን ወደአንተ ናቸው”፡ 2 ዜና 14–20፤ 26፤ 30፡ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) 2026 (እ.አ.አ)
“ሐምሌ 20–26 (እ.አ.አ)። ‘አይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው’”ኑ፣ ተከተሉኝ፡ 2026 (እ.አ.አ)
የንጉስ ኢዮሳፍጥ ጸሎት ፣ በኪሌይ ሬ
ሐምሌ 20–26 (እ.አ.አ)፡ “አይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው”
2 ዜና 14–20፤ 26፤ 30
የይሁዳ መንግሥት ተከበበ። ሶስት ኃያል የጠላት አሕዛብ ጦር ለጦርነት ተዘጋጅቶ በአንድ ላይ እየገሰገሰ ነበር። በዚህ ተስፋ አስቆራጭ የችግር ጊዜ፣ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ወደ ሰማይና ምድር ንጉሥ ዘወር አለ። ኢዮሣፍጥ ሕዝቡን በቤተ መቅደስ ሰብስቦ ጸለየ። ድክመታቸውን በማመን ነጻ ይወጡ ዘንድ ተማጸነ። በምላሹ፣ ጌታ እንዲጠብቃቸው እንዲህ ሲል ቃል ገባ፡- “አትፍሩ፣ አትደንግጡም” (2 ዜና 20፡17)።
እኛን ለማጥፋት የሚያስፈራራ ወራሪ ጦር በደጃችን ላይኖር ይችላል፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በመከራ እና በክፋት እንደተከበብን ይሰማናል። ነጻ የመውጣት መንገዳችን ኢዮሣፍጥ ከፈለገው ጋር አንድ ነው፣ ጸሎታችንም እንደ እርሱ ሊሆን ይችላል፡- “አምላካችን ሆይ… የምናደርገውን አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው” (2 ዜና 20:12)
በ2 ኛ ዜና 14–30፣ ስለ ኢዮሣፍጥ እና ስለ ሌሎች የይሁዳ ነገሥታት ታነባላችሁ። በእምነታቸው ላይ ያተኮሩ ተሐድሷቸው፣ ድላቸው እና ተግዳሮታቸው በእናንተ ሕይወት ውስጥ እንዴት ተግባራዊ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስቡ።
ስለ 2 ዜና አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ዜና” የሚለውን ይመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
2 ዜና 14–16
በእግዚአብሔር መታመን ሰላም ያመጣልኛል።
አሳ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ጊዜ ዛሬ ላይ ልክ እንደሁላች ብዙ ፈተናዎች አጋጥመውት ነበር። ያጋጠሙትን ፈተናዎች በምታነቡበት ጊዜ እምነት የጣለበትን እና በጊዜ ሂደት እንዴት ያ እንደተለወጠ አስተውሉ።
|
ማጣቀሻ |
አሳ ያጋጠሙት ፈተናዎች |
አሳ እምነቱን የጣለበት |
|---|---|---|
ማጣቀሻ 2 ዜና 14፡9–12 | ||
ማጣቀሻ 2 ዜና 15፡1–8 | ||
ማጣቀሻ 2 ዜና 16፡1–10 |
አንዳንድ ጊዜ በጌታ መታመን ለምን እናቆማለን? ከአሳ ሕይወት ሌላ ምን ትማራላችሁ?
እንዲሁም ሽማግሌ ዲ“Our Relationship with God [ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 78–80) ይመልከቱ።
2 ዜና 18
በብዙዎች ተቀባይነት ባያገኝም እንኳ እውነትን ማስከበር እችላለሁ።
ነቢዩ ሚክያስ ነገሥታቱ ኢዮሣፍጥና አክዓብ ከሶርያ ጋር ባደረጉት ጦርነት ድል እንደሚቀዳጁ እንዲተነብይ ብዙ ግፊት ሳይደረግበት አልቀረም። ያንን ግፊት የሚያሳይ ማስረጃ በ2 ዜና 18፡1–12 ውስጥ ፈልጉ። በቁጥር 13-27 ላይ ስለ ሚክያስ ድፍረት እና ቁርጠኝነት ምን ማረጋገጫ ታገኛላችሁ? (በቁጥር 14 ላይ ሚክያስ የስላቅ ምላሽ እንደሰጠ አስተውሉ፤ ትክክለኛው መልሱ ቁጥር 16 ላይ ነው።) የሚክያስ ቃል በቁጥር 28-34 ላይ የተፈጸመው እንዴት ነው?
ሚክያስ ያጋጠመውን ዓይነት ተጽዕኖ ሊያጋጥሟችሁ የሚችልባቸው አንዳንድ ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው? ለጌታ እና ለአስተምሮቱ ለመቆም ድፍረት የሚሰጣችሁ ምንድን ነው?
በንጉሥ ኢዮሣፍጥ ዘመን ሦስት የአሕዛብ ሃገሮች ኢየሩሳሌምን ወረው ነበር።
2 ዜና 20፡1–25
በአስቸጋሪ ጊዜያት ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ነቢያቱ መመለስ እችላለሁ።
2 ዜና 20፡1–12ን ስታነቡ፣ ብዙ አሕዛብ ይሁዳን ለማጥቃት በመጡ ጊዜ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ያደረገውን ተመልከቱ። በሚያጋጥሟችሁ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የእሱን ድርጊቶች እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ትችላላችሁ?
ለኢዮሣፍጥ ጸሎት የጌታ ምላሽ በቁጥር 14-17 ይገኛል። በአስቸጋሪ ጊዜያት እናንተን ወይም የምታውቁትን ሰው የሚያጽናኑ የትኞችን ሀረጎች ማግኘት ትችላላችሁ?
በማግስቱ የኢየሩሳሌም ሰዎች የጠላትን ጦር ለመገናኘት ወጡ። 2 ዜና 20:20 ን ስታነቡ፣ ኢዮሣፍጥ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ የሰጣቸውን መልእክት ፈልጉ። የተናገራቸው ቃላት የተፈጸሙት እንዴት ነው? (ቁጥር 22-23 ይመልከቱ)። እግዚአብሔር በእርሱ በማመናችሁ እና ነቢያቱን በመከተላችሁ እንዴት ባርኳችኋል?
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፡ “የእኔ ተሞክሮ አንዴ ከነቢዩ መግለጫዎች ኋላ የጥያቄ ምልክቶችን ማስቀመጥ አቁማችሁ በምትኩ ቃለ አጋኖ ስታስቀምጡ እንዲሁም ስታደርጉት፣ በረከቶቹ እንደሚፈሱ ነው። ‘ነቢዩ እንደ ነብይ የሚናገረው መቼ ነው፣ የማይናገረውስ መቼ ነው ?’ ብዬ ራሴን አልጠይቅም። የእኔ ፍላጎት፣ ‘እንዴት እሱን መምሰል እችላለሁ?’ የሚል ነው” (በሌይን ጆንሰን፣ “Russell M. Nelson: A Study in Obedience,” ኢንዛይን 1982፣ 24)።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፡4–6፤ “A Secure Anchor (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ፤ “Make inspired choices,” ለወጣቶች ጥንካሬ፡ ምርጫ የማድረግ መመሪያ (2022)፣ 4–5።
A Secure Anchor
ቀላል የእውነት መግለጫዎችን ለዩ። ሽማግሌ ኒል ኤ. ማክስዌል እንዲህ አስተምረዋል፡ “ቅዱሳት መጻህፍት ብዙ የትምህርት እንቁዎችን ይሰጡናል። የመንፈስ ብርሃን በተለያዩ ገፅታዎቻቸው ላይ ሲበራባቸው፣ በሰማያዊ ስሜት ያንጸባርቃሉ እንዲሁም ልንከተለው የሚገባውን መንገድ ያበራሉ” (“According to the Desire of [Our] Hearts,” ኢንዛይን፣ ህዳር 1996፣ 21)። ቅዱሳት መጻህፍትን በምታጠኑበት ጊዜ አጫጭር ነገር ግን ኃይለኛ መልዕክቶችን ለመለየት፣ ምልክት ለማድረግ እና ለማሰላሰል ጊዜ ወሰዱ። አንዳንድ ምሳሌዎች በ2 ዜና 14፡11፤ 15:7፤ 18:13፤ 20:15፤ 26፡5 ውስጥ ይገኛሉ። ሌላ ምን “የትምህርት እንቁዎችን” ልታገኙ ትችላላችሁ?
2 ዜና 26፡3–21
ትዕቢት ወደ ጥፋት ይመራል።
እንደሌሎች የይሁዳ ነገሥታት ሁሉ፣ የዖዝያን መንግሥት በታላቅ ክንዋኔዎች የጀመረ ቢሆንም በአሳዛኝ ሁኔታ ተጠናቋል። ይህንን መሰል ነገር በ2 ዜናዎች 26 ውስጥ ፈልጉ። የዖዝያን ሕይወት የተለወጠበት ጊዜ መቼ ነበር ትላላችሁ?
ቁጥር 16-23ን ስታነቡ በዚህ ጊዜ በቤተመቅደስ ውስጥ ካህናት ብቻ እንዲያጥኑ የተፈቀደላቸው መሆኑን አስታውሱ። ንጉሥ ዖዝያን እግዚአብሔርን ያልታዘዘው ለምን ይመስላችኋል? ከዚህ አሳዛኝ ሁኔታ ምን ትማራላችሁ?
በተጨማሪም “Be Thou Humble,” መዝሙሮች፣ ቁጥር 130 ይመልከቱ።
2 ዜናዎች 30
አስታራቂ መሆን እችላለሁ።
በ2 ዜና 30፣ ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉሥ ነበር። ተቀናቃኙን የእስራኤል መንግሥት እስራኤላውያን ለብዙ ዓመታት ሊያደርጉት ያልቻሉትን ፋሲካ ለማክበር በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጋበዘ (ቁጥር 1-12 ይመልከቱ)። በይሁዳ የሚገኙ እስራኤላውያን እንግዶችም ሆነ ጋባዦቻቸው ባደረጉት ግብዣና ስለተቀበሉበት መንገድ ምን አስደንቃችኋል?
በጣም ረጅም ጊዜ ሆኖት ስለነበረ ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ አንዳንድ ጎብኚዎች በፋሲካ በዓል እንዴት እንደሚሳተፉ በዝርዝር አያውቁም ነበር። 2 ዜና 30፡18–27ን ስታነቡ ከሕዝቅያስ ምላሽ እና መልሱ ካስከተለው ውጤት ምን ትማራላችሁ?
በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “አስታራቂዎች ይፈለጋሉ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ.)፣ 98 ይመልከቱ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
2 ዜና 14–16፤ 20
እግዚአብሔርን ማመን እችላለሁ።
-
በጌታ የመታመንን ሃሳብ ለማስተዋወቅ፣ ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ እንደ ጃንጥላ ወይም ጃኬት ያለ እንዳያረጥባችሁ የምታምኑትን ነገር ለልጆቻችሁ ልታሳዩ ትችላላችሁ። እነዚህን ነገሮች ለምን ማመን እንደምንችል እንዲናገሩ አድርጉ። ከዚያም ያንን በጌታ ላይ ካለን እምነት ጋር እንዲያወዳድሩ እርዷቸው። እርሱ መንፈሳዊ ደህንነት እንዲሰጠን ለምን እንተማመንበታለን?
-
ንጉሥ አሳ እና ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በጌታ በመታመን ለችግሮች እንዴት ምላሽ እንደሰጡ እንዲያውቁ ልጆቻችሁን መርዳት ትችላላችሁ (2 ዜና 14፡11፤ 20፡3–5፣ 12 ተመልከቱ)። ጌታን እንደምታምኑት ማሳየት የምትችሉበትን መንገድ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።
2 ዜና 20:1–29
እግዚአብሔር ጸሎቴን አድምጦ ይመልስልኛል።
-
የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ልጆቻችሁ የኢዮሣፍጥን ጸሎት ታሪክ እና የጌታን መልስ እንዲረዱ ሊያግዛቸው ይችላል። እናንተ እና ልጆቻችሁ እግዚአብሔር ጸሎታችሁን የሰማበትን እና የመለሰበትን ጊዜ ማካፈል ትችላላችሁ። መልሶቹ እናንተ ባልጠበቃችሁት መንገድ ወይም ጊዜ የመጡበትን ጊዜ ለማካተት አስቡ። እንደ “I Pray in Faith” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 14) ያለ የጸሎት መዝሙር የልጆቻችሁን እምነት ለመገንባት ሊረዳ ይችላል።
2 ዜና 26፡3–23
ትሁት መሆን እችላለሁ።
-
ስለ ትዕቢት አደገኛነት ለመማር ልጆቻችሁ በብሎኮች ወይም በትንሽ ኩባያዎች ግንብ መገንባት ይችላሉ። እያንዳንዱን ብሎክ ወይም ኩባያ ግንቡ ላይ ሲያስቀምጡ ከ2 ዜና 26፡3–15 ላይ ከሚገኘው የዖዝያን ስኬቶች መካከል አንዱን እንዲለዩ እርዳቸው። ግንቡን ከጨረሱ በኋላ ዖዝያን እንዴት ረጅም እና ጠንካራ አድርጎ ሊያቆየው እንደሚችል ከልጆቻችሁ ጋር ተወያዩ። እንዲወድቅ ሊያደርገው የሚችለው ምንድን ነው? ከዚያም ቁጥር 16ን ስታነቡ፣ “ለጥፋት ል[ባችን] ታበየ” ምን ማለት እንደሆነ መናገር ትችላላችሁ። በቁጥር 16-23 ላይ በዖዝያን ላይ የሆነውን ለልጆቻችሁ አካፍሉ። የገነቡትን ግንብ እንዲያፈርሱ አድርጓቸው። ትሑት ለመሆን ምን ማድረግ እንደምንችል ተነጋገሩ።
ንጉስ ሕዝቅያስ እና ህዝቡ እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ © Lifeway Collection/licensed from goodsalt.com
2 ዜና 30
አስታራቂ መሆን እችላለሁ።
-
ከላይ ያለው ሥዕል የሚያሳየው ሕዝቅያስ ከእስራኤል መንግሥት የይሁዳን ጎረቤቶች ፋሲካ እንዲያከብሩ የጋበዘበትን ጊዜ ነው። ይህን ምስል ከልጆቻችሁ ጋር በመመልከት 2 ዜና 30፡18–19ን ማንበብ ትችላላችሁ፣ ይህም አንዳንድ እንግዶች በሙሴ ህግ መሰረት ራሳቸውን እንዳላጠቡ ይገልጻል። ሕዝቅያስ ምን አደረገ? ይህ እንግዶቹ ምን እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል? ልጆቻችሁ ከሌሎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ሕዝቅያስን እንዴት መምሰል እንደሚችሉ እንዲያስቡ እርዷቸው።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።