“ሐምሌ 13–19 (እ.አ.አ)። ‘በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ታመነ”፡ 2 ነገሥት 16-25 “ኑ፥ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ሐምሌ 13–19 (እ.አ.አ)። ‘በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ታመነ’” ኑ፣ ተከተሉኝ፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
የእስረኞች ማምለጥ፣ በጄምስ ጃኩስ ጂሴፍ ቲሶት እና ሌሎች
ሐምሌ 13–19 (እ.አ.አ)፡ “በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ታመነ”
2 ነገሥት 16–25
የነቢዩ ኤልሳዕ አገልግሎት አስደናቂ ቢሆንም፣ በሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት ያሉ ሰዎች ንሰሃ አልገቡም። በጊዜ ሂደት የአሦር መንግሥት አሥሩን የእስራኤል ነገዶች አሸነፈና በታተናቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የደቡባዊው የይሁዳ መንግሥት ብዙም የተሻለ አልነበረም፤ በዚያም የጣዖት አምልኮ ተስፋፍቶ ነበር።
በዚህ ሁሉ መንፈሳዊ ውድቀት ውስጥ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ዘገባዎች ለተወሰነ ጊዜ ሕዝባቸውን ወደ ጌታ የመለሱ ሁለት ጻድቃን ነገሥታትን ይጠቅሳሉ። አንደኛው ሕዝቅያስ ነበር። በእሱ የግዛት ዘመን አሶሮር የይሁዳን አብዛኛውን ቦታ ተቆጣጥሮ ነበር። ሕዝቅያስና ሕዝቡ ግን ኢየሩሳሌምን በተአምራዊ መንገድ ባዳነው ጌታ ላይ እምነት አሳይተው ነበር። በኋላም፣ ከሌላ የክህደት ጊዜ ቀጥሎ ኢዮስያስ ነገሠ። የህጉን መጽሐፍ እንደገና በመገኘቱ ተነሳስቶ፣ ኢዮስያስ የብዙ ወገኖቹን ሃይማኖታዊ ህይወት የሚያድሱ ማሻሻያዎችን አመጣ።
እንደ እስራኤል እና ይሁዳ፣ ሁላችንም ጥሩም መጥፎም ምርጫዎችን እናደርጋለን። ሕይወታችን አንዳንድ ማሻሻያዎች እንደሚያስፈልገው ስንገነዘብ በይሁዳ ታሪክ ጨለማ አመታት ውስጥ ከነበሩት ከእነዚህ ሁለት ብሩህ ሁኔታዎች ማበረታቻ ማግኘት እንችላለን። ምናልባት የሕዝቅያስ እና የኢዮስያስ ምሳሌዎች “በእግዚአብሔር [እንድንታመን]” (2 ነገሥት 18፥22) ሊያነሳሱን ይችላሉ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
2 ነገሥት 18–19
እምነቴ ሲፈተን ለጌታ ታማኝ ሆኜ መቆየት እችላለሁ።
አብዛኞቻችን እምነታችንን የሚፈታተኑ ገጠመኞች አሉን። ለሕዝቅያስና ለሕዝቡ፣ የአሦር ሠራዊት ወደ ኢየሩሳሌም በቀረበ ጊዜ ከእነዚህ ፈተናዎች አንዱ ደረሰባቸው። እናንተ 2 ነገሥት 18–19ን ስታነቡ፣ በዚያ ጊዜ እናንተ በኢየሩሳሌም እንደምትኖሩ አድርጋችሁ አስቡ። ለምሳሌ በ2 ነገሥት 18፡28–37፣ 19:10–13 የአሦራውያንን ስድብ በምትሰሙበት ጊዜ ምን ይሰማችሁ ነበር? ምን ታደርጉ ነበር? አሦራውያን እስራኤላውያን በጌታ እንዳይታመኑ ያደረጓቸውን ምክንያቶች ዛሬ ላይ ሰይጣን እምነታችንን እንድንጠራጠር ከሚሰጠን ምክንያቶች ጋር አወዳድሩ። እንዲሁም የአሦራውያንን ምክንያቶች እናንተ በጌታ ከምታምኑበት ምክንያት ጋር ማነፃፀር ትችላላችሁ።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሕዝቅያስ ካደረገው ድርጊት ምን ትማራላችሁ? (2 ነገሥት 19፥1–7፣ 14–19ን ይመልከቱ)። ጌታ እንዴት ምላሽ ሰጠ? (2 ነገሥት 19፥35–37ን ይመልከቱ)። ሕዝቅያስ ታማኝ ሆኖ የቀጠለው ለምን ይመስላችኋል? (2 ነገሥት 18፡5–7 ይመልከቱ)። በአስቸጋሪ ጊዜያት ጌታ እንዴት እንደደገፋችሁ አሰላስሉ። በእሱ ላይ ያላችሁን እምነት ለመጨመር ምን ለማድረግ መነሳሳት ይሰማችኋል?
የፕሬዘዳንት ጄፍሪ አር. የሆላንድ መልእክት “Fear Not: Believe Only!” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2022፣ 34–36) ለፍርሃት ወይም ለጥርጣሬ የሚሆን ጠቃሚ ምክር አለው። እንደ “Let Us All Press On” (መዝሙሮች፣ ቁ. 243) ያለ መዝሙር አበረታታች መልዕክት ሊኖረው ይችላል። በእነዚህ መገልገያዎች ውስጥ እናንተን የሚረዳችሁ ምን ታገኛላችሁ?
እንዲሁም 2 ዜና 31–32፤ 3 ኔፊ 3–4፤ ዮርግ ክሌቢንጋት፣ “Valiant Discipleship in the Latter Days,” ሊያሆና ግንቦት 2022፣ 107–10 ይመልከቱ።
የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት መርጃን ይጠቀሙ። ቅዱሳት መጻህፍትን እንድትረዱ ቤተክርስቲያን ብዙ መገልገያዎችን ትሰጣለች። ለምሳሌ፣ በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ የቅዱሳን መጻህፍት መመሪያ፣ ርዕሶች እና ጥያቄዎች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን መጽሔቶችን ማግኘት ትችላላችሁ። በተጨማሪም፣ ብሉይ ኪዳንን በምታነቡበት ጊዜ፣ ኑ፣ ተከተለኝ በሚለው ርዕስ ውስጥ “በአእምሮ መያዝ ያለባቸው ሃሳቦች” በሚለው ውስጥ ጠቃሚ አውድ እና ግንዛቤዎችን ማግኘት ትችላላችሁ። “Jesus Will Say to All Israel, ‘Come Home’ የሚለው ርዕስ የ2 ነገሥት 16–25ን ጥናት ሊረዳ ይችላል።
2 ነገሥት 19፥20–37
ሁሉም ነገሮች በጌታ እጆች ናቸው።
የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ሠራዊቱ ኢየሩሳሌምን እንደሚቆጣጠር የሚያምንበት በቂ ምክንያት ነበረው (2 ነገሥት 17፤ 18፡33–34፤ 19፡11–13 ተመልከቱ)። ጌታ ግን ስለ ሰናክሬም በነቢዩ በኢሳይያስ በኩል የሚተላለፍ መልእክት ነበረው። በ2 ነገሥት 19፡20–34 ውስጥ ተመዝግቧል። በጌታ መልእክት ውስጥ በጌታ እና በእቅዱ ላይ እንድትታመኑ የሚያደርጋችሁን ምን እውነቶችን ታገኛላችሁ?
2 ነገሥት 21–23
ቅዱሳት መጻህፍት ልቤን ወደ ጌታ ሊያዞሩ ይችላሉ።
አንድ መንፈሳዊ ነገር እንደጎደላችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል? ምናልባት ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ግንኙነት ይበልጥ ጠንካራ መሆን እንደሚችል ተስምቷችሁ ይሆናል። ወደ እርሱ ለመመለስ ምን ረዳችሁ? 2 ነገሥት 21–23ን ስታነቡ እነዚህን ጥያቄዎች አሰላስሉ በንጉሥ ምናሴ መሪነት የይሁዳ መንግሥት ከጌታ እንዴት እንደራቀ (2 ነገሥት 21ን ተመልከቱ) እና ንጉስ ኢዮስያስ ራሳቸውን ወደ እርሱ እንዲመልሱ እንዴት እንደረዳቸው 2 ነገሥት 22–23። ኢዮስያስና ሕዝቡ እንዴትና ለምን ተለወጡ? (2 ነገሥት 22፡8–11፤ 23፡1–6፣ 21፣ 24 ይመልከቱ)።
ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምቦል የንጉሥ ኢዮስያስን ታሪክ “በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ካሉት ምርጥ ታሪኮች አንዱ” ብለው ጠርተውታል (የቤተክርስትያን ፕሬዘዳንቶች ትምህርቶች፡ ስፔንሰር ደብሊው ኪምቦል [2006]፣ 62)። ስለ ንጉስ ኢዮስያስ የተናገረውን የፕሬዘዳንት ኪምባልን ቃል አንብቡ (ገጽ 62–64)። ቅዱስ ቃሉ በእናንተ ውስጥ “[በኃይል ሲሠራ]” ያጋጠማችሁን ነገር ማሰብ ትችላላችሁ። እንደዚህ አይነት ተጨማሪ ልምዶችን ለማግኘት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
እንዲሁም አልማ 31፡5፤ “Josiah and the Book of the Law” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ።
Josiah and the Book of the Law
2 ነገሥት 23:1–25
ቃል ኪዳን በእኔ እና በጌታ መካከል ያለ ፍፁም የነፍስ መሰጠት ነው።
በ2 ነገሥት 23፡3 ላይ ኢዮስያስ ስለገባው ቃል ኪዳን የሚያስደንቃችሁ ምንድን ነው? ምዕራፍ 23ን ማንበብ ስትቀጥሉ፣ ኢዮስያስ ለጌታ ያለውን ቁርጠኝነት ለማሳየት ምን እንዳደረገ አስተውሉ (በተጨማሪም በዚህ ንድፍ መጨረሻ ላይ ያለውን ሥዕል ተመልከቱ)። ለእርሱ ያላችሁን ቁርጠኝነት እንዴት ማሳየት ትችላላችሁ?
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
2 ነገሥት18:3–6፤ 19:14–19
የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን ማመን እችላለሁ።
-
በ2 ነገሥት 18፡3፣ 5–6 ልጆቻችሁ ሕዝቅያስን ጥሩ ንጉሥ ያደረገውን እንዲያውቁ እርዷቸው። ከዚያም 2 ነገሥት 19፡14–19ን አብራችሁ ስታነቡ፣ በጌታ እንደሚታመን እንዴት እንዳሳየ ማወቅ ይችላሉ። የኢየሱስን ምስል በማሳየት ለምን እርሱን እንደምናምነው መናገር ትችላላችሁ። በጌታ እንደምንታመን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
2 ነገሥት 22:1–7
የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያምኑኝ ይችላሉ።
-
በ2 ነገሥት 22፡1 ላይ ኢዮስያስ ሲነግሥ ዕድሜው ስንት እንደነበር ልጆቻችሁ እንዲያውቁ እርዷቸው። ስለ ኢዮስያስ በቁጥር 2 ላይ ምን እንማራለን? ጌታን መከተል እና ወደ “ቀኝም ግራም” አለማለትን የሚያሳይ አክቲቪቲ አስቡ።
-
በ2 ነገሥት 22፥3–7 ውስጥ የተገለጹት ሠራተኞች “የታመኑ [ስለነበሩ]” ቤተመቅደሱን እንደገና ለመገንባት በሚውለው ገንዘብ እምነት ተጥሎባቸው ነበር (ቁጥር 7)። እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ ስለምትታመኑባቸው ነገሮች ማውራት ትችላላችሁ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንደ ተጠቀሱት ሰራተኞቹ እምነት የሚጣልብን ለመሆን እንዴት እንችላለን?
አንድ ጸሐፊ ለንጉሥ ኢዮስያስ የተሸበለለ ብራና ሲያመጣ የሚያሳይ ስዕል፣ በሮበርት ቲ. ባሬት
2 ነገሥት 22፡8–11፤ 23፡2–32
ቅዱሳት መጻሕፍት ኢየሱስ ክርስቶስን እንድከተል ያስተምሩኛል።
-
በ2 ነገሥት 22-23 ውስጥ ያለውን የንጉሥ ኢዮስያስን ታሪክ ለማስተዋወቅ፣ የቅዱሳት መጻህፍትን ቅጂ በክፍል ውስጥ መደበቅ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ እንዲፈልጉት ጋብዟቸው። ከዚያም ከኢዮስያስ ቄሶች አንዱ ቅዱሳት መጻህፍትን በቤተመቅደስ ውስጥ ባገኘ ጊዜ የሆነውን ማካፈል ትችላላችሁ (2 ነገሥት 22፡8–11 ይመልከቱ፤ እንዲሁም “ንጉሥ ኢዮስያስ”ን በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 148–49 ይመልከቱ)። ቅዱሳት መጻህፍት ባይኖሩን ኖሮ በእኛ ላይ ምን ሊሆን ይችል ነበር? ዛሬ ቅዱሳት መጻህፍት ለእኛ በመኖራቸው ለምን እንደምትደሰቱ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።
1:36King Josiah
-
2 ነገሥት 23፡2–3ን ካነበባችሁ በኋላ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ “እግዚአብሄርን ተከት[ላችሁ] [እንድትሄዱ]” ስላነሳሷችሁ ቅዱሳት መጻሕፍት ማውራት ትችላላችሁ (ቁጥር 3)። እንዲሁም ስለ ቅዱሳት መጻህፍት እንደ“Search, Ponder, and Pray” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 109) አይነት መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ።
2 ነገሥት 23፡1–3
ቃል ኪዳኔን ከእግዚአብሔር ጋር እጠብቃለሁ።
-
ኢዮስያስ እና ህዝቡ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በተማሩ ጊዜ፣ እነርሱን ለመኖር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር። ስለዚህ ነገር 2 ነገሥት 23፡1–3ን ከልጆቻችሁ ጋር አንብቡ እንዲሁም ህዝቡ ስለጌታ ትእዛዛት ያላቸውን ስሜት የሚያሳዩ ቃላትን ወይም ሀረጎችን እንዲያገኙ እርዷቸው። ልጆቻችሁ ቆመው “ቃል ኪዳን ገቡ” ምን ማለት እንደሆነ ሊናገሩ ይችላሉ። ከዚያም ባሉበት በመራመድ “እግዚአብሄርን ተከት[ሎ] መሄድ]” ምን ማለት እንደሆነ መነጋገር ይችላሉ። በመቀጠል፣ እጃቸውን በልባቸው ላይ በማድረግ ቃል ኪዳኖቻችንን “በፍፁም ል[ባችን]” መጠበቅ የምንችልባቸውን መንገዶች ሊጠቁሙ ይችላሉ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።