“በአእምሮ ሊያዝ የሚገቡ ሀሳቦች፥ ‘ኢየሱስ ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ይላል፣ “ወደቤት ኑ፣”’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስትያን፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“በአእምሮ ሊያዝ የሚገቡ ሀሳቦች፥ ‘ኢየሱስ ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ይላል፣ “ወደቤት ኑ”’” ኑ፥ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስትያን፥ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
በአእምሮ ሊያዝ የሚገቡ ሀሳቦች
“ኢየሱስ ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ይላል፣ ‘ወደቤት ኑ’”
በሲና ምድረበዳ ውስጥ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች በተራራ ስር ሰበሰበ። እዚያ ጌታ በቅርቡ ነፃ የወጡ ባሪያዎችን ወደ ኃያል ህዝብ መለወጥ እንደሚፈልግ አወጀ። “የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ” (ዘጸአት 19፥6) አላቸው። እጅግ በጣም ትልልቅ እና ጠንካራ በሆኑ ጠላቶች በሚከበቡበት ጊዜም እንኳን እነርሱ እንደሚለሙ እና እንደሚበለፅጉ ቃል ገባ።
ይህ ሁሉ የሚሆነው እስራኤላውያን ብዙ ወይም ጠንካራ ወይም ችሎታ ያላቸው በመሆናቸው አልነበረም። “ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ” (ዘጸአት 19፥5) ይሆናል ብሎ ጌታ አብራራ። ታላቅ የሚያደርጋቸው የራሳቸው ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር ሃይል ነበር።
ሆኖም እስራኤላውያን ሁል ጊዜ ድምፁን አልታዘዙም፣ ከጊዜም በኋላ ቃል ኪዳኑን መጠበቅ አቆሙ። ብዙዎች ሌሎች አማልክትን ማምለክ እና በአካባቢያቸው ያሉትን ልምዶች መከተል ጀመሩ። ከሌላው ሁሉ የሚለዩ ህዝቦች ያደረጋቸውን ነገር ማለትም ከጌታ ጋር የቃል ኪዳን ግንኙነታቸውን ተው። ያለ እግዚአብሔር ሃይል ጥበቃ ጠላቶቻቸውን የሚያስቆም ምንም አልነበረም።
መበታተን
ከ735 እስከ 720 ም.ዓ. ገደማ መካከል፣ አሶራውያን ከአሥራ ሁለቱ ነገዶች ወደ አሥሩ የሚገኘውን የሰሜኑን የእስራኤል መንግሥት በመውረር በሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያንን ወደ ተለያዩ የአሶር ግዛቶች በምርኮ ወሰዱ። እነዚህ እስራኤላውያን ከትውልድ አገራቸው ስለተወገዱና ወደ ሌሎች ብሔራት በመበተናቸው በከፊል “የጠፉ ነገዶች” በመባል ይታወቃሉ። ነገር ግን እነርሱ በተጨማሪ በጥልቅ ስሜት ውስጥ ጠፍተዋል፥ ከጊዜ በኋላ እንደ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሰዎች የመሆን ስሜታቸውን አጥተዋል።
በጊዜ ሂደት በደቡባዊ የይሁዳ ግዛት የሚገኙ ህዝቦች ከጌታ ፈቀቅ አሉ። አሶራውያን አብዛኞቹን መንግሥት አጠቁ እንዲሁም ድል ነሱ፤ በተአምራዊ ሁኔታ የተጠበቀችው ኢየሩሳሌም ብቻ ነበረች። በኋላም፣ በ597 እና 580 መሃል ባቢሎናውያን ቤተመቅደሱን እንዲሁም ብዙ ሰዎችን በመማረክ ኢየሩሳሌምን አጠፉ። ከ70 ዓመታት ገደማ በኋላ፣ የይሁዳ ቀሪዎች ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ቤተመቅደሱን እንደገና እንዲገነቡ ተፈቅዶላቸው ነበር። ቢሆንም፣ አብዛኞቹ በባቢሎን ቆዩ።
የኢየሩሳሌም በናቡዘረዳን መደምሰስ፣ በዊልያም ብራሴይ ሆል © Providence Collection/licensed from goodsalt.com
ትውልዶች እያለፉ ሲመጡ፣ ከሁሉም ነገዶች የመጡ እስራኤላዊያንን “ወደማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ [ተበትነው” ነበር (ዘካሪያስ 7፥14)። አንዳንዶቹን ጌታ ወደ ሌላ ሃገር ወሰዳቸው። ሌሎቹ ደግሞ ምርኮን ሽሽት ወይም ለፖለቲካዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ከእስራኤል ወጡ።
እነዚህን ክስተቶች ሁሉ የእስራኤል መበታተን እንላለን። ለበርካታ ምክንያቶች ስለ መበታተን ማወቅ አስፈላጊ ነው። አንደኛ ነገር፣ ይህ የብሉይ ኪዳን ዋና ርዕስ ነው፥ ብዙ የብሉይ ኪዳን ነቢያት እስራኤልን ወደ መበታተን ስላመጣው መንፈሳዊ ውድቀት ምስክሮች ነበሩ። አስቀድመው አይተውት አስጠንቅቀውም ነበር። አንዳንዶቹ በዚያ መሃል ኖሩ። በብሉይ ኪዳን ውስጥ የኢሳይያስን፣ የኤርምያስን፣ የአሞጽን እና ሌሎችን ነቢያትን መጻህፍት በመጨረሻዎች ክፍል ስታነቡ ይህንን ማስታወሱ ጠቃሚ ነው። ይህ በአእምሮአችሁ እንዳለ፣ ስለ አሦር እና ባቢሎን፣ ስለ ጣዖት አምልኮ እና ስለ ምርኮ፣ ስለ ጥፋት እና በመጨረሻም ስለ ዳግም መመለስ ያላቸውን ትንቢት ስታነቡ ምን እየተናገሩ እንደሆነ ታውቃላችሁ።
የእስራኤልን መበታተንን መረዳት መፅሐፈ ሞርሞንንም በደንብ ለመረዳት ይረዳችኋል፣ ምክንያቱም መፅሐፈ ሞርሞን የተበታተነ የእስራኤል ቅርንጫፍ መዝገብ ክፍል ስለሆነ ነው። ይህ መዝገብ የሚጀምረው ባቢሎናውያን ከማጥቃታቸው ጥቂት ጊዜ ቀደም ብሎ ወደ 600 ም.ዓ. አካባቢ የሌሂ ቤተሰቦች ከኢየሩሳሌምን ሲሺሹ ነው። ስለ እስራኤል መበተን ትንቢት ከተናገሩ ነቢያት መካከል ሌሂ አንዱ ነበር። እንዲሁም ቤተሰቦቹ፣ የእስራኤልን ቤት ቅርንጫፍ አካል በመውሰድ በአለም ሌላኛው ክፍል፣ በአሜሪካ ውስጥ በመትከል፣ ያንን ትንቢት እንዲፈፀም አግዘዋል።
መሰባሰብ
የእስራኤል መበታተን ግን የታሪኩ ግማሽ አካል ነው። ጌታ ህዝቡን አይረሳም፣ እንርሱን ቢተዉትም እንኳ አይተዋቸውም። እስራኤል እንደምትበታተን የተነገሩት ብዙ ትንቢቶች አንድ ቀን እንደሚሰበስባቸው ተስፋን የያዙም ነበሩ።
ያም ቀን ዛሬ ነው—የእኛ ቀን። መሰባሰቡ ተጀምሯል። በ1836 (እ.አ.አ)፣ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች በሲና ተራራ ስር ከሰበሰበ በኋላ በሺዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በኋላ፣ ሙሴ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ለጆሴፍ ስሚዝ “ከምድር አራት ማዕዘናትን የእስራኤልን መሰብሰቢያ ቁልፎችን” ለመስጠት ተገለጠ (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 110፥11)። አሁን እነዚህን ቁልፎች በሚይዙ ሰዎች መሪነት፣ የጌታ አገልጋዮች መሄድ ከሚችሉበት፣ የእስራኤል ነገዶች ከእያንዳንዱ ሃገር እየተሰበሰቡ ናቸው።
ሙሴ፣ ኤልያ እና ኤሊያስ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ታዩ፣ በ ጌሪ ኢ. ስሚዝ
ፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ይህንን መሰብሰብ “ዛሬ በምድር ላይ እየተከናወነ ያለው እጅግ አስፈላጊ ነገር” ነው ብለውታል። ምንም ነገር በትልቅነት አይወዳደርም፣ ምንም ነገር በአስፈላጊነቱ አይወዳደርም፣ ምንም ነገር በግርማዊነት አይወዳደረውም። ምርጫችሁ ከሆነ፣ የምትፈልጉ ከሆነ፣ የዚያ ታላቅ ነገር አካል መሆን ትችላላችሁ።”
እንዴት መርዳት እንችላለን? እስራኤልን መሰብሰብ ማለት ምን ማለት ነው? አሥራ ሁለቱን ነገዶች በአንድ ወቅት ወደ ነበሩበት ምድር መመለስ ማለት ነው? በእርግጥም፣ ከዚያ እጅግ የላቀ፣ እጅግ በጣም ዘለአለማዊ የሆነ ማለት ነው። ፕሬዘዳንት ኔልሰን እንዳብራሩት፤
“ስለ መሰብሰብ፣ ስናወራ እያልን ያለነው ይህን ቀላል እውነት ነው፤ እያንዳንዱ የሰማይ አባት ልጅ፣ በሁለቱም መጋረጃ በኩል ያሉት፣ የኢየሱስ ክርስቶስን የተመለሰው ወንጌል መልእክትን መስማት ይገባቸዋል። …
“በማንኛውም ግዜ መጋረጃው በሁለቱም በኩል በማንንም ከእግዚአብሄር ጋር ቃልኪዳን ለመግባት እና አስፈላጊ የጥምቀት እና የቤተመቅደስ ስርዓቶችን ለመቀበል የሚረዳ ማንኛውንም ነገር በምታደርጉበት ጊዜ ሁሉ እስራኤልን ለመሰብሰብ እየረዳችሁ ነው። እንደዚያ ቀላል ነው።”
ይህ የሚሆነው፣ ኢሳይያስ እንዳለው፣ “አንድ በአንድ” (ኢሳይያስ 27፥12) ወይም ኤርሚያስ አስቀድሞ እንዳለው፣ “ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን” ነው (ኤርምያስ 3፥14)።
እስራኤልን መሰብሰብ ማለት የእግዚአብሔርን ልጆች ወደ እርሱ መመለስ ማለት ነው። እነርሱን ከእርሱ ጋር ወደ የቃል ኪዳኑ ግንኙነታቸው መመለስ ማለት ነው። ከረጅም ጊዜ በፊት ለማቋቋም ያቀደውን “ቅዱስ ሕዝብ” እንደገና ማቋቋም ማለት ነው (ዘጸአት 19፥6)።
ወደቤት ኑ
ቃል ኪዳን ስለገባችሁ እናንተ የእስራኤል ቤት አካል ናችሁ። ተሰብስባችኋል፣ እና ሰብሳቢም ናችሁ። የቃል ኪዳኑ ህዝብ ለምእተ አመታት የዘለቀ አስደናቂ ታሪክ ከፍ እያለ ነው፣ እናንተ ደግሞ ቁልፍ ተሳታፊዎች ናችሁ። “ኢየሱስ ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ይላል፣ ‘ወደቤት ኑ’”፣ ያም ጊዜ አሁን ነው።
የሰብሳቢዎች መልእክት ይህ ነው፥ ወደ ቤታችሁ ወደ ኪዳኑ ኑ። ወደቤት ወደ ፅዮን ኑ። የእስራኤል ቅዱስ ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤት ኑ፣ እና እርሱም ወደ አባታችሁ ወደ እግዚአብሔር ያመጣችኋል።