“ሐምሌ 6–12 (እ.አ.አ)። ‘እስራኤል ዘንድ ነቢይ [አለ]”፡ 2 ነገሥት 2–7፣ “ኑ፥ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ሐምሌ 6–12 (እ.አ.አ)። ‘እስራኤል ዘንድ ነቢይ [አለ]’” ኑ፥ ተከተሉኝ፡ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
በ፣ በአኒ ሄንሪ ናደር
ሐምሌ 6–12 (እ.አ.አ)፡ “እስራኤል ዘንድ ነቢይ [አለ]”
2 ነገሥት 2–7
የነቢይ ዋናው ተልእኮ ስለ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር እና መመስከር ነው። ስለ ነቢዩ ኤልሳዕ ያለን መዝገብ ግን ብዙ ትምህርቱን ወይም ምስክርነቱን አያካትትም። መዝገቡ ልጅን ከሞት ማስነሳትን ጨምሮ ኤልሳዕ የሰራቸውን ተአምራቶች (2 ነገሥት 4፥18–37ን ይመልከቱ)፣ እንዲሁም በጥቂት ምግብ እጅግ ብዙ ህዝብን የመገበበትን (2 ነገሥት 4፥42–44ን ይመልከቱ)፣ እና ለምጻምን የፈወሰበትን (2 ነገሥት 5፥1–14 ይመልከቱ) ያካትታሉ። ስለዚህ ኤልሳዕ ስለ ክርስቶስ የተናገረው ቃል ባይኖረንም፣ ስለ ክርስቶስ የሚመሰክሩት የኤልሳዕ አገልግሎት እና ተአምራት አሉን። የጌታ ሕይወት ሰጪ፣ ገንቢ እና ፈዋሽ ኃይል ኃይለኛ መገለጫዎች ናቸው። በሕይወታችን ውስጥ አንዳንድ ጊዜ ከምናስበው በላይ ተአምራት ይከሰታሉ። እነርሱን ለማየት፣ ኤልሳዕ በፈራው ወጣት አገልጋዩ ፈንታ ሲጸልይ የነበረውም እምነት ልንሻ ይገባናል፡ “አቤቱ፣ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን እባክህ ግለጥ” (2 ነገሥት 6፥17)።
ስለ 2 ነገሥት ለበለጠ ማብራሪያ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ነገሥታት፣ መፅሐፈ” ይመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
2 ነገሥት 2–6
እግዚአብሔር በህይወቴ ውስጥ ተአምራትን ሊሰራ ይቻለዋል።
ተአምራት የእግዚአብሔርን ኃይል ያሳዩናል። ልክ ንጹህ ውሃ እንደሚያስፈልገው ምድረ በዳ (2 ነገሥት 2፡19–22 ተመልከቱ) ወይም መገኘት እንደሚገባው የጠፋ መጥረቢያ (2 ነገሥት 6፡4–7 ይመልከቱ) ምድራዊ ችግሮችን እንድናሸንፍ ሊረዱን ይችላሉ። ከሁሉም በላይ ግን ተአምራት ወደ ጌታ ሊመልሱን ይችላሉ። እናንተ 2 ነገሥት 2–6 ስታነቡ፣ የምታገኟቸውን ተአምራቶች ለመዘርዘር አስቡ እንዲሁም ከእያንዳንዱ የምትማሩትን መንፈሳዊ ትምህርቶች አሰላስሉ።
እንዲሁም ኤልሳዕ ያደረጋቸውን ተአምራት ኢየሱስ ክርስቶስ ካደረጋቸው ተአምራት ጋር ማወዳደር ትችላላችሁ (2 ነገሥት 4፡8–37 እና ሉቃስ 7፡11–16፤ 2 ነገሥት 4፡42–44 እና ዮሐንስ 6፡1–13፤ 2 ነገሥት 5፡1–15 እና ሉቃስ 17፡11–19)። እነዚህ ተአምራት ስለ አዳኙ እና ስለ ነቢያቱ ምን ያስተምሯችኋል?
በተጨማሪም 2 ኔፊ 26፡12–13፤ 27:23፤ ሞሮኒ 7፡35–37፤ “Seek and expect miracles” በራስል ኤም ኔልሰን “The Power of Spiritual Momentum,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022፣ 99–100 ይመልከቱ።
ኤልሳዕ የሱናማዊቱን ልጅ እያስነሳ፣ በፍሬድሪክ ሌይተን
2 ነገሥት 4፥8–17፤ 7፥1–16
ጌታ በነቢያቱ የተናገረውን ቃሉን ይፈጽማል።
ጌታ ኤልሳዕ ብዙውን ጊዜ ሊሆኑ የማይችሉ ስለሚመስሉ ነገር ግን ስለሚፈጸሙ ነገሮች ትንቢት እንዲናገር አነሳስቶታል። 2 ነገሥት 4፡8–17፤ 7፡1–16ን ስታነቡ ዛሬ ላይ በነቢያቱ በኩል ለሚመጣ የጌታ ቃል እንዴት ምላሽ እንደምትሰጡ አስቡ። በህይወት ካሉ ነቢያት ምን ትምህርቶች፣ ትንቢቶች ወይም ተስፋዎች ሰምታችኋል? እነዚያን ቃላት በእምነት ለመተግበር ምን እያደረጋችሁ ነው?
እንዲሁም 3 ኔፊ 29፡6፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፡37–38 “Teachings of Presidents” collection” ስብስብ፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።
2 ነገሥት 5
ትሁት እና ታዛዥ ከሆንኩ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊፈውሰኝ ይችላል።
2 ነገሥት 5ን በምታነቡበት ጊዜ የንዕማንን ለምጽ ከሚገጥማችሁ መንፈሳዊ ፈተና ጋር ለማነጻጸር አስቡ።
በሕይወታችሁ ውስጥ ስለመከራችሁ ከጌታ ነቢያት ምሪትን እንድትፈልጉ የሚያበረታታችሁ እንደ “ታና]ሿ] ብላቴና” ያለ ሰው አለ? (ቁጥር 2-3፣ 13 ይመልከቱ)።
ጌታ እንደ “[መታጠብ እና ንጹህ መሆን]” ቀላል የሚመስል ነገር እንድታደርጉ እየጋበዛችሁ ያለው ምንድን ነው? (ቁጥር 13)። የእሱን ቀላል ግብዣዎች እንዳትቀበሉ ምን እየከለከላችሁ ሊሆን ይችላል?
እናንተ እንደ ንዕማን ትሕትና ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?
የናዕማን ተሞክሮ በእስራኤል አምላክ ላይ ባለው እምነት ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንዳሳደረ አስተውሉ (ቁጥር 15ን ይመልከቱ)። ከዚህ ምን ትማራላችሁ?
በተጨማሪም ሉቃስ 4፥27፤ 1 ጼጥሮስ 5፥5–7፤ አልማ 37፥3–7; ኤተር 12፥27፤ ኤል. ዊትኒይ ክሌይተን፣ “Whatsoever He Saith unto You, Do It, ሊያሆና ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 97–99፤ “Naaman and Elisha” (ቪድዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።
Naaman and Elisha
ቅዱሳት መጻህፍትን ከህይወታችሁ ጋር አመሳስሉ። አንዳንድ ጊዜ በአንድ ታሪክ ውስጥ አካላዊ ነገሮችን ከመንፈሳዊ ነገሮች ጋር ስታወዳድሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የግል ትርጉም ማግኘት ቀላል ነው። ለምሳሌ፣ 2 ነገሥት 2–7ን በምታጠኑበት ጊዜ፣ በሕይወታችሁ ውስጥ ያሉ ሁኔታዎችን ከምጽ፣ ከተውሶ መጥረቢያ፣ ከዮርዳኖስ ወንዝ ወይም ከትልቅ ወራሪ ሠራዊት ጋር ማነጻጸር ትችላላችሁ። በእነዚህ ምእራፎች ውስጥ ጌታ ለእናንተ ምን መልእክት አለው?
2 ነገሥት 6፥8–23
“ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉ።”
ክርስቶስን ለመከተል በምትሞክሩበት ጊዜ፣ እንደ ኤልሳዕ ወጣት አገልጋይ—በቁጥር እንደተበለጣችሁ እንዲሁም ፍረሃት ተሰምቷችሁ ያውቃል? 2 ነገሥት 6፡8–23ን በምታጠኑበት ጊዜ በእሱ ቦታ እንደሆናችሁ አስቡ። ስለ ራሳችሁ ፈተናዎች፣ ሀላፊነቶች ወይም ወንጌልን ለመኖር ስለምታደርጉት ጥረት በተመለከተ ይህ ጽሁፍ ያላችሁን አስተሳሰብ እና ስሜት እንዴት ይለውጣል?
ስታሰላስሉ፣ የፕሬዘዳንት ሄነሪ ቢ. አይሪንግን ቃላት አስቡ፥ “ልክ እንደ ኤልሳዕ አገልጋይ፣ ከምታዩአቸው ተቃዋሚዎች ይልቅ ከእናንተ ጋር ያሉት ይበልጣሉ። አብረዋችሁ ያሉት አንዳንዶቹ በምድራዊ አይናችሁ አይታዩም። ጌታ ከፍ ያደርጋችኋል፣ ይህን የሚያደርገው አንዳንድ ጊዜ ሌሎች ከእናንተ ጋር እንዲቆሙ በመጥራት ነው” (“O Ye That Embark,” ሊያሆና፣ ህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 58)።
“[ከአንተ] ጋር ያሉት”ን (ቁጥር 16)— እግዚአብሔር እናንተን እንዲረዱ በህይወታችሁ ያስቀመጣቸውን ሰዎች ዝርዝር ለማውጣት አስቡ። መንፈሳዊ አይኖቻችሁን በመክፈት እነሱን ለይታችሁ እንድታውቋቸው እንዲረዳችሁ እርሱን ልትጠይቁት ትችላላችሁ። እናንተ ሌሎችን እንድትረዱ በሌሎች ህይወት ውስጥ አስቀምጧችሁ ሊሆን ይችላል። አንዳችሁ ከሌላችሁ ጥንካሬን እና ድጋፍን እንዴት ማግኘት ትችላላችሁ?
ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፡88 ላይ የገለፀውን አይነት ድጋፍ መቼ ተሰምቷችሁ ያውቃል?
በተጨማሪ የእህት ሚሼል ዲ. ክሬግ “Eyes to See” [ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ) 15-17) መልእክትን ማጥናት ትችላላችሁ። “እግዚአብሔር ምን እንዳይ ይፈልጋል?” በማለት ራሳችሁን ጠይቁ።
በ2 ነገሥት 6፡8-23 ላይ ያለውን ታሪክ በመጥቀስ፣ ሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራስባንድ እንዲህ ብለዋል፡- “ፍርሃታችንን ለማስወገድ እና አጋንንቶችን ለማሸነፍ የተላኩ የእሳት ሰረገሎች ሊኖሩን ወይም ላይኖሩን ይችላሉ፣ ነገር ግን ትምህርቱ ግልፅ ነው። ጌታ ከእኛ ጋር ነው፣ ስለእኛ ያውቃል፣ እንዲሁም እርሱ ብቻ መባረክ በሚችልበት መልኩ ይባርከናል። ጸሎት ሀሳባችንን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በሃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ ላይ ለማተኮር የሚያስፈልገንን ጥንካሬ እና መገለጥ ወደታች ሊጠራ ይችላል። ጌታ አንዳንድ ጊዜ ፍርሃት ሊሰማን እንደሚችል ያውቃል። እኔ እንደዚያ ተሰምቶኝ ያውቃል፣ እናንተም እንደዛው። … በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ አለም ተጽእኖን በሚቆጥርበት መንገድ በቁጥር ጥቂቶች ልንሆን እንችላለን ነገር ግን መንፈሳዊ ዓይኖቻችንን ስንከፍት ‘ከእኛ ጋር ያሉት ከእነሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉ’ (2 ነገ 6:16)” (“(Be Not Troubled” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 18፣ 19)። ጭንቀት ወይም ፍርሃት የሚሰማውን ሰው ለመርዳት እነዚህን ቃላት እንዴት ትጠቀማላችሁ?
በተጨማሪም “Dearest Children, God Is Near You,” መዝሙሮች፣፣ ቁጥር 96 ይመልከቱ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
2 ነገሥት 4
እግዚአብሔር በህይወቴ ውስጥ ተአምራትን ሊሰራ ይችላል።
-
ልጆቻችሁ ተአምር ምን እንደሆነ እንዲረዱ ከረዳችሁ በኋላ የቻሉትን ያህል ብዙ የተአምራት ምሳሌዎችን እንዲዘረዝሩ ጋብዟቸው። በወንጌል አርት መጽሐፍ ወይም ኑ፣ ተከተሉኝ ውስጥ ያሉ ሥዕሎች ሊረዱ ይችላሉ። ከዚያም በ2 ነገሥት 4፡1–7፣ 14–17፣ 32–35፣ 38–44 ውስጥ ተአምራትን መፈለግ ይችላሉ። እነዚህ ተዓምራት ስለ ሰማይ አባት ምን ያስተምራሉ?
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ እግዚአብሔር በተአምራት እንዴት ፍቅሩን እንዳሳየ መናገር ትችላላችሁ። እንዲሁም እንደ “God’s Gracious Love” (የወንጌል ላይብረሪ) ያለ መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ።
እንደ ምስክር ቁም፣ በክዋኒ ፖቪ ዊንደር
2 ነገሥት 5:1–15
እግዚአብሔር በነቢዩ በኩል ያዘዘውን ለማድረግ መምረጥ እችላለሁ።
-
በ2 ነገሥት 5፡1–3፣ 9–14 ላይ ያለውን ታሪክ ልጆቻችሁ እንዲማሩ እርዷቸው። በዚህ ሳምንት ዝርዝር ውስጥ “ኤልሳዕ ንዕማንን ፈወሰ” (በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 134-37) ወይም የንዕማንን ሥዕል ለመጠቀም አስቡ። ኤልሳዕ ሕመሙን እንደሚፈውስ ቢናገርም ንዕማን በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ መታጠብ ያልፈለገው ለምንድን ነው? ንዕማን የኤልሳዕን መመሪያ በመከተሉ የተባረከው እንዴት ነው? መታዘዝ እንደምትፈልጉ እርግጠኛ ባትሆኑም ጌታን ስለታዘዛችሁበት ልምድ አንዳችሁ ለሌላው ልታካፍሉ ትችላላችሁ።
1:52Elisha Heals Naaman
-
በተጨማሪም በ2 ነገሥት 5:13 ላይ የንዕማን አገልጋዮች ነቢዩን ኤልሳዕን ለመታዘዝ የረዳውን አጽንኦት ልትሰጡ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ጓደኞቻቸው ወይም የቤተሰቦቻቸው አባላት ነቢዩን እንዲያዳምጡ እና እንዲታዘዙ መርዳት ስለሚችሉባቸው መንገዶች ማውራት ይችላሉ።
2 ነገሥት 6:8–17
ብቻዬን አይደለሁም።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ በፈረሶች፣ በሰረገሎች እንዲሁም ሰይፍ በያዘ ሰራዊት እንደተከበባችሁ ማሰብ ትችላላችሁ። ምን ሊሰማችሁ ይችላል? ምንስ ታደርጋላችሁ? 2 ነገሥት 6፡16–17ን ስታነቡላቸው ልጆቻችሁ አይኖቻቸውን መጨፈን ይችላሉ። (በተጨማሪም “ኤልሳዕ እና የጌታ ሰራዊት” በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች 138-39 ወይም በዚህ ዝርዝር መጨረሻ ላይ ያለውን ሥዕል ይመልከቱ።) “ዓይኖቹን… ግለጥ” (ቁጥር 17) ወደሚሉት ቃላት ሲደርሱ ልጆቻችሁ ዓይኖቻቸውን እንዲገልጡ ጠይቋቸው። አገልጋዩ ስላየው ነገር ተናገሩ። ብቻችሁን የሆናችሁ በሚመስል ጊዜ እንኳን በችግሮቻችሁ ጊዜ ጌታ ከእናንተ ጋር እንደሆነ ስለተሰማችሁ ስሜት ለልጆቻችሁ አጋሩ።
1:9Elisha and the Lord’s Army
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ይመልከቱ።