“ነሐሴ 31–መስከረም 6 (እ.አ.አ) ‘እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን’፦ መዝሙረ ዳዊት 102-103፤ 110፤ 116-119፤ 127-128፤ 135-139፤ 146-150” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026 እ.አ.አ)
“ነሐሴ 31–መስከረም 6 (እ.አ.አ) “እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን”፦ ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
Reverential Return [በአንብሮት መመለስ]፣ በኬልሲ እና ጀሲ ላይትዌቭ
ነሐሴ 31–መስከረም 6 (እ.አ.አ) ፦“እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን”
መዝሙረ ዳዊት 102–103፤ 110፤ 116–119፤ 127–128፤ 135–139፤ 146–150
ለመዝሙረ ዳዊት መፅሐፍ የተለመደው የአይሁድ ባህላዊ ስም ቴሂሊም፣ ሲሆን ትርጉሙም “ውዳሴ” ማለት ነው። ይህ ቃል እንዲሁ ሃሌሉያ ከሚለው ቃል ጋር ይዛመዳል (ትርጉሙም “ያህዌህን አመስግኑ” ወይም “ጌታን አመስግኑ” ማለት ነው)። የመዝሙረ ዳዊትስ ዋና መልእክት ለማጠቃለል አንድ ቃል መምረጥ ቢኖርባችሁ፣ ውዳሴ ጥሩ ምርጫ ይሆናል። አአንዳንዶቹ መዝሙሮች “እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚለውን ቀጥተኛ ግብዣ ይዘዋል (በተለይም መዝሙረ ዳዊት 146–50 ተመልከቱ)፣ እና ሁሉም የአምልኮ እና የውዳሴ ስሜት ሊያነቃቁ ይችላሉ። መዝሙረ ዳዊት በጌታ ኃይል፣ በምህረቱ እና እርሱ ባደረጋቸው ታላላቅ ነገሮች ላይ አምነን እንድንቀበል ይጋብዙናል። ከእነዚህ ለየትኛውም ነገሮች እርሱን ልንከፍል አንችልም፣ ነገር ግን ልናወድሰው እንችላለን። ያ ውዳሴ ለተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ቅርጾች ሊኖሩት ይችላል—ያም መዘመርን፣ መጸለይን ወይም ምስክርነት መስጠትን ሊያካትት ይችላል። ብዙውን ጊዜ ወደ ጌታ እና የእርሱን ትምህርቶች ወደ መከተል ጥልቅ ቁርጠኝነት ይመራል። በሕይወታችሁ ውስጥ “ጌታን አመስግኑ” ማለት ማንኛውም ትርጉም ቢኖረውም፣ መዝሙረ ዳዊትን በማንበብ እና በማሰላሰል የበለጠ መነሳሳትን ማግኘት ትችላላችሁ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
መዝሙረ ዳዊት 102–3፤ 116
ጌታ በመከራዎቼ ሊያጽናናኝ ይችላል።
መዝሙረ ዳዊት 102፥1–11 ብዙውን ጊዜ በችግር ጊዜ የሚመጡትን የጭንቀት እና የመገለል ስሜቶችን እንዴት እንደሚገልጽ አስተውሉ። እናንተ ወይም ሌሎች እንደዚ አይነት ስሚት ተሰምቷችሁ ያውቅ ይሆናል። እናንተ መዝሙረ ዳዊት 102፥12–28፤ 103፤ 116ን ስታነቡ፣ በፈተናዎች ውስጥ “የእግዚአብሔርን ስም መጥራት” እንደምትችሉ እምነት የሚሰጡ ሀረጎችን ፈልጉ (መዝሙረ ዳዊት 116፥13)። በእርሱ ላይ ተስፋ የሚሰጡ ሀረጎችን ምልክት ማድረግ፣ ማስታወስ ወይም ለሌሎች ማጋራት ትፈልጉ ይሆናል።
ኢሳያስ 25፥8፤ ዕብራውያን 2፥17–18፤ አልማ 7፥11–13፤ ከሚሌ ኤን. ጆንሰን፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ እፎይታ ነው፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023(እ.አ።አ)፣ 81–83፤ “Where Can I Turn for Peace?”። (መዝሙር፣ ቁጥር 129)።
ካርል ሄንሪክ ብሎች (1834-1890 [እ.አ.አ])፣ Christ Healing the Sick at Bethesda[ክርስቶስ በቤተ ሳይዳ የታመሙትን እየፈወሰ]፣ 1883 (እ.አ.አ)፣ በዘይት ቀለም በሸራ ላይ የተሳለ፣ 100 ¾ x 125 ½ ኢንች። ብሪገም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የሥነጥበብ ሙዚየም፣ በጃክ አር. እና በሜሪ ሎይስ ዊትሊ ገንዘብ የተገዛ፣ 2001 (እ.አ.አ)።
መዝሙረ ዳዊት 110፤ 118
ኢየሱስ ክርስቶስ በመዝሙረ ዳዊት ላይ የተነገሩትን ትንቢቶች ፈጽሟል።
መዝሙሮች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት እና አገልግሎት የሚጠቁሙ ምንባቦችን ይዟል። እነዚህም ምሳሌዎች ናቸው፥
-
መዝሙረ ዳዊት 110፥1–4 (ማቴዎስ 22፥41–45፤ ዕብራውያን 5፥4–10፤ 6፥20 ተመልከቱ)
-
መዝሙረ ዳዊት 118፥22 (ማቴዎስ 21፥42፤ የሐዋርያት ስራ 4፥10–11፤ 1 ጴጥሮስ 2፥7 ተመልከቱ)
-
መዝሙረ ዳዊት 118፥25–26 (ማቴዎስ 21፥9 ተመልከቱ)።
እነዚህ ጥቅሶች ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ያስተምሯችኋል? ስለሱ እነዚህን ነገሮችን ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
መዝሙረ ዳዊት 119
የእግዚአብሔር ቃል በመንገዱ ላይ ይጠብቀኛል።
መዝሙረ ዳዊት 119 ውስጥ ህይወታችንን ወደ ሰማያዊው አባት ለመመለስ ከሚደረግ ጕዞ ጋር የሚያመሳስሉ ብዙ ሐረጎች ይገኛሉ። በምታነቡበት ጊዜ እንደ መሄድ፣ መንገድ፣ መንገዴ፣ እግሮች፣ እና መራቅ የመሳሰሉ ቃላትን ፈልጉ። የራሳችሁን የሕይወት ጉዞ—የት እንደነበራችሁ፣ አሁን ያላችሁበት እና የት አቅጣጫ እየሄዳችሁ እንደሆነ አስቡበት። ወደ ቤት ዳግም ለመመልስ ስላላችሁ ጉዞ በተመለከተ ከዚህ መዝሙር ምን ትማራላችሁ? የሌሎችን መንገድ በመመልከት ምን ተማራችሁ? በዚህ መዝሙር መሠረት በትክክለኛው ጎዳና ላይ ለመቆየት እንዲረዳችሁ እግዚአብሔር ምን አዘጋጀ?
አንድን መንገድ ወይም ካርታ መከተል በተሳካ ሁኔታ ወደ አንድ ቦታ ለመጓዝ የረዳችሁን ጊዜ አስቡ። ያ ልምምድ እግዚአብሔርን ስለመከተል ምን ያስተምራችኋል?
በብዙ ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ጌታ እና ነቢዮቹ ስለ አንድ መንገድ ይናገራሉ ከታች አንዳንድ ምሳሌዎች ይገኛሉ፦ እነዚህን ጥቅሶች በመመርመር ያገኘኸውን ነገር መጻፍ ወይም ለሌሎች ማካፈል ትችላለህ።
|
ቅዱሳት መጻህፍት |
ከእግዚአብሄር መንገድ ምን እማራለሁ? |
|---|---|
ቅዱሳት መጻህፍት ምሳሌ 8፥10–19 | |
ቅዱሳት መጻህፍት ማቴዎስ 16፥15–14 | |
ቅዱሳት መጻህፍት | |
ቅዱሳት መጻህፍት | |
ቅዱሳት መጻህፍት | |
ቅዱሳት መጻህፍት |
እነዚ እውነታዎች በእግዚአብሄር መንገድ ላይ እንዴት እንድትቆዩ ይረዷችኋል?
ከፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን የሚከተለው ምክር ምን ተጨማሪ ማስተዋል መማር ትችላላችሁ?
“በሕይወት ጉዞአችን ስኬታማ መሆን ከፈለግን መለኰታዊ መመሪያዎችን መከተል አለብን። እንዲህ ብሎ አስተማረ፣ “ባሰባችሁት ነገር ሁሉ ወደ እኔ ተመልከቱ፤ አትጠራጠሩ፣ አትፍሩ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥36)። መዝሙር እንዲህ ሲል ጽፏል፣ ‘ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው’ [መዝሙር 119፥105]። …
“በሕይወት ጉዟችሁ ብዙ መሰናክሎች ያጋጥማችኋል እና አንዳንድ ስህተቶችን ትሰራላችሁ። መንፈሳዊ መመሪያ ስሕተትን እንድታውቁና አስፈላጊውን ማስተካከያ እንድታደርጉ ይረዳችኋል። ወደተሳሳተ አቅጣጫ መሄድህን አቁሙ። ቅዱሳን መጻሕፍትን በጥንቃቄ አጥኑ ከዚያም “ወደ ዘለዓለማዊው ህይወት በሚመራው በዚህ በቀጭኑና ጠባቡ ጎዳና” ላይ ለመጓዝ የሚያስፈልገውን ንስሐ መግባትና ማስተካከል ትጀምራለህ። [2 ኔፊ 31፥18]” (“Living by Scriptural Guidance፣” ኢንዛይን፣ ህዳር 2000 (እ.አ.አ)፣ 17)
ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ “The Prodigal and the Road That Leads Home፣”ሊያሆና ተመልከቱ፣ ህዳር፣ 2023 (እ.አ.አ)፣ 86–88።
መዝሙረ ዳዊት 134፥36
ጌታ ከማንኛውም ጣዖት የበለጠ ኃይል አለው
በሐሰት አማልክት መታመን ሞኝነት ለምን እንደሆነ በመዝሙረ ዳዊት 135፥15–18፣ ውስጥ የተሰጡትን ምክንያቶች ልብ በሉ። ከጣዖት ጋር የሚመሳሰል ምን ነገር እንድታምን ሊገፋፋችሁ ይችላል? በመዝሙረ ዳዊት 134–36 ውስጥ የተገለጹትን ጌታ ማድረግ የሚችላቸውን ኃይለኛ ነገሮች መዘርዘር ትችላላችሁ። ለእናንተ ምን ኃይለኛ ነገሮችን አድርጎላችኋል?
መዝሙረ ዳዊት 139
ጌታ የልቤን ሃሳብ ያውቃል።
በመዝሙረ ዳዊት 139 ውስጥ ጌታ እናንተን እንደሚያውቅ ፣ ሃሳባችሁን እና ድርጊቶቻችሁን ፣ ጥንካሬዎቻችሁን እና ድክመቶቻችሁን እንደሚረዳችሁ እንድትረዱ ምን አገዛችሁ? ይህ እውነት በምርጫዎቻችሁ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?
መዝሙረ ዳዊት 146–50
“እግዚአብሔርን አመስግኑ።”
እነዚህን የመጨረሻ የውዳሴ መዝሙሮች በምታነቡበት ጊዜ ጌታን ለማመስገን ስላላችሁ ምክንያቶች አስቡ። እርሱን ማመስገን ለምን አስፈላጊ ነው? እርሱን የምታመሰግኑበት መንገዶች ምንድን ናቸው?
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
መዝሙረ ዳዊት 102፥1–2
ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያፅናናኝ እና ተስፋ ሊሰጠኝ ይችላል።
-
እናንተ ወይም ከልጆቻችሁ አንዱ መዝሙረ ዳዊት 102፥1–2 ማንበብ ትችላላችሁ፣ አምላክ በችግሮቻችን ወቅት እንዴት እንደሚረዳን እንመለከታለን። የሱን እርዳታ እንዴት ማግኘት እንችላለን? እርዳታን አስፈልጓችሁ እግዚአብሔር ፀሎታችሁን እንደሰማ የተሰማችሁን ጊዜ እርስ በርስ ተካፈሉ።
መዝሙር 119፥105
የእግዚአብሔር አመለካከት ከእኔ ይበልጣል ቃል እንደ ብርሃን ነው።
-
ልጆቻችሁ በጨለማ ውስጥ መሆን ምን እንደሚሰማቸው ማውራት ያስደስታቸው ይሆናል። ወይም በጨለማ ውስጥ ማድረግ የሚከብዳቸውን ነገሮች መወያየት ይችላሉ። ዓይኖቻቸው ጨፍነው አንድ ነገር እንዲያደርጉ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ ስዕል መሳል፣ ከመዝሙረ ዳዊት 119፥105 ስለ ብርሃንና ስለ እግዚአብሔር ቃል ምን ያስተምረናል?
-
የሰማይ አባታችን በመንገዱ እንድንመላለስ የሚረዳን አንድ ነገር ለማግኘት የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከቱ፦ መዝሙር 119፥47–48፤ 119፥105፤ 1 ኔፊ 11፥25፤ 2 ኔፊ 31፥20። በእግዚአብሔር መንገድ ለመፅናት ምን ማድረግ አለብን?
-
ልጆቻችሁ በመዝሙረ ዳዊት 119፥105 ላይ የተጠቀሱትን ነገሮች በስዕል መመልከት ያስደስታቸው ይሆናል። ጥቅሱን በሚያነቡበት ጊዜ ስዕሎቹን በቅደም ተከተል ማስቀመጥ ትችላላችሁ። በተጨማሪም “Teach Me to Walk in the Light [በብርሃን እንድሄድ አስተምረኝ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 177) ወይም “I Will Walk with Jesus[ከኢየሱስ ጋር እራመዳለሁ]” የመሳሰሉ ተዛማጅ መዝሙሮችን አብራችሁ መዘመር ትችላላችሁ (ከወንጌል ላይብረርይ)።
መዝሙረ ዳዊት 139፥1-3፣ 23-24
የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ያውቁኛል እናም ይወዱኛል።
-
ስለ እያንዳንዱ ልጆቻችሁ የምታውቋቸውን ነገሮች ዝርዝር ማዘጋጀትን አስቡ። ዝርዝሮቹን አንድ በአንድ ስታነቡ ልጆቻችሁ ስለ ማን እየተናገራችሁ እንደሆነ እንዲገምቱ ጠይቋቸው። ከዚያም መዝሙረ ዳዊት 139፥1-3ን በጋራ ካነበባችሁ በኋላ የሰማዩ አባት እና ኢየሱስ ስለ እኛ የሚያውቋቸውን ነገሮች ዘርዝሩ።
-
የመዝሙረ ዳዊት 139፥23-24 ቃላት በወረቀት ወይም በቦርድ ላይ ጻፍ። ልጆቻችሁ አምላክ ሊያደርግልን የሚችላቸውን ነገሮች የሚገልጹትን ሃሳቦች እንዲያሰምሩባቸው ጋብዟቸው። እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች እንዲያረግ ለምን እንፈልጋለን?
መዝሙረ ዳዊት 146፥1፣ 5–9
በጌታ ማመስገን እችላለሁ።
-
ምናልባት ልጆቻችን አንድ ሰው ያመሰገናቸውን ወይም ጥሩ ሥራ እንደሰሩ የነገራቸውን ልምዶችን ማካፈል ይችሉ ይሆናል። በመዝሙረ ዳዊት 146፥6–9 ላይ ጌታ ካደረጋቸው መልካም ነገሮች መካከል የተወሰኑትን አካፍሉ( ልጆቻችሁ የማያውቋቸውን ቃላት እንዲረዱ እርዷቸው)። ልጆቻችሁ አምላክ ስለሚያደርግባቸው ሌሎች ነገሮች እንዲናገሩ ጋብዟቸው። ለእነዚህ ነገሮች እንዴት ልናመሰነው እንችላለን?
በቤት ውስጥ መማር፤ ለሌሎች ማካፈል ፕሬዝደንት ረስልኤም. ኔልሰን ቤት “የወንጌል መማሪያ መአከል” መሆን እንዳለበት አስተምረዋል (“ምሳሌያዊ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆን፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 13)። በዚህ ሳምንት በግል ወይም በቤተሰብ በመዝሙር መጽሐፍ ላይ ያላችሁን ጥናት ለማስፋት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? ከጥናታችሁ በኋላ የተማራችሁትን እና የተሰማችሁን ነገር ለሌሎች ለማካፈል ሞክሩ። ይህን ማድረግ የምትችሉት በንግግር፣ በጽሑፍ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በቤተክርስቲያን ውስጥ ነው።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።