“መስከረም 7–13። ‘እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል’፦ ምሳሌ 1-4፤ 15-16፤ 22፤ 31፤ መክብብ 1፤ 11 ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) (2026 እ.አ.አ)
“መስከረም 7–13 “እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል፣’ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ ከህጻናት ጋር፣ በዳይሊን ማርሽ
መስከረም 7–13፤ “እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል”
ምሳሌ 1–4፤ 15–16፤ 22፤ 31፤ መክብብ 1–3፤ 11–12
የምሳሌ መጽሐፍ፣ አፍቃሪ የሆኑ ወላጆች የሰጧቸው ጥበብ ያዘሉ ምክሮች ስብስብ እንደሆነ አድርገህ ልትመለከተው ትችላለህ (ምሳሌ 1፥8ን ተመልከት)። ዋናው መልዕክቱ ጥበብን በተለይም የእግዚአብሔርን ጥበብ የምትፈልግ ከሆነ ሕይወታችሁ መልካም ይሆናል የሚል ነው። ነገር ግን ምሳሌ በመክብብ ነው የተከተለው፣ “ያን ያህል ቀላል አይደለም” የሚል ይመስላል። በመክብብ ውስጥ የተጠቀሰው ሰባኪው “ጥበብን [ያ]ውቅ ዘንድ ል[ቡ]ን ሰጠ” ነገር ግን “ትካዜ” እና “የሚጨምር ሀዘንን” አገኘ (መክብብ 1፥17–18)። በተለያዩ መንገዶች መጽሐፉ ይህን ጠየቀ፣ “ሁሉም ነገር ከንቱ፣ ጊዜያዊ እና እርግጠኛ ያልሆነ እንደሆነ በሚመስለው ዓለም ውስጥ ትክክለኛ ትርጉም ይኖር ይሆን?”
እና ይሁን እንጂ ሁለቱ መጽሐፎች ሕይወትን በተለያየ እይታ ቢመለከቱትም ሁሉቱም ተመሳሳይ እውነታዎችን ያስተምራሉ። መጽሃፈ መክብብ ይህን አወጀ፦ “የነገሩን ሁሉ ፍፃሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፣ ትዕዛዙንም ጠብቅ” (መክብብ 12፥13)። ይህ ምሳሌ ውስጥ በሙሉ የሚገኝ አንድ አይነት መርሆ ነው፦ “በፍፁም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን። (ምሳሌ 3:5፤ እንዲሁም ቁጥር 7ን ተመልከቱ). ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ስናምንና ስናከብር ሕይወታችን ፍጹም ባይሆንም፣ የተሻለች ነው።
ስለእነዚህ መጽሐፍት ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መጽሐፈ ምሳሌ” እና “መጽሐፈ መክብብ” የሚሉትን ተመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ምሳሌ 1–4፤ 15–16፤ መክብብ 1–3፤ 11–12
“ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ።”
መጽሐፈ ምሳሌ በጥበብ ግንዛቤዎች የተሞላ ነው። “ጥበብ” እንዲሁም እንደ “እውቀት” እና “መረዳት” ያሉ ተዛማች ቃላትን በምሳሌ 1–4፤ 15–16፣ መክብብ 1–3፤ 11–12 ውስጥ ሲታገኟቸው ምልክት አድርጉባቸው። እነዚህ ምዕራፎች ስለጥበብ በሚያስቡበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያሳድራሉ? ባገኙት ነገር ላይ በመመስረት “እግዚአብሔር [የሚሰጠውን] ጥበብ” እንዴት ይገልፁታል? (ምሳሌ 2፥6)። ከእግዚአብሔር ጥበብ ምን በረከቶች ይመጣሉ?
ማቴዎስ 7፥21–27፤ 25፥1–13 ተመልከቱ።
ሌሎች እየተማሯቸው ያሉትን እንዲያካፍሉ እግዟቸው። ተማሪዎች ስለ አዳኙ እና ስለ ወንጌሉ የሚማሩትን ነገር እርስ በርሳቸው እንዲያካፈሉ ዕድል ስጧቸው። ይህን ማድረግ የሚማሩትን እውነቶቸ የራሳቸው እንዲያደርጓቸው እና እንዲገልጿቸው ይረዳቸዋል። በሌሎች ሁኔታዎች ውስጥ እውነቶችን በማካፈል ችሎታቸው ረገድ ድፍረት እንዲያገኙ ይረዳቸዋል” (በአዳኘ መንገድ ማስተማር፣ 26)። ለምሳሌ ያህል፣ ተማሪዎቹ የአምላክን ጥበብ የሚገልጹ ጥቅሶችን ከምሳሌ ወይም ከመክብብ መጽሐፍ ላይ እንዲጽፉ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ከዚያም ተማሪዎች የተማሩትን እንዲናገሩ ጋብዟቸው።
ምሳሌ 1፥7፤ 2፥5፤ 3፥7፤ 15፥33፤ 16፥6፤ 31፥30፤ መክብብ 11–12
“በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን”
በምሳሌና በመክብብ መፅሐፍ ውስጥ የሚገኘው ሌላው ገፅታ ደግሞ “እግዚአብሔርን መፍራት” ነው። በምታነቡበት ጊዜ ይህን ሐረግ ተመልከቱ። እግዚአብሄርን መፍራት ሲባል ምን ማለት ነው? ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “Therefore They Hushed Their Fears [በሚለው መልእክት ውስጥ ግንዛቤዎችን ለማግኘት ሞክሩ]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2015(እ.አ.አ) 46-49)። የጌታ ፍርሃት ከሌሎች ዓይነት ፍርሐቶች የሚለየው እንዴት ነው?
እንዲሁም ምሳሌ 8፥13ተመልከቱ።
ምሳሌ 3፥5–7፤ 4
“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሄር ታመን፣”
አንድ ሰው በራሱ መረዳት ከመታመን ይልቅ “በጌታ መታመን” እንደሚሻል ለማሳመን ምን ማድረግ ትችላለህ? (ምሳሌ 3፥5)። የትኞቹን ንጽጽሮች ወይም የማስተማሪያ ትምህርቶች ትጠቀማለህ? በምሳሌ 3፥5-7 ላይ በሚገኘው ሃሳብ ላይ ስታሰላስሉ እንደሚከተለው ያሉትን አረፍተ ነገሮች እንዴት መጨረስ እንደምትችል አስብ፦ በጌታ መታመን … በራሳችን ማስተዋል መታመን …
ለምንድን ነው በራሳችን መረዳት መማር ጥበብ ያልሆነው? ጌታ እምነት የሚጣልበት መሆኑን ያወቃችሁት እንዴት ነው?
ያም ሆኖ፣ አንዳንድ ጊዜ በጌታ መታመን ይከብደን ይሆናል። ያ የሆነው ለምንድን ነው? ሽማግሌ ጄሪት ዋይ ጎንግ አንዳንድ ምክንያቶችን እና ጠቃሚ ምክሮችን ያቀርባል “Trust Again” (ሊያሆና፣ ህዳር 2021 97-99)። በዚህ መልእክት ውስጥ አንድ ሰው በጌታ ላይ ያለውን እምነት እንዲመልስ የሚረዱ ምን ታሪኮችን ወይም ትምህርቶችን ታገኛላችሁ?
ምሳሌ 3፥6 እና ምሳሌ 4 ሕይወትን “ከመንገድ” ወይም “ከጎዳና” ጋር ያመሳስሉታል። አምላክ “ጎዳናህን ያቀናልሃል” ምን ማለት ይመስላችኋል? (ምሳሌ 3፥6)። በምዕራፍ 4 ላይ “የእግርህን መንገድ አቅና” እንድታሰላስሉ የሚረዳችሁ ምን አገኛችሁ?(ቁጥር 26)። ለምሳሌ ቁጥሮች 11–12 እና 18–19 ትክክለኛውን መንገድ መከተል ስለበረከቶች ምን ያስተምራሉ? ቁጥር 26-27 ለእናንተ ምን ማለት ነው?
2 ኔፊ 31፥19-21፤ “ጌታ ሆይ፣ አንተን እከተልሃለሁ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 220 ተመልከቱ።
ምሳሌ 15፤ ምሳሌ 16፥24-32
“የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች።”
በምሳሌ 15-16 ውስጥ የተወሰኑት ምሳሌዎች ከሌሎች ጋር በተለይም ከምትወዱት ጋር የምትነጋገሩበትን መንገድ ለማሻሻል ሊያነሳሳችሁ ይችላል። ለምሳሌ ከ “ሻካራ ቃል” ይልቅ “የለዘበን መልስ” የተጠቀሙበትን ለየት ያሉ ጊዜዎች ያስቡ (ምሳሌ 15፥1)።
በተጨማሪም አዳኙ በምሳሌ 15፥1-4፣ 18 (ማርቆስ 12፥13-17፤ ዮሐንስ 8፥1-11ን ተመልከቱ) ላይ የሚገኙትን ትምህርቶች በተግባር ላይ ያዋለባቸውን ጊዜያት ማስታወስ ትችላላችሁ። ከሌሎች ጋር በምታደርጉት ግንኙነት የሱን ምሳሌውን እንዴት መከተል ትችላላችሁ?
በምሳሌ 16፥2415፤ 16፥24-32 ላይ የሚገኘው ምክር በዛሬው ጊዜ በኤሌክትሮኒክ የመገናኛ ዘዴዎች ላይ ሊሠራ የሚችለው እንዴት ነው? በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በጽሑፍ መልእክት አማካኝነት ለማካፈል ምክር ለመስጠት የሚረዱ ጥቅሶችን ለማግኘት ሞክር።
በተጨማሪም ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “ኢየሱስን መከተል: ሰላማዊ መሆን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022፣ 17-20፤ ሮናልድ ኤ ራስባንድ፣ “ቃላት አስፈላጊ ናቸው፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2024 (እ.አ.አ)፣ 70-77፤ ለወጣቶች ጥንካሬ፤ ምርጫዎችን ለማድረግ መመሪያ( 2022) (እ.አ.አ)፣ 11-12።
ልባም ሴትን ማን ማግኘት ይችላል? II፣ በሉዊስ ፓከር
ምሳሌ 31፥10–31
“እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች።”
ምሳሌ 31፥10–31 ስለ “ልባም ሴት” ወይም ታላቅ መንፈሳዊ ጥንካሬ፣ ችሎታ እና ተፅዕኖ ያላት ሴትን ይገልፃል። እነዚህ እያንዳንዱ ጥቅሶች ስለእርሷ የሚሉትን በራስዎ ቃላት ለማጠቃለል መሞከር ይችላሉ። ከእነዚህ ባሕርያት መካከል የትኛውን መሞከር ትችላችሁ?
መክብብ 1–3፤ 12
ምድራዊ ሕይወት ጊዜያዊ ነው።
መክብብ 1–2 እንደሚጠቅሰው በዚህ ዓለም ውስጥ ያሉ ብዙ ነገሮች “ከንቱ” (ወይም ጊዜያዊ እና ብዙ ጊዜ የማይጠቅሙ) እንደሆኑ ማስታወስ ለእርሶ ለምን ይጠቅማል? በመክብብ12 ውስጥ ለሕይወት ዘላለማዊ ዋጋዎችን የሚሰጥ ምን ያገኛሉ?
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ምሳሌ 1፥7፤ 2፥5፤ 15፥33፤ 16፥6፤ መክብብ 12፥13
“እግዚአብሔርን ፍሩ” ማለት “ውደዱት” እና “ታሀዘት ነው።
-
የቤተሰብ አባላት ምሳሌ 1፥7፤ 2፥5፤ 16፥6፤ መክብብ 12፥13ን እንዲገነዘቡ ለመርዳት መፍራት የሚለውን ቃል በ አክብሮት፣ ፍቅር፣ ወይም ታዛዥነት መተካት ሊረዳ ይችላል ( እንዲሁም ዕብራውያን 12፥28ተመልከቱ)። ይህ ስለእነዚህ ጥቅሶች በምናስብበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያሳድራል? እግዚአብሔርን እንደምንፈራ የምናሳየው እንዴት ነው?
ምሳሌ 3፥5–7
“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሄር ታመን፣”
-
አንተም ሆንክ ልጆችህ ከምሳሌ 3: 5-7 ጋር የሚስማሙ እርምጃዎችን ልትወስዱ ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ ልብን በእጆችህ በመስራት፣ ወደ አንድ ጐን በመጠምዘዝ፣ በቦታው በመሄድና ዓይኖችህን በመጠቆም። ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሉ ልባችን እንደምናምን እንዴት ማሳየት እንችላለን?
-
“በራስ ማስተዋል አትደገፍ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማሳየት ((ምሳሌ 3፡5) ልጆቻችሁ እንደ ግድግዳ በጠንካራ እና በረጋ ነገር ላይ እንዲደገፉ መጋበዝ አስቡበት። ከዚያም ጠንካራ ያልሆነን ነገር ለምሰሌ የቁም መጥረጊያን ለመደገፉ መሞከር ይችላሉ። ወይም ደግሞ እንደ መጽሐፍ ወይም የወረቀት ቍራጭ ያሉ የተለያዩ ጥንካሬ ያላቸውን ነገሮች በትር ወይም እርሳስ በመደገፍ መሞከር ይችላሉ። በራሳችን “የግል መረዳት” ሳይሆን በጌታ መታመን (ቁጥር 5) ለምንድን ነው አስፈላጊ የሆነው?
ጌታን ማመንን መማር፣ በ ካርሀኢ ፒተርሶን
ምሳሌ 15፥1፣ 18
መልካም ቃላትን መጠቀም እችላለሁ።
-
ምናልባት አናንተና ልጆቻችሁ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ማወቅ ያስፈልገዋል የምትሉትን ሰው ልታስቡ ትችላላችሁ። ምሳሌ 15፥1 በጋራ አንብቡ፣ ከዚያም ልጆቻችሁ ከዚህ ጥቅስ ያሰቡትን ሁኔታ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አግዟቸው። ምናልባት አንዳንድ “ቀለል ያሉ መልሶችን” መለማመድ ትችላላችሁ። ስለ ደግነት የሚናገር መዝሙር፣ ለምሳሌ “Love Is Spoken Here” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 190–91) ይህን መርህ ሊያጠናክር ይችላል።
-
“ለቁጣ የዘገየ” መሆን ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ(ምሳሌ 15፥1) እናንተ ወይም ልጆቻችሁ እናንተ( ወይም የምታውቀው ሰው) ቁጣ ተሰምቷችሁ ደግነት ለማሳየት የመረጣችሁባቸውን አጋጣሚዎች ልትነግሯቸው ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ በፍጥነት “ለቁጣ የዘገየ” መሆን የምንችልባቸውን ነገሮች እንዲያስቡ አግዟቸው። ለምሳሌ፣ ስለ ኢየሱስ ለማሰብ፣ የሰማይ አባትን እርዳታ ለመጠየቅ፣ የህፃናት ክፍል መዝሙር ለማስታወስ ወይም ከተቻለ ራሳችንን ለማግለል ፈጣን መሆን እንችላለን።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።