ኑ፣ ተከተሉኝ
ህዳር 23-29 (እ.አ.አ)። “እግዚአብሔርን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ”፣ አሞጽ፤ አብድዩ፣ ዮናስ


“ህዳር 23-29 (እ.አ.አ)። ‘እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ፣‘ “አሞጽ፤ አብድዩ፣ ዮናስ፦” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [(2026) እ.አ.አ]

“ህዳር 23-29 (እ.አ.አ)። ‘እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ፣‘” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ዮናስ በባህር ዳር ታጠበ

ዮናስ በነነዌ በውቅያኖስ ዳርቻ ላይ፣፣ በዳንኤል ሉዊስ

ህዳር 23-29 (እ.አ.አ)፦ “እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ”

አሞጽአብድዩዮናስ

ዮናስ ወደ ተርሴስ በሚሄድ መርከብ ውስጥ ነበር። በመርከብ ወደ ተርሴስ መጓዝ ምንም ስህተት አልነበረም ነገር ግን ከነነዌ ማለትም የእግዚአብሔርን መልዕክት ለማድረስ ዮናስ መሄድ ከነበረበት ቦታ በጣም እርቆ መገኘቱ እንጂ። መርከቡ ታላቅ ማዕበል ባጋጠማት ጊዜ፣ ዮናስ ባለመታዘዙ ምክንያት እንደነበረ አወቀ። በዮናስ ጥያቄ መሰረት፣ ማዕበሉን ለማቆም መርከበኞቹ በባሕሩ ጥልቅ ውስጥ ወረወሩት። የዮናስ እና የአገልግሎቱ መጨረሻ ይመስል ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር በዮናስ ላይ ተስፋ አልቆረጠም ነበር—ልክ በነነዌ ሰዎች ላይ፣ በእስራኤል ቤት ላይ እና በእያንዳንዳችን ላይ ተስፋ እንዳልቆረጠ ሁሉ።

ስለዚህ ዛሬም እንደ ዮናስ፣ አሞጽ፣ አብድዩ እና በነቢያቶቻችን ዛሬም መልእክት እየላከ ንስሐ ከገባን ለዘላለም እንደማንጣል። እግዚአብሔር ከሚገልጣቸው “ምስጢሮች” ሁሉ (አሞጽ 3፡7 ተመልከቱ)፣ ይህ በጣም ውድ ከሆኑት መካከል አንዱ ነው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ለመለወጥ ጊዜው አልረፈደም። አሁንም ከእርሱ ጋር በገባናቸው ቃል ኪዳኖች እንድንኖር ሊረዳን ይፈልጋል፣ እና ሌላ እድል ሊሰጠን ፈቃደኛ ነው።

ስለእነዚህ መጽሐፍት ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “አሞጽ፣” “አብድዩ፣” እና “ዮናስ” የሚሉትን ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

አሞጽ 3፥1–87፥10–15

የሴሚናሪ ምልክት
ጌታ በነቢያቱ በኩል እውነትን ይገልጣል።

አሞጽ 3፥3–6 ላይ፣ ነቢዩ አሞጽ ከምንሰማቸው ወይም ከምናያቸው ምልክቶች ልንደርስባቸው የምንችላቸውን መደምደሚያዎች ምሳሌዎችን አቅርቧል፤ አንበሳ ሲያገሣ ያደነውን ማርኮ ነበረበት አንድ ወፍ ወጥመድ ውስጥ ከተያዘ፤ እዚያ ማጥመጃው መሆን አለበት። በ ቁጥሮች 7–8፣ ውስጥ አሞጽ ይህን አመክንዮ ለነብያቶች ተግባራዊ አደረገ። አንድ ነቢይ ትንቢት ሲናገር ምን መደምደሚያ ላይ መድረስ እንችላለን? ከአሞጽ 7፥10–15 ስለ ነቢያት ሌላ ምን ትማራላችሁ?

ጌታ በነቢያቱ ምን ገለጠላችሁ?

ሽማግሌው ኡሊስ ሶሬስ “ነቢያት መኖራቸው የእግዚአብሔር ፍቅር ምልክት ነው” ብለዋል (“ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይናገራሉ፣” ሊያሆና ፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ) 99)። ይህን ዓረፍተ ነገር እንዴት እንደምታጠናቅቁ አስብ፡ “እግዚአብሔር እንደሚወደኝ አውቃለሁ፣ ምክንያቱም እሱ ነቢያትን እንደሚልክ…” ሊረዱ የሚችሉ አንዳንድ ጥቅሶች እነሆ፡- ዘዳግም 18፥18ሕዝቅኤል 3፥16–17ኤፌሶን 4፥11-141 ኔፊ 22፥2ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፥4–684፥36–38107፥91–92

ዛሬ ነቢያት አያስፈልጉም ብሎ ​​ለሚሰማው ሰው ምን ትሉታላችሁ?

በተጨማሪም፣ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “ነቢያት፣” በየወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

አሞጽ 4–5

“እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ።”

አሞጽ 4፥6–13፣ መሠረት፣ እስራኤላውያን ፈተና ካጋጠማቸው በኋላ ጌታ ምን እንደሚሆን ተስፋ አድርገው ነበር? (በተጨማሪ ሔለማን 12፥3 ተመልከት)። ፈተናዎቻችሁ በእግዚአብሔር ያልተላኩ ሊሆኑ ቢችሉም፣ ወደ እርሱ እንድትመለሱ እድሎችን እንዴት ሰጡሃችሁ?

አሞጽ 5፥ 4፣ 14-15ን በምታነብበት ጊዜ፣ ጌታ እንዴት እንደ ቸርነት እንዳደረገላችሁ አስብ። እሱን መፈለግ እንዴት ሕይወትን አመጣላችሁ?

አሞጽ 8፥11–12

የእግዚአብሔር ቃል የመንፈስ ርሃብን እና ጥማትን ያረካል።

አሞጽ 8፥11–12ን ሲያነቡ ርሃብ ለምን ያለእግዚአብሔር ቃል ከመኖር ጋር መልካም ንፅፅር እንደሆነ አስቡ (እንዲሁም ዮሐንስ 6፥26–352 ኔፊ 9፥50–5132፥3ሄኖስ 1፥4–8ተመልከቱ)። በመንፈሳዊ ሲትራቡ እንዴት ታውቃላችሁ?

እነዚህ ጥቅሶች ለታላቁ ክህደትም ይሠራሉ (ርዕሶች እና ጥያቄዎች “ክህደት”፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ተመልከት)። ይህ መንፈሳዊ “ረሃብ” የእግዚአብሔርን ልጆች ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው? ዳግም መመለሱ መንፈሳዊ ረሃብህን ያረካው እንዴት ነው?

በተጨማሪም “The Great Apostasy [ታላቁ ክህደት]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

16:36

The Great Apostasy

አብድዩ 1፥21

“አዳኞች … በጽዮን ተራራ ላይ” የተባሉት እነማን ናቸው?

አብድዩ 1፥21ን በመጥቀስ፣ ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ በቤተመቅደስ ውስጥ የሙታን ስርአቶችን ስንቀበል አዳኞች እንደምንሆን አብራርተዋል (“የመዝጊያ ንግግር፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2004 (እ.አ.አ)፣ 105 ተመልከቱ)። ያንን ሥራ በጥቂቱ ቢሆን አዳኝ ለኛ ካደረገልን ጋር እንዴት ይመሳሰላል? ይህን ሥራ መሥራታችሁ ወደ አዳኝ የመቅረብ ስሜት እንዲሰማችሁ የረዳችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም፣ “Holy Temples on Mount Zion[ቅዱሳት መቅደሶች በጽዮን ተራራ ላይ]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 289፤ ተመልከቱ።

የወጣቶች ቡድን ከቤተመቅደስ ውጭ

ዮናስ 1–4

ጌታ ወደ እርሱ ለሚመለሱ ሁሉ መሃሪ ነው።

ነነዌ በግፍ እና በጭካኔ የምትታወቅ የእስራኤል ጠላት ነበረች። ለዮናስ፣ ንስሐ ለመግባት መዘጋጀታቸው ከእውነታው የራቀ ይመስላል። የዮናስን አመለካከት ( ዮናስ13–4ተመልከቱ) ከአልማ እና ከሞዛያ ወንድ ልጆች ስሜቶች ጋር ማነፅፀር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ( ሞዛያ 28፥1–5አልማ 17፥23–25ተመልከቱ)። ከ ዮናስ3 ለመለወጥ ዝግጁ ለማይመስሉ ሰዎች እራሱ ወንጌልን ለማካፈል የሚያነሳሱ ምን ነገሮችን ተማራችሁ?

ትንቢተ ዮናስን ስታነቡ የጌታን ምህረት የሚያሣዩ ምሳሌዎችን ፈልጉ። ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔር የእስራኤል ጠላቶች ለነበሩት ለነነዌ ሕዝብ ምህረትን ሲሰጥ፣ ዮናስን “ደስ አላሰኘውም” እንዲሁም “ተቆጥቶ” ነበር (ዮናስ 4፥1)። በ ምዕራፍ4ውስጥ እግዚአብሔር ዮናስን ምን ለማስተማር እየሞከረ ይመስላችኋል? ምህረቱን በህይወታችሁ እንዴት እንዳገኛችሁ አሰላስሉ። የበለጠ መሐሪ እንድትሆኑ የሚረዳችሁ ከዮናስ ምን ትማራላችሁ?

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ይህ እሁድ የወሩ አምስተኛ ሰንበት ስለሆነ የልጆች ክፍል አስተማሪዎች የመማሪያ እንቅስቃሴ በ“አባሪ ለ፡ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ልጆችን ለዕድሜ ልክ ማዘጋጀት” እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ።

አሞፅ 3፥7

ነቢያት የኢየሱስ ክርስቶስ መልእክተኞች ናቸው።

  • ልጆቻችሁ አሞፅ 3፥7፣ን እንዲረዱ ለመርዳት ለአንዳቸው አንድ ቀላል መልእክት በሹክሹክታ መናገር እና መልእክቱን ለሌሎች ልጆች እንዲያካፍሉ መጠየቅ ትችላላችሁ። በዚህ አክቲቪቲ ውስጥ ያለው መልእክተኛ እንደ ነቢይ የሆነው እንዴት ነው? ጌታ ነቢያትን የሚሠጠን ለምንድን ነው?

  • ነቢያት ስለሚያደርጉት ነገር የበለጠ ለማወቅ እናንተ እና ልጆቻችሁ ከአሁኑ የቤተክርስቲያኑ ፕሬዝዳንት የመጡ የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች መከለስ ትችላላችሁ። እንደ “Follow the Prophet [ነብዩን ተከተሉ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 110-11) ያለ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ። የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመከተል ለምን እንደመረጣችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።

ልጆች ቅዱሳት መጻሕፍትን በቃል እንዲያስታውሱ እርዷቸው። ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ ስኮት ይህን አጋርተዋል፡-“የቅዱሳት መፃህፍት ጥቅሶችን በቃል ማስታወስ አዲስ ጓደኛን እንደማፍራት ነው። በችግር ጊዜ የሚረዳ፣ ማነሳሻን እና ማፅናኛን የሚሰጥ፣ እናም አስፈላጊ ለውጦችን ለማድረግ የሚረዳ የመነቃቃት ምንጭ የሆነ አዲስ ሰው እንደማግኘት ነው” (“የቅዱሳት መጻህፍት ሃይል፣” ኤንዛይን፣ ህዳር 2011 (እ.አ.አ)፣ 6)። ልጆቻችሁ አሞጽ 3፥7ን በሙሉ ወይም በከፊል እንዲያስታውሱ ለመርዳት፣ አንድ ላይ ጻፉት እና ደጋግሙት። ከዚያም ልጆቻችሁ ሙሉውን ጥቅስ ከትውስታ እስኪደግሙ ድረስ ጥቂት ቃላትን በአንድ ጊዜ መደምሰስ ወይም መሸፈን ትችላላችሁ።

አሞጽ 8፥11–12

የወንጌል ዳግም መመለስ የክህደት ረሃብእንዲያከትም አድርጓል።

  • አሞጽ 7፥10-12ን በምታነቡበት ጊዜ ልጆቻችሁ የተራቡ እንደሆኑ እንዲያስመስሉ ጋብዟቸው። የእግዚአብሔርን ቃል ስንራብ ምን ይሰማናል? ምናልባት ልጆቻችሁ የምትወዷቸውን አንዳንድ ጥቅሶች አንዳችሁ ለሌላችሁ በምታካፈሉበት ጊዜ እየበሉ እንደሆኑ ሊያስመስሉ ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁ ከታላቁ ክህደት የመጣውን “ረሃብ” እና በዳግም መመለሡ እንዴት እንዳበቃ እንዲገነዘቡ ለመርዳት የቅዱሳን ጽሑፎች መመሪያን፣ “ክህደት” (የወንጌል ላይብረሪ) መጠቀም ትችላላችሁ፣ ወይም “ከአዲስ ኪዳን በኋላ” (በአዲስ ኪዳን ታሪኮች፣ 167–70) ልትጠቀሙ ትችላላችሁ። በዘመናችን ጌታ ወንጌሉን ስለመለሰ አመስጋኝ ስለሆናችሁበት ምክንያት እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ።

    2:52

    After the New Testament

ዮናስ 1፥3

አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜም እንኳን ጌታ እርሱን እንድታዘዝ ይረዳኛል፣።

  • ልጆቻችሁ የዮናስን ታሪክ እንዲያውቁ ለመርዳት፣ “ነቢዩ ዮናስ”ን በየብሉይ ኪዳን ታሪኮች መከለስ ትችላላችሁ፣ እንዲሁም የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ተመልከቱ)። ከዚያም የሚከተሉትን መጠየቅ ትችላላችሁ

    • ዮናስ ጌታን ባልታዘዘ ጊዜ ምን ተፈጠረ? ( ዮናስ 1፥4-17ተመልከቱ)።

    • ዮናስ ንሰዓ ለመግባት ምን አደረገ? ዮናስ 1፥10-122፥1–4፣ 93፥1-4ተመልከቱ)

    • ዮናስ ሲታዘዝ ምን ተፈጠረ? (ዮናስ 3፥5ተመልከቱ)።

    2:30

    Jonah the Prophet

  • ልጆቻችሁ የዮናስን ታሪክ በመድገም ወይም በመተግበር ሊደሰቱ ይችላሉ። ጌታ ለእናንተ ከባድ የሆነ ነገር እንድታደርጉ የፈልገበትን አንዳንድ ልምዶችን ለሌሎች አካፍሉ። እርሱን እንድትታዘዙ የረዳችሁ እንዴት ነው?

ዮናስ 1፥4

ጌታ ወደ እርሱ ለሚመለሱ ሁሉ መሃሪ ነው።

  • ምናልባት ልጆቻችሁ ዮናስን ስለ ገጠመኙ ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉት ሊያስመስሉ ይችላሉ። ምን ጥያቄዎችን ይጠይቁት ይሆን? ዮናስ ስለ ጌታ የተማረውን ለማወቅ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ አበረታቷቸው። ለምሳሌ ዮናስ ስለ ጌታ ምሕረት ምን ሊሉ ይችላሉ? (ለምሳሌ፣ ዮናስ 2፥7-103፥104፥2)።

ኢየሱስ ከጣሪያው ወደ ወረደው ሰው ቀረበ

ክርስቶስ እና በደዌ የተመታው ሰው፣ በጄ. ከርክ ሪቻርድስ

  • አዳኝ ለሌሎች ምሕረት ሲያደርግ ልጆቻችሁ ምሳሌዎችን እንዲያስቡ እርዷቸው፣ እንደ ማርቆስ 2፥3-12ሉቃስ 23፥33-34፣ እና ዮሐንስ 8፥1-11። እናንተ እና ልጆቻችሁ የእነዚህን ምሳሌዎች ምስሎች መፈለግ ትችላላችሁ። ለሌሎች መሐሪ ለመሆን ምን አጋጣሚዎች አሉን?

ተጨማሪ ሃሳቦችን፣ ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።

ዮናስ ከጀልባው ላይ ተጥሎ ወደ ባሕሩ ሲወርድ የአንድ ትልቅ ዓሣ ጥላ እምብዛም አይታይም።

ዮናስ እና ዓሣ ነባሪ፣ በኬቨን ካርደን

የህፃናት የእንቅስቃሴ ገጽ፦ እርሱን እንድንታዘዝ ይረዳናል፣ አስቸጋሪ ቢሆንም።