“ህዳር 9–15 (እ.አ.አ)። ‘የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና’“፦ዳንኤል 1–6” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [(2026) እ.አ.አ]
“ህዳር 9–15 (እ.አ.አ) ‘የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና፣’“ ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
ዳንኤል የናቡከደነፆርን ህልም ሲፈታ፣ በግራንት ሮምኒ ክላሰን
ህዳር 9–15 (እ.አ.አ)፦ “የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና”
ዳንኤል 1–7
መቼም በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ እምነት ምክንያት ማንም ሰው ወደ እሳት እቶን ውስጥ ወይም ወደ አንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ሊወረውራችሁ አያስፈራራችሁም። ነገር ግን ማንኛችንም የእምነት ፈተና ሳይገጥመን በዚህ ሕይወት ውስጥ ማለፍ አንችልም። እንግዲያው ሁላችንም እንደ ዳንኤል፣ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ በወጣትነት ዕድሜያቸው በኃያሉ የባቢሎን መንግሥት ተማርከው ከነበሩት ሰዎች ምሳሌ መጠቀም እንችላለን ( 2ኛ ነገሥት 24፥10–16ተመልከቱ)። በተለያዩ እሴቶች በማያውቁት ባህል ተከበው እምነታቸውን እና የጻድቅ ወጋቸውን ለመተው ትልቅ ፈተና ገጠማቸው። ነገር ግን ለቃልኪዳኖቻቸው ታማኝ ሆኑ። ይህን ያደረጉት እንዴት ነው? እነዚያን ትንሽ እና ቀላል ነገሮች አደረጉ—እነሱም መጸለይ፣ መፆም፣ መልካም ጓደኞችን መምረጥ፣ በእግዚአብሔር መታመን እና ለሌሎች ብርሃን መሆን ናቸው። ልክ ዮሴፍ በግብጽ እና አስቴር በፋርስ እንዳደረጉት ሁሉ፣ ዳንኤል እና ጓደኞቹ በባቢሎን ውስጥ እምነታቸውን ጠበቁ እናም እግዚአብሔር አሁንም ድረስ በዚህ ቀን አማኞችን የሚያነሳሳ ታምራትን ሰራ።
ስለመጽሐፈ ዳንኤል አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ዳንኤል” የሚለውን ተመልከቱ፡፡
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ዳንኤል 1፤ 3፤ 6
እምነቴ ሲፈተን በእግዚአብሔር መታመን እችላለሁ።
በአንድ መልኩ፣ ሁላችንም በባቢሎን ውስጥ ነው የምንኖረው። መስፈርቶቻችንን ለመጣስ እና በክርስቶስ ከማመን ለመራቅ ብዙ ጊዜ ፈተናዎች ያጋጥሙናል። ዳንኤል1፣ 3፣ እና 6ን ሲታነቡ ዳንኤል፣ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ ስህተት እንደሆኑ የሚያውቁትን ነገሮች እንዲያደርጉ የተገፉበትን መንገዶች አስተውሉ። ለእነዚህ ሁኔታዎች ምን ምላሽ ሰጡ? ዳንኤል 1፥10-13፣ 3፥15–18፤ 6፥10ተመልከቱ) የእምነታቸው ውጤቶች ምንድን ነበሩ? ተቃውሞ ሲገጥማችሁ በጌታ እንድትታመኑ ከሚረዳችሁ ከእነዚህ ተሞክሮዎች ምን ተማራችሁ? እንዲሁም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦
-
ስህተት እንደሆነ የሚታውቁትን ነገር እንድታደርጉ ግፊት የተሰማችሁ መቼ ነው? ትእዛዙን ስለጠበቃችሁ ጌታ እንዴት ባረካችሁ?
-
እምነታችሁ ወደምትፈልጉት ተአምራት ካልመራችሁስ? (ለምሳሌ፣ አልማ14፥8–13ተመልከቱ)። በ ዳንኤል 3፥13–18፣ ውስጥ በሚያነቡት መሰረት ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ ይህን ጥያቄ እንዴት ይመልሱታል ብላችሁ ታስባላችሁ? የእነርሱ ምሳሌነት ፈተናዎቻችሁን የምትመለከቱበትን መንገድ የሚነካው እንዴት ነው?
-
የእናንተ የጽድቅ ምርጫዎች ሌሎችን በጌታ ወደ ታላቅ እምነት ሊመራቸው የሚችለው እንዴት ነው? (ዳንኤል 2፥47፤ 3፥28–29)። ምርጫዎቻችሁ በሌሎች ላይ ሊያመጡ የሚችሉትን ተጽእኖ አስቡ።
በተጨማሪም ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “Be Not Afraid, Only Believe [አትፍሩ እመኑ ብቻ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 76–24ን ተመልከቱ።
ሁሉንም ለማሳተፍ ሞክሩ። አዳኙ “… ሁሉም ወደ እሱ እንዲመጡ እና ከቸርነቱ እንዲካፈሉ ይጋብዛል (2 ኔፊ 26፡33)። ቤተሰባችሁን ወይም ክፍላችሁን እያስተማራችሁ ከሆነ፣ ለሁሉም ሰው በሆነ መንገድ እንዲሳተፍ እድል መስጠት የምትችሉባቸውን መንገዶች አስቡ። ለምሳሌ፣ ለማሰላሰል እና አስተያየት ለመስጠት ለእያንዳንዱ ሰው የቅዱሳት መጻህፍት ምንባብ፣ የጉባኤ መልእክት ክፍል፣ ወይም ከመዝሙር አንድ ቁጥር መስጠት ትችላላችሁ። ማንም ሰው እንዲሳተፍ ጫና አታድርጉ፣ ነገር ግን እድሎችን ስጧቸው።
ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ በእሳት እቶን ውስጥ፣ በዊልያም ማጉን
ዳንኤል 2
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ያለች የእግዚአብሔር መንግስት ናት።
ዳንኤል የናቡከደነፆር ህልም የወደፊት ዓለማዊ መንግስታትን እንደሚተነብይ በራዕይ አማክኝነት አየ እንዲሁም “ለዘላለም የማይፈርስ” የእግዚአብሔር የወደፊት መንግስትንም አየ (ዳንኤል 2፥44)። ሽማግሌ ዲ.ታድ ክርስቶፈርሰን እንዳስተማሩት፣ “ቤተክርስቲያኗ ያቺ በኋለኛው ቀን የተተነበየችው መንግስት ናት፣” “በሰው ሳይፈጠር ነገር ግን በሰማይ እግዚአብሔር የተዋቀረ እና ‘እጅ ሳይነካው ከተራራ የተፈነቀለ’ ምድርንም ለመሙላት እየተንከባለለ እንዳለ ድንጋይ [ናት]” (“Why the Church [ለምን ቤተክርስቲያን]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣111)። የድንጋዩን መግለጫ በ ዳንኤል 2፥34–35፣ 44–45፣ ውስጥ ስታነቡ ስለእግዚአብሔር የኋለኛው ቀን መንግስት አስቡ። ይህ ትንቢት እንዲፈጸም በመርዳት ረገድ የእናንተ ሚና ምንድን ነው?
እንዲሁም “Hark, All Ye Nations!፣” መዝሙር፣ ቁጥር 264 “God Gave Them Knowledge” (video) ተመልከቱ ChurchofJesusChrist.org
God Gave Them Knowledge
ዳንኤል 2፥1–30
ራዕይን መቀበል መንፈሳዊ ዝግጅትን ይጠይቃል።
ዳንኤል 2፥1–15ን ስትገመግም በዳንኤል ቦታ ራሳችሁን ብታገኝ ምን እንደሚሰማችሁ አስብ። ዳንኤል ምን አደረገ? ( ዳንኤል 2፥16–18ን ተመልከቱ)። አምላክ ዳንኤልን ያዘጋጀው እንዴት እንደሆነ ከዳንኤል 1፥17 ምን ትምህርት ማግኘት ትችላላችሁ? ዳንኤል የጌታን እርዳታ ካገኘ በኋላ ከተናገራቸው ቃላትና ድርጊቶች ምን ትምህርት ማግኘት ትችላላችሁ? (ዳንኤል 2፥19–30 ተመልከቱ)።
ዳንኤል 7፥13–14
ኢየሱስ ክርስቶስ የዘላለም አባት ልጅ ነው።
በአዳኝ ምድራዊ አገልግሎት ወቅት፣ ብዙ አይሁዶች በዳንኤል 7፥13 ላይ የሚገኘውን “የሰው ልጅ” የሚለውን ማዕረግ የሚመጣውን መሲሕ ለማመልከት አድርገው ይመለከቱት ነበር። ከዳንኤል 7፥13–14 ስለ መሲሑ ምን ተማራችሁ? (እንዲሁም ሙሴ 6፥57ተመልከቱ)።
አዳኝ እራሱን ብዙ ጊዜ “የሰው ልጅ” ሲል ይጠራል። አንዳንድ ምሳሌዎችን መከለስን አስቡ፡- ማቴዎስ 25፥31፤ ማርቆስ 9፥31፤ 10፥45። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለ ራሱ ምን እያስተማረ ነው? በማርቆስ 14፥61–64፣ ኢየሱስ ይህን መጠሪያ የተጠቀመው በሟች ህይወቱ የመጨረሻ ቀን ነው። የእሱን ቃል የሰሙት ሰዎች የሰጡትን ምላሽ ልብ በሉ። ዳንኤል ስለ ሰው ልጅ የተናገረው ትንቢት በማርቆስ 15 ላይ በእርሱ ላይ ስለደረሰው ነገር ያላችሁን ስሜት የሚነካው እንዴት ነው?
ኢየሱስ “የሰው ልጅ” መሆኑን በማወጁ እንደተጠላ ሁሉ አናንተም እውነትን በመናገራችሁ ስደት ሊደርስባችሁ ይችላል። በዳንኤል 7፥13–14 ያለውን ትንቢት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥29፣ 46 ካሉት ተስፋዎች ጋር አወዳድሩ።
በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49፥–16፤ የቅዱሳን መጻህፍት መመሪያ፤ “Son of Man [የሰው ልጅ]፣” ወንጌል ቤተመጻህፍት ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ዳንኤል 1፤ 3፤ 6
አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳ ኢየሱስ ትክክል የሆነውን እንዳደርግ ይረዳኛል።
-
ልጆቻችሁ በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ ካሉት አነቃቂ ታሪኮች እንዲማሩ ለመርዳት በዳንኤል 1፣ 3 እና 6 ላይ የተከናወኑትን ክንውኖች ሥዕሎች ማግኘት ትችላላችሁ (የዚህ ሳምንት የእንቅስቃሴ ገጽ ወይም Gospel Art Book [ወንጌል ጥበብ መጽሐፍ]፣ ቁጥር 23፣ 25፣ 26ተመልከት)። ከዚያም ሥዕሎቹን ፊት ለፊት አስቀምጣችሁ አንድ ልጅ አንዱን ገልብጦ ስለሚወክለው ታሪክ እንዲናገር መጋበዝ ትችላላችሁ። (ለእርዳታ፣ “ዳንኤልንና ጓደኞቹን፣” “ሲድራቅን፣ ሚሳቅን፣ እና አብድኔጎን፣” እና “ዳንኤል እና የአንበሶች ዋሻ” በብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 154–56፣ 160–62፣ 163–65 ተመልከት።)
1:39Daniel and His Friends
1:39Shadrach, Meshach, and Abed-nego
1:45Daniel and the Lions’ Den
-
ዳንኤል እና ጓደኞቹ በዳንኤል 1፣ 3 እና 6ላይ እንዳሉት ልጆቻችሁ የተሳሳተ ምርጫ እንዲያደርጉ ግፊት ሲደረግባቸው ሁኔታዎችን እንዲያስቡ እርዷቸው። ከባድ ቢሆንም ትክክለኛውን ምርጫ በማድረጋችሁ እንዴት እንደተባረካችሁ እርስ በርሳችሁ አካፍሉ። እንዲሁም ከዚህ ርዕስ ጋር የተዛመደ እንደ “Choose the Right [ትክክለኛውን ምረጥ]” (መዝሙሮች፣ ቁጥር 239ን) አይነት መዝሙር በአንድነት ልትዘምሩ ትችላላችሁ።
የቃሉን ጥበብ ማመን።
ዳንኤል 1፥1-17
የሰማይ አባት ሰውነቴን እንድንከባከብ ይፈልጋል።
-
ዳንኤል እና ጓደኞቹ የንጉሱን ስጋ እና ወይን አለመቀበላቸውን ታሪክ ማንበባችን የሰማይ አባት ዛሬ የሰጠንን የጤና ህግን በተመለከተ ውይይት ሊያነሳሳ ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89ተመልከቱ)። ምናልባት ዳንኤል እና ጓደኞቹ የተቀበሉትን በረከቶች መፈለግ እና በጥበብ ቃል ውስጥ ከተገቡት በረከቶች ጋር ማወዳደር ትችላላችሁ (ዳንኤል 1፥15-17 እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥18–21ተመልከቱ)።
ዳንኤል 2
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ያለች የእግዚአብሔር መንግስት ናት።
-
ዳንኤል 2፥31–35፣ 44–45ን ከልጆቻችሁ ጋር ስታነብ የናቡከደነፆርን ሕልም በሥዕል እንዲያሳዩ ልትጋብዛቸው ትችላለህ። በሕልሙ ውስጥ ያለው ድንጋይ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደሚወክል እንዲረዱ እርዷቸው። ከዚህ ህልም ስለ ቤተክርስቲያን ምን እንማራለን? በኋለኞቹ ቀናት የሰማይ አባት ቤተክርስቲያኑን ለማቋቋም ያደረጋቸውን አንዳንድ ነገሮች ልጆቻችሁ ሊሰይሙ ይችላሉ። እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ፣ ከቤተክርስቲያን ዳግም መመለስ የተገኙ ክስተቶችን ምስሎች ማሳየት ትችላላችሁ ( የወንጌል የስነጥበብ መጽሐፍ፣ ቁጥሮች 90–95ተመልከቱ።
ዳንኤል 6
የሰማይ አባት ብዙ ጊዜ እንድጸልይ ይፈልጋል።
-
ወደ የሰማይ አባት መጸለይ ለዳንኤል በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ዳንኤል 6ን አብራችሁ ስታነቡ እናንተ እና ልጆቻችሁ ስለዚህ ጥያቄ መነጋገር ትችላላችሁ። ከዚያም መጸለይ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ እርስ በርሳችሁ ልትነግሩ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሲጸልዩ የሚያሳዩትን ሥዕል መሳል ያስደስታቸው ይሆናል። የትም ብንሆን ወይም የምንፈልገው ወደ የሰማይ አባት መጸለይ እንደምንችል እርስ በእርሳቸው ለማስተማር ስዕሎቻቸውን ሊጠቀሙ ይችላሉ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።