“ህዳር 30–ታህሳስ 6 ‘በምሕረት ደስ ይለዋል’፦ ሚክያስ፤ ናሆም፤ ዕንባቆም፤ ሶፎንያስ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ህዳር 30–ታህሳስ 6 ‘በምሕረት ደስ ይለዋል፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
በመጀመሪያ ቃል ነበር፣፣ በኢቫ ቲሞቲ
ህዳር 30–ታህሳስ 6 (እ.አ.አ) “በምሕረት ደስ ይለዋል”
ሚክያስ፤ ናሆም፤ ዕንባቆም፤ ሶፎንያስ
ብዙውን ጊዜ ብሉይ ኪዳንን ማንበብ ማለት ስለጥፋት የተነገሩ ትንቢቶችን ማንበብ ማለት ነው።። ጌታ ስለ ፍርዱ ክፉዎችን ለማስጠንቀቅ ነብያትን በተደጋጋሚ ጠርቶ ነበር። የሚክያስ፣የናሆም፣ የዕንባቆም እና የሶፎንያስ አግልግሎቶች መልካም ምሳሌዎች ናቸው። እነዚህ ነብያት በወቅቱ ጠንካራ እና ኃያል የመሰሉትን—የነነዌን፣ የባቢሎንን አንዲሁም የኢየሩሳሌምን ከተሞች መውደቃቸውን በዝርዝር ተንብየዋል። ነገር ግን ያ ከሺዎች ዓመታት በፊት ነበር። ዛሬ እነዚህን ትንቢቶች ማንበብ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?
ምንም እንኳን እነዚያ ኩራተኞች እና ክፉ ከተሞች ቢወድሙም፣ ኩራት እና ክፋት አሁንም እንደቀጠለ ነው። በልቦቻችን ውስጥም እንኳን ዱካቸውን ሊሰማን ይችላል። የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእነዚህ ክፋቶች እንዴት እንደምንመለስ ይገልጻሉ። ዛሬም ቃላቶቻቸውን የምናነብበት አንዱ ምክንያት ይህ ሊሆን ይችላል። የጥፋት ነበያቶች ብቻ አልነበሩም—የነፃ መውጣትም ነብያት ነበሩ። የጥፋት መግለጫዎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ እና ይቅርታውን እንዲቀበሉ በተጋበዙት ግብዣዎች ተሞልተዋል። ሚክያስ እንዳስተማረው ጌታ እኛን በማውገዝ አይደሰትም ነገር ግን “በምሕረት ደስ ይለዋል” (ሚክያስ 7:18)። ይህ የጌታ የጥንት መንገድ ነበር፣ እንዲሁም ዛሬም የእርሱ መንገድ ነው። “መንገዱ ዘላለማዊ ነው” (ዕንባቆም 3፥6)።
ስለእነዚህ መጽሐፍት ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ሚክያስ፣” “ናሆም፣” “ዕንባቆም፣” እና “ሶፎንያስ” የሚሉትን ተመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ሚክያስ 6፥1–8
“እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድን ነው?”
ሚክያስ “ወደ እግዚአብሔር ፊት [መጥቶ] በልዑል አምላክ ፊት [መስገድ]” ምን እንደሚመስል እንድናስብ ይጋብዘናል (ሚክያስ 6፥6)። እግዚአብሔር ሕይወቶን ሲገመግም ለእርሱ ምን ጠቃሚ እንደሆነ ቁጥሮች 6–8 ምን ይጠቁሞታል?
እንድሁም ዴል ጂ.ረንለንድን፣ “Do Justly, Love Mercy, and Walk Humbly with God [ጽድቅን አድርግ፣ ምሕረትን ውደድ፣ እና ከእግዚአብሔር ጋር በትሕትና ተመላለሱ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 109–12 ተመልከቱ።
“እግዚአብሔር መልካም ነው፣ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው” (ናሆም 1፥7)።
ናሆም 1
እግዚአብሔር ሃያል እና መሐሪ ነው።
የናሆም ተልእኮ እስራኤሎችን ስለበታተነው እና ይሁዳን በጭካኔ ስላጠቃው የእብሪተኛው የአሴሪያ ኢምፓየር ዋና ከተማ—የነነዌን ውድመት መተንበይ ነበር። ናሆም የእግዚአብሔርን ቁጣ እና አቻ የሌለው ኃይል በመግለፅ ጀመረ፣ ነገር ግን ስለእግዚአብሔር ምህረት እና መልካምነትም ተናገረ። እነዚህን እያንዳንዳቸውን እና የምታስተዋሉትን ሌሎች የእግዚአብሔርን ባህሪያት እንድትረዱ የሚረዳችሁን በምዕራፍ1 ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች ፈልጉ። ስለጌታ እነዚህን እያንዳንዱን ነገሮች ማወቅ ለምን ጠቃሚ ይመስሎታል?
ዕንባቆም
የጌታን ፍቃድ እና ጊዜ ማመን እችላለሁ።
ነብያቶችም ቢሆኑ አንዳንድ ጊዜ ስለጌታ መንገዶች ጥያቄዎች አሏቸው። በይሁዳ ክፋት በተንሰራፋበት ጊዜ የኖረው ዕንባቆም ጥያቄዎችን ለጌታ በማቅረብ መዝገቡን ጀመረ ( ዕንባቆም 1፥1–4ይመልከቱ)። የዕንባቆምን ችግርች እንዴት ያጠቃልሉታል? በዛሬው ጊዜ ሰዎች ስለእግዚያብሄር ምን ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ? ተመሳሳይ ስሜቶች ኖራሃችሁ ያውቃል? እንዲሁም የሱን ጥያቄዎች በማርቆስ 4፥37–38 እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–6 ከሚገኙት በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ካሉት ጋር ማወዳደር ትችላላችሁ።
ጌታ ለዕንባቆም ጥያቄዎች ይሁዳን ለመቅጣት ከለዳውያንን (ባቢሎናውያኖችን) እንደሚልክ በመናገር መልስ ሰጠ ( ዕንባቆም 1፥5–11ይመልከቱ)። ነገር ግን ዕንባቆም ጌታ “ክፉው [ባቢሎን] የበለጠ ጻድቅ [ይሁዳ] የሆነውን ሰው እንዲገድል” ሲፈቅድ ኢፍታዊ ስለሚመስል ተቸግሮ ነበር ( ቁጥር 12–17ተመልከቱ)። በ ዕንባቆም 2፥1–4 ውስጥ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ሲኖራችሁ ጌታን ለማመን ምን የሚያነሳሳ ነገር አገኛችሁ?(በተጨማሪም ማርቆስ 4፡39–40፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፡7–8፤ “God Will Lift Us Up [እግዚአብሔር ያነሳናል]” [ቪዲዮ]፣ የወንጌል ላይብረሪ)።
God Will Lift Us Up
ምዕራፍ 3 የዕንባቆም የምስጋና እና የእምነት ጸሎት ነው። በምዕራፍ 3 ላይ ያለው የዕንባቆም ቃና ከምዕራፍ 1 የሚለየው እንዴት ነው? ከቁጥር 17–19 እንድታሰላስሉ የሚረዳችሁ ሃሳብ እነሆ፡ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ጊዜያዊ እና መንፈሳዊ በረከቶችን ዘርዝሩ። ከዚያ ጊዜያዊ በረከቶችን እንዳጣችሁ አስብ። ይህ ስለ ሌሎች በረከቶች ምን እንዲሰማችሁ ሊያደርግ ይችላል? በቁጥር 18 ለምን በመከራ ጊዜ “በጌታ መደሰት” በቁጥር 17 እንደተገለጸው ከባድ ሊሆን የሚችለው? ሕይወት ኢ-ፍታዊ ሲመስልም በእግዚአብሔር ታላቅ እምነትን እንዴት እንደሚያዳብሩ ያሰላስሉ።
በተጨማሪም፣ ጌሪት ደብሊው ጎንግ፣ “All Things for Our Good {ሁሉም ነገር ለእኛ ለበጎ ነው]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2024 (እ.አ.አ)፣ 41-44፤ “Lead, Kindly Light [መሪ ፣ ደግ ብርሃን]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 97፤ Topics and Questions፣ “Seeking Answers to Questions [ለጥያቄዎች መልስ መፈለግ]፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።
ትእግስተኛ ይሁኑ። አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄዎቻችን መልሶችን በፍጥነት እንፈልጋለን፣ ነገር ግን መንፈሳዊ ግንዛቤዎች ጊዜን ይወስዳሉ እንዲሁም በግፊት ሊሆኑ አይችሉም። ጌታ ለዕንባቆም እንደነገረው “ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገ[ሱት]” (ዕንባቆም 2፥3)።
ሶፎንያስ
“እናንተ የምድር ትሑታን ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ፈልጉ።”
የሶፎንያስን ትንቢቶች በምታነብበት ጊዜ ወደ ጥፋት ያመሩትን አመለካከቶች እና ባህሪያት ያስተውሉ—በተለይ ሶፎንያስ 1፥4–6፣12፤ 2፥8፣ 10፣15፤ 3፥1–4ተመልከቱ። ከዚያም እግዚአብሔር የሚጠብቃቸውን ሰዎች ባህሪዎች— ሶፎንያስ 2፥1–3፤ 3፥12–13፣ 18–19ተመልከቱ። ጌታ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ለእናንተ ምን መልዕክት እንዳለው ይሰማችኋል?
ሶፎንያስ 3፥14–20
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር በጽዮን ደስ ይለዋል።
ሶፎንያስ 3፥14–20ን ካነበባችሁ በኋላ፣ ይህን ዓረፍተ ነገር ምን ያህል መንገዶች ማጠናቀቅ እንደምትችሉ ተመልከቱ፤ “ደስ ይበላችሁ በፍጹምም ልብ ደስ ይበላችሁ” ምክንያቱም … ለመደሰት ስለእነዚህ ምክንያቶች ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? አነዚህን ጥቅሶች በ 3ኛ ኔፊ17 ላይ ከተገለጹት ተሞክሮዎች ጋር በማነጻጸር እና ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተን ጨምሮ ስለህዝቡ ያለውን ስሜት አስቡ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ሚክያስ 5፥2
ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ተወለደ።
-
ልጆቻችሁ ጠቢባኑ ሕፃኑን ኢየሱስን በቤተልሔም እንዲያገኙ የረዳቸው የሚክያስ ትንቢት መሆኑን ላያውቁ ይችላሉ። ሚክያስ 5፥2 እና ማቴዎስ 2፥1–6ን በመጠቀም ልጆቻችሁ ልምዳቸውን በሠርቶ ማሳያ ሊያሳዩ ይችላሉ። ከዚያም የኢየሱስ መወለድ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ እና ነቢያት ከመወለዱ ከብዙ አመታት በፊት ስለ ጉዳዩ ያውቁ እንደነበር መናገር ትችላላችሁ።
ቅዱስ ሕፃን ተወለደ፣ በዳና ዉድ
ናሆም 1፥7
“እግዚአብሔር መልካም ነው፣ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው።”
-
ናሆም 1፥7ን ካነበቡ በኋላ ልጆቻችሁ ቀላል የሆነ “ምሽግ” መገንባት ወይም መሳል ይችላሉ (በዚህ ዝርዝር ውስጥ የአንዱ ሥዕል አለ)። ሰዎች ምሽግ የሚያስፈልጋቸው አንዳንድ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ቀናችንን ምንድን ነው “የመከራ ቀን” የሚያደርገው? ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ እንደ ምሽግ የሆነው እንዴት ነው?
ዕንባቆም 2፥3
እግዚአብሔር የገባውን ቃል ሁል ጊዜ ይፈጽማል።
-
ዕንባቆም 2፥3ን ለማስተዋወቅ እናንተና ልጆቻችሁ ጥሩ ስለሆኑት ነገሮች ማውራት የምትችሉት ግን ከጠበቅን በኋላ ነው፤ ልክ መብሰል እንደሚያስፈልገው ፍሬ ወይም መጋገር እንደሚያስፈልገው ሊጥ። ፍሬውን ወይም ሊጡን ሳይዘጋጅ ለመብላት ብንሞክር ምን ይሆናል? ከዚያም ጌታ በዓለም ላይ ያለውን ክፋት መቼ እንደሚያቆም ማወቅ ስለሚፈልግ ስለ ነቢዩ ዕንባቆም መናገር ትችላላችሁ። የጌታን መልስ በ ሐጌ 2፥-7አንብብ። ልጆቻችሁ አምላክ ቃል የገባቸውን ነገሮች እንዲያስቡ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ከእያንዳንዱ ምሳሌ ጋር አንድ ላይ “ ጠብቁት ምክንያቱም በእርግጥ ይመጣል” ማለት ትችላላችሁ።
ዕንባቆም 2፥14
ምድርን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት እንድትሞላ መርዳት እችላለሁ።
-
ዕንባቆም 2፥14ን በምሳሌ ለማስረዳት እናንተና ልጆቻችሁ ኢየሱስ ያደረጋቸውን ወይም ያስተማራቸውን ነገሮች በሚወክሉ ሥዕሎች ወይም ቃላት አንድ ማሰሮ ወይም ሌላ ዕቃ መሙላት ትችላላችሁ። ዓለምን በጌታ እውቀት እንዲሞላ እንዴት መርዳት እንችላለን?
-
እንዲሁም ለልጆቻችሁ የዓለምን ካርታ ማሳየት ትችላላችሁ (የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ካርታዎች ቁጥር 7፣ “የዓለም ካርታ” የሚለውን ተመልከቱ)። የሚኖሩበትን ቦታ እና የሚያውቋቸው ሚስዮናውያን ያገለገሉበትን ቦታ እንዲያገኙ እርዷቸው። እንደ “We’ll Bring the World His Truth [እውነቱን ለአለም እናመጣለን]፣” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 172–73) ያሉ ወንጌልን ስለማካፈል የሚያወሡ መዝሙሮችን ልትዘምሩም ትችላላችሁ። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሌሎች ምን ልንነግራቸው እንችላለን?
ሶፎንያስ 3፥14–20
ኢየሱስ ክርስቶስ ከተከተሉት ጋር ደስ ይለዋል።
-
በ ሶፎንያስ 3፥14–20ልጆቻችሁ “በመዘመር፣… ደስ ይበላችሁ እና በፍጹም ልባችሁ ሐሤት አድርጉ” እንዲሉ የሚያደርጋቸውን ነገር መፈለግ ትችላላችሁ። ምናልባት አንዳንድ አስደሳች መዝሙሮችን አንድ ላይ መዘመር እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ ስላገኙት ደስታ ማውራት ትችላላችሁ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።