“ታህሳስ 14፟–፟20 (እ.አ.አ)። ሚልክያስ፦ ‘ወድጃችኋለው ይላል እግዚአብሔር’”፣ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ታህሳስ 14፟–፟20 (እ.አ.አ)። ሚልክያ፦ ‘ወድጃችኋለው ይላል እግዚአብሔር’”፣ ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 14፟–፟20 (እ.አ.አ)፦ “ወድጃችኋለው ይላል እግዚአብሔር”
ሚልክያስ
“ወድጃችኋለው፣” በነብዩ ሚልክያ አማካኝነት ጌታ ለህዝቦቹ ተናገረ። ነገር ግን በትውልዶች በመከራ እና ምርኮኝነት የተሰቃዩ እስራኤላውያን ጌታን እንዲህ ጠየቁት፣ “በየት ነው የወደድከን?” (ሚልክያስ 1፥2)። እስራኤላውያን ካሳለፉት መከራ በኋላ ታሪካቸው በእውነት እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ሕዝብ ያለው ፍቅር ታሪክ ነው ወይ ብለው አስበው ይሆናል። በአንዳንድ መንገዶች፣ የሰው ልጅ ድክመት እና አመፅ ታሪክ ሆኖ ማየት ቀላል ነው። ነገር ግን በዛ ሁሉ ውስጥ፣ እግዚአብሔር በፍቅር መድረሱን አላቆመም ነበር። የያዕቆብ ወንድ ልጆች ወንደማቸውን ዮሴፍን ቢበድሉም እንኳን፣ ጌታ ከረሃብ አዳናቸው ( ኦሪት ዘፍጥረት 45፥4–8ተመልከቱ)። እስራኤሎች በበረሃ ሲያጉረመርሙ፣ እግዚአብሔር በመና መገባቸው ( ኦሪት ዘጸአት 16፥1–4ተመልከቱ)። እስራኤላውያን ቢተዉትም፣ ወደ ሌላ አማልክት ፊታቸውን ቢያዞሩም፣ እና ቢበታተኑም እንኳንም ነገር ግን ንስሃ ከገቡ እንደሚሰበስባቸው እና “በታላቅ ምህረት” እንደሚያድናቸው ቃል ገባላቸው ( ኢሳይያስ 54፥7ተመልከቱ)። በእውነቱ፣ ብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ታጋሽ፣ የሚጸና ፍቅር ታሪክ ነው። እናም ይህ ታሪክ ዛሬም ይቀጥላል። እየሱስ ክርስቶስ “የጽድቅ ፀሐይ፣” ሚልክያስ እንደጠራው “ፈውሱም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣” ብሎ ተነበየ (ሚልክያስ 4፥2ተመልከቱ)። እርሱ ለጥንት እስራኤልና ለሁላችን ስላለው የእግዚአብሔር ፍቅር ታላቁ ማረጋገጫ ነው።
ስለሚልክያስ መጽሐፍ የበለጠ መረጃ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ሚልክያስ” የሚለውን ተመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ሚልክያስ 1–4
“ወደ እኔ ተመለሱና እኔ ወደ እናንተ እመለሳለሁ።”
በሚልክያስ ጊዜ፣ እስራኤላውያን ቤተመቅደስን በኢየሩሳሌም እንደገና ገንብተው ነበር፤ ነገር ግን እንደ ህዝብ ከጌታ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንደገና መገንባት ይኖርባቸው ነበር። ሚልክያስን ሲያጠኑ፣ ጌታ እስራኤላውያንን የጠየቀውን ወይም እነርሱ የጠየቁትን ጥያቄዎች ፈልጉ። ከጌታ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለመገምገም እና ወደ እርሱ ለመቅረብ እንዲረዳችሁ እራሳችሁን ተመሳሳይ ጥያቄዎችን መጠየቅን አስቡ (የተወሰኑ ምሳሌዎች ከታች ተጠቅሰዋል)።
-
ጌታ ለእኔ ያለውን ፍቅር እንዴት ተሰምቶኛል? ( ሚልክያስ 1፥2ተመልከቱ)።
-
እኔ ለጌታ የማቀርበው መባ በእርግጥ እርሱን ያከብረዋልን? ( ሚልክያስ 1፥6–11ተመልከቱ)።
-
በምን ዓይነት መንገዶች ነው ወደ ጌታ “መመለስ” የሚገባኝ? ( ሚልክያስ 3፥7ተመልከቱ)።
-
እግዚአብሔርን በሆነ ዓይነት መንገድ እየሰረኩት ነው? ( ሚልክያስ 3፥8–11ተመልከቱ)።
-
በአስቸጋሪ ጊዜያት ያለኝ አመለካከቴ ለጌታ ያለኝን ስሜት የሚያንፀባርቀው እንዴት ነው? ( ሚልክያስ 3፥13–15፤ እንዲሁም 2፥17ተመልከቱ)።
ሚልክያስ 1፥6–14
ጌታ “ንፁህ መስዋትነትን” ይጠይቃል።
በ ሚልክያስ 1፣ ላይ ስለተገለጸው መባ ስታነብ ካህናቱ ስለሚያቀርቡት መሥዋዕት ምን አስተዋላችሁ? እነዚህ መስዋእቶች ካህናቶቹ ለጌታ ስላላቸው ስሜት ምን ይጠቁማሉ? ( ሚልክያስ 1፥13ተመልከቱ)። ለጌታ የምታቀርቡትን መባ ወይም መስዋዕት ዝርዝር ማውጣትን አስቡ። በዝርዝሩ ላይ ላሉት እያንዳንዱ ንጥል ነገር “የረከሰ” መባ ወይም “ንጹሕ” መባ ሊያደርገው የሚችለውን አስቡሚልክያስ 1፥7–11።
ሚልክያስ 3፥8–12
አስራትን በመክፈል እምነቴን ሳሳይ ጌታ የሰማይ መስኮቶችን ይከፍታል።
አስራት እንደምትከፍል የተረዳ ጓደኛ እንዳላችሁ አስቡ። “ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ?” ጓደኛችሁ ይጠይቃችኋል። ሚልክያስ 3፥8–12 በምታነቡበት ጊዜ ስለዚህ አስቡ። የጓደኛችሁን ጥያቄ ለመመለስ የሚረዳችሁ ምን አግኝታችሃል? ጓደኛችሁ ስለ አስራት ሌላ ምን እንዲረዳ ትፈልጋላችሁ? ለበለጠ እገዛ፣ የሽማግሌ ኒል አንደርሰንን “Tithing: Opening the Windows of Heaven [አስራት፡- የሰማይ መስኮቶችን ይከፍታል]” (ሊያሆና፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ) 32-35) መልእክት ውስጥ መፈለግ ትችላላችሁ።
-
ጌታ ለምን አስራት እንድንከፍል ይፈልጋል?
-
አንድ ሰው አሥራት እንዳይከፍል የሚከለክለው ምንድን ነው? እነዚህን መሰናክሎች እንዴት ማሸነፍ እንችላለን?
-
አሥራት መክፈል በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት የሚያጠናክረው እንዴት ነው?
አሥራት በምትከፍሉበት ጊዜ ጌታ እንዴት እንደባረካችሁ ለጓደኛችሁ ማካፈል ትችላላችሁ። “Lesson Number 1—Significant but Subtle Blessings [ትምህርት ቁጥር 1—ጉልህ የሆኑ ግን ስውር በረከቶች]” በሚለው ርዕስ ውስጥ ሀሳቦችን ማግኘት ትችላላችሁ በሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር መልእክት“The Windows of Heaven [የሰማይ መስኮቶች]” (ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 17–18)። አስራት በመክፈል ምን አይነት ሰዎች እንሆናለን?
“የሰማይን መስኮት ይከፈትላችኋልል” (ቁጥር10) የሚለው ሃረግ ለእናንተ ምን ማለት ነው? ምናልባት መስኮቱን ወደ ውጭ በመመልከት እና ስለ መስኮቶች ዓላማዎች ማሰብ ትችላላችሁ። አሥራት ስንከፍል ጌታ እንዴት እንደሚባርከን ለመግለጽ “የሰማይ መስኮቶች” መጠቀም ጥሩ መንገድ የሆነው ለምንድን ነው?
Vision in the Kirtland Temple [በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ የነበሩ ራዕዮች]፣ በጋሪ ስሚዝ
ሚልክያስ 4፥5-6
“ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።”
ሞሮኒ ሚልክያ 4፥5–6 ን ለጆሴፍ ስሚዝ ሲጠቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ከሚነበበው በትንሹ ልዩነት” ነበረው (የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥36–39)። የሞሮኒ የተለየ ዘገባ የዚህን ትንቢት መረዳት ላይ ምን ይጨምራል? በተለይም እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን አሰላስሉ፡-
-
አባቶች እነማን ናቸው? (ዘዳግም 29፥13ተመልከቱ) ምን አይነት ቃልኪዳን ነው የተገባላቸው? (አብርሃም 2፥9–11ተመልከቱ)። እነዚህን ቃልኪዳኖች ለመፈጸም እንዴት ትረዳላላችሁ?
-
ልባችሁን ወደ ቅድመአያቶቻችሁ ስለመመለስ የረዳችሁን ምን ተመክሮ አላችሁ? ይህ ለእግዚአብሔር እቅድ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ስለኤልያስ መምጣት እና ይሄ ትንቢት ዛሬ እንዴት እየተከናወነ እንደሆነ የበለጠ ለመማር፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥13–16 እና የሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “The Sealing Power [የማተም ኃይል]” (ሊያሆና፣ ህዳ. 2023 (እ.አ.አ) 19–22 ተመልከቱ)። ኤልያስ ስለመጣ አመስጋኝ የሆናችሁት ለምንድን ነው?
እንዲሁም ጌሪት ደብሊው ጎንግን፣ “We Each Have a Story [እያንዳንዳችን ታሪክ አለን]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ) 43–46፣ “Turn Your Hearts [ልባችሁን አዙሩ]፣” መዝሙር፣ቁጥር 291 “The Sealing Power [የማተም ኃይል]” ChurchofJesusChrist.org።
The Sealing Power
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ሚልክያስ 1፥2
ጌታ ይወደኛል፡፡
-
በ ሚልክያ 1፥2“[ጌታ] የወደደን?” የሚለውን ጥያቄ እናንተና ልጆቻችሁ እንዴት ልትመልሱ ትችላላችሁ? እሱ እንደሚወዳችሁ የምታውቁትን ምክንያት እርስ በርሳችሁ አካፍሉ። ምናልባት ልጆቻችሁ የእርሱን ፍቅር የሚያስታውሷቸውን ሥዕሎች እየሳሉ ይሆናል።
ልጆችን በወንጌል ውይይት አሳትፉ። ትንንሽ ልጆችን እያስተማራችኋቸው ከሆነ፣ በወንጌል ውይይቶች ውስጥ እነሱን ለማሳተፍ የፈጠራ መንገዶችን ማሰብ ያስፈልጋችሁ ይሆናል። ለምሳሌ ልጆቻችሁ ኳሱን በዙርያቸው ሊያሳልፉ ይችላሉ ኳሱን ሲይዙ፣ ኢየሱስ እንደሚወዳቸው የሚያውቁበትን አንድ ምክንያት ሊያጋሩ ይችላሉ።
ሚልክያስ 3፥8–12
አስራት ስከፍል ጌታ ይባርከኛል።
-
ልጆቻችሁ ስለአስራት እንዲማሩ እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? በዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ላይ እንደ ሳንቲሞች ያሉ 10 ትናንሽ ነገሮችን እንዲቆጥሩ መጠየቅ ትችላላችሁ። ከዚያም ከዕቃዎቹ አንዱን ከቀሪው ሊለዩ ይችላሉ ይህ ለጌታ አሥራት የምንሰጠው ያህል ነው። ሚልክያስ 3፥8-12፣ እንደሚለው፣ ጌታ ለምን አስራት እንድንከፍል ይፈልጋል? (እንዲሁም “ነቢዩ ሚልክያስ፣” በ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ 171–72 “የመጀመሪያዎቹ ነገሮች መጀመሪያ!” [ቪዲዮ]፣ የወንጌል ላይብረሪን ተመልከቱ)
0:58Malachi the Prophet
1:18First Things First!
-
ሚልክያስ 3፥10ን አንድ ላይ ስታነብ “የሰማይ መስኮቶች” የሚለውን ሐረግ ስታነብ ልጆቻችሁ በመስኮት አጠገብ እንዲቆሙ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ወይም “የሚቀበሉበት ቦታ አይበቃም” የሚለውን ሐረግ በምሳሌ ለማስረዳት በብርጭቆ እስኪፈስ ድረስ ውሃ በውስጥ አፍስሱ። አሥራት በምትከፍሉበት ጊዜ እግዚአብሔር የሰጣችሁን በረከቶች ለልጆቹ ንገራቸው። ልጆቻችሁ እነዚህን በረከቶች የሚወክሉ ምስሎችን ይሳሉ እና በቤታችሁ ውስጥ ባለው መስኮት ላይ ወይም አጠገብ ሊሰቅሏቸው ይችላሉ።
ሚልክያስ 4፥5-6
ኤልያስ ልባችንን ወደ ቤተሰባችን ሊመልስ መጣ።
-
በ ሚልክያስ 4፥5-6፣ ልጆቻችሁ ስለሚልክያስ ትንቢት አስመልክቶ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ምላሾችን ሊለዩ ይችላሉ፦ ማንን ጌታ ለመላክ ቃል ገብቷል?? መቼ ይህ ሰው ይመጣል ብሎ ነበር? ምን ጌታ ያደርጋል ብሎ ተናግሯል? ለምን ይህ ሰው መምጣት አስፈለገው? የት ይህ ትንቢት ተፈጽሟል? (ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 110፥13-16 ተመልከቱ።
-
በ ሚልክያስ 4፡5 ላይ ያለው የተስፋ ቃል እንዴት እንደተፈፀመ ለማወቅ፣ እንዲሁም በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 26–30 ውስጥ “ጆሴፍ እና ኦሊቨር የክህነት ቁልፎችን ተቀበሉ” የሚለውን መገምገም ትችላለህ። እንደ “The Hearts of the Children [የልጆች ልብ]” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 92) ያለ መዝሙር ልጆቻችሁ ኤልያስ መምጣት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ እንዲያውቁ መርዳት ትችላላችሁ። እንዲሁም እናንተ እና ልጆቻችሁ ልባችሁን ወደ ቅድመ አያቶቻችሁ እንድትመልሱ የሚያግዙ እንቅስቃሴዎችን በFamilySearch.org/discovery፣ን FamilySearch Tree app፣ ወይም My Family booklet መጎብኘት ይችላሉ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።