ኑ፣ ተከተሉኝ
ታህሳስ 7–13 (እ.አ.አ)። “ቅድስና ለእግዚአብሔር” ሐጌ 1፥2፤ ዘካርያስ 1፥4፤ 7፥14


“ታህሳስ 7–13 (እ.አ.አ)። “ቅድስና ለእግዚአብሔር” ሐጌ 1፥2፤ ዘካርያስ 1፥4፤ 7፥14፣ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“ታህሳስ 7–13 (እ.አ.አ)። “ቅድስና ለእግዚአብሔር” ፣ ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ላኢዬ ሐዋዪ ቤተመቅደስ በደመናማ ሰማይ ስር

ላኢዬ ሐዋዪ ቤተመቅደስ

ታህሳስ 7–13 (እ.አ.አ)፦ “ቅድስና ለእግዚአብሔር”

ሐጌ 1፥2ዘካርያስ 1፥47–14

ከአስርተ ዓመታት ምርኮ በኋላ ነብያት ሔጌን እና ዘካርያስን ጨምሮ የእስራኤላውያን አንድ ቡድን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ ተፈቅዶላቸው ነበር። በዚህ ቡድን ውስጥ የተወሰኑት ቤተ መቅደሱ ከመውደሟ በፊት ምን ትመስል እንደነበር አስታወሱ። ቤተመቅደሱ እንደገና የጌታን “የቀድሞ ክብር” (ሐጌ 2፥3)፣ ይመስል ይሆን ብለው ለሚገረሙ ሰዎች፣ ነብዩ ሐጌ የጌታን የማበረታቻ ቃላት እንዲህ ተናገረ፦ “እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ በርቱና ስሩ ይላል እግዚአብሔር፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና፣ … አትፍሩ።” “ይህንንም ቤት በክብር አሞላዋለው፣ … በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ።” (ሐጌ 2፥4–5, 7, 9).

ነገር ግን ቤተመቅደሱ ብቻ አልነበረም መልሶ መገንባትን ያስፈለገው። በብዙ መንገድ የእግዚአብሔር ህዝቦች በመንፈስ ፈራርሰው ነበር። እናም የተቀደሰ ሕዝብን መልሶ መገንባት ድንጋይ ከመቁረጥና የተቀደሰ ቤት እንዲሠራ ከማስቀመጥ የበለጠ ነገር ይወስዳል። “ቅድስና ለእግዚአብሔር” የሚለው ጽሑፍ በቤተ መቅደሱ ግድግዳ ላይ ብቻ ሳይሆን “በፈረሶች ደወሎች” እና “በኢየሩሳሌም ባለ ማሰሮ ሁሉ” ላይ መቀረጽ አለበት ማለት ነው። (ዘካርያስ 14፥20–21) እንዲሁም በእያንዳንዱ ልብ ላይ የተቀረጹ መሆን አለባቸው።

ስለሐጌ እና ዘካርያስ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ሐጌ” እና “ዘካርያስ” የሚሉትን ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሐጌ12፥1–9

የሴሚናሪ ምልክት
“መንገዶትን ያስቡ።”

ኢየሩሳሌምን መልሶ ለመገንባት ብዙ የሚሰሩ ጠቃሚ ነገሮች ነበሩ። ነገር ግን እስራኤላውያን ከተመለሱ በግምት 15 ዓመታት ካለፉ በኋላ የቤተመቅደስ መልሶ ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት ስላልተሰጠው ጌታ አዝኖባቸው ነበር ( ሐጌ 1፥2–5፤ እንዲሁም ዕዝራ 4፥24ተመልከቱ)። በተለይ ሐጌ 12፥1–9፣ ስታነቡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስቡ፡-

  • እስራኤላውያን ቤተ መቅደሱን ስላልጨረሱ ምን መዘዝ አጋጠማቸው?

  • ጌታ የእርሱን ቤት ገንብተው ከጨረሱ ምን ዓይነት በረከቶችን ቃል ገባላቸው?

  • ጌታ ለናንተ ያለውን መልዕክት በ ሐጌ 1፥5-7ምንድ ነው? ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ከጌታ ጋር እንዴት ማስማማት ትችላላችሁ? በህይወታችሁ እግዚአብሔርን በማስቀደም የተባረካችሁት መቼ ነው?

ቀደምት ኋለኛው ቀን ቅዱሳን በሐጌ ዘመን ከእስራኤላውያን ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ አጋጥሟቸው ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95ተመልከቱ)። ጌታ ስለ ቤተ መቅደሶች ስላለው ስሜት ከእነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ምን ትማራላችሁ?

እንድሁም ዴል ጂ. ረንለንድ፣ “Jesus Christ Is the Treasure [ኢየሱስ ክርስቶስ ሀብት ነው]፣” ሊያሆና፣ህዳር 2023 (እ.አ.አ) 96–99፣ ቴሬንስ ኤም. ቪንሰን፣ “True Disciples of the Savior [እውነተኛ የአዳኝ ደቀመዝሙር]፣” ሊያሆና፣ህዳር 2019 (እ.አ.አ) 9–11፤ “We Love Thy House, O God [እግዚአብሔር ሆይ ቤትህን እንወዳለን]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 247 “የፕሮቮ ከተማ ማእከል ቤተመቅደስ ተጠናቀቀ” (ቪዲዮ) ተመልከቱChurchofJesusChrist.org

7:17

Provo City Center Temple Completed

ዘካርያ 1–37–814

ጌታ ቅዱስ ሊያደርገኝ ይችላል።

በእናንተ አስተያየት፣ በዕለት ተዕለት ነገሮች ላይ “ቅድስና ለጌታ” እንዲቀረጽ ማድረግ ምን ዋጋ አለው?ዘካርያስ 14፥20 (እንዲሁም ዘጸአት 28፥36–38ተመልከቱ) ዛሬ በቤተመቅደሶች ላይ መቀረጹ ምን ዋጋ አለው? ይህ ሃረግ ለእናንተ ምን ማለት ነው? ቅድስናን የዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ አካል ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? ጌታ ለህዝቡ ያቀረበውን ግብዣ በምታነቡበት ጊዜ በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ አሰላስሏቸው፦ ዘካርያስ 1፥1–63፥1–77፥8–108፥16–17

ዘካርያስ 2፥10–118፥1–814፥9–11፣ 20–21 ወደፊት ሁላችንም በቅድስና ከጌታ ጋር ስንኖር ሕይወት ምን እንደሚመስል ለማወቅ ማንበብ ትችላላችሁ። ዘካርያስ ስለኢየሩሳሌም የወደፊት ዕጣ ፈንታ ስለተቀበለው ራዕይ ምን ያስደንቃችኋል? በማህበረሰባችሁ ውስጥ ማየት የምትፈልጉት እዚህ ምን አገኛችሁ? በዘካርያስ በተገለጸው ሁኔታ ውስጥ ለመኖር መዘጋጀት የምትችሉት እንዴት ነው?

ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ወደ ኢየሩሳሌም እየገባ

“እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሁትም ሆኖ በውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል” (ዘካርያስ 9፥9)። Triumphal Entry [የድል አገባብ]፣ በሃሪ አንደርሰን

ዘካርያስ 9፥9–1111፥12–1312፥1013፥6–714፥1–9

ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የተገባው መሲህ ነው።

በርካታ የዘካርያስ ጽሁፎች የኢየሱስ ክርስቶስን ምድራዊ አገልግሎት እና የመጨረሻ ዳግም ምፅዓትን ይጠቁማሉ። ከዚህ በታች አንዳንድ የዘካርያስ ትንቢቶች እና ፍጻሜያቸውን የሚገልጹ ጥቅሶች አሉ። በምታነቡበት ጊዜ ራሳችሁን ጠይቁ፣ ይህ ስለ አዳኝ ምን ያስተምረኛል?

  • ዘካርያስ 9፥9–11 ( ማቴዎስ 21፥1–111ኛ ጴጥሮስ 3፥18–19ተመልከቱ)

  • ዘካርያስ 11፥12–13 ( ማቴዎስ 26፥14–1627፥1–7ተመልከቱ)

  • ዘካርያስ 12፥10 ( ዮሐንስ 19፥37ራዕይ 1፥7ተመልከቱ)

  • ዘካርያ 13፥6–714፥1–9 ( ማቴዎስ 26፥31ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥47–53ተመልከቱ)

ዘካርያስ 9፡9–11 እንደተገለጸው ኢየሱስን በኢየሩሳሌም ከሚቀበሉት ሰዎች መካከል መሆን ምን ይመስል ነበር? ወደ ህይወታችሁ፣ ቤቶቻችሁ እና ማህበረሰባችሁ እንዴት ልትቀበሉት ትችላላችሁ?

በተጨማሪም የቅዱሳን ጽሑፎች መመሪያ፣ “መሲሕ፣” የወንጌል ቤተ መጻሕፍት፤ “ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም በድል መግባቱ” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት፤ ሮናልድ ኤ. ራስባንድ፣ Hosanna to the Most High God [ሆሣዕና ለልዑል እግዚአብሔር]ሊያሆና ግንቦት 2023፣ 108–12 ተመልከቱ።

1:22

The Lord's Triumphal Entry into Jerusalem

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሐጌ 1፥2–8።

“መንገዳችሁን አስቡ።”

  • ሐጌ 1፥2–5ን ክፍል ከልጆቻችሁ ጋር ስታነቡ፣ ጌታ በህዝቡ ያልተደሰተበትን ምክንያት እንዲያውቁ እርዷቸው። ምናልባት ልጆቻችሁ ቁጥር 6 ላይ አንድ ሀረግ መርጠው ስእል ይሳሉ። እርስ በእርሳቸው ሊያሳዩት እና እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚወክል መገመት ይችላሉ። ጌታ ከሚፈልገው ውጪ በሆኑ ነገሮች ላይ ጊዜ ስናሳልፍ፣ እንደ መብላት እንጂ አለመጠገብ የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ለጌታ አስፈላጊ ለሆኑት ነገሮች ጊዜ መስጠት የምትችሉበትን መንገድ እርስ በርሳችሁ መነጋገር ትችላላችሁ።

  • በተጨማሪም ቁጥር 8ን ለልጆቻችሁ ማንበብ ትችላላችሁ እና “ወደ ተራራ ውጡ፣” “እንጨት አምጡ” እና “[የጌታን] ቤት እንዲሰሩ” እንዲመስሉ መጋበዝ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ጌታ እንዲያደርጉ የጠየቃቸውን ነገሮች ጨምሮ በተለመደው ቀን የሚያደርጉትን ዝርዝር መዘርዘር ይችላሉ። ጌታ በዝርዝራቸው ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች በመዞር ልጆቻችሁን “መንገዳቸውን እንዲያስቡ” ጠይቋቸው።

ቤትን ያማከለ ትምህርት። ፕሬዝደንት ረስልኤም. ኔልሰን ቤት “የወንጌል መማሪያ መሃከል” መሆን እንዳለበት አስተምረዋል (“ምሳሌያዊ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆን፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 113)። ቤተሰባችሁ “መንገዳችሁን አስቡ” የሚለውን የሐጌን ምክር ስታጠኑ በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ አምላክን እንዴት ማስቀደም እንደምትችሉ መነጋገር ትችላላችሁ።

ዘካርያስ 3፥1–7

ቃል ኪዳኖችን ማድረግ እና መጠበቅ የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንድመስል ይረዳኛል።

  • ዘካርያስ በራእይ “የረከሰ ልብስ የለበሰ” አንድ ሊቀ ካህን አየ (ዘካርያስ 3፥3)። መልአኩም ንጹሕ ልብስ ሰጠው። ዘካርያስ 3፡1–7ን አብራችሁ በማንበብ የቆሸሹ ልብሶችና ንጹሕ ልብሶች ምን እንደሚወክሉ በመናገር ልጆቻችሁ ጠቃሚ እውነቶችን እንዲያውቁ መርዳት ትችላላችሁ። ከተጠመቅን በኋላም ከኃጢአታችን እንዴት እንነጻለን? የጥምቀት ቃል ኪዳናችን “በጌታ መንገድ እንድንመላለስ” የሚረዳን እንዴት ነው?

  • እናንተና ልጆቻችሁ በዚህ ዝርዝር ውስጥ እንዳለው የጥምቀትን ሥዕል ልትመለከቱ ትችላላችሁ። በጥምቀት ጊዜ ለምን ነጭ እንለብሳለን? እንዲሁም ስለ ጥምቀት መዝሙር መዘመር ትችላለህ፣ ለምሳሌ “When I Am Baptized [እኔ ስጠመቅ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 103)፤ መዝሙሩ ጌታ እንድንጠመቅ የሚፈልገው ለምን እንደሆነ ምን ያስተምራል?

አባት ሴት ልጁን በወንዝ ሲያጠምቅ

ዘካርያ 9፥9–1111፥1213፥6–7

ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የተገባው መሲህ ነው።

  • ዘካርያስ 9፥​9 ላይ ኢየሱስ በሟች ሕይወቱ የመጨረሻ ሳምንት ወደ ኢየሩሳሌም በመጣበት ወቅት የተነገረውን ትንቢት ልጆቻችሁ በዓይነ ሕሊናቸው ለመመልከት ይፈልጉ ይሆናል። ለዚህ እንዲረዳችሁ በዚህ ዝርዝር ውስጥ እንዳለው የዝግጅቱን ምስል አሳያቸው። እንዲሁም “The Savior Goes to Jerusalem [አዳኙ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዳል]” በአዲስ ኪዳን ታሪኮች፣ 110-12 ውስጥ አብራችሁ አንብቡ። ልጆቻችሁ በሥዕሉ ላይ “በጣም ደስ የሚላቸውን” ሰዎችን ሊጠቁሙ ይችላሉ። ንጉሱ ማን ነው? ዘካርያ 9፥9 እርሱን ለምን እናመሰግነዋለን?

    1:35

    Chapter 44: The Savior Goes to Jerusalem

  • ልጆቻችሁ በዘካርያስ የተነገሩትን ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ከሚገልጹ የአዲስ ኪዳን ጥቅሶች ጋር እንዲያወዳድሩ መርዳት ትችላላችሁ። አንዳንድ ምሳሌዎች እነሆ፦ ዘካርያስ 9፥9 እና ማቴዎስ 21፥5–9ዘካርያስ 9፥11 እና 1 ጴጥሮስ 3፥18–19ዘካርያስ 11፥12 እና ማቴዎስ 26፥14–16ዘካርያስ 13፥7 እና ማቴዎስ 26፥31። ከእነዚህ ጥቅሶች ስለአዳኙ ምን እንማራለን?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።

በተለያዩ ቋንቋዎች “ቅድስና ለጌታ” እና “የጌታ ቤት” የሚነበቡ ምልክቶች በብዙ ቤተመቅደሶች ላይ

“ቅድስና ለጌታ” በሁሉም ቤተመቅደስ ላይ ይታያል

የመጀመርያ ተግባር ገጽ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈሴን ሊያነጻ ይችላል።