“ታህሳስ 21–27 (እ.አ.አ)። “እርሱን ጠብቀነዋል እናም ያድነናል”፦ገና ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ታህሳስ 21–27 (እ.አ.አ)። “እርሱን ጠብቀነዋል እናም ያድነናል፣”፦ ገና ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
[For unto Us a Child Is Born] ህፃን ተወልዶልናልና፣ በስሞን ዴዌይ
ታህሳስ 21–27 (እ.አ.አ)፦ “እርሱን ጠብቀነዋል እናም ያድነናል”
ገና
ብሉይ ኪዳን በጉጉት የመጠበቅን መንፈስ ይዟል። በዛ መልኩ፣ በትንሹ ልክ እንደ የገና ወቅት ነው። ከአዳም እና ሔዋን ጀምሮ፣ የብሉይ ኪዳን ፓትርያርኮች፣ ነብያቶች፣ ገጣሚዎች እና መልካም ቀናትን ወደፊት የተመለከቱ ሰዎች በመሲሁ የመታደስ እና የመዳን ተስፋ ተሞልተው ነበር። እናም እስራኤላውያን በተደጋጋሚ ያንን ተስፋ ይፈልጉ ነበር—በግብፅ ወይም በባቢሎን በምርኮም ሳሉ ወይም በራሳቸው ሃጢያት ወይም አመፃ ውስጥ በነበሩ ጊዜ። በዛም ሰዓት ሁሉ ነብያት መሲህ፣ አዳኝ “ለተማረኩት ነፃነትን ለማወጅ” እንደሚመጣ አስታወሷቸው (ኢሳይያስ 61፥1)።
ያ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ሲወለድ እውን መሆን ጀመረ። ታላቁ የእስራኤል አዳኝ በበረት ተወለደ እና በግርግም ውስጥ ተኛ ( ሉቃስ 2፥7ተመልከቱ)። ነገር ግን የጥንት እስራኤላውያን አዳኝ ብቻ አልነበረም። ሃዘናችሁን ለመሸከም፣ ለበደላችሁም ለመቁሰል፣ በእርሱም ቁስል ትፈወሱ ዘንድ—ሊያድናችሁ መጣ ( ኢሳይያስ 53፥4–5ተመልከቱ)። ለዚህ ነው የገና በዓል እስከዛሬ ድረስ በጉጉት ደስታ የተሞላ የሆነው። መሲሁ ከ2000 ዓመታት በፊት መጣ እናም በምንሻው ግዜ ሁሉ በሕይወታችን ውስጥ መምጣቱን ይቀጥላል።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
በአዳኚኜ እደሰታለሁ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም ደስታን ስላመጣ የገና በዓል እንደ ደስታ ወቅት ይታወቃል። አዳኙ ከመወለዱ ከክፍለ ዘመናት በፊት፣ የብሉይ ኪዳን ነብያት ስለሚመጣው መሲህ ሲናገሩ ደስታ ተሰማቸው። ከሚከተሉት ምንባቦች ውስጥ የተወሰኑትን ያንብቡ፣ እና የአዳኙን ተልዕኮ ለጠበቁ ሰዎች ለምን ውድ እንደሆኑ አስቡ፦ መዝሙረ ዳዊት 35፥9፣ ኢሳይያስ 25፥8–9፤ 44፥21–24፤ 51፥11፤ ሶፎንያስ 3፥14–20፤ ሙሴ 5፥5–11። እነዚህ ምንባቦች ለእናንተ ውድ የሆኑት ለምንድን ነው? እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ደስታን የሚሰጡበት ምክንያት ምንድን ነው?
በተጨማሪም ዳሊን ኤች ኦክስን፣ “Good Tidings of Great Joy [የታላቅ ደስታ መልካም የምስራች]” (የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት የገና አምልኮ፣ ታህሳስ 4 2022 (እ.አ.አ)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት “Joy to the World [ደስታ ለአለም]፣” መዝሙር ቁጥር 201 ተመልከቱ።
ምልክቶች ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳስታውስ ይረዱኛል።
ብዙ ከገና በዓል ጋር የሚያያዙ ወጎች ወደ ክርስቶስ የሚጠቁሙ ምልክታዊ ትርጉሞች ሊኖራቸው ይችላል። በዚህ ዓመት ብሉይ ኪዳንን በምታጠኑበት ጊዜ፣ የአዳኙን ብዙ ምልክቶች ተገንዝባችሁ ይሆናል። የተወሰኑት ከታች ተዘርዝረዋል። እነዚህን ማጥናትን እና ስለእርሱ የሚያስተምራችሁን ለመመዝገብ አስቡ።
-
ኮኮብ ( ዘኍልቍ 24፥17፤ ማቴዎስ 2፥2፤ ራዕይ 22፥16)።
-
እረኛ (መዝሙረ ዳዊት 23፤ ሉቃስ 15፥4፟–7፤ ዮሐንስ 10፥11)
-
በግ (ኦሪት ዘፍጥረት 22፥8፤ ኦሪት ዘጸአት 12፥5፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፥18–20)።
-
ውኃ (ኦሪት ዘጸአት 17፥1–6፤ ኤርምያስ 2፥13፤ ሕዝቅኤል 47፥1–12፤ ዮሐንስ 4፥7–14)።
-
ድንጋይ (1ኛ ሳሙኤል 2፥2፤ 2ኛ ሳሙኤል 22፥2–3፤ መዝሙረ ዳዊት 118፥22–23፤ ኢሳይያስ 28፥16፤ ኤፌሶን 2፥20)።
-
ቁጥቋጥ (ኢሳይያስ 11፥1–2፤ ኤርምያስ 23፥5፤ 33፥15)።
-
ብርሃን (መዝሙረ ዳዊት 27፥1፤ ኢሳይያስ 9፥2፤ 60፥19፤ ሚክያስ 7፥8፤ ዮሐንስ 8፥12)።
በቅዱሳን ፅሁፎች ውስጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ሌሎች ምን ምልክቶች፣ ምንባቦች እና ዘገባዎች አገኛችሁ?
2ኛ ኔፊ 11፥4፤ ሞዛያ 3፥14–15፤ ሞዛያ 6፥63፤ “የክርስቶስ ዓይነቶች ወይም ምልክቶች፣” እና “ኢየሱስ ክርስቶስ፣” ሁለቱም በቅዱሳን ጽሑፎች መመሪያ (ወንጌል ቤተ መጻሕፍትን) ተመልከቱ።
“ሰሙም ድንቅ መካር ተብሎ ይጠራል።”
ኢየሱስ ክርስቶስ በብዙ ስሞች እና ማዕረጎች ተጠርቷል። በሚቀጥሉት ጥቅሶች ውስጥ ርዕሶችን ተመልከቱ መዝሙረ ዳዊት 23፥1፤ 83፥18፤ ኢሳይያስ 7፥14፤ 9፥6፤ 12፥2፤ 63፥16፤ አሞጽ 4፥13፤ ዘካሪያስ 14፥16፤ ሙሴ 7፥53። ሌላ ምን ስያሜዎችን ታስባላችሁ? በገና መዝሙሮች ውስጥ የምታገኙትን የኢየሱስ ክርስቶስን ስያሜዎች በማዳመጥ ልትደሰቱ ትችላላችሁ። እያንዳንዱ ስያሜ ስለእርሱ በምታስቡበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያሳድራል?
በሚመጣው አመት እሱን ለማስታወስ የሚረዳችሁን የአዳኝን ማዕረግ ወይም ሚና መምረጥ አስቡበት።
በተጨማሪም ክውንተን ኤል. ኩክ፣ “Personal Peace in Challenging Times [በአስቸጋሪ ጊዜዎች ያለ የግል ስላም]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ) 89-92፤ “Hark! ተመልከቱ። The Herald Angels Sing [መልእክተኛ መላእክት ይዘምራሉ]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 209።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ብሉይ ኪዳን ስለ ኢየሱስ ያስተምረኛል።
-
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ውይይት ለመጀመር እናንተ እና ልጆችዎ አንዳንድ የገና ጌጦች ሊኖራችሁ ይችላል። ምናልባት የገና ኮከብ፣ መብራቶች ወይም ስጦታ እንዴት አዳኝን እንደሚያስታውሳችሁ ማውራት ትችሉ ይሆናል። ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስን ሊያመለክት ለሚችል አንድ ነገር ከሚከተሉት ቅዱሳት መጻህፍት አንዱን ወይም ከዛ በላይ መመልከት ትችላላችሁ፡- ዘፍጥረት 22፥8፣ ዘኍልቍ 24፥17፣ መዝሙረ ዳዊት 23፥1፣ 27፥1። ምናልባት ልጆቻችሁ ሲያነቡ ከእያንዳንዱ ጥቅስ ጋር የሚሄድ ሥዕል ወይም ማስዋቢያ ሊይዙ ይችላሉ። ኢየሱስ እንደ በግ፣ ኮከብ፣ እረኛ ወይም ብርሃን የሆነው እንዴት ነው? የገናን መዝሙር አብራችሁ ለመዘመር አስቡበት፣ እንደ፦ “Stars Were Gleaming [ኮኮቦች ያበራሉ]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 37።
-
በተጨማሪም ልጆቻችሁ ኢሳይያስ 9:6ን ስታነብላቸው በዚህ መግለጫ መጨረሻ ላይ ያለውን ሥዕል መመልከት ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ “ሕፃን ተወለደ” የሚለውን ሐረግ ሲሰሙ ወደ ሕፃኑ ኢየሱስ እንዲጠቁሙ ጠይቋቸው። በብሉይ ኪዳን ነቢያት ኢየሱስ እንደሚወለድ ያውቁ እንደነበር ምስክርነታችሁን አካፍሉ።
-
በሚቀጥለው ዓመት የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለመማር ስትዘጋጁ ከልጆቻችሁ ጋር በዚህ ዓመት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለእርሱ ምን እንደተማሩ መከለስን አሰቡ። የተማሩትን ለማስታወስ እንዲረዳችሁ በዚህ ግብዓት ውስጥ ያሉ ዝርዝሮች እና ግላዊ ማስታወሻዎችን መከለስ ትችላላችሁ። ወጣት ልጆች የ ብሉይ ኪዳን ታሪኮችን በመመልከት ወይም ኑ ተከተሉኝ ውስጥ ያሉ ምስሎችን በማየት ሊጠቀሙ ይችላሉ። የትኞቹ ትንቢቶች ወይም ታሪኮች ጎልተው ታዩ? ስለ አዳኙ ምን ተማርን?
የገና በዓል ወጎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊጠቁሙ ይችላሉ።
-
የእስራኤል ቤተሰቦች ልባቸውን እና አዕምሮአቸውን ወደ ጌታ ለማድረግ የሚረዳ እንደ ፋሲካ እና ሌሎች ድግሶች ያሉ ባህሎች ነበሯቸው ( ኦሪት ዘጸአት 12ተመልከቱ)። እናንተ እና ልጆቻችሁ በገና በዓል ጊዜ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ለማተኮር የሚረዱ ምን ዓይነት ባህሎች አሏችሁ? ከቤተሰባችሁ ታሪክ ውስጥ ምን ዓይነት ባህሎችን ታውቃላችሁ? ለመጀመር የምትፈልጉትን አንዳንድ ባህሎች እንደ ቤተሰብ መወያየትን ልታስቡ ትችላላችሁ። አንዳንድ ሃሳቦች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፣ የተቸገረን ሰው ማገልገል፣ ለአዳኝ እንደ “ስጦታ” የምታቀርቡትን ነገር መምረጥ፣ ጓደኛን የቀዳሚ አመራር የገና በዓል አምልኮን አብሮት እንዲመለከት መጋበዝ (broadcasts.ChurchofJesusChrist.org)፣ የራሶን የገና በዓል መዝሙር መፃፍ ወይም የክርስቶስን ልደት መልዕክት ለማካፈል የፈጠራ መንገድን ማግኘት።
በቤት ውስጥ፣ መማር እና መኖር አይነጣጠሉም። “በቤት ውስጥ የወንጌል አግባብነት ወዲያውኑ ይታያል። እዚያ ወንጌሉን አብራችኋቸው የምትማሩት ሰዎች፣ በየቀኑ በወንጌሉ ስትኖሩ አብረዋችሁ የሚሆኑት ሰዎች ናቸው። እንደውም ብዙ ጊዜ ወንጌልን መኖር ወንጌልን እንዴት እንደምንማር ነው። ወንጌልን በቤት ውስጥ ስትማሩ እና ስታስተምሩ፣ የምትማሩትን ነገር ከምታደርጉት ነገር ጋር ለማገናኘት መንገዶችን ፈልጉ። ቤታችሁ ስለወንጌሉ የምታወሩበት ብቻ ሳይሆን እርሱን ለመኖር ጥረት የምታደርጉበት እንዲሆን ፍቀዱ” (በአዳኝ መንገድ ማስተማር፣ 31)።
የልደት ትዕይንት ምሳሌ፣ በኤታን ብራውን
የሰማይ አባት አዳኝ እንዲሆነኛ ልጁን እንደስጦታ ሰጠኝ።
-
ልጆቻችሁ የክርስቶስን ውልደት ክብር እና ደስታ እንዲሰማቸው እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? “The Christ Child [የክርስቶስ ልጅ]” (የወንጌል ቤተ መጻሕፍት) የሚለውን ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ ወይም በጋራ ማቴዎስ 1፥18–25፤ 2፥1–12፤ ሉቃስ 1፥26–38፤ 2፥1–20 አንብቡ። እያንዳንዱ ልጅ ከቪዲዮው ወይም ከቅዱስ ፅሁፍ ዘገባው ውስጥ አንድን ሰው በመምረጥ ያ ሰው ስለአዳኙ እንዴት እንደተሰማው ማካፈል ይችላል። ከዚያ ስለ እሱ ያላችሁን ስሜት እርስ በርሳችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ።
17:57The Christ Child
-
ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ ደስታን ስላስገኛችሁብት ስለሰጣችሁት ወይም የተቀበላችሁት ስጦታዎች ማውራት ትችላላችሁ። ከዚያም ኢሳይያስ 25፥9ን አብራችሁ ማንበብ ትችላላችሁ እና የሰማይ አባት አዳኝን ስለላከልን ለምን እንደምትደሰቱ መናገር ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዳኛችን ያለውን ሚና በተሻለ ሁኔታ እንዲገነዘቡ ለመርዳት ኢሳይያስ 25፥8–9፤ 53፥3–5፤ እና ሆሴዕ 13፥14 እንዲያነቡ ጋብዟቸው። እነዚህ ጥቅሶች ጌታ እንዴት እንደሚያድነን ምን ያስተምሩናል?
-
እንዲሁም እንደ “Away in a Manger [ከግርግም ራቅ]” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 42-43) ወይም “O Little Town of Bethlehem [ኦ የቤተልሄም ትንሽ ከተማ]” (መዝሙር፣ ቁጥር 208) ያሉ የገና መዝሙር አብራችሁ መዘመር ትችላላችሁ። የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚወዷቸው እንዲያውቁ ልጆችዎ በመዝሙር ውስጥ ሀረጎችን እንዲያገኙ እርዷቸው።
ተጨማሪ ሃሳቦችን፣ ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።