“ጥቅምት 19–25 (እ.አ.አ)። “በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ”፦ ኤርምያስ 1፥3፤ 7፤ 16–18፤ 20፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ጥቅምት 19–25 (እ.አ.አ)። “በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
ኤርምያስ፣ በዋልተር ሬን
ጥቅምት 19–25 (እ.አ.አ)፦ “በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ”
ኤርምያስ 1–3፤ 7፤ 16–18፤ 20
በመጀመሪያ ኤርምያስ ጥሩ ነብይ የሚሆን አልመሰለውም ነበር። “እናገር ዘንድ አላውቅም” ብሎ ተቃወመ (ኤርምያስ 1፥6)። ጌታም “ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ” ብሎ አረጋገጠለት (ቁጥር9)። ኤርምያስ ልምድ የሌለው “ልጅ” እንደሆነ ተሰማው (ቁጥር6)፣ ነገር ግን እግዚአብሔር፣ እርሱ ካሰበው በላይ ዝግጁ እንደሆነ ገለፀ—ለዚህ ጥሪ ከመወለዱ በፊት ተሹሞነበር ( ቁጥር5ተመልከቱ)። ስለዚህ ኤርምያስ ፍርሃቱን ወደ ጎን ትቶ ጥሪውን ተቀበለ። አስመሳይ ቅድስናቸው ከጥፋት እንደማያድናቸው የኢየሩሳሌምን ነገስታቶች እና ካህናት አስጠነቀቀ። መናገር የማይችል የመሰለው “ልጅ” የእግዚአብሔር ቃል “እንደሚነድድ ያለ እሳት በል[ቡ]” ሊሰማው ቻለ እናም ዝም ማለት አልቻለም (ኤርምያስ 20፥9)።
የኤርምያስ ታሪክ የእናንተም ታሪክ ነው። ከመወለዳችሁ በፊት እግዚአብሔር ያውቃቹሃል እናም ስራውን በምድር ላይ እንድሰሩ አዘጋጀቶችሃል። ከሌሎች ነገሮች መካከል ያ ስራ ኤርምያስ የተነበየውን ያካትታል፦ እሱም የእግዚአብሔርን ህዝብ አንድ በአንድ ወደ “ጽዮን ለማምጣት” መሰብሰብን ያካትታል (ኤርምያስ 3፥14)። ምን እንደምናደርግ ወይም ምን እንደምንናገር በትክክል ባናውቅም እንኳን፣ “ከአንተ ጋር ነኝና … አትፍራ ይላል እግዚአብሔር” (ኤርምያስ 1፥8፣19)።
ስለ ኤርምያስ አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኤርምያስ” የሚለውን ይመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ኤርምያስ 1፥4–19፤ 7፥1–7፤ 20፥8–9
ነብያት የሚጠሩት የእግዚአብሔርን ቃል እንዲናገሩ ነው።
አስቡ አንድ ስለ ነብይ ሰምቶ ለማያውቅ ጓደኛችሁ የነብዩ ኤርምያስን ጽንሰ-ሀሳብ በመጠቀም ነብይ እንዲት እንደሚጠራ መግለጽ ትችላላችሁ ኤርምያስ 1፥4–19። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ስለእግዚአብሔር ነብይ የሚያስተምር ምን አገኛችሁ? በተጨማሪም ኤርምያስ 7፥1–7፤ 20፥8–9እና እንደዚህ ያሉ መዝሙሮችን “We Listen to a Prophet’s Voice [የነቢዩን ድምጽ እንሰማለን]” (መዝሙር፣ ቁ. 22)ተመልከቱ።
በተጨማሪም ጓደኛችሁን አሁን በህይወት ስላለነብይ ለማስተማር ትፈልጉ ይሆናል። በነዚህ ቁጥሮች ውስጥ የሚረዳ ነገር አገኛችሁ? ለምሳሌ በዘመናችን ያሉ ነቢያት “ሥር የሚያወጡልን” ወይም “የሚገፉን” እንዴት ነው? “የሚገነቡት” እና “የሚተክሉት” ምንድን ነው? (ኤርምያስ 1፥10)። ዛሬ በህይወት ያሉት ነብያችን በእግዚአብሔር እንደተጠሩ ማወቅ የቻላችሁት እንዴት ነው?
በተጨማሪም የእምነት አንቀጾች1፥6 9፤ “Why Do We Have Prophets? [ለምንድን ነብያት ያሉን?]” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።
Why Do We Have Prophets?
ኤርምያስ 1፥5
ከመወለዴ በፊት እግዚአብሔር ያውቀኝ ነበር።
በ ኤርምያስ 1፥5ውስጥ ኤርምያስ ሰለራሱ ምን ተማረ? አዲስ እንደተጠራ ነብይ ማወቅ ያለበት አስፈላጊ መረጃ ምንድን ነው?
በ ኤርምያስ 1፥5ውስጥ ኤርምያስ ሰለራሱ የተማራቸው ነገሮች በእናንተ ላይም እውነት ናቸው። ከመወለዳችሁ በፊት እግዚአብሔር ያውቃችኋል እናም ለተለየ ሃላፊነቶች አዘጋጅቷችኋል። ከመወለዳችሁ በፊት ስለነበረችሁ ህይወት ለማወቅ( አልማ 13፥1–4፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥53–56፤ እና አብርሐም 3፥22–23አንብቡ)። የደረሳችሁበትን እውነታ በዝርዝር አስቀምጡ። ይህ መረጃ ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?
እነዚህ እውነታዎች እንዴት በሽማግሌ አህመድ ኤስ. ኮርቢት ህይወት ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ እንደፈጠረ ለማወቅ ከ “You Can Gather Israel! [እስራኤልን መሰብሰብ ትችላላችሁ]” መልእክት ተማሩ። (ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 63–63)። ስለቅድመ ሕይወታችሁ ማወቅ በምድራዊ ሕይወታችሁ አኗኗር ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችለው እንዴት ነው?
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ስለቀድሞ ህይወታችን የተናገሩት ይህ ነው
የሰማይ አባታችሁ ለብዙ ጊዜ አውቆአችዋል። በዝህን ወቅት እንደ ወንድ ልጁና ሴት ልጅ ወደ ምድር መጥታችሁ ለምድር ላይ ታላቅ ሥራው መሪዎች እንድትሆኑ መረጣችሁ። የተመረጣችሁ ለአካልችሁ ባህርይ ሳይሆን ለመንፈስ ባህሪያችሁ ነው። ይህም በጀግንነት፣ በጉብዝና፣በልበ ንፁህ ታማኝነት፣ ለእውነት ጥማት፣ ለጥበብ በመራብ እና ሌሎችን ለማገልገል ፍላጎትን ያመጣል።
“ከእነዚህ ባህሪዎች የተወሰኑትን ከመወለዳችሁ በፊትት አዳብራችኋቸዋል። ሌሎችን በጽናት ስትፈልጓቸው በምድር ላይ ማዳበር ትችላላችሁ” (“Decisions for Eternity [ዘላለማዊ ውሳኔዎች]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 107)።
ስለቀድሞ ህይወታችሁ እውነታ ማስታወስ ስለሚኖርባችሁ አንዳንድ ሁኔታዎች ማስታወስ ስለሚኖርባችሁ ነገሮች አስቡ። ስለእነዚህ እውነታዎች እራሳችሁን ለማስታወስ ምን ታደርጋላችሁ?
እንዲሁም ራስል ኤም ኔልሰን፣ “Decisions for Eternity [ዘላለማዊ ውሳኔዎች]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 106-9፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች “ቀድሞ መለየት፣” “ቅድመ ህይወት፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።
በኤርምያስ 2፥13፣ ውስጥ ጌታ የህዝቡን መንፈሳዊ ሁኔታ “ከተሰባበሩ ጕድጓዶች” ጋር እና ራሱን “ከሕይወት ውኃ ምንጭ” ጋር አነጻጽሯል።
ኤርምያስ 2፤ 7
“እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል።”
እስራኤላውያን ይኖሩባት በነበረችው ደረቅ ምድር ውስጥ ውድ የሆነውን ውኃ የውኃ ጉድጓዶች በሚባሉ የከርሰምድር ማጠራቀሚያ ውስጥ ያጠራቅሙ ነበር። በ ኤርምያስ 2፥13 ውስጥ የተጠቀሰው “የተቀደዱት ጉድጓዶች” ምንን የሚወክሉ ይመስሎታል? በውኃ ጉድጓዶች ከመመካት ይልቅ ውኃን ከምንጭ መቀበል ለምን የተሻለ ይሆናል? “የሕያውን ውኃ ምንጭ” መተው ማለት ምን ማለት ነው? ኤርምያስ 2 እና7ን ሲታነቡ ህዝቡ የእግዚአብሔርን የህይወት ውኃ እንዴት እንደተዉ አስተውሉ(ለምሳሌ፣ ኤርምያስ 2፥26–28፤ 7፥2–11ተመልከቱ)። የህይወት ውሃ ከአዳኛችን ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? የህይወት ውሃ እንዴት እንደተቀበላችሁ አስቡ።
ኤርምያስ 7 የሚናገረው ወደ “ጌታ ቤት ስለሚገቡ…ጌታን ለማምለክ” ሰዎች ይናገራል ነገር ግን ተግባራቸው ከአምልኮታቸው ጋር አይመሳሰልም (ቁጥር 2–11ተመልከቱ)። በ ቁጥሮች 21–23ውስጥ እግዚአብሔር ለእርሶ ምን ዓይነት መልዕክቶች እንዳለው ይሰማዎታል?
የተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ትምህርቶችን ተጠቀሙ። አብዛኛውን ግዜ የጌታ ነብያት መንፈሳዊ እውነታን ከታወቁ ዕቃዎች ጋር ያነጻጽራሉ። ወንጌልን ስትማሩም ሆነ ሰታስተምሩ እንደዚሁ ለመጠቀም አስቡበት። ለምሳሌ ኤርምያስ 2፥13ን በዓይነ ሕሊናችሁ ለመመልከት በተሰነጠቀ ወይም በተሰበረ ዕቃ ውስጥ ውኃ ማስገባት ወይም ከመጠጥ ምንጭ መጠጣት ትችላላችሁ። ኢየሱስ እንደ “የሕይወት ውኃ ምንጭ” የሆነው እንዴት ነው? (ኤርምያስ 2፥13)። ከህይውት ውኃ የምንጠጣው እንዴት ነው?
ኤርምያስ 3፥14–18፤ 16፥14–21
እግዚአብሔር ህዝቦቹን ይሰበስባል።
በኤርምያስ 16፥14–15፣ ኤርምያስ በኋለኛው ቀን የእስራኤልን ስብስብ ከዘፀአት እስራኤል ከግብፅ መውጣት ጋር አመሳስሎታል። በእናንተ አመለካከት፣ መሰብሰቡ ከዘፀአት ይልቅ ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?
ኤርምያስ 3፥14–18; 16፥14–21 ውስጥ ሰለስብስባው እንዴት እንደሚካሄድ ምን ይጠቁማል?
በመልእክቱ “የእስራኤል ተስፋ፣” ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ይህ ሁሉ እስራኤልን የመሰብሰብ ክፍል እንደሆነ፣ ይህም “ዛሬ በምድር ላይ እየተከናወነ ያለው እጅግ አስፈላጊ ነገር” ነው ብለዋል (worldwide youth devotional [የአለም አቀፍ የወጣቶች አምልኮ] ሰኔ 3፣ 2018 (እ.አ.አ)]፣ 8፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት)። መልእክቱን አንብቡ ወይም አዳምጡ፣ እና (ሀ) ፕሬዘዳንት ኔልሰን የእስራኤልን መስብስብ እንዴት እንደሚገልጹ፣ (ለ) አስፈላጊነቱን እንዴት እንደገለጹ እና (ሐ) እንዴት እናንተ የስብስቡ አካል መሆን እንደምትችሉ ማወቅ ትችሉ እንደሆነ ተመልከቱ።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ኤርምያስ 1፥5
ከመወለዴ በፊት የሰማይ አባት ያውቀኝ ነበር።
-
በኤርምያስ 1፥5 ላይ የተገለፁትን አስፈላጊ እውነታዎች ለማስተማር ለልጆቻችሁ የህፃን ምስል አሳዩ ( ወይም ከተቻለ የልጆቻችሁን የልጅነት ምስል መመልከት ትችላላችሁ)። ከመወለዳቸው በፊት ይኖሩበት የነበረውን ቦታ ያውቁ እንደሆነ ጠይቋቸው። እንዲሁም ቅዱሳት መፃህፍትን ሰለቀድሞ ህይወት የሚናገር እንደ “I Lived in Heaven [በሰማይ ኖርያለሁ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 4) ያለ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ።
-
ልጆቻችሁ የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ፣ “ቀድሞ ህይወት” በቅዱሳት መጻሕፍት መመሪያ ውስጥ እንዲያገኙ ልትረዱዎቸው ትችላላችሁ። ሰለቀድሞ ህይወት “ምን፣” “መቼ፣” እና “ምን” ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ፈልጉ።
ኤርምያስ 1፥4–19።
ነብያት የሚጠሩት የጌታን ቃል እንዲናገሩ ነው።
-
ከቅዱሳን መፅሐፍት ውስጥ ያሉ ነብያት ወይም በህይወት ያለ ነብይ ምስል ለማሳየት አስቡ (የተወሰኑትን እዚህ Church magazines [የቤተክርስቲያን መጽሔቶች]፣ Gospel Art Book [የወንጌል ጥበብ መጽሐፍ]፣ እና ኑ፣ ተከተሉኝታገኛላችሁ)። ልጆቻችሁ ስለነበያት የሚያውቁትን እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው።
-
ከኤርምያስ 1፣ እንደ ቁጥር 5፣7፣10፣ እና 19 ውስጥ ሰለነበያት ለማስትማር የሚረዱ ቁጥሮችን ምረጡ። ልጆቻችሁ እያንዳንዳቸው ከጥቅሶቹ አንዱ ቁጥር መምረጥ፣ ማንበብ እና ስለ ነቢያት የተማሩትን ማካፈል ይችላሉ።
ኤርምያስ 16፥14–16
የሰማይ አባት ልጆች ወደ እሱ እንዲመለሱ መርዳት እችላለሁ።
-
ኤርምያስ 16፥16ን ሰታነቡ ልጆቻችሁ በክፍል ውስጥ ያሉትን እቃ እንደ “ዓሳ” ወይም “ማጥመጃ” እንዲያስመስሉ አድርጉ። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን በዚህ ቁጥር ውስጥ ያሉ አሳ አጥማጆችን እና አዳኞችን ከሚስዮናውያን ጋር አነፃፅረዋል ( “The Gathering of Scattered Israel [የተበተኑትን እስራኤላውይን መሰብሰብ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2006 (እ.አ.አ)፣81 ተመልከቱ)። ሚስዮናውያን ምን ያደርጋሉ? የተበተኑትን እስራኤላውያን እንደ “ዓሳ” እና “ማጥመጃ” ለመርደት ምን እናድርግ?(“ከፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ለልጆች የተላከ መልዕክት” [ቪዲዮ]፣ ChurchofJesusChrist.orgተመልከቱ)።
3:30Video: A Message for Children from President Russell M. Nelson
ኤርምያስ 18፥1–6።
ሸክላ ሰሪው ሸክላውን እንደሚቀርፀው ሁሉ ጌታ የእኔን ህይወት እንዲመራ እፈቅድለታለሁ።
-
እነዚህን ጥቅሶች ለማሰስ ሸክላ እንዴት እንደሚሰራ ሊወያዩ ወይም ሊያሳዩ ትችላላችሁ (በዚህ ንድፍ መጨረሻ ላይ ያለውን ምስል ተመልከቱ)። በ ኤርምያስ 18፥1–6፣ ውስጥ ጌታ ለእኛ ምን መልዕክት አለው? በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ እንደ የሸክላ ጭቃ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? (እንዲሁም ኢሳይያስ 64፥8ይመልከቱ)። እኛን ከሸክላ ጋር የሚያነጻጽረን ሌላ ታሪክ፣ የሽማግሌው ሪቻርድ ጄ. ሜይንስ መልእክትን “The Joy of Living a Christ-Centered Life [ክርስቶስን ያማከለ ህይወት መኖር ደስታን ያመጣል]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ) 27-30)ተመልከቱ።
ለተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።