“ጥቅምት 5–11 (እ.አ.አ)። ‘በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል‘፦ኢሳይያስ 50–57” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]
“ጥቅምት 5–11 (እ.አ.አ)። “በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)
በክርስቶስ ላይ ማፌዝ፣ በካርል ሄንሪክ ብሎች
ጥቅምት 5–11 (እ.አ.አ)፦ “በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል”
ኢሳይያስ 50–57
ኢሳይያስ በአገልግሎት ዘመኑ ሁሉ ስለሃያል አዳኝ ተናግሯል። እነዚህ ትንቢቶች እስራኤላውያን ከክፍለ ዘመናት በኋላ በባቢሎን ምርኮ ውስጥ በሚሆኑ ጊዜ በተለየ ውድ ይሆኑ ነበር። የባቢሎንን ግንቦች ሊያፈርስ የሚችል ሰው በእርግጥ ሃያል ድል አድራጊ ነው። ነገር ግን ያ ኢሳይያስ በ ምዕራፎች 52–53፣ ውስጥ የጠቀሰው መሲህ ዓይነት አይደለም፦ “የተናቀ ከሰውም የተጠላ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው።… እኛ ግን እንደተመታ በእግዚአብሔርም እንደተቀሰፈ እንደተቸገረም ቆጠርነው” (ኢሳይያስ 53፥3–4)።
እንደዚህ ዓይነት ያልተጠበቀ አዳኝ በመላክ እግዚአብሔር ስለትክክለኛ ነፃ መውጣት አስተማረን። ከጭቆና እና ከመከራ ሊያድነን እግዚአብሔር “የተጨቆነን እና የተሰቃየን” ላከ። አንበሳ በሚጠበቅበት ቦታ ጠቦትን ላከ ( ኢሳይያስ 53፥7ተመልከቱ)። በእርግጥ የእግዚአብሔር መንገዶች የእኛ መንገዶች አይደሉም ( ኢሳይያስ 55፥8–9ተመልከቱ)። ኢየሱስ ክርስቶስ ነፃ ያወጣን እስር ቤቱን በመክፈት ሳይሆን በዚያ ውስጥ የእኛን ቦታ በመውሰድ ነው። እርሱ ራሱ በመሸከም ከጭንቀት እና ከሀዘን ሰንሰለታችን ነፃ ያደርገናል ( ኢሳይያስ 53፥4–5፣12ተመልከቱ)። የሚያድነን በርቀት ሆኖ አይደለም። “ዘላለማዊ ቸርነት” በማሳየት ተግባሩ “ከአናንተ ዘንድ [ሳይፈልስ]” ከእኛ ጋር አብሮ ይሰቃያል (ኢሳይያስ 54፥8፣10)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ኢሳይያስ 50–52
ለጌታ ህዝቦች የወደፊቱ ብሩህ ነው።
እስራኤላውያን በምርኮ ውስጥ ብዙ ዓመታትን ቢያሳልፉም—ምንም እንኳን ያ ምርኮ የተሳሳቱ ምርጫዎቻቸው ውጤት ቢሆንም—ጌታ የወደፊታቸውን በተስፋ እንዲመለከቱ ፈለገ። ከኢሳይያስ መልህክት ላይ ተስፋ የሚሰጣችሁን ምን አገኛችሁ? እንደሚከተለው አይነት ቻርት ለማጥናት ሊረዳዎት ይችላል፦
|
ስለእግዚአብሔር ምን ተማርኩ (ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ 50፥2፣ 5–9፤ 51፥3–8፣ 15–16፤ 52፥3፣ 9–10ተመልከቱ) | |
|
የተስፋ መልህክት (ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ 50፥9፤ 51፥3-5፣ 11–12, 22–23፤ 52፥9–10ተመልከቱ። | |
|
ተስፋን እውን ለማድረግ ምን ማድረግ እችላለሁ ( ለምሳሌ፣ ኢሳይያስ 50፥–10፤ 51፥1-2፣ 6-9፤ 52፥1–3፣ 9-11ተመልከቱ)። |
በተጨማሪም ሞዛያ 12፥20–24፤ 15፥13–18፤ 3 ኔፊ 20፥29–46፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 113፥7-10፤ ራስል ኤም. ኔልስን፣ “ወደፊትን ጊዜ በእምነት ተቀበሉ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 73-76 ተመልከቱ።
Because of Love [በፍቅር ምክንያት]፣ በአንጄላ ጆንሰን
ተማሪዎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጡ እርዱ እንደ አስተማሪ የምታደርጉት ምንም ነገር የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያውቁ እና ፍቅራቸው እንዲሰማቸው ከመርዳት በበለጠ ተማሪዎችን አይባርክም (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 8)። ኢሳይያስ 50-57ን ለሌሎች ለማስተማር ስትዘጋጁ፣ በእስራኤል ችግሮች፣ ኢሳይያስ ስለ ክርስቶስ በተነገረው ትንቢቶች እና ራሳቸው ትግል መለኰታዊ እርዳታ በማግኘት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲገነዘቡ እንዴት መርዳት እንደምትችሉ አስቡ።
ትንቢተ ኢሳይያስ 53
ኢየሱስ ክርስቶስ የእኔን ሃጢያት እና ሃዘኖች በራሱ ላይ ወሰደ።
በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ የተወሰኑ ምዕራፎች የኢየሱስ ክርስቶስን የቤዛነት ተልዕኮ ኢሳይያስ53፣ የበለጠ ቆንጆ አድርገው ይገልፃል። የሚከተሉትን ኃይለኛ ትምህርቶች በተሻለ ለመረዳትና ለመተግበር እንደሚከተሉት ያሉትን እንቅስቃሴዎች ተመልከቱ:-
-
ታሪኮችና ፊልሞች ብዙውን ጊዜ ሰዎችን የሚያድኑ ጀግኖችን የሚገልጹት እንዴት አሰላስሉ እና ተወያዩ። እነዚያን መግለጫዎች በ ኢሳይያስ53፣ ወስጥ ካነበቡት የአዳኙ መግለጫዎች ጋር ማነፃፀር ይችላሉ።
-
እያንዳንዱን ጥቅስ ሲታነቡ አዳኙ—የተሸከማቸውን “ህመሞች፣” “ሃዘኖች” እና “መተላለፎች”—ለሁሉም ሰው በለተይም ለእናንተ የተሰቃየውን ነገሮች ቆም ብላችሁ አሰላሰሉ ። እንደ “እኛ” እና “የእኛ” የሚሉትን ቃላት “እኔ” እና “የእኔ” በሚሉ ቃላት መተካት ይችላሉ። እነዚህ ጥቅሶች ምን ዓይነት ስሜቶችን ወይም ሃሳቦችን በውስጦ ያስነሳሉ?
-
“My Kingdom Is Not of This World [የኔ መንግስት ከዚህ አለም አይደለም]” የሚለውን ቪድዮ ለመመልከት አስቡ በ ኢሳይያስ53ውስጥ ያሉ ትንቢቶች እንዴት እንደተፈፀመ መነጋገር ትችላላችሁ። አዳኙ ስለእናንተ የተሸከማቸው አንዳንድ ህመሞች እና ሃዘኖች ምንድን ናቸው?
5:25My Kingdom Is Not of This World
-
በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአት ስርየት ዙሪያ የተከናወኑትን ክስተቶች የሚያሳዩ ስዕሎችን ፈልጉ (የወንጌል ስዕሎች መፅሐፍ፣ ቁጥር 56-60 ተመልከቱ)። ከዚያም በሥዕሎቹ ውስጥ ያሉትን ክስተቶች የሚገልጹ ሐረጎችን በኢሳይያስ 53 ላይ መፈለግ ትችላለህ። እነዚህ አስተምሮዎች ምን እንድታደርጉ ያነሳሳችኋል?
በተጨማሪም “Behold the Great Redeemer Die፣” መዝሙር፣ ቁጥር 191 ተመልከቱ።
ኢሳይያስ 54፤ 57፥15–19።
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ እንድመለስ ይፈልጋል።
በሃጢያቶቻችን ወይም በክፋቶቻችን ምክንያት ሁላችንም ከጌታ የራቅን መስሎ የሚሰማን ጊዜ አለ። አንዳንዶች ይቅር አይለንም ብለው ተስፋን ቆርጠዋል። በዚህ ዓይነት ጊዜ ውስጥ ኢሳይያስ 54 እና 57 ማረጋገጫ እና ማበረታቻ ለማግኘት የሚነበቡ ታላቅ ምዕራፎች ናቸው። በተለይ በ ኢሳይያስ 54፥4–10፤ 57፥15–19፣ ውስጥ ስለ አዳኙ ምህረት እና ለእናንተ ስላለው ስሜት ምን ትማራላችሁ? ስለእርሱ እነዚህን ነገሮች ማወቅ በሕይወቶ ውስጥ ምን ልዩነት ያመጣል?
ፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ አስተማሩ፤
ህይወታችን እንዴን አይነት ውድመት እንዳለው ምንም ግድ የለውም። ኃጢያታችን እንዴት እንደቀላ፣ ምሬታችን እንዴት ዝልቅ እንደሆነ፣ እኛም እንዴት ብቸኛ፣ የተጣችል፣ ወይም ልባችን የተሰበረ መሆኑም ግድ የለውም። ተስፋ የሌላቸውም፣ ተስፋ ቆርጠው ያሉትም፣ እምነትን የከዱትም፣ ሀቀኝነታቸውን አሳልፈው የሰጡትም፣ ወይም እግዚአብሔርን የሰደቡትም እንደገና ለመገንባት ይችላሉ።
የወንጌል አስደሳች ዜና ይህ ነው፥ በአፍቃሪ የሰማይ አባታችን እና መጨረሻ በሌለው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል በተሰጠው የደስታ እቅድ ምክንያት፣ ከውድቀት ለመዳን ከመቻላችን በተጨማሪ፣ ስጋዊ አስተሳሰብን ለማለፍ እና የዘለአለም ህይወት ወራሾች እና ለመግለጽ የማይቻለው የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች ለመሆን እንችላለን። (“He Will Place You on His Shoulders and Carry You Home፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016, 102)።
ፓትሪክ ኪረን፣ “የእግዚአብሄር ሀሳብ እናንተን ወደ ቤቱ ማምጣት ነው፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2024 (እ.አ.አ)፣ 87-89 ተመልከቱ።
ኢሳይያስ 55–56
እግዚአብሔር ለሁሉም “ቃልኪዳ[ኑ]ን [እንዲ]ይዙ” ይጋብዛል።
ለብዙ ትውልዶች እስራኤል እንደእግዚአብሔር የቃልኪዳን ህዝብ ተደርጋ ተቆጠረች። ይሁን እንጂ፣ የእግዚአብሔር እቅድ ሁሌም ከአንድ አገር የበለጠን ያካትታል፣ ምክንያቱም “የተጠ[ሙት] ሁሉ” “ወደ ውኃ [እንዲመጡ]” ተጋብዘዋል (ኢሳይያስ 55፥1)። ኢሳይያስ55 እና56ን ሲያነቡ ይህን በአዕምራችሁ ውስጥ ያስቀምጡ እናም የእግዚአብሔር ህዝብ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ አሰላስሉ። ከእርሱ “[የተለዩ]” ሆነው ለሚሰማቸው ሰዎች የእግዚአብሔር መልዕክት ምንድን ነው? (ኢሳይያስ 56፥3)። “ቃል ኪዳኔን የሚይዙ” ስለተባሉ ሰዎች ያሉትን ዝንባሌዎች እና ተግባሮች በሚገልፁ ጥቅሶች ላይ ምልክት ማድረግን ያስቡ ( ኢሳይያስ 56፥4–7ይመልከቱ)።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ኢሳይያስ 51–52
ጌታ “ጥንካሬውን በኔ ላይ እንዳረግ” ይጋብዘኛል።
-
ልጆቻችሁ በኢሳይያስ 51፥9, 17፤ 52፥1-2፣ 9 ላይ “ንቁ ፣” “ተነሡ” እና “ብርታትህን ልበሱ” የሚሉትን ሐረጎች ሲሰሙ ደስ ሊላቸው ይችላል። ይህን ካደረጋችሁ በኋላ በመንፈስ ንቁ መሆን፣ መነሣትና ብርታት ማግኘት ሲባል ምን ማለት እንደሆነ መወያየት ትችላላችሁ። በዚህ ጥቅስ ውስጥ ጌታ የሚጠይቀን ምን እንድናደርግ ነው?
-
ልጆቻችሁ ደግሞ ኢሳይያስ 51፥1፣ 4፣ 7ን በማንበብ ጌታ የሚናገረው ለማን እንደሆነና ምን እንዲያደርጉ እንደሚፈልግ ለይተው ማወቅ ይችላሉ። እግዚአብሔርን “መስማት” ሲባል ምን ማለት ነው? እግዚአብሄርን “እንደምንሰማው” ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ኢሳይያስ 53፥3–9
ኢየሱስ ክርስቶስ የእኔን ሃጢያት እና ሃዘኖች በራሱ ላይ ወሰደ።
-
እናንየኢየሱስ ክርስቶስ መከራና ሞት የወንጌል ስዕሎች መፅሐፍ፣ ቁጥር፣ 56፣ 57፣ 58)። ከዚያም ኢሳይያስ 53፥3–9፣ በጋራ ማንበብና በሥዕሎቹ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ነገር የሚገልጹ ቃላትን መፈለግ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ እነዚህ እውነቶች ከመፈጸማቸው በመቶዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ኢሳይያስ እንደተናገረ እንዲገነዘቡ አግዟቸው። ሰዎች ይህን ያህል ብዙ ዓመታት ሳይቆዩ እነዚህን ነገሮች ማወቃቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (አልማ 39፥15-19 ተመልከቱ)።
-
ኢሳይያስ 53፥4ን ካነበቡ በኋላ “እርሱ ሕመማችንን ተሸከመ፣ ሀዘናችንንም ተሸከመ።” ልጆቻችሁ አንድን ከባድ ነገር ለማንሣት ልሞክሩ( ወይም ማንሣት የሚመስል ነገር ልታደርጉ) ትችላላችሁ። ህመም፣ ስቃይ እና ሀዘን እንዴት ከባድ እና ለመሸከም የከበደ ሊሆን እንደሚችል ይናገሩ። ኢየሱስ የእኛን “ህመም”፣ “ሀዘን”፣ እንዲሁም “በደል” ወይም ኃጢአት ለምን ተሸከመ?( በተጨማሪም አልማ 7፥11-12)።
ኢሳይያስ 55፥6
እኔ ጌታን መፈለግ እና መጥራት እችላለሁ።
-
ልጆቻችሁን ስለ ኢሳይያስ 55፥6፣ ለማስተማር የኢየሱስን ስዕል በአንድ ክፍል ውስጥ ደብቃችሁ ማስቀመጥ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ስዕሉን እንዲፈልኙ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ፤ እንዲሁም “እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት” የሚሉትን አንድ መንገድ መጥቀስ ትችላላችሁ። “Seek the Lord Early [እግዚአብሔርን አስቀድማችሁ ፈልጉት]” አይነት መዝሙር (የልጆች መዝሙር ፣ 108) ሀሳብ ሊሰጣቸው ይችላል። ከዚያም ከልጆቹ መካከል አንዱ ሥዕሉን እንዲደብቅና እንቅስቃሴውን እንዲደጋገም ልታደርጉ ትችላላችሁ።
ኢሳይያስ 55፥8–9
የጌታ መንገድ ከእኔ ይበልጣል።
-
ኢሳይያስ 55፥9ን ካነበቡ በኋላ፣ ለልጆቻችሁ መድረክ ላይ ቆመው ከፍ ስትሉ ነገሮች እንዴት እንደሚለዩ መናገራቸው አስደሳች ሊሆን ይችላል። ወይም ኢሳይያስ 55፥9 ለእነሱ ምን ትርጕም እንዳለው በስዕል ሊገልጹ ይችላሉ። ከዚያም ከኛ የላቁትን የጌታን መንገዶች መወያየት ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ ኃጢአተኞችን የሚይዝበት መንገድ ምንድን ነው?(ማርቆስ 2፥15-17ን ተመልከት)። አምላክ ሌሎችን የሚመራበት መንገድ ምንድን ነው?(ማቴዎስ 20፥25-28ን ተመልከት።) በጌታ መንገዶችና ሃሳቦች ላይ እምነት መጣል እንዴት እንደተማራችሁ ለልጆቻችሁ አካፍሏቸው።
ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።