ኑ፣ ተከተሉኝ
መስከረም 28–ጥቅምት 4 (እ.አ.አ)። “ሕዝቤን አጽናኑ”፦ ኢሳይያስ 40–49


“መስከረም 28–ጥቅምት 4 (እ.አ.አ)። “ሕዝቤን አጽናኑ”፦ ኢሳይያስ 40-49፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) 2026 (እ.አ.አ)

“መስከረም 28–ጥቅምት 4 (እ.አ.አ)። ‘ሕዝቤን አጽናኑ’ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ አይነ ስውርን ሲፈውስ

አይነ ስውርን በመፈወስ ላይ፣ በካርል ሃይንሪክ ብሎክ፣ በፌሬሪክስቦርግ ብሔራዊ ታሪክ ሙዚየም።

መስከረም - ጥቅምት 4፦ “ሕዝቤን አጽናኑ”

ኢሳይያስ 40–49

“አጽናኑ” የኢሳይያስ ምዕራፍ 40 መጀመሪያ ቃል ነው። በነብዩ መልዕክት ውስጥ የተለየ ቃናን፣ የተለየ አፅንዖትን መጀመሪያ ምልክት ያደርጋል። ኢሳይያስ ቀደም ሲል የጻፋቸው መጻሕፍት በእስራኤልና በይሁዳ ኃጢአት ምክንያት ስለሚመጣው ጥፋትና ምርኮ ያስጠነቅቁ ነበር። ሆኖም እነዚህ ትንቢቶች የተነገሩት ከ150 ዓመታት በኋላ ማለትም ኢየሩሳሌም እና ቤተ መቅደሱ ከወደሙና ሕዝቡ በባቢሎን በግዞት ከተወሰዱ በኋላ ነው። ነገር ግን እነዚህ ትንቢቶች ለተሸነፉት፣ ተስፋ ለቆረጡት እስራኤላውን ብቻ ሳይሆን ለወደፊትም ዘልቆ ይደርሳሉ። አንዳንድ ጊዜ የተሸነፍን፣ ተስፋ የቆረጥን እንዲሁም የጠፋን መስሎ ለሚሰማን እኛን ይናገሩናል።

ለእነሱ እና ለእኛ የኢሳይያስ መልዕክት ቀላል ነው፦ “አትፍሩ” (ኢሳይያስ 43፥1)። ሁሉም አልጠፋም። እግዚአብሔር አልረሳዎትም፣ እና ከቁጥጥሮ ውጪ ለሚመስሉ ሁኔታዎች ኃይል አለው። “ሰማያትን የፈጠረው” ጌታ (ኢሳይያስ 42፥5)፣ ከባቢሎን፣ ከኃጢአት፣ ከያዛችሁ ነገር ሁሉ የበለጠ ኃያል አይደለምን? “ተቤዥቼሃለሁና ወደ እኔ ተመለስ”፣ ብሎ ይለምናል (ኢሳይያስ 44፥22)። ሊፈውስ፣ ሊመልስ፣ ሊያጠነክር፣ ይቅር ሊል እና ሊያፅናና ይችላል—ለእርሶ የሚያስፈልግን ማንኛውንም ነገር ሁሉ፣ እርስዎን ለመቤዠት።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኢሳይያስ 40–49

የሴሚናሪ ምልክት
ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያፅናናኝ እና ተስፋ ሊሰጠኝ ይችላል።

እስራኤላውያን በባቢሎን በግዞት በነበሩበት ወቅት ብዙዎች፣ አምላክ የመረጣቸው የቃል ኪዳን ሕዝብ መሆናቸውን ለዘላለም አጥተው ይሆን ብለው አስበው ሊሆን ይችላል። ኢሳይያስ 40–49ን ሲያነቡ መፅናናትን እና ተስፋን የሰጦትን ገፆች ይፈልጉ። በሚያገኙት በእያንዳንዱ ገፅ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እግዚአብሔር ለ እርሶ የሚለውን ነገር ያሰላስሉ ወይም ይመዝግቡ። ልትጀምሩት የምትችሉባቸው የተወሰኑ ጥቅሶች እነሆ፦

  • 40፥11፣ 29–31

  • 41፥10–13፣ 17–18

  • 42፥6–7

  • 43፥1-7፣ 25

  • 44፥1–4፣ 21–24

  • 46፥3–4

  • 49፥7–16

ጌታ ስለ አምላክ ስለ እሱ ምን እንድታውቅ ይፈልጋል?

How Firm a Foundation [እንዲት ፅኑ መሰረት]”(መዝሙር፣ ቁጥር 85) የሚለው መዝሙር በኢሳይያስ 41፥1043፥2–546፥4 ላይ የሚገኙትን የኢሳይያስ ቃላት እንደያዘ አስተውላችሁ ይሆናል። ይህን መዝሙር በመዘመርና በማዳመጥ ከኢሳይያስ መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኙት ጥቅሶች ጋር ተመሳሳይነት ለማግኘት ሞክሩ። ጌታ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉትን ተስፋዎች የገባውን ቃል በህይወታችሁ የፈፀመው እንዴት ነው?

በተጨማሪም ፓትሪክ ኪረን፣ “He Is Risen with Healing in His Wings: We Can Be More Than Conquerors፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 37-40 ተመልከቱ።

ተጨማሪ ጥቅሶችን ተጠቀሙ። አንዳንድ ጊዜ ጥናታችንን ከመጽሐፈ ሞርሞን ጥቅሶች ጋር በማቀናጀት ብሉይ ኪዳንን በተሻለ መረዳት እንችላለን። ለምሳሌ የመጽሐፈ ሞርሞን ነቢያት ኔፊ እና ያዕቆብ በነሃስ ሰሌዳዎች ላይ የኢሳይያስን ጽሑፎች ማግኘት ችለዋል(1 ኔፊ 19፥22-23)፣ እናም ስለ አዳኙ ለማስተማር እነዚህን ትንቢቶች ተጠቅመዋል። ኔፊ እና ያዕቆብ ኢሳይያስ 48–49 እንዴት ለህዝባቸው እንዳመሳሰሉት ለመማር 1ኛ ኔፊ22 ተመልከቱ። እነዚህ ምዕራፎች ከራችሁ ሕይወት ጋር እንዲመሳሰሉ ሊረዳችሁ ይችላል።

ሰፊና ጥልቀት የሌለው ወንዝ

እግዚአብሔርን በመታዘዝ “ሰላም … እንደ ወንዝ” ሊኖረን ይችላል (ኢሳይያስ 48፥18)።

ኢሳይያስ 40–49

“አንተ የእኔ አገልጋይ ነህ።”

በመላ ኢሳይያስ 40–49 ውስጥ እግዚአብሔር ስለእርሱ “አገልጋይ” እና ስለእርሱ “ምስክር” ይናገራል። እነዚህ ቃላት ኢየሱስ ክርስቶስን(ኢሳይያስ 42፡17)፣ የእስራኤልን ቤት(ኢሳይያስ 45፡4) እና አይሁድ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ቤተ መቅደሱን እንዲገነቡ የፈቀደው ንጉሥ ቂሮስን(ኢሳይያስ 44፡26፡2845፡1–4) ሊያመለክቱ ይችላሉ። በተጨማሪም እነዚህ ጥቅሶች እንደ አምላክ አገልጋይ እና ምስክር እንዴት ሊጠቅሟችሁ እንደሚችሉ አስብ። ለምሳሌ፣ እንደነዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን ያሰላስሉ፦

ኢሳይያስ 40፥1–3፣ 9–1143፥9–12 የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር የሆኑት በምን መልኩ ነው? የእሱ ምስክር እንደመሆናችሁ መጠን ልታካፍሊአቸው የምትችሏቸው “ምሥራቾች” ምንድን ናቸው? የፍርድ ቤት ችሎት ውስጥ ለምስክርነት እንትቀርቡ ተጠርታችሁ እንደነበር መገመት ትችላላችሁ። በዚህ የፍርድ ሂደት ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ በኢሳይያስ 43፥11 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን ሃሳብ በመናገር ተከሰሰ። ኢየሱስ የተናገረውን ለመደገፍ ምን ማስረጃ ልታቀርቡ ትችላላችሁ? ከሕይወታችሁ ምን ማስረጃ ታቀርባላችሁ?

ኢሳይያስ 41፥8–1342፥644፥21 እግዚአብሔር ምን እንዲያደርጉ ጠርቶዎታል? እርሱን ለማገልገል ያላችሁን መደበኛ የቤተክርስቲያን ጥሪዎች እንዲሁም ሌሎች የቃልኪዳን ሃላፊነቶችን አስቡ። እንዴት “ሰርቷችኋል” ወይም የእርሱ አገልጋይ እንድትሆን ያዘጋጃችሁ እንዴት ነው? በምታገለግሉበት ጊዜ የሚደግፋችሁ እንዴት ነው?

ኢሳይያስ 49፥1–9 በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የምታደርጉት ጥረትና የምታቀርቡት አገልግሎት “ከንቱ” እንደሆነ በሚሰማችሁ ጊዜ ሊረዷችሁ የሚችሉ ምን መልዕክቶች ታገኛላችሁ?(ቁጥር4)።

ኢሳይያስ 40፥3–8፣ 15–2342፥15–1647፥7–11

የእግዚአብሔር ኃይል ከዓለማዊ ኃይል የላቀ ነው።

ኢሳይያስ ከከበባቸው ከተቃዋሚ ዓለማዊ ኃይል ጋር ሲነፃፀር አቻ ስለሌለው የእግዚአብሔር ኃይል በተደጋጋሚ ለህዝቦቹ አስገነዘበ። ኢሳይያስ 40፥3–8፣ 15–2342፥15–16፤ እና 47፥7–11 ን ሲታነቡ ይህንን መልዕክት ለማግኘት ማክሩ( ምዕራፍ 47 የእስራኤል ማራኪ ለነበረችው ለባቢሎን እንደተጻፈ ልብ በሉ)። እነዚህ ምንባቦች ስለዓለማዊ ነገሮች ምን ያስተምሮታል? ስለእግዚአብሔር ምን ያስተምሮታል? ይህ መልዕክት ለአይሁዶች በምርኮ ውስጥ ለምን ጠቃሚ እንደነበር አሰላስሉ። ለእርሶ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ኢሳይያስ 48፥1049፥13–16

ጌታ ከመከራዬ ሊያነፃኝ ይችላል።

ኢሳይያስ 48፥10ን ስታነብ ስለ ራስህ “የመከራ እቶን” አስቡ። ጌታ “የሚያነፃችሁ” እንዴት ነው? ኢሳይያስ 49፥13–16 መከራ ሲደርስባችሁ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም “The Refiner’s Fire” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

5:2

The Refiner's Fire

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ኢሳይያስ 40፥3–5

“የጌታን መንገድ” ለማዘጋጀት እረዳለሁ።

  • ኢሳይያስ 40፥3–5 ላይ እንደተገለጸው “የጌታን መንገድ ማዘጋጀት” ሲባል ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል በምሳሌ ለማስረዳት አንዳንድ መንገዶችን እንመልከት። ለምሳሌ፣ እናንተና ልጆቻችሁ የተጣመመ ነገር ማቅናት ፣ የቆሸሸ ወለል ማጽዳት ወይም ድንጋያማ በሆነ መሬት ላይ ግልጽ የሆነ ጎዳና መዘርጋት ትችላላችሁ የመጥምቁ ዮሐንስን እና የጆሴፍ ስሚዝን ፎቶዎች ማሳየትም ይችላሉ ( የወንጌል የስነጥበብ መጽሐፍ፣ ቁጥሮች 3587ተመልከቱ። ለጌታ መምጣት መንገዱን እንዴት ነው ለማዘጋጀት የረዱት? ( ሉቃስ 3፥2–18ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥3ይመልከቱ)። እንዴት መርዳት እንችላለን? አሮናዊ የክህነት ስልጣን ተሸካሚዎች የጌታን መንገድ ለማዘጋጀት እንዴት እንደሚረዱ ለመነጋገር ይህ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84:26ተመልከቱ)።

ኢሳይያስ 43፥10

የጌታ ምስክር መሆን እችላለሁ።

  • ኢሳይያስ 43፥10ን በጋራ ካነበባችሁ በኋላ ምስክር መሆን ሲባል ምን ማለት እንደሆነ መወያየት ትችላላችሁ። ያጋጠማችሁን ገሮች ለሌሎች አካፍሉ፣ ለምሳሌ እናንተ የቀመሳችሁትን ምግብ፣ የጎበኛችሁትን ቦታ ወይም የምታውቁትን ሰው “ምስክር” መሆን ትችላላችሁ። የጌታ ምስክር መሆን ሲባል ምን ማለት ነው? የጌታ ምስክር መሆን ሲባል ምን ማለት ነው?

ኢሳይያስ 44፥3–445፥8

ጌታ በረከቱን በእኔ ላይ “ያፈስሳል”።

  • ልጆቻችሁ እነዚህን ጥቅሶች ካነበቡ በኋላ አንድን ተክል ውሃ በማጠጣት ጌታ በእነሱ ላይ ስላፈሰሰው በረከት ማውራት ይችላሉ። አንድን ተክል ውኃ ስናጠጣው ምን ይሆናል? የጌታ በረከቶች እንድናድግ የረዱን እንዴት ነው?

ትልቅ የውቅያኖስ ማዕበል።

“ጽድቅህ እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል”(ኢሳይያስ 48፥18)።

ኢሳይያስ 48፥17–18

የእግዚአብሄርን ትእዛዛት መጠበቅ ሰላም ያስገኛል።

  • ስለ ወንዞችና ስለ ውቅያኖስ ሞገዶች የሚያሳዩ ስዕሎች ወይም ቪዲዮዎች ልጆቻችሁ ኢሳይያስ 48፥18ን በዓይነ ሕሊናቸው እንዲመለከቱ ሊረዷቸው ይችላሉ። ልጆቻችሁ እንደ ወንዝ እና እንደ ባሕር ሞገዶች እጆቻቸውን እና ክንዶቻቸውን በማንቀሳቀስ ይደሰቱ ይሆናል። ሰላም እንደወንዝ መሆን የሚችለው እንዴት ነው? ጽድቅ እንደ ማዕበሎች መሆን የሚችለው እንዴት ነው? የእግዚአብሄርን ትእዛዛት መጠበቅ እንደ ወንዝ ሰላምና እንደ ማዕበል ጥንካሬ እንዲሰማችሁ እንዴት እንደረዳችሁ ተናገሩ።

  • ስለ ትእዛዛት መዝሙር አብራችሁ ዘምሩ፣ ለምሳሌ እንደ “ትእዛዛትን ጠብቁ” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 146-47)። ይህ መዝሙር የእግዚአብሄርን ትእዛዛት መጠበቅ ያለብን ለምን እንደሆነ ምን ያስተምረናል?

ኢሳይያስ 49፥14–16

ጌታ መቼም አይረሳኝም።

  • ኢሳይያስ 49፥14–16 ለወደፊቱ ጊዜ ለልጆቻችሁ ትልቅ ማጽናኛ ሊሆንላቸው ይችላል። ቁጥር 14ን በምታነቡበት ጊዜ ሰዎች እንደተረሱ ወይም እንደተተዉ እንዲሰማቸው ሊያደርጉ ስለሚችሉን ነገሮች ልትወያዩ ትችላላችሁ። ጌታ እንዳልረሳን እንዴት እናውቃለን?

  • ቍጥር 15–16ን ለማስተዋወቅ ልጆቻችሁን ፈጽሞ ስለማይረሱት የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ መጠየቅ ትችላላችሁ። በኢሳይያስ 49፥15-16 መሠረት ጌታ መቼም ቢሆን የማይረሳን ለምንድን ነው? ከዚያም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ስሜት ለሌሎች ማካፈል ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።

ኢየሱስ አንድ ወንድና አንዲት ልጅ ጋር።

ገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት፣ በአኒ ሄንሪ ናዴር

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፦የጌታ ምስክር መሆን እችላለሁ።