ኑ፣ ተከተሉኝ
ጥቅምት 12–18 (እ.አ.አ)። “ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል”፦ ኢሳይያስ 58–66


“ጥቅምት 12–18 (እ.አ.አ)። “ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል”፦ ኢሳይያስ 58–66,‘” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 (እ.አ.አ)]

“ጥቅምት 12–18 (እ.አ.አ)። “ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል” ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ በምኩራብ ውስጥ ለሰዎች ጥቅልል ​​ሲያነብ

ኢየሱስ በናዝሬት በምኩራብ ውስጥ፣ በግሬግ ኦልሰን

ኢሳይያስ 12–18፦ “ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል”

ኢሳይያስ 58–66

በምድራዊ አገልግሎቱ የመጀመሪያዎቹ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ባደገበት መንደር በናዝሬት ውስጥ አንድ ምኩራብን ጎበኘ። እዚያም ከቅዱሳን መጽሐፍት ለማንበብ ቆመ፣ የኢሳይያስን መጽሐፍ ከፈተ እና አሁን ኢሳይያስ 61፥1–2፣ ብለን የምናውቀውን አነበበ። ከዚያም እንዲህ አስታወቀ፣ “ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ።” ይህ የአዳኙ ቀጥተኛ የሆነ የተቀባው እርሱ እንደሆነ፣ “ልበሰባራዎችን የሚፈውስ” እና “ለታሰሩትም መፈታትን የሚሰብክ” እንደሆነ የገለፀበት አንዱ መንገድ ነው ( ሉቃስ 4፥16–21ይመልከቱ)። ይህ ቅዱስ ጽሁፍ በእርግጥ በዚያን ቀን ተፈጸመ። እናም ልክ እንደሌሎች ብዙ የኢሳይያስ ትንቢቶች፣ በዘመናችን ውስጥ እየተፈጸመ ነው። አዳኙ ወደ እርሱ የሚመጡትን ልባቸው የተሰበረውን ሁሉ መፈወሱን ቀጠለ። አሁንም ነጻነት የሚያስፈልጋቸው ብዙ ምርኮኞች አሉ። መዘጋጀት የሚጠይቅ ታላቅ ነገር ወደፊት አለ—እሱም እግዚአብሔር “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር [የሚፈጥርበት]” (ኢሳይያስ 65፥17) እና “ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ [የሚያበቅልበት]” ጊዜ ነው (ኢሳይያስ 61፥11)። ኢሳይያስን ማንበብ እግዚአብሔር ላደረገው ነገር፣ እያደረገ ላለው ነገር እና ለህዝቦቹ ለሚያደርገው ነገር አይኖቻችንን ይከፍታል።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኢሳያስ 58፥3–12

የሴሚናሪ ምልክት
ጾም መንፈሳዊ ኃይልን ይገነባል እንዲሁም የተቸገሩ ሰዎችን ይባርካል።

ለምንድን ነው ምግብ እያለ ሰዎች በፍቃዳቸው ያለምግብ የሚሄዱት? ኢሳያስ 58፥3–12ን ስታነቡ ለምን ምክንያት እንደምትጾሙ እንዲሁም ጌታ ይህን ትህዛዝ ለምን እንደሰጠ አስቡ። የሚቀጥሉት የምታስቡባቸው አንዳንድ ጥያቄዎች ናቸው፥

  • ለምንድነው አንዳንድ ጊዜ ጾም ከበረከት ይልቅ እንደ ሸክም የሚታሰበው? (ኢሳያስ 58፥3–5ተመልከቱ)። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉት የጌታ ትምህርቶች ለእናንተ ያንን አመለካከት የሚቀይሩላችሁ እንዴት ነው?

  • “የክፋትን እስራት” እና “ቀንበርን ሁሉ መስበር” ምን ማለት ሊሆን ይችላል? (ኢሳይያስ 58፥6)። መፆም እንዴት ሌሎችን ሊባረክ ይችላል? (ቁጥር 7ተመልከቱ)።

  • ፆም በ ኢሳይያስ 58፥8–12፣ ውስጥ የተጠቀሱትን በረከቶች ያመጣሎት እንዴት ነው ?

Is Not This the Fast That I Have Chosen?[እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን?]” በሚለው መልዕክቱ ውስጥ (ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 22–25)፣ ፕሬዝዳንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ እንዴት ሰዎች በፆም እና በፆም በኩራት እንዴት እንደተባረኩ ብዙ ምሳሌዎችን አካፈለዋል። በሕይወትዎ ውስጥ ተመሳሳይ በረከቶችን የተመለከቱት እንዴት ነው?

በተጨማሪም Bless Our Fast, We Prayመዝሙር፤ ቁጥር 138፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “ጾምና የጾም በኩራት፣” የወንጌል ላይብረሪ፣ ተመልከቱ።

የምታስተምሩቸውን ሰዎች እወቁ። “ክርስቶስ መሰል አስተማሪ መሆን የምታስተምሯቸውን ሰዎች ማወቅ እና በልባቸው ውስጥ ያለውን ነገር ለመረዳት መጣርን ያካትታል… እንዴት የበለጠ መማር እንደሚችሉ ማወቅ ትችላላችሁ። ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ በጥንቃቄ ማዳመጥ እና መመልከት ትችላላችሁ። ከሁሉም በላይ መንፈስ ብቻ መስጠት የሚችለውን ግንዛቤ ለማግኘት መጸለይ ትችላላችሁ። አንድ ሰውን የበለጠ ስታውቁ እሱ ወይም እሷ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ የበለጠ ግላዊ ትርጉም እና ኃይል እንዲያገኙ ለመርዳት ትችላላችሁ። “የአንድ ሰውን ጥማት ስትረዱ በአዳኙ የሕይወት ውኃ እንዴት እንደምታረኩት መንፈስ ሊያስተምራችሁ ይችላል” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 13)።

ኢሳይያስ 58፥13-14

ጌታን በሰንበት ቀን ማክበር ደስታን ያመጣል።

የሰንበት ቀን ለእናንተ “ደስታ” ነው? ኢሳይያስ 58፥13-14ን ስታጠኑ በጌታ ቀን እንዴት የበለጠ ደስታን እንደምታገኙ አስቡ። ለምሳሌ ያህል፣ “በቅዱስ ቀን ፈቃድህን ከመፈጸም መመለስ” ሲባል ምን ማለት ሊሆን ይችላል? “ራስህን ለጌታ በመስጠት” እና “የራስህን መንገድ በማድረግ” መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ሰንበት አስደሳች ነች፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 129–32 ተመልከቱ።

ኢሳይያስ 59፥9–2161፥1–363፥7–9

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ እና ቤዛዬ ነው።

ኢሳይያስ 58–66 ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የቤዛነት ተልዕኮ ብዙ ማጣቀሻዎችን ያገኛሉ። በምትማሩበት ግዚ ተመልከቱቸው በተለይም አዳኝን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋሉትን ርዕሶች እና ቃላት ልብ በሉ። ለምሳሌ፦

  • ኢሳይያስ 59፥16-21 ስለ “አማላጅ” መግለጫ ምን ያስደንቃችኋል? በ ቁጥር 9-15፣ ውስጥ አዳኝ የተገለጹትን ሁኔታዎች እንዴት ያሸንፋል?

  • ኢየሱስ ክርስቶስ ለናዝሬት ህዝቦች አዳኘ እንደሆን ሲገልፅ ከኢሳይያስ 61፥1–3 ጠቅሷል (ሉቃስ 4፥16–21፤ በተጨማርም “ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን አወጀ፣” የሚለውን ቪዲዮ ከየወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ)። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በተገለፀው መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተን ወይም ሌሎችን የባረከው እንዴት ነው? በአመድ ፋንታ ቁንጅናን የሰጠው እንዴት ነው?

    3:24

    Jesus Declares He Is the Messiah

  • የትኞቹን “የጌታን ፍቅራዊ ደግነት” መጥቀስ ትችላላችሁ? (ኢሳይያስ 63፥7–9ተመልከቱ)።

  • ኢሳይያስ 58–66፣ ውስጥ አዳኙን የሚገልፁ ሌሎች ምን ማጣቀሻዎችን አገኙ?

እንዲሁም ሞዛያ 3፥7ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥46–53ን ይመልከቱ።

አንድ ወንድ እጆቹን በዘይት አምፖል ላይ ዘርግቶ የሴት መብራትን ለማብራት ሲሞክር

A Gift of Light [የብርሃን ስጦታ]፣ በኤቫ ቲሞቲ

ኢሳይያስ 6062

“እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናል።”

ኢሳይያስ60 እና62 ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዓለምን በመጨረሻው ቀናት እንዴት እንደሚባርክ ለማስተማር ስለብርሃን እና ጨለማ፣ ስለአይኖች እና ማየት ይናገራሉ። ለእነዚህ ሃሳቦች በተለይ በ ኢሳይያስ 60፥1–5፣ 19–2062፥1–2፣ ውስጥ ተመልከቱ። እነዚህን ምዕራፎች ስታነቡ እግዚአብሔር ልጆቹን ከጨለማ ወደ ብርሃን እንዴት እየሰበሰበ እንዳለ አሰላስሉ። በዚህ ስራ ውስጥ ሚናችሁ ምንድን ነው?

በተጨማሪም 1 ኔፊ 22፥3–123 ኔፊ 18፥24ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥9፤ ቦኒ ኤች. ኮርደን፣“That They May See [እንዲያዩት]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ) 78–80ን ተመልከቱ።

ኢሳይያስ 64፥1–565፥17–2566

ክርስቶስ በሚሊኒየም ወቅት በምድር ላይ ይነግሣል።

ኢሳይያስ “የቀድሞው ጭንቀት [ስለሚረሳበት]” ቀን ተናገረ (ኢሳይያስ 65፥16)። ይህ ትንቢት በርካታ ፍጻሜዎች ሲኖረው፣በሙሉ ትርጉሙ፣ ያ ቀን ገና ይመጣል—ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመለስበት ጊዜ። ኢሳይያስ ይህን የወደፊት ቀን በሚከተሉት ውስጥ ገልጿል፣ ኢሳይያስ 64፥1–565፥17–2566። “ደስታ” እና “ሐሤት” የሚሉትን ቃላት ምን ያህል ጊዜ እንደተጠቀመ ያስተውሉ። ለምንድን ነው የአዳኙ መመለስ ለእናንተ የደስታ ቀን የሚሆነው? ለእርሱ መምጣት ለመዘጋጀት ምን ማድረግ ይቸላሉ?

በተጨማርም የእምነት አንቀጾች1፥10፤ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የቤተ ክርስቲያን የወደፊት ዕጣ፤ ዓለምን ለአዳኝ ዳግም ምጽአት ማዘጋጀት ነው፣” ኢዛይን፣ ሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ)13–17።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ኢሳይያስ 58፥6-11

ጾም እኔንም እና ሌሎችን በረከት የሚፈልጉ ይባርካል።

  • ምናልባት ልጆቻችሁ እንዲጾሙ ለማበረታታት ምርጡ መንገድ ዝግጁ ሲሆኑ ጌታ ለዚህ ህግ ያለውን አላማ እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ኢሳይያስ 58፥6-11ን አብራችሁ በማንበብ እንደዚህ ላሉ ጥያቄዎች መልስ ፈልጉ፤ ለምንደ ነው የምንጾመው? የምንጾመው እንዴት ነው? በቅዱሳት መጻሕፍት መመሪያ ውስጥ Fast, Fasting [ጾም] የሚለውን መመልከት ትችላላችሁ።

  • ስለጾም ትርጉም ያለው ልምድ ካላችሁ ለልጆቻችሁ አካፍሉ። እንዲሁም ስለጾሙ ለማያውቅ ጓደኛቸው ጌታ ይህን ህግ ለምን እንደሰጠ እንዴት እንደሚያስረዱ ጠይቋቸው።

ኢሳይያስ 58፥13-14

ሰንበት ለእኔ አስደሳች ሊሆን ይችላል።

  • ኢሳይያስ 58፥13-14፣ ካነበባችሁ በኋላ የሳምንቱን ቀናት በቀን መቁጠሪያ ላይ በመጠቆም ልጆቻችሁ ከእናንተ ጋር ያሉትን ቀናት እንዲናገሩ መጋበዝ ትችላላችሁ። ወደ ሰንበት ስትደርሱ ያን ቀን “ደስታ” ብለው እንዲጠሩት ጠይቋቸው። የሰንበት ቀን ለእናንተ “ደስታ” ለምን እንደሆነ ንግሩዎቸው።

  • በሰንበት “በጌታ ደስ ሊላችሁ” የምትችሉበትን መንገድ እርስ በርሳችሁ አካፍሉ። ምናልባት ልጆቻችሁ ሃሳባቸውን ይሳሉ እና “የሰንበት ደስታ ሣጥን” ውስጥ ያስቀምጧቸዋል። ከዚያም በሰንበት ስለሚደረጉ ነገሮች ሀሳብ ሲፈልጉ ከሳጥኑ ውስጥ አንድ ሀሳብ ይጎትታሉ።

የኢየሱስ ምስል

የእኛ ብርሃን፣ በዳን ዊልሰን

ኢሳይያስ 60፥1–3

አዳኙ ለእኔ እንደ ብርሃን ነው።

  • ኢሳይያስ 60፥1–3 በምታነብበት ጊዜ ልጆቻችሁ ዓይኖቻቸውን እንዲጨፍኑ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። “ብርሃን” የሚለውን ቃል ሲሰሙ ዓይኖቻቸውን እንዲከፍቱ እና “ጨለማ” የሚለውን ቃል ሲሰሙ እንደገና እንዲዘጋቸው ጠይቋቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌሉ ወደ የሰማይ አባት የምንመለስበትን መንገድ ለማየት እንደሚረዱን ብርሃን እንደሆኑ አስረዱ።

ኢሳይያስ 65፥17–25

ኢየሱስ ዳግም ሲመጣ ሰላምን እና ደስታን ያመጣል።

  • ኢሳይያስ 65፥17–25 እንደተገለፀው አዳኙ ዳግም ሲመጣ ምድር ምን ትመስላለች። ይህን ቁጥር ከልጆቻችሁ ጋር ስታነቡ ኢሳይያስ እንደገለፀው አዲሱ ምድር እንዴት እንደሚለይ ተመልከቱ። ይህ ጊዜ “ለዘላለም የምንደሰትበት” ጊዜ ለምን ይሆናል? (ቁጥር 18)።

  • እንደ “When the Savior Comes Again [አዳኙ እንደገና ሲመጣ]” (የወንጌል ላይብረሪ) የመሠለ ስለዳግም ምጽዓት የሚያወሣ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ። ስለ አዳኝ መመለስ በጉጉት የምትጠብቁትን እርስ በርሳችሁ አካፍሉ። ለዛ ቀን ለመዘጋጀት ምን ማድረግ እንችላለን?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።

ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ፣ ብርሃን የሚወጣ

“ብርሃንሽ መጥቶአልና የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ አብሪ” (ኢሳይያስ 60፥1)። ብርሃን እና ሕይወት፣ በማርክ ማብሪ

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ፡ ሰንበት ለእኔ አስደሳች ሊሆን ይችላል።