በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ሁሉ ቅድስና ለጌታ
ቅድስና ለጌታ የዕለት ተዕለት ኑሮን የተቀደሰ ያደርገዋል። ወደ ጌታ እንዲሁም አንዳችን ወደሌላችን እንድንቀርብ እና የበለጠ ደስተኞች እንድንሆን ያደርገናል።
የእኛ በቅርብ ጊዜ ያደረገው የዳግም የጎንግ ቤተሰብ መሰባሰብ የተሰጥዖ ትዕይንት ያካትት የነበረ ሲሆን፣ የተጠናቀቀውም በአባቶች የቀልድ ውድድርነበር።
ነገር ግን ይህ ውድድር ያልተለመደ ነበር። በአንደኛው ቡድን አያት (እኔ) እና 12 እና 11 ዓመት እድሜ ያላቸው ሁለት ሴት የልጅ ልጆች ይገኙበታል። በሌላኛው ቡድን ውስጥ ደግሞ በወንድሜ ልጅ መመሪያ የሚሰጠው የጌሪት ደብሊው. ጎንግን አይነት የአባቶች ቀልድ እንዲናገር የሚታዘዘው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መተግበሪያ ነበር። አያት ጌሪት ጎንግ ከAI [ሰው ሰራሽ አስተውሎት] ጌሪት ጎንግ ጋር ሲወዳደሩ።
የልጅ ልጆቼ እና እኔ ጀመርን።
መኪናውን የሚያጋጭን ዳይኖሰር ምን ይባላል? ታይራኖሳረስ ሬክስ።
AI [ሰው ሰራሽ አስተውሎት] አያት ጌሪት ጎንግ—እንደ ጌሪት ደብሊው. ጎንግ እንዲያስብ ትዕዛዝ ይሠጠዋል። እንደ እርሱ ተናገር።
AI [ሰው ሰራሽ አስተውሎት] ጌሪት ጎንግም፦ “ሞቅ ያለ፣ አሳቢ እና አነቃቂ ስልቱን በማካተት የጌሪት ጎንግን ድምጽ ተመሥሎ የቀረበ የአባቶች ቀልድ እነሆ፦ ፥ ትሁቱዛፍ ሰዎችን የሚያስቀው ለምንድር ነው? መነሻ ሥር መሠረቱፍቀር ስለሆነ እና ወደ ሌሎች የሚደርስ የደግነት ቅርንጫፎች ስላሉት። እኛም ልክ እንደዛኛው ዛፍ፣ ከመነሻ ሥር መሠረታችን ጥንካሬን እንዲሁም መልካምነት ለሌሎች ከማሣየት ሀሴትን እናገኛለን።”
ታዲያ፣ ምን ይመሥላችኋል? ለዚያም ነው የአባቶች ቀልድ ተብለው የሚጠሩት።
ለመሳቅ፣ ደስታን ለማግኘት፣ ነገሮችን በአመስጋኝ ዕይታ ለመመልከት የሚያስችሉ ጥሩ አጋጣሚዎች በዙሪያችን ሁሉ ይገኛሉ። ወንጌላችን በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የደስታ እና የቅድስና ወንጌል ነው። ቅድሥና ነገሮችን ለቅዱስ ዓላማ ይለያል። ይሁን እንጂ ቅድስና የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን ቅዱሥ በሆነው ነገር እንድንሞላም—ይኸውም፣ በዚህ ዓለም አሜኬላና እሾህ መካከል በዕለት እንጀራችን ደሥ እንድንሠኝም ይጋብዘናል። ከጌታ ጋር ለመመላለስ ቅዱስ መሆን አለብን፤ ምክንያቱም እርሱ ቅዱስ ነውና ፥ እንዲሁም፣ ቅዱስ እንድንሆን ለመርዳት፣ ጌታ ከእርሱ ጋር እንድንሄድ ይጋብዘናል።
እኛ እያንዳዳችን ታሪክ አለን። እህት ጎንግ እና እኔ እናንተን በተለያዩ ቦታዎች እና ሁኔታዎች ውስጥ የምትገኙትን የቤተክርስቲያኗን አባላት እና ጓደኞች —ስናገኛችሁ—ቅድስና ለእግዚአብሔር በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ሁሉ መሥጠትን አስመልክቶ ያላችሁ ታሪክ ያነቃቃናል። ከቅድስና ጋር የተያያዙትን ሰባቱን መርሆች ትኖራላችሁ፦ ከእግዚአብሔር ጋር ጥልቅ ዝምድና መመሥረት፣ የጋራ ፍላጎት እና አንዳችን ለሌላችን ርህራሄ ማሣየት፣ ለእግዚአብሔር፣ ለቤተሰብ እና ለጓደኞች ቁርጠኝኛ መሆን እንዲሁም ለእነርሱ ቃል ኪዳን መግባት እርሱም —ኢየሱስ ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ መሆን አለበት።
እያደገ የመጣው መረጃ ይህንን በገሃድ የሚታይ እውነታ አጉልቶ ያሣያል፦፥ የሐይማኖት አማኞች የሆኑ ሠዎች በአማካ ሲታይ መንፈሳዊ ቁርጠኝነት ወይም ግንኙነት ከሌላቸው ሰዎች ይበልጥ ደስተኞች፣ ጤናማና ረክተው የሚኖሩ ናቸው። በደስታ እና በህይወት እርካታ፣ በአእዕምሮና በአካል ጤንነት፣ ሕይወትን በትርጉም እና በዓላማ በመኖር፣ .በመልካም ባህሪና በጎነት፣ ቅርብ በሚያደርግ ማህበራዊ ግንኙነቶች በመኖር፣ የተረጋጋ የገንዘብእና የቁሳዊ ነገሮች ባለቤት በመሆን እንኳን—በእያንዳዱ ከላይ በተዘረዘሩት መለኪያዎች የሐይማኖት እምነት ተሳታፊዎች ያብባሉ።
በሁሉም የእድሜ ክልል እና የሥነ ሕዝበ አወቃቀር ቡድኖች ውስጥ የተሻለ የአካል እና የአእምሮ ጤና እንዲሁም የላቀ የህይወት እርካታን ያገኛሉ።
ተመራማሪዎች “ሃይማኖታዊ መዋቅራዊ እርጋታ” ብለው የሚጠሩት ነገር በሕይወት አስገራሚና ያልተጠበቁ ክስተቶች ውስጥ ግልጽነትን፣ አላማን እና ጥንካሬን ይሰጣል። እምነት ያለው ቤተሠብ እና ማህበረ ቅድሳን በሌላ እምነት ያሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህዝቦች የሚሰማቸውን የመነጠል እና የብቸኛነት ስሜት ያስወግዳሉ። ቅድስና ለጌታ ጸያፍ ንግግሮችን አይቀበልም፣ በሌሎች ላይ ማሽሟጠጥን አይቀበልም፣ በማህበራዊ ሚዲያ ገንዘብ ለማግኛነት የሚሰሩ ቁጣን እና ፅንፈኝነትን የሚያራምዱ አልጎሪዝሞችን አይቀበልም። ቅድስና ለጌታ፣ ቅዱስ እና ጥልቅ አክብሮት ያለውን ነገር ይቀበላል፤ በእምነት፣ በነፃነት፣ በደስታ፣ በተሻለ ማንነታችን በእምነት እርሱን መከተልን ይቀበላል።
በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ሁሉ ቅድስና ለጌታ መስጠት ምን ይመስላል?
በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ሁሉ ቅድስና ለጌታ መስጠት፣ የወንጌል ቃል ኪዳኖችን፣ መስዋዕትነትን፣ እና አገልግሎትን በእውነተኛነት እና ለጥቃት በሚያጋልጥ ሁኔታ በህይወታቸው ውስጥ ያጋሩ ለአንድ ዓመት በትዳር የቆዩ፣ ሁለት አማኝ ወጣት ጎልማሶችን ይመስላል።
እርሷ እንዲህ በማለት ትጀምራለች፣ “የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ስጀምር በሐዘንና ተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ነበርኩ። እግዚአብሔር ከጎኔ እንደሌለ ይሠማኝ ነበር። አንድ ምሽት፣ ከአንድ ጓደኛዬ ‘አልማ 36ን አንብበሽ ታውቂያለሽ?’ የሚል ፅሁፍ ደረሰኝ።
“ማንበብ በጀመርኩ ጊዜ፣” ብላ አለች “በውስጤ ሰላምና ፍቅር ተሠማኝ። በደንብ የታቀፍኩኝ ያህል ተሰማኝ። አልማ 36፥12ን ሳነብ፣ የሰማይ አባት ስሜቴን በትክክል ያውቅ እንደነበር እና ያየኝ እንደነበርም አወቅኩኝ።”
እንዲህ ስትል ቀጠለች፣ “ከመጋባታችን በፊት ስለ አስራት የጠለቀ ምስክርነት እንደሌለኝ ለእጮኛዬ በታማኝነት ነግሬው ነበር። ሌሎች ሰዎች ብዙ የሚሰጡበት ነገር እያላቸው እግዚአብሔር እኛ ገንዘብ እንድንሰጥ የፈለገው ለምንድን ነው? እጮኛዬም እግዚአብሔር የእኛን ገንዘብ ፈልጎት ሳይሆን ነገር ግን እኛ የተጠየቅነውን ነገር እንደምንታዘዝ ለማዋቅ እንደሆነ በማስረዳት አገዘኝ። አሥራት መክፈል እንድጀምር ገፋፋኝ።
“በእርግጥም ምስክርነቴ እያደገ ሲሄድ አየሁ፣” ብላ አለች። “አንዳንድ ጊዜ ገንዘብ ለሚያስፈልጉን ነገሮች በቂ ሳይሆን ይቀራል፣ ሆኖም ብዙ በረከቶች እንዳገኘንና በተወሰነ መልኩ ደሞዛችን በበቂ ሁኔታ ሲያኖረን አይተናል።”
በተጨማሪም፣ “በነርስ የህክምና ትምህርት ክፍሌ ውስጥ፣” ብላ አለች፣ “ብቸኛ የቤተክርስቲያኗ አባል እና ብቸኛዋ ያገባች ሰው እኔ ብቻ ነበርኩ። የክፍል ጓደኞቼ እኔን በመለየት ስለ እምነቴ፣ የቤተመቅደስ ልብስ በመልበሴ ወይም በጣም በልጅነቴ ባለትዳር በመሆኔ አሉታዊ የሆኑ አስተያየቶችን ይሠጡኝ ስለነበር፣ ብዙ ጊዜ ከክፍል ስወጣ የመበሳጨት ወይም የማልቀስ ስሜት ይሰማኝ ነበር።”
እንዲህም በማለት ቀጠለች፣ “በዚህ ባለፈው የትምህርት ዘመን ስለእምነቴ እንዴት በተሻለ መንገድ መናገር እንዳለብኝና ጥሩ የወንጌል ምሳሌ መሆን እንደምችል ተማርኩ። ብቻዬን የመቆም እና ባመንኩበት ነገር ጠንካራ የመሆን ችሎታዬ በመፈተኑ ምክንያት እውቀቴ እና ምስክርነቴ አደጉ።
ወጣቱ ባል በማከልም እንዲህ አለ፣ “ወደ ሚስዮን ከመሄዴ በፊት ለኮሌጅ ቤዝቦል እንድጫወት ግብዣዎች ቀርበውልኝ ነበር። ግብዣዎቹን ወደ ጎን በማድረግ እግዚአብሔርን የማገልገልን ከባድ ውሳኔ ወሠንኩኝ። እነዚያን ሁለት ዓመታት በምንም ነገር አለውጣቸውም።
“ወደ ቤት ስመለስ፣” ብሎ አለ፣ “አስቸጋሪ ለውጥ እንደሚሆንብኝ ብጠብቅም፣ እራሴን ይበልጥ ጠንካራ፣ ፈጣን እንዲሁም ጤናማ ሆኜ አገኘሁት። ከመሄዴ በፊት እወረውር ከነበረው የበለጠ በጥንካሬ እወረውር ነበር። ከመሄዴ በፊት ከቀረቡልኝ ግብዣዎች ይበልጥ፣ ከምመኘው ትምህርት ቤት ጨምሮ ለመጫወት ብዙ ግብዣዎች ቀረቡልኝ። ከሁሉም በላይ ደግሞ፣” ብሎ አለ “ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ፣ በጌታ ላይ ታመንሁ።”
እንዲህ ሲል ደምድሟል፣ “እንደ ሚስዮናዊ፣ የሰማይ አባት በጸሎታችን ውስጥ ሀይል እንደሚሰጠን ቃል እንደገባልን አስተምሬያለሁ፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ያ ለራሴም እንደሚሠራ እረሳዋለሁ።”
በሚስዮናዊነት በማገልገል ለጌታ ቅድስናችንን መግለጻችን የሚያስገኛቸው በረከቶች ብዙና የተሟሉ ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ጊዜ እና ሌሎች ሁኔታዎች በቀላሉ አይሟሉም። ነገር ግን ከሁሉም የእድሜ ክልል እና አስተዳደግ የመጡ ሚስዮናውያን ቅድስናን ለጌታ በቅድስና ሲሠጡ፣ ነገሮች በጌታ ጊዜና መንገድ አዎንታዊ ውጤት ይኖራቸዋል።
አሁን 48 ዓመት በሆነው አስተያየት፣ አንድ አረጋዊ ሚስዮናዊ እንዲህ በማለት ያጋራል፣ “አባቴ ወደሚስዮን እንድሄድ ሳይሆን የኮሌጅ ትምህርት እንድማር ፈልጎ ነበር። ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የልብ ድካም በሽታ ገጠመውና በ47 ዓመቱ ሞተ። የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ። ከአባቴ ጋር የነበሩኝን ነገሮችን ማስተካከል የምችለው እንዴት ነው?
“በኋላ፣” እንዲህ በማለት ቀጠለ፣ “በሚስዮን ለማገልገል ከወሰንኩ በኋላ አባቴ የቤተመቅደስ ልብሥ ለብሶ በሕልሜ አየሁት። ሰላማዊና እርካታ ያለው እንዲሁም በማገልገሌ ደስተኛ ሠው ሆኖ ነበር።”
ይህም አረጋዊ ሚስዮናዊ እንዲህ በማለት ያክላል፣ “ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 138 እንደሚያስተምረው፣ አባቴ በመንፈስ አለም ውስጥ ሚስዮናዊ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል አምናለሁ። አባቴ በ17 አመቱ ጀርመንን ለቆ የወጣውን እና ከቤተሰቦቹ ጠፍቶ እንደገና የተገኘውን ቅድመ አያታችንን እንደረዳቸው አምናለሁ።”
ሚስቱ አክላ፣ “በባሌ ቤተሰብ ውስጥ ካሉት አምስት ወንድማማቾች መካከል፣ አራቱ በሚስዮን ያገለገሉት የኮሌጅ ዲግሪ ያላቸው ናቸው።”
በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ሁሉ ቅድስና ለጌታ መስጠት እግዚአብሔር በህይወቱ እንዲያሸንፍ መፍቀድን የተማረ ተመላሽ ሚስዮናዊን ይመስላል። ቀደም ብሎ፣ በጣም የታመመን ሰው እንዲባርክ ሲጠየቅ፣ ይህ ሚስዮናዊ እንዲህ አለ፣ “እምነት አለኝ፤ እንዲያገግም እባርከዋለሁ። ሆኖም፣” ተመላሽ ሚስዮናዊው እንዲህ አለ፣ “በዚያች ቅጽበት ለምፈልገው ነገር ሳይሆን፣ ጌታ ሰውየው እንደሚያስፈልገው ለሚያውቀው ነገር መፀለይ እንዳለብኝ ተማርኩኝ። ያንን ወንድም ሰላምና መጽናናት ያገኝ ዘንድ ባረክሁት። ከዚያም በሰላም አረፈ።”
በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ሁሉ ቅድስና ለጌታ መስጠት ከመንፈሳዊው ዓለም ጋር ለመገናኘት፣ ለማጽናናት እና ለማበርታት ወደ መጋረጃው የሚደርስን አነስተኛ ተግባር ይመስላል። በአንድ የታወቀ የዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያለ አስተዳዳሪ በርቀት ብቻ የሚያውቃቸው ግለሰቦች ስለ እርሱ እንደሚጸልዩ እንደሚሠማው ተናግሯል። እነዚህ ግለሰቦች ሕይወታቸውን ለዩኒቨርሲቲው የሰጡ ከመሆኑም ሌላ ለተልእኮውና ለተማሪዎቹ እንክብካቤ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
አንዲት እህት ባሏ ለእርሷና ለልጆቻቸው ታማኝ ካልሆነው በኋላ በየቀኑ የምትችለውን ታደርጋለች። እርሷን እና እሷን የሚመስሉትን ሌሎች በጥልቅ አደንቃለሁ። አንድ ቀን የታጠቡ ልብሶችን እያጣጠፈች ሳለች፣ እጇን በተደራረቡት የቤተመቅደስ ልብሶች ላይ አድርጋ በረጅሙ በመተንፈስ፣ “ምን ዋጋ አለው?” አለች። “ቃል ኪዳኖችሽ ከእኔ ጋር ናቸው” የሚል ለስላሳ ድምፅ ሲያረጋግጥላት ተሰማት።
ሌላ እህት ደግሞ ለ50 ዓመታት ያህል ከአባቷ ጋር ግንኙነት ለመመሥረት ትናፍቅ ነበር። “አስተዳደጌም” አለች፣ “ወንድሞቼ እና አባቴ በአንድ በኩል፤ እኔ ብቸኛዋ ሴት ልጅ ደግሞ በሌላ በኩል ነበርኩ። እኔ የምፈልገው ነገር ቢኖር ለአባቴ ‘ጨዋ ልጅ’ መሆን ብቻ ነበር።
“ከዚያም እናቴ አረፈች! በእኔና በአባቴ መካከል የነበረችው ብቸኛዋ አገናኝ እርሷ ነበረች።
“አንድ ቀን፣” እህት እንዲህ አለች፣ “እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፣ ‘አባትሽን ጋብዥውና ከአንቺ ጋር ወደ ቤተመቅደስ ውሰጂው።’ ይህም ከአባቴ ጋር በእግዚአብሔር ቤት በወር ሁለት ጊዜ የማደርገው ግንኙነት ጀምሬ ነበር። አባቴን እንደምወደው ነገርኩት። እሱም እንደሚወደኝ ነገረኝ።
“በጌታ ቤት ውስጥ ጊዜያችንን ማሣለፋችን ፈውሶናል። እናቴ በምድር ሣለች ልትረዳን አልቻለችም ነበር። የተሰበረውን በመጠገን ለመርዳት ከመጋረጃው በሌላኛው በኩል ከመንፈስ ዓለም ሆና መገኘት አስፈልጓታል። ቤተመቅደሱ እንደ ዘለአለማዊ ቤተሰብ ወደ ሙሉነት እና ወደ ፈውስ የምናደርገውን ጉዞ ፈጸመልን።
አባትየው እንዲህ ይላል፣ “የቤተመቅደስ ቡራኬ ለእኔ እና ለአንዲት ብቸኛ ሴት ልጄ ታላቅ መንፈሳዊ ተሞክሮ ነበር። አሁን አብረን መሳተፍ ላይ እንገኛለን እንዲሁም ፍቅራችን እየተጠናከረ እንደሆነም ይሠማናል።”
በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ሁሉ ቅድስና ለጌታ መስጠት፣ የምንወዳቸውን ሰዎች በሞት በአጣናቸው ጊዜ የሚሰማንን ስሜታዊ ጊዚያቶች ያካትታል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ውዷ እናቴ ጂን ጎንግ ከ98ኛ ዓመት ልደቷ ጥቂት ቀናት በፊት በፀጥታ እና በሠላም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።
እናቴን፣ “የማርሽ ሜሎና የለውዝ ድብልቅ ቸኮሌት፣ ነጭ የቸኮሌት ዝንጅብል ወይም የእንጆሪ አይስክሬም ትወጂያለሽ?” ብላችሁ ብትጠይቋት፣ እናቴም፣ “አዎን፣ እባካችሁን እያንዳንዱን መቅመስ እችላለሁ?” ብላ ትመልሳለች። ለእናት አይ የሚል ማን ነው፣ በተለይ ሁሉንም የህይወትን ተሞክሮዎች ሁሉ ማጣጣም የምትወድ ከሆነ?
አንድ ጊዜ እናቴን ህይወቷን ይበልጥ የቀረፀው የትኞቹ ውሳኔዎች እንደሆኑ ጠየቅኳት።
እንዲህ አለች፣ “የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል በመሆን መጠምቄ እና ከሀዋኢ አባትህ ወደ አገኘሁበት ወደ [አሜሪካ] ወደ ዋናው ምድር መሄዴ ናቸው።”
የ15 አመት ልጅ ሆና የተጠመቀችው፣ የትልቅ ቤተሰቧ ብቸኛ አባል በመሆን ወደ ቤተክርስቲያናችን የተቀላቀለችው እናቴ፣ ህይወቷን እና ሁሉንም የቤተሰባችንን ትውልዶች ሁሉ በባረከ በእግዚአብሔር ትታመን ነበር እንዲሁም ከእርሡ ጋር የቃል ኪዳን እምነት ነበራት። የቤተሰባችሁን አባላት እንደምትናፍቁ፣ እናቴ ትናፍቀኛለች። ሆኖም፣ እናቴ እንዳልጠፋች አውቃለሁ። አሁን እሷ እዚህ የለችም። እሷን እና በዕለት ተዕለት ቅድስና ለእግዚአብሔር በመሥጠት ደፋር ምሣሌዎች ሆነው የሞቱን ሁሉ አከብራለሁ።
እርግጥ ነው፣ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ሁሉ ቅድስና ለጌታ መስጠት ብዙ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቅዱስ ቤት መምጣትንም ያካትታል። የቤተክርስቲያኗ አባላትም ሆንን ጓደኞች ይህ እውነት ነው።
ሦስት ጓደኛሞች ወደ ባንኮክ ታይላንድ ቤተመቅደስ የእንግዶች ማስጎብኛ ጊዜ መጡ።
አንደኛው፣ “ይህ እጅግ ታላቅ የፈውስ ቦታ ነው” አለ።
የጥምቀት ገንዳ ባለበት ክፍል ውስጥ፣ ሌላኛው ደግሞ፣ “እዚህ በምሆንበት ጊዜ፣ ታጥቤ እንድነጻ እና ዳግመኛ ኃጢአት ላለመሥራትእፈልጋለሁ” አለ።
ሦስተኛው፣ “መንፈሳዊ ኃይሉ ይሰማችኋል?” አላቸው።
ቤተመቅደሶቻችን በአራቱ ቅዱስ ቃላት ግብዣ ያቀርባሉ እንዲሁም እንዲህ በማለት ያውጃሉ፦
“ቅድስና ለጌታ።
ቅድስና ለጌታ የዕለት ተዕለት ኑሮን የተቀደሰ ያደርገዋል። ወደ ጌታ እና ወደ እርስ በእርስ ያቀርበናል እንዲሁም ደስተኛ ያደርገናል እና ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ እና ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንድንኖር ያዘጋጀናል።
እንደ ጓደኛዬ፣ የሰማይ አባታችሁ ይወደናል ወይ ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል። መልሱ የሚታወቅ ነው፣ በእርግጥም አዎ! ነው እያንዳንዱን ቀናችንን ለጌታ ቅዱስ ስናደርግ የእርሱ ፍቅር ሊሰማን ይችላል። ይህን ለማድረግ የምጸልየው በቅዱሱ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።