2020–2024
የአጠቃላይ ባለስልጣናትን፣ የክልል ሰባዎችን እና አጠቃላይ መሪዎችን መደገፍ
የጥቅምት 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


4:17

የአጠቃላይ ባለስልጣናትን፣ የክልል ሰባዎችን እና አጠቃላይ መሪዎችን መደገፍ

ወንድሞች እና እህቶች፣ አሁን፣ የአጠቃላይ ባለሥልጣናትን፣ የአካባቢ ሰባዎችን እና የቤተክርስቲያኗን አጠቃላይ መሪዎችን ስም፣ የድጋፍ ድምፅ ትሰጧቸው ዘንድ ስለማቀርብ ዕድለኛ ነኝ፡፡

እባካችሁ፣ ባላችሁበት ቦታ፣ ድጋፋችሁን በተለመደው መንገድ እንድትገልፁ እንጠይቃኋለን። ማንኛውንም ለድጋፍ የቀረቡ ጥቆማዎች የሚቃወሙ ካሉ፣ የካስማቸውን ፕሬዚዳንት እንዲያነጋግሩ እንጠይቃለን።

ራስል ማሪዮን ኔልሰን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነቢይ፣ ገላጭ፣ እና ባለራዕይ፤ ዳለን ሄሪስ ኦክስ የቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ፤ እንዲሁም ሔንሪ ቢኒየን አይሪንግ የቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ አድርገን እንድንደግፍ ቀርቧል።

ይህንን የምትደግፉ ማሳወቅ ትችላላችሁ።

ይህን የምትቃወሙ ካላችሁም እንደዚሁ አሳውቁ።

ዳለን ኤች. ኦክስን የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን ፕሬዚዳንት፣ እንዲሁም ጀፍሪ አር. ሆላንድን ደግሞ የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት አድርገን እንድንደግፍ ቀርቧል።

ይህን የምትደግፉ እባካችሁን አሳዩ።

ይህን የምትቃወሙ እንደዚሁ አሳውቁ።

የሚከተሉትን የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባላት አድርገንእንድንደግፍ ቀርቧል፦ ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ ክውንተን ኤል. ኩክ፣ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ ኒል ኤል. አንድርሰን፣ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ፣ ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን፣ ዴል ጂ. ሬንላንድ፣ ጌሪት ደብልዩ ጎንግ፣ ዮልሲስ ሶሬስ እና ፓትሪክ ኪሮን።

ይህን የምትደግፉ እባካችሁ አሳዩ።

ይህን የምትቃወሙ፣ በተመሳሳይ መልኩ አሳዩ።

የቀዳሚ አመራርን እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን አባላትን እንደ ነቢይ፣ ባለራዕዮች እና ገላጮች አድርገን እንድንደግፍ ቀርቧል።

ይህን የምትደግፉ ሁሉ እባካችሁ አሳዩ።

የምትቃወሙም በተመሳሳይ አይነት ምልክት አሳዩ።

በሐሙስ ጥቅምት 3 ቀን (እ.አ.አ) ባካሄድነው የጠቅላላ ጉባኤ የአመራር ስብሰባ 6 አዳዲስ የአካባቢ ሰባዎች እንደተጠሩ እና በቤተክርስቲያኗ ድረ-ገፅ ይፋ እንደተደረጉ እናሳስባለን። እነዚህን ወንድሞች በአዲሱ ምድባቸው እንድትደግፏቸው እንጋብዛችኋለን።

ይህን የምትደግፉ እባካችሁ አሳዩ።

የምትቃወሙም በተመሳሳይ ምልክት አሳዩ።

ሌሎቹን አጠቃላይ ባለስልጣናት፣ የክልል ሰባዎች እና አጠቃላይ መሪዎች እንድንደግፍ ቀርቧል።

ይህን የምትቀበሉ እጃችሁን አንስታችሁ አሳዩ።

ይህን የምትቃወሙ ካላችሁ እንደዚሁ አሳዩ።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ለቤተክርስቲያኗ አመራር ያላችሁን እምነት እና ጸሎታችሁን ስለምትቀጥሉ እናመሰግናችኋለን።

በአካባቢ ሰባዎች የሚደረጉ ለውጦች

የሚቀጥሉት የአካባቢ ሰባዎች በአጠቃላይ ጉባኤ ክፍል በሆነው የመሪዎች ክፍለ-ጊዜ ተረጋግጠዋል፦

ሚጌልኤ. አቪላ፣ ዣን ፒይር ኤ.ኤል. ሃቦኮ፣ ራሚሮ ኢባራ ሳንቼዝ፣ ጆርጅ ካቴምቦ ንጆጉ ሙኔኔ፣ ኤ.ኤንሪኬ ቴሼራ፣ ፍራንሲስኮ ቭላኑኤቫ ሮሃስ።