ሊያሆና
ከእኔ ጋር ተራመድ
ጥር 2026 (እ.አ.አ) ሊያሆና


ወርሀዊ የ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ጥር 2026 (እ.አ.አ)

ከእኔ ጋር ተራመድ።

የ2026 የወጣቶች ጭብጥ ወደ እግዚአብሔር ስትቀርቡ፣ ሁልጊዜ —ከእናንተ ጋር እንደሚሄድ ለማስታወስ ይረዳችኋል።

የወጣት ሴቶች አጠቃላይ አመራር

ከግራ ወደ ቀኝ፡ ታማራ ደብሊው ሩኒያ፣ የመጀመሪያ አማካሪ፤ ኤሚሊ ቤሌ ፍሪማን፣ ፕሬዝዳንት፤ እና አንድሪያ ሙኖዝ ስፓናውስ፣ ሁለተኛ አማካሪ

ብቻችሁን አይደላችሁም

የማትችሉትን ነገር እንድታደርጉ ተጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? ምናልባት እናንተ በቂ ጥንካሬ ወይም ብልህነት አልተሰማችሁም ይሆናል፣ ወይም ሌሎች እንዳይስቁባችሁ እና እንዳይነቅፏችሁ ብላችሁ ትጨነቁ ይሆናል። እንደዚህ አይነት ስሜት ከተሰማችሁ ብቻችሁን አይደላችሁም።

ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ሄኖክ የሚባል ሰው ነበር። እግዚአብሔር ሄኖክን ለህዝቡ ንስሐን እንዲሰብክ ጠየቀው፤ እነዚህ —በምድር ላይ ታይተው የማያውቁ በጣም ክፉዎች ነበሩ።

ሄኖክ ይህን ማድረግ እንደሚችል አላሰበም ነበር። እርሱ በጣም ወጣት እንደሆነ፣ ማንም እንደማይወደው፣ እና “ለመናገር የዘገየ” እንደሆነ ለእግዚአብሔር ነገረው (ሙሴ 6፡31 ተመልከቱ)።

ነገር ግን እግዚአብሔር ለሄኖክ ቃል ኪዳን ሰጠው። ለፈሪውም ሰው እንዲህ አለው፥ ሂድና እንዳዘዝኩህ አድርግ፣ እናም ማንም አይጎዳህም። አፍህን ክፈት፣ እናም ይሞላል፣ እኔም የምትናገረውን እሰጥሀለሁ፣ ሁሉም ስጋ ለባሽ በእጄ ላይ ነውና፣ እና መልካም እንደሚመስለኝም አደርጋለሁ።ሙሴ 6፥32፣ 34

“ከእኔ ጋር ተራመድ።” እንዴት ያለ ቀላል እና የሚያምር ግብዣ ነው።

እግዚአብሔር ለሄኖክ ደፋር ከሆነ በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደሚሆን ቃል ገባለት። እግዚአብሔር ሄኖክን ኃያል ያደርገው እናም የበለጠ እንዲሰራ ያበረታው እንዲሁም ሊገምተው ከሚችለው በላይ እንዲሆን ይረዳው ነበር።

ከአዳኝ ብዙ ስሞች አንዱ አማኑኤል ነው፣ ወይም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” (ማቴዎስ 1፡23)ነው። ከእኛ ጋር መሄድ የጌታ ስም እና ባህሪይ ነው። ምርጫው የኛ ነው—እኛም ከእርሱ ጋር እንራመዳለንን?

በአሁኑ ጊዜ፣ ሄኖክን የምንመለከተው እንደ እምነት ሰው እና እንደ ታላቅ ነቢይ እና መሪ ነው። ነብይ ከሆነው ሄኖክ በፊት ግን፣ ራሱን የሚጠራጠር ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር መሄድን የመረጠ ትንሹ ሄኖክ ነበረ።

ህይወት አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ፣ በቂ መሆናችሁ በማይሰማችሁ ጊዜ፣ ጌታ ለእናንተ፣ እና ለሄኖክ የገባውን ቃል እስታውሱ። አብሯችሁ ይራመዳል። ለአንድ እርምጃም ቢሆን ብቻችሁን አይተዋችሁም።

አማኑኤል። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው።

የወጣት ሴቶች አጠቃላይ አመራር

የወጣት ወንዶች አጠቃላይ አመራር

ከግራ ወደ ቀኝ፡ ዴቪድ ጄ. ዎንደርሊ፣ የመጀመሪያ አማካሪ፤ ቲሞቲ ኤል ፋርነስ፣ ፕሬዝዳንት፣ እና ሴን አር ዲክሰን፣ ሁለተኛ አማካሪ

በእርሱ እርዳታ ሁሉንም ነገር ማድረግ ትችላላችሁ።

ልክ እንደ እናንተ ወጣቶች፣ አስፈላጊ የክህነት ሀላፊነቶችን እንዲወጣ እግዚአብሔር ሄኖክን ጠየቀው። የእርሱ ተግባር ለክፉ ሰዎች ንስሐን መስበክ ነበር። ሄኖክ ጥርጣሬውን ገለጸ። “[እኔ] ግን ልጅ ነኝ” አለ። “ህዝቦች ሁሉ አይወዱኝም፤ … አፌ ኰልታፋ ነውና፤ ስለዚህ እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ? ሙሴ 6፥31

ጌታ በኃይል እና በማረጋጋት ምላሽ ሰጠ። “ሂድና እንዳዘዝኩህ አድርግ። … አፍህን ክፈት፣ እናም ይሞላል … ። መንፈሴ በአንተ ላይ አርፏል …፣ ተራሮችም ከአንተ ፊት ይሸሻሉ…፣ ስለዚህ ከእኔ ጋር ተራመድ” (ሙሴ 6 32, 34)።

ሔኖክ እግዚአብሔር አንድን ሥራ ሲሰጠን፣ ብቻችንን እንደማንጋፈጥ ተረዳ። ከክርስቶስ ጋር ቃል ኪዳን ስንገባ እና ቃል ኪዳኑን ስንጠብቅ፣ ከእርሱ ጋር እንራመዳለን እኒሁም ኃይሉን እንካፈላለን—በእጆቹ ውስጥ መሳሪያዎች እንሆናለን።

ልክ እንደ ሄኖክ፣ እናንተ ወሳኝ ሚና አላችሁ፡ ማገልገል፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ ማገልገል፣ ቅዱስ ቁርባንን ማስተዳደር፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት፣ የወንጌል ደረጃዎችን መኖር፣ ንስሃ መግባት፣ ለተልእኮዎች መዘጋጀት እና ሌሎችም። ከአቅም በላይ የሆነ ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል። ብቁ እንዳልሆናችሁ ሊሰማችሁ ይችላል። ያ ምንም አይደለም። ለብቻ ስለማድረግ አይደለም። ከእግዚአብሔር ጋር ለመራመድ ዛሬን—በዚህ ቀን እና በየቀኑ—ስለ መምረጥ ነው።

በእርሱ እርዳታ ሁሉንም ነገር ማድረግ ትችላላችሁ። ከተፈጥሮአዊ አቅማችሁ በላይ ያበረታችኋል፣ ይቅር ይላችኋል እና ያስችላችኋል። ይወዳችኋል። እንደ ወጣት ወንዶች አጠቃላይ አመራር፣ እንወዳችኋለን እናም የ2026ን (እ.አ.አ) አበረታች ጭብጥ “ከእኔ ጋር መራመድ” የሚለውን ጭብጥ ለመፈተሽ አብረናችሁ ለመሆን እንጠባበቃለን።

የወጣት ሴቶች አጠቃላይ አመራር