“ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች,” ሊያሆና፣ ጥር፣ 2026 (እ.አ.አ)
ወርሐዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ ጥር 2026 (እ.አ.አ)
ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች
(2 ጴጥሮስ 1፥4)
የደኅነት እቅድ እውቀት ውድ የሆነ እይታን ይሰጠናል፣ ደስታችንን ያበለጽጋል፣ እናም ፈተናዎቻችንን እና መከራዎቻችንን እንድናሸንፍ ያጠነክረናል።
ክርስቶስ ሁለት ደቀ መዛሙርት ሲጠራ፣ በጌሪ ኢ. ስሚዝ
ሐዋርያው ጴጥሮስ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለሆኑት ሲያሳስብ “የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል፣ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፡
“ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፡ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን”(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡ 3-4፣ አጽንዖት ተጨምሯል)።
የሰማይ አባት እቅድ የእኛን ዘላለማዊ ማንነታችንን እና አላማን የሚገልጹ እጅግ በጣም ግዙፍ እና ውድ እውነታዎችን እና ተስፋዎችን ይገልጻል።
“የቤተሰብ፡ አዋጅ ለአለም የተሰጠ አዋጅ” ላይ እንደተብራራው”፡
‘የሰው ልጆች በሙሉ —ወንድና ሴቶች —በእግዚአብሔር አምሳል ነው የተፈጠሩት። እያንዳንዱም በሰማይ ወላጆች የተወደዱ የመንፈስ ሴት እና ወንድ ልጆች ናቸው፣ እናም ይህ ስለሆነም፣ እያንዳንዱ መለኮታዊ ተፈጥሮ እና ፍጻሜም አላቸው።
በቅድመ ምድራዊ ህይወት ውስጥ፣ የመንፈስ ወንድ እና ሴት ልጆች እግዚአብሔርን እንደ ዘላለማዊ አባታቸው ያውቁትም ያመልኩትም ነበር፣ እናም ልጆቹ ስጋዊ አካልን አግኝተው ምድራዊ አጋጣሚዎችን በማግኘት ወደ ፍጹምነት ለመሻሻል እና በመጨረሻም እርሱ ወይም እርሷ እንደ መለኮታዊ እጣቸው ዘላለማዊ ህይወትን ወራሽ እንዲሆኑ የሚያደርገውን አላማውን ተቀብለው ነበር።
የሰማይ አባት ለልጆቹ የእቅዱን መመሪያዎች እና የተወደደውን ልጁን ምሳሌ ከተከተሉ፣ ትእዛዛቱን ቢጠብቁ እና በእምነት እስከ መጨረሻው ከጸኑ፣ “ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነውን ዘለአለማዊ ህይወት” እንደሚኖራቸው ቃል ገብቷል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፡7)።
የእግዚአብሔር ስራ በልጆቹ እድገት እና ከፍ ከፍ ማድረግ ላይ ያሚያተኩር ነው። እያንዳንዱ የእቅዱ ገጽታ ወንድና ሴት ልጆቹን ለመባረክ የተነደፈ ነው ምክንያቱም “የነፍሳት ዋጋ በፊቱ ታላቅ ነው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፡10)።
የአብ ታላቁ እቅድ
በሰማይ በነበረ ታልቅ ስብሰባ፣ የሰማይ አባት ለመንፈሳዊ ልጆቹ ለዘላለማዊ ሂደታቸው እና ደስታቸው የሚሆናቸውን እቅድን አቀረበላቸው።
እነዚህ ሊኖሩበት የሚችሉትን ምድርን እንሰራለን፤
“እና ጌታ አምላክ የሚያዛቸውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ እንደሚያደርጉ ለማየት፣ በዚህ እንፈትናቸዋለን፤
እና የመጀመሪያ ሁኔታቸውን የጠበቁትም ይጨመርላቸዋል፤ እና ይህን የመጀመሪያውን ሁኔታቸውን ያልጠበቁትም ከዚህ አይነት መንግስት ውስጥ የመጀመሪያው ሁኔታቸውን ከጠበቁት ጋር ክብር አይኖራቸውም፤ እና ሁለተኛ ሁኔታቸውን የጠበቁትም በራሳቸው ላይ ክብር ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ይጨመርላቸዋል።
እና ጌታ እንዲህ አለ፥ ማንን እልካለሁ? አንዱም እንደ ሰው ልጅ መለሰ፥ እዚህ አለሁ፣ እኔን ላከኝ። እና ሌላም መለሰ እና እንዲህም አለ፥ በዚህ አለሁ፣ እኔን ላከኝ። እና ጌታ እንዲህ አለ፥ የመጀመሪያውን እልካለሁ።
እና ሁለተኛውም ተቆጣ፣ እና የመጀመሪያ ሁኔታውን አልጠበቀም፤ እናም በዚያም ቀን፣ ብዙዎች ተከተሉት” (አብርሐም 3፡24-28)።
ልብ በሉ በቅድመ ምድራዊ ስብሰባ ውስጥ የቀረበው አንድ እቅድ ብቻ ነበር—የአብ እቅድ። የሰማይ አባታችን፣ “ምን እናድርግ?” የሚለውን እንደ ጥያቄ አላነሳም። እርሱ ተጨማሪ እርዳታን፣ ምክሮችን፣ ወይም ፕሮፖዛል አልጠየቀም። ይልቁንም፣ የዕቅዱን መሠረታዊ ነገሮች አቅርቦ “ማንን ልላክ?” ሲል ጠየቀ። የጥያቄዎቹ ጽንሰ ሃሳብ የእቅዱን ውሎችን እና ሁኔታዎችን ለማስፈጸም ማን መላክ እንዳለበት ነው የሚያተኩሩት።
የተቃዋሚውም አመፅ የሚያስከትለውን መዘዝም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ተገልጿል።
ስለዚህ ሰይጣን ስለዐመፀብኝና እኔ እግዚአብሔር አምላክ የሰጠሁትን የሰው ነጻ ምርጫ ለማጥፋት ስለፈለገ፣ እና ደግሞም የራሴን ሀይል ለእርሱ እንድሰጠው ሰለፈለገ ዘንድ፣ በአንድያ ልጄ ሃይል እንዲጣል አደረግሁኝ፤
“እና እርሱም ሰይጣን፣… አዎን፣ እንዲሁም ድምጼን የማያደምጡትን ሁሉ የሚያታልለው እና ሰዎችን እንዳያዩ አድርጎ በፈቃዱም እንደ እስርኞች የሚመራቸው፣ እንዲሁም የሀሰት አባት ዲያብሎስ ሆነ” (ሙሴ 4:3–4፣ አጽንዖት ተጨምሯል)።
ሳጥናኤል በቅድመ ምድራዎ ስብሰባ ውስጥ በአብዛኛዎቹ ተሳታፊዎች ድምጽ የተሰጠበትን እቅድ አላቀረበም። በምርጫ ብልጫ የተሸነፈ ርህሩህ ሰው አይደለም። እርሱ አመፀ! ኩራት፣ ትዕቢት እና ራስ ወዳድነት በአብ እቅድ ላይ ለማመፅ አነሳስቶታል።
የአብ እቅድ እና የአዳኙ ወንጌል
እቅዱ የዘላለም ሕይወትን በረከቶች ለሰው ልጆች ሁሉ የሚያቀርቡትን የአብ እና የወልድን ስራዎች ይገልጻል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ቃል የተገባልንን በረከቶች የምንቀበልበትን መንገድ ትምህርት፣ መርሆች፣ እንዲሁም ወንዶች እና ሴቶች ማመን እና መከተል ያለባቸውን ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች ይመሰርታል። “ከኢየሱስ ክርስቶስ በስተቀር ሰው ሊድንበት የሚችል ምንም አይነት ስም ከሰማይ በታች የተሰጠ የለም” (2 ኔፊ 25፡20)። እርሱ “መንገድና እውነት ህይወትም [ነው]፤ [በእርሱ] በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሀንስ 14፥6፣ አጽኖት ተጨምሮበታል)።
ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ገልጸዋል፦
እቅዱ፣ ፍጥረት እንዲኖር ያስፈልገዋል፣ እናም ያ በምላሹ ውድቀትን እና ቤዛነትን እንዲኖሩ ያስፈልጋል። እኚህ ሶስቱ ናቸው የእቅዱ መሰረታዊ ነገሮች። የገነት አፈጣጠር የመጣው ከእግዚአብሄር ነው። ማችነት እና ሞት ወደ አለም የመጣው በአዳም ውድቀት ነው።[2 ኔፊ 2፡25 ይመልከቱ፤ ሙሴ 6፡48]። አለመሞት እና የዘላለም ሕይወት ዕድል የቀረበው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ነው።[2 ኔፊ 2፡21–28 ይመልከቱ]። …
… ወደ ምድር ለተወሰነ አጭር ጊዜ መጥተናል፣ ፈተናዎቻችንን እና መከራዎቻችንን በጽናት እንቋቋማለን፣ እናም ወደ ፊት እና ወደ ላይ ወደ ክብር መገኛችን እንመለሳለን። [መዝሙር 116:15፡ አልማ 42፡8]። [በማችነታችን ጊዜ] የእግዚአብሔርን እቅድ ከተረዳን እና አመስጋኝ ከሆንን እና ለትእዛዛቱ ታዛዥ ከሆንን ሀሳቦቻችን እና ተግባሮቻችን በእርግጥ የበለጠ ዓላማ ይኖራቸዋል። [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፡20–21 ይመልከቱ]።”
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የእቅዱ ርዕሶች
የአብን እቅድ የተለያዩ ርዕሶችን በመለየት እና በማጥናት ጠቃሚ እውነቶችን በመፅሐፈ ሞርሞን፡ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ውስጥ እንማራለን። ለምሳሌ፣ የሚከተሉትን የተመረጡ የርዕሶችን ናሙና ተመልከቱ፡-
“ምህረት የተሞላበት የታላቁ የፈጣሪ ዕቅድ” (2 ኔፊ 9፡6)።
“የአምላካችን ዕቅድ” (2 ኔፊ 9፡6)።
“የደህንነት እቅድ” (ጄሮም፣ አልማ 24፡14)።
“የቤዛነት እቅድ” (አልማ 12፡25፣ 26, 30,32,33፣ 42፡11, 13)።
“የዳግም መመለስ እቅድ” (አልማ 41፡2)።
“የደስታ እቅድ” (አልማ 42፡16)።
“ታላቁ የምህረት እቅድ” (አልማ 42፡31)።
እኚህ እያንዳንዳቸው ርዕሶች የአብን ውድ የሆኑ የተስፋ እቅዶችን በግልፅ እንድንረዳ እና ስለ ሟች ህይወታችን ያለንን አላማ እና ትርጉም አመለካከት ያበለጽጉልናል።
በጉልህ፣ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ለእግዚአብሔር እቅድ በብዛት ጥቅም ላይ የዋለው ርዕስ የሚያተኩረው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል በተደረገው ቤዛነት ላይ ነው።
አልማ እንዳስታወቀው፣ “ከዓለም መፈጠር ጀምሮ በነበረው የቤዛነት ዕቅድ ባይሆን ኖሮ፣ የሙታን ትንሳኤ ሊሆን ባልቻለም ነበር፣ ነገር ግን የተነገረውን የሙታን ትንሳኤ የሚያመጣ የቤዛነት ዕቅድም ተዘጋጅቶ ነበር” (አልማ12፡25)።
አልማ እንዲህ ብሏል፣ “እናም የእግዚአብሔር ልጅ ህዝቡን ሊያድን እንደሚመጣና፣ ለህዝቡ ኃጢያት ክፍያ እንደሚሰቃይና እንደሚሞት፣ እናም ሰዎች እንደስራቸው በመጨረሻውና በፍርዱ ቀን እንዲፈረድባቸው በፊቱ ይቆሙ ዘንድ ትንሳኤን ያመጣ ዘንድ በድጋሚ ከሙታን እንደሚነሳ ማመን ጀምሩ።”አልማ 33፡22
መንገዱ ተዘጋጅቷል።
የእግዚአብሔርን ታላቅ የማዳን፣ የመቤዠት፣ የዳግም መመለስ፣ የምሕረት እና የደስታ እቅድ ስናስብ ነፍሳችን በምስጋና መወጠር አለባት። የደኅነት እቅድ እውቀት ውድ የሆነ እይታን ይሰጠናል፣ ደስታችንን ያበለጽጋል፣ እናም ፈተናዎቻችንን እና መከራዎቻችንን እንድናሸንፍ ያጠነክረናል።
የሰማይ አባት ወደ እርሱ እንድንመለስ ይናፍቃል። ይጋብዛል እናም ለረከቶችን ቃል ገብቷል፣ ነገር ግን እርሱ የሰጠንን ሥነ ምግባር አገልግሎት እንድንጠቀም አያስገድደንም፣ አይገፋፋም፣ ወይም አይገድበውም። የተወደደውን የልጁን ምሳሌ በመከተል ወደ እርሱ ለመመለስ መስራት እና መምረጥ አለብን።
እጁ አሁንም ተዘርግተዋል፣ በኤልዛቤት ታየር
መንገዱ ተዘጋጅቷል፣ እናም የምንመለከት ከሆነ ለዘለዓለም እንኖራለን” (አልማ 37፡ 46፣ አጽንዖት ተጨምሯል)።
የሰማይ አባት ለልጆቹ የመለኮታዊ እቅድ ደራሲ መሆኑን በደስታ እመሰክራለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን እና ቤዛችን ነው። እና የጌታ የኋለኛው ቀን ሐዋርያት አንዱ እንደመሆኔ፣ እርሱ በእርግጥ “መንገድ፣ እውነት እና ሕይወት” እንደሆነ እመሰክራለሁ።ኢየሱስም እንዲህ ብሏል፣ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ”(ዮሀንስ 14፥6፣ አጽንዖት ተጨምሯል)።
© 2026 by Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ ታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፤ 6/19። የ ወርሃዊ የሊያሆና መልእክት፣ ጥር 2026 (እ.አ.አ)ትርጉም Amharic. 19932 506