2025
ከዚህ ህይወት በኋላ፤ ለአንዳንድ ጥያቄዎች መልሶች
ሐምሌ 2025 (እ.አ.አ)


ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሐምሌ 2025 (እ.አ.አ)

ከዚህ ህይወት በኋላ

ለአንዳንድ ጥያቄዎች መልሶች

የሰማዩ አባት እቅድ ከሞት በኋላ ስላለ ህይወት ምልከታ እና ሰላምን ሊሰጡን ይችላሉ።

በደመና ውስጥ ያለ መሰላል

ማብራሪያ በቶማስ አርኖውድ

ከሞትን በኋላ ምን ይከሰታል?

ምናልባትም ይህ ሁሉም ሃይማኖት የሚጠየቅ ጥያቄ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ በኩል ያሉን መልሶች ሃያል ናቸው። ይህ ህይወት መጨረሻው አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሳኤ ስለተነሳ፣ መንፈሶቻችን ከአካሎቻችን ጋር ዳግም ይዋሃዳሉ፣ እናም ሁላችንም አንድ ቀን በትንሳኤ እንነሳለን።

በርግጥ፣ ያሉንን ሌሎች ጥያቄዎች ሊመልሱልን የሚችሉ በዘመናዊ ራእይ አማካይነት ወደ እኛ የመጡ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች አሉ። እንደነዚህ ያሉት ጥቂት ጥያቄዎች፣ ከአጭር መልሶቻቸው ጋር እዚህ ቀርበዋል።

የመንፈስ አካላት ምን ይመስላሉ?

መንፈስ “የጠራ እና ንፁህ”’’ ፣ የሆነ ነገር ነው (ትምህርት እና ቃልኪዳን 131፥7)። የመንፈስ አካላት የጎልማሳ ሰው ሰውነት አይነት ናቸው።

የመንፈስ ዓለም የት ነው?

እዚሁ፣ በዙሪያችን ነው።

በመንፈስ ዓለም ውስጥ የሚከናወነው ምንድነው?

ሌሎች ነገሮችን ጨምሮ፣ ወንጌልን የተቀበሉ መንፈሶች ወንጌልን ላልተቀበሉ መንፈሶች ለመስበክ ተደራጅተዋል። እነዚያ መንፈሶች ለመቀበልም ሆነ ላለመቀበል መምረጥ ይችላሉ።

ከሞት የተነሱ አካላት ምን ይመስላሉ?

ከሞት የተነሱ አካላት ሊሞቱ አይችሉም፣ስጋና አጥንት ናቸው፣እናም ፍጹም ናቸው። የከበሩ እና ያማሩ ናቸው። “ከሞት ከተነሳ ወንድ ወይም ሴት ይልቅ ለማየት ይበልጥ የሚያምር ሌላ ነገር የለም።’’

በሰለስቲያል መንግስት እየተከናወነ ያለው ምንድነው?

በከፍተኛው የሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ያሉ እነዚያ እንደ ሰማዩ አባታችን ይሆናሉ እናም የተሟላ ሃሴትን ይለማመዳሉ። አብ ያለውን ሁሉ ይቀበላሉ። በስራው እና በክብሩ ውስጥ ይሳተፋሉ። የራሳቸውን ዘለዓለማዊ የመንፈስ ልጆችን ይዘው፣ ለዘለዓለም በጋብቻ ስለተጣመሩ አሁን ዘለዓለማዊ ቤተሰቦች በመሆን ይኖራሉ።

በዚህ ህይወት በፍጹም የማያገቡ ሰዎችንስ በሚመለከት ምን ይሆናል?

የሰማዩ አባት በፍጹምነት ጻድቅ እና መሃሪ ነው። “ጌታ ትእዛዛቱን ለሚጠብቁ፣ ለቃልኪዳኖቻቸው ታማኝ ለሆኑት እና ትክክል የሆነውን ለሚመኙ ወንዶች እና ሴቶች ልጆቹ በዘለዓለማዊው ዓለም ምንም አይነት በረከት እንደማይነፍጋቸው ቃል ገብቷል።”

ወላጆቼ በቤተመቅደስ ተጣምረው ነበር፣ አሁን ግን በፍቺ ተለያይተዋል። ከማን ጋር እጣመራለሁ?

“በቃል ኪዳን ውስጥ ተወልደህ ሊሆን ይችላል” (ያም ማለት፣ ወላጆችህ በቤተመቅደስ ውስጥ ከተጣመሩ በኋላ ተወልደህ ሊሆን፣ ወይም ወላጆችህ እርስ በርሳቸው ከተጣመሩ በኋላ በቤተመቅደስ ውስጥ ከወላጆችህ ጋር ተጣምረህ ሊሆን ይችላል። በሁለቱም መንገድ፣ ወላጆችህ በፍቺ ለመለያየት የመረጡ እንኳ ቢሆን እና የተጣመሩበትንም ቢሰርዙት እንኳ በረከቶችህ እንዳሉ ይቀጥላሉ።

የወላጆችህ ምርጫዎች በረከቶችህ ላይ ሊያሳድሩ የሚችሉት ተጽዕኖ አይኖርም። ለአንተ አስፈላጊው ነገር በታማኝነት መቆየት እና ለራስህ የቤተመቅደስ በረከቶችን መሻትህ ነው። የቤተሰብህን ግንኙነቶች በተመለከተ፣ “ፍላጎቱ እና ምርጫው በፈቀደ መጠን እያንዳንዱ ግለሰብ ማንናውንም በረከት የሚቀበል መሆኑን የሰማይ አባት የሚያረጋግጥ’’ በመሆኑ ‘’በጌታ ልትታመን እናም የእርሱንም ማጽናናት ልትሻ’’ ይገባል።

ራሳቸውን በማጥፋት የሞቱ ሰዎች ምን ይሆናሉ?

ራሳቸውን በማጥፋት የሞቱ ሰዎች ምን እንደሚሆኑ አናውቅም፣ እናም (ልክ እንደሌሎቹ ሁሉ፣ በስተመጨረሻ) ልንፈርድባቸው አንችልም። ‘’የምንወዳቸው ሰዎች፣ የመሪዎች፣ እና የባለሙያዎች ከፍተኛ ጥረት ቢኖርም፣ ራስን ማጥፋትን ሁል ጊዜ ልንከላከለው የምንችለው ነገር አይደለም። …

‘’አንድ ግለሰብ የገዛ ህይወቱን/ቷን ማጥፋቱ/ቷ ትክክል አይደለም። ይሁን እንጂ፣ የግለሰቡን አስተሳሰብ፣ ድርጊቶች፣ እና የተጠያቂነት ደረጃ ሊፈርድ የሚችለው እግዚአብሄር ብቻ ነው ( 1ኛ ሳሙኢል 16፥7ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 137፥9 ይመልከቱ)። …

‘’የሚወዱትን ሰው ራሱን በማጥፋቱ ያጡት እነዚያ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በሃጢያት ክፍያው ተስፋን እና ፈውስን ሊያገኙ ይችላሉ።’’

ማስታወሻዎች

  1. ኤተር 3:16; የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንቶች ትምህርቶች: ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ (1998), 131–32 ተመልከቱ።

  2. የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንቶች ትምህርቶች፤ ብሪግሃም ያንግ (1997 እ.አ.አ)፣ 279 ተመልከቱ።

  3. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 138 ተመልከቱ።

  4. አልማ 11፥45ተመልከቱ።

  5. ሉቃስ 24፥39 ተመልከቱ።

  6. አልማ 11:43 ተመልከቱ።

  7. ሎሬንዞ ስኖው፣ የሎሬንዞ ስኖው ትምህርቶች፣ ed። ክላይድ ጄ. ዊሊያምስ (1996 እ.አ.አ)፣ 99።

  8. ሙሴ 1፥39 ይመልከቱ።

  9. መዝሙር 16፥11; 3ኛ ኔፊ 28:10; ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 76፥59፣ 62; 130:2; 132፥19–23 ተመልከቱ።

  10. ዳሊን ኤች. ኦክስ፣ የጥቅምት 1993(እ.አ.አ)አጠቃላይ ጉባኤ፣ (ኤንዛይን ህዳር 1993 (እ.አ.አ)፣ 75)

  11. አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ-በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል፣ ይመልከቱ። 38.4.2.8 ፣ የወንጌል ላይብረሪ።

  12. አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ38.4፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት።

  13. አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ38፣6፣20 ፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት።