መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
28.ለሞቱ ሰዎች የሚደረጉ የቤተመቅደስ ሥርዓቶች


“28. ለሞቱ ሰዎች የሚደረጉ የቤተመቅደስ ሥርዓቶች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“28. ለሞቱ ሰዎች የሚደረጉ የቤተመቅደስ ሥርዓቶች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ማጥመቂያ ገንዳ

28.

ለሞቱ ሰዎች የሚደረጉ የቤተመቅደስ ሥርዓቶች

28.0

መግቢያ

በቤተመቅደሶች ውስጥ የሚከናወኑ ሥርዓቶች፣ ቤተሰቦች ለዘለዓለም አብረው እንዲሆኑና በእግዚአብሔር ፊት የደስታን ሙላት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

የሰማይ አባት ልጆች ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ እያንዳንዱ ንስሃ መግባት፣ የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግ ሥርዓቶችን ለመቀበል ብቁ መሆን እንዲሁም ከእያንዳንዱ ሥርዓት ጋር ተያያዥ የሆኑትን ቃል ኪዳኖች ማክበር አለባቸው።

የሰማይ አባት፣ ብዙዎቹ ልጆቹ በሥጋዊ ህይወታቸው እያሉ እነዚህን ሥርዓቶች እንደማይቀበሉ ያውቅ ነበር። ሥርዓቶችን የሚቀበሉበትን እና ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን የሚገቡበትን ሌላ መንገድ አቅርቧል። በቤተመቅደስ ውስጥ ሥርዓቶች በውክልና ሊከናወኑ ይችላሉ። ይህ ማለት በህይወት ያለው ሰው ለሞተው ሰው በውክልና ሥርዓቶችን ይቀበልለታል ማለት ነው። በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ፣ የሞቱ ሰዎች ለእነርሱ በውክልና የተደረጉላቸውን ሥርዓቶች ለመቀበል ወይም ላለመቀበል መምረጥ ይችላሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥19፣ 32–34፣ 58–59 ይመልከቱ)።

የቤተክርስቲያኗ አባላት የደህንነትን እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግን ሥርዓቶች ያልተቀበሉ በሞት የተለዩ ዘመዶችን እንዲለዩ ይበረታታሉ። ከዚያም አባላት ለእነዚያ ዘመዶች የውክልና ሥርዓቶችን ይፈጽማሉ።

አባላት የቤተሰብ ስሞችን ለቤተመቅደስ ስራ ያላዘጋጁ ከሆኑ (28.1.1 ይመልከቱ)፣ ሥርዓት የሚያስፈልጋቸው የሞቱ ሰዎች ሥም በቤተመቅደስ ውስጥ ሊገኝ ይችላል።

28.1

የውክል ሥርዓቶች አጠቃላይ መመሪያዎች

በሞቱበት ጊዜ ዕድሜያቸው 8 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የነበሩ ሟቾች በእነሱ ምትክ የውክልና ሥርዓቶች ሊደረግላቸው ይችላል። በ28.3 ውስጥ ከተገለጸው በስተቀር፣ ከሚከተሉት ውስጥ አንዳቸው የሚሟሉ ከሆነ ከሞቱ 30 ቀናት እንዳለፋቸው ለሁሉም ሟቾች የውክልና ሥርዓቶች ሊደረጉ ይችላሉ

  • የሟቹ የቅርብ ዘመድ (ያልተፋታ የትደር ጓደኛ፣ ጎልማሳ ልጅ፣ ወላጅ ወይም ወንድም እና እህት) ስሙን ለቤተመቅደስ ሥርዓት ያቀርባሉ።

  • ሥርዓቶችን ለመፈጸም ፈቃድ የሚሰጠው በሟቹ የቅርብ ዘመድ ነው (ያልተፋታ የትደር ጓደኛ፣ ጎልማሳ ልጅ፣ ወላጅ ወይም ወንድም እና እህት)።

ከላይ ከተጠቀሱት ሁኔታዎች አንዳቸውም የማይሟሉ ከሆነ፣ የቤተመቅደስ የውክልና ሥርዓቶች የሚከናወኑት ሟቹ ሰው ከተወለደ ከ110 ዓመታት በኋላ ነው።

28.1.1

የሞቱ ሰዎችን ስሞች ለቤተመቅደስ ሥርዓቶች ማዘጋጀት

ከተቻለ፣ የቤተመቅደስ ሥርዓቶች ከመፈፀማቸው በፊት የሟች የቤተሰብ አባላትን የሚለይ መረጃ ወደFamilySearch.org መግባት አለበት (25.4.2 ይመልከቱ።)

28.1.1.1

የቤተሰብ አባላትን ስሞች ማስገባት

ለውክልና የቤተመቅደስ ሥርዓቶች ስሞችን በሚሰጡበት ጊዜ፣ በአጠቃላይ አባላት የሚዛመዷቸውን ሰዎች ስም ብቻ መስጠት አለባቸው።

28.1.2

ለሞቱ ሰዎች በሚደረጉ የቤተመቅደስ ሥርዓቶች ላይ ማን ሊሳተፍ ይችላል

ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ያላቸው ሁሉም አባላት ለሞቱ በሚደረጉ የውክልና ጥምቀት እና ማረጋገጫ መቀበል ላይ ላይ መሳተፍ ይችላሉ። የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበሉ አባላት ለሞቱ በሚደረጉ በሁሉም የቤተመቅደስ ሥርዓቶች ላይ መሳተፍ ይችላሉ። 26.3 ይመልከቱ።

28.1.4

መርሃ ግብር ማውጣት

አባላት ለሞቱ ሥርዓቶችን ከማከናወናቸው በፊት ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋቸው ይሆናል። ለእያንዳንዱ የቤተመቅደስ አድራሻ መረጃ እና የጊዜ ሰሌዳ መስፈርቶች temples.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

28.2

ለሞቱ ሰዎች የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን ማከናወን

አንድ አባል የውክልና ሥርዓቶችን በሚያከናውንበት ጊዜ፣ ከአባሉ ጋር ተመሳሳይ የውልደት ጾታ ላለው ሟች ሰው ብቻ ወኪል ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።

28.2.1

ለሞቱ ሰዎች መጠመቅ እና ማረጋገጫ መቀበል

የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ያለው ማንኛውም አባል በጥምቀት የስራ ምደባ እንዲያገለግል ሊጋበዝ ይችላል። አንዳንድ የሥራ ምደባዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • ለጥምቀቶች በውክልና መስራት።

  • ለውክልና ጥምቀቶች ምስክር በመሆን መስራት።

  • ማረጋገጫዎችን ለመቀበል በወኪልነት መስራት።

  • ደንበኞችን መርዳት።

የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች እና በአሮናዊ ክህነት ውስጥ ያሉ ካህናት የሙታን ጥምቀትን እንዲያከናውኑ ሊጋበዙ ይችላሉ። የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች ለሙታን ማረጋገጫዎችን እንዲሰጡ ሊጋበዙ ይችላሉ።

የቤተመቅደስ ቡራኬን የተቀበሉ ወንዶች ብቻ የሚከተሉትን ለማድረግ ይጋበዛሉ፦

  • የጥምቀት መዝጋቢ በመሆን ለማገልገል።

  • የማረጋገጫ መዝጋቢ በመሆን ለማገልገል።

28.2.2

የቤተመቅደስ ቡራኬ (የመጀመሪያውን ክፍል ጨምሮ)

ለሞቱ የውክልና የቤተመቅደስ ቡራኬ በሚከናወንበት ጊዜ የቤተመቅደስ ቡራኬው የመጀመሪያ ክፍል የሚከናወነው እና የሚመዘገበው ለብቻው ነው (27.2 ይመልከቱ)። የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ያለው ማንኛውም አባል እነዚህን ሥርዓቶች ለመቀበል ወኪል ሆኖ ሊሰራ ይችላል።

28.2.3

ከትዳር ጓደኛ ጋር መታተም እና ልጆችን ከወላጆች ጋር ማተም

የሞቱ ሰዎች በህይወት እያሉ ካገቧቸው የትዳር ጓደኞቻቸው ጋር በቤተመቅደስ መታተም ይችላሉ። የሞቱ ሰዎች በህይወት ካሉ ወይም ከሞቱ ልጆቻቸው ጋርም መታተም ይችላሉ። የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ያለው የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ ማንኛውም አባል በእትመት ሥርዓቶች ላይ ወኪል ሆኖ ሊሰራ ይችላል።

28.3

ልዩ ሁኔታዎች

ይህ ክፍል በ28.1 ውስጥ ያሉ አንዳንድ መመሪያዎች የማይተገበሩባቸውን ሁኔታዎች ያብራራል።

28.3.1

ከውልደት በፊት የሞቱ ልጆች (ሞተው የተወለዱ እና የጨነገፉ ልጆች)

ከውልደት በፊት ለሞቱ ልጆች የቤተመቅደስ ሥርዓቶች አያስፈልጉም ወይም አይደረጉም። ለተጨማሪ መረጃ 38.7.3 ይመልከቱ።

28.3.2

ስምንት ዓመት ሳይሞላቸው የሞቱ ልጆች

ትናንሽ ልጆች በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምክንያት ተቤዥተዋል እንዲሁም “በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ [ድነዋል]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137፥10። በዚህ ምክንያት ስምንት ዓመት ሳይሞላቸው ለሞቱ ልጆች ጥምቀት ወይም የቤተመቅደስ ቡራኬን የመቀበል ሥርዓት አይደረግም። ሆኖም፣ በቃል ኪዳኑ ውስጥ ላልተወለዱ ወይም በህይወት እያሉ ያንን ሥርዓት ያልተቀበሉ ልጆች ከወላጆች ጋር ሊታተሙ ይችላሉ (18.1 ይመልከቱ)።