ላይብረሪ
አባሪ


አባሪ

የሰማይ አባታችሁ ቅዱስ ስርዓቶችን እንድትቀበሉ ይጋብዛችኋል። እነዚህ ስርዓቶች ቃል ኪዳኖችን ያካትታሉ - ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ገብተሃል፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ቃል ገብቷል። እነዚህን ቃል ኪዳኖች ታደርጋላችሁ፣ ለምሳሌ፣ ስትጠመቁ እና ማረጋገጫ በተሰጣችሁ ጊዜ፣ እና በጌታ ቤት ውስጥ ለዘመንና ለዘላለም በታተማችሁ ጊዜ። ቃል ኪዳኖችን መፈጸም እና መጠበቅ ደስታን ያመጣላቹሃል እናም ከእርሱ ጋር የዘላለም ሕይወት መደሰት የምትችሉበትን ወደ እርሱ መገኘት እንድትመለሱ የሚረዳችሁን የእግዚአብሔርን ኃይል እንድታገኝ ያስችላቹሃል።

እነዚህን ቃል ኪዳኖች ስትፈጽሙ ለእግዚአብሔር ቃል የገባችሁትን እና እርሱ ስለገባላችሁ ቃል የበለጠ ለማወቅ (አጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል3.5፣ የወንጌል ቤተመጻህፍትን ተመልከቱ)።

ከታች ያሉትን ጥያቄዎች አሰላስሉ። የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለመቀበል ቃለ መጠይቅ ሲደረግላችሁ የምትጠይቋቸው ጥያቄዎች ናቸው፣ ነገር ግን ቃለ መጠይቅ እስኪደረግላችሁ ድረስ አትጠብቁ። በፈለጋችሁት ጊዜ የራሳችሁን መንፈሳዊ መገምገም አድርጉ።

የወጣት ሴቶች ጭብጥ፣ የአሮናዊ ክህነት ቡድን ጭብጥ፣ አስርቱ ትእዛዛት እንዲሁም በራሳችሁ ግምገማ ውስጥ አጋዥ መሳሪያዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

ለወጣቶች የቤተ መቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለመጠይቅ ጥያቄዎች

  • በዘለአለም አባት እግዚአብሔር፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ እምነት እና ምስክርነት አለህ/አለሽ?

  • ስለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና እንደ አዳኝ እና ቤዛነት ስላለው ሚና ምስክርነት አለህ/አለሽ?

  • ዳግም ስለተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምስክርነት አለህ/አለሽ?

  • የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንትን እንደ ነቢይ፣ ባለ ራዕይ እና ገላጭ እንዲሁም በምድር ላይ ያሉትን ሁሉንም የክህነት ቁልፎች እንዲጠቀሙ ስልጣን እንደተሠጣቸው ብቸኛ ሰው አድርገህ/ሽ ትደግፋለህ/ትደግፊያለሽ? የቀዳሚ አመራርን እና የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባላትን እንደ ነቢያት፣ ባለራዕዮች እና ገላጮች አድርገህ/ሽ ትደግፋለህ/ትደግፊያለሽ? ሌሎች አጠቃላይ ባለሥልጣናትን እና የአከባቢ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ትደግፋለህ/ትደግፊያለሽ?

  • ጌታ እንዲህ ብሏል ሁሉም ነገሮች በፊቴ “በንጽህና ይሰሩ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥41). በአስተሳሰብህ/ሽ እና በባህሪህ/ሽ ውስጥ የሥነ–ምግባር ንጽህና እንዲኖርህ/ርሽ ጥረት ታደርጋለህ/ታደርጊያለስሽ? የንጽህና ህግን ታከብራለህ/ታከብሪያለሽ?

  • በግል እንዲሁም በህዝብ ፊት በምታሳየው/በምታሳዪው ባህርይ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን አስተምህሮቶች ትከተላላህ/ትከተያለሽ?

  • የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን የሚቃረኑ ማንኛውንም ትምህርቶች፣ ልምምዶች ወይም አስተምህሮቶች ትደግፋለህ/ፊያለሽ ወይም ታስተዋውቃለህ/ቂያለሽ?

  • የሰንበትን ቀን በቤትም ሆነ በቤተክርስቲያን ቅዱስ አድርጎ ለመጠበቅ፤ በስብስባዎች ለመገኘት፤ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ለመዘጋጀት እና በብቁነት ለመውሰድ፤ እንዲሁም ህይወትህን/ህይወትሽን ከወንጌል ህግጋት እና ትዕዛዛት ጋር አስማምተህ/ሽ ለመኖር ትጥራለህ/ትጥሪያለሽ?

  • በምታደርገው/ጊው ነገር ሁሉ ሐቀኛ ለመሆን ትጥራለህ/ሪያለሽ?

  • ሙሉ አስራት ትከፍላለህ/ትከፍያለሽ?

  • የጥበብ ቃልን ትረዳለህ/ትረጃለሽ እና በዚህም ትታዘዛለህ/ትታዘዣለሽ?

  • እንደ ንስሐ አካል በመሆን የክህነት ሥልጣን ባላቸው ሊፈቱ የሚገባቸው ከባድ ኃጥያቶች በህይወትህ/ሽ ውስጥ አሉ?

  • ወደ ጌታ ቤት ለመግባት እና በቤተ መቅደስ ሥርዓቶች ላይ ለመሳተፍ ብቁ እንደሆንክ/ሽ ይሰማሀል/ሻል?

የወጣት ሴቶች ጭብጠ

“እኔ መለኮታዊ ፍጥረት የሆንኩኝ እና ዘለዓለማዊ እጣፋንታ ያለኝ የተወደድኩ የሰማያዊ ወላጆች ሴት ልጅ ነኝ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር እንደመሆኔ መጠን እንደ እርሱ ለመሆን እጥራለሁ። ግላዊ ራዕይን እሻለሁ፣ በሱም መሰረት እተገብራለሁ እንዲሁም በተቀደሰ ስሙ ሌሎችን አገለግላለሁ።

በሁሉም ጊዜ እና በሁሉም ነገር እንዲሁም በሁሉም ቦታ የእግዚአብሔር ምስክር ሆኜ እቆማለሁ።

በዘላለማዊ ህይወት ውስጥ ከፍ ከፍ ለመደረግ ብቁ ለመሆን ስጥር፣ የንስሀ ስጦታን አጥብቄ ይዛለው እንዲሁም በየቀኑ ለመሻሻል እሻለሁ። በእምነት ቤቴን እና ቤተሰቤን አጠነክራለሁ፣ የተቀደሱ ቃል ኪዳኖችን እፈጽማለው እንዲሁም እጠብቃለሁ፣ የቤተመቅደስ ስርዓቶችን እና በረከቶችን እቀበላለሁ

የአሮናዊ ክህነት ብድን ጭብጥ

“እኔ የእግዚአብሔር ውድ ልጅ ነኝ፣ እናም እኔ እንድሰራው የሚፈልገው ስራ አለው።

በሙሉ ልቤ፣ በሙሉ ኃይሌ፣ እና ጉልበቴ እግዚአብሔርን እወዳለሁ፣ ቃል ኪዳኖቼን እጠብቃለሁ እንዲሁም የእርሱን ክህነት ከቤቴ ጀምሮ ሌሎችን ለማገልገል እጠቀማለሁ።።

ለማገልገል፣ ታማኝ ለመሆን፣ ንስሃ ለመግባት እና በየቀኑ ለመሻሻል በየቀኑ ስጥር፣ የቤተ መቅደስ በረከቶችን እና የወንጌልን ዘላቂ ደስታ ለመቀበል ብቁ እሆናለሁ።

እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር በመሆን ታታሪ ሚስዮናዊ፣ ታማኝ ባል እና አፍቃሪ አባት ለመሆን እዘጋጃለሁ።

ሁሉም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡና የኃጢያት ክፍያውን በረከቶች እንዲቀበሉ በመጋበዝ አለምን ለአዳኙ ዳግም ምፅዓት በማዘጋጀት እረዳለሁ።”

አሥርቱ ትእዛዛት

  • ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።

  • የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።

  • የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ።

  • የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።

  • አባትህንና እናትህን አክብር።

  • አትግደል።

  • አታመንዝር።

  • አትስረቅ።

  • በሐሰት አትመስክር።

  • አትመኝ።

ዘጸአት 20፥3–17 ተመልከቱ።