ወላጆች
2 እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ማውራት ይፈልጋል።


አብና ወልድ ለጆሴፍ ስሚዝ በቅዱስ ቁጥቋጦ ውስጥ ተገለጡ

2

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ማውራት ይፈልጋል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፥2–3

የወንጌል ዳግም መመለስ የጀመረው ጆሴፍ ስሚዝ የተባለ ታዳጊ ልጅ ሲጸልይ እና የሰማይ አባትና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመልሱለት ነው። እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኑን በህያው ነቢያት አማካይነት መምራቱን ቀጥሏል። ልጆቹ የሆናችሁትን ዐናንተምን፣ በመንፈስ ቅዱስ ሊያናግር ይፈልጋል። መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደሚናገራችሁ ማወቅ መማር ልታገኟቸው ከምትችሏቸው በጣም ጠቃሚ ችሎታዎች አንዱ ነው።

ዘለአለማዊ እውነቶች

መንፈስ ቅዱስ ወደ ሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመራችኋል። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ትልቅ ሚና ነው። እንዲሁም ንስሐ እንድትገቡ እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንድትከተሉ ያነሳሳቹኋል ስለዚህ የኃጢያት ክፍያውን በረከቶች እንድታገኙ ያነሳሳቹኋል። ንስሐ ስትገቡ መንፈስ ያነጻቹሃል እና እንድትለወጡ ይረዳቹሃል።

መንፈስ ቅዱስ ለአእምራችሁ እና ለልባችሁ ይናገራል። ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጡ መልዕክቶች በብዙ መንገዶች ወደ አዕምራችሁ ሊመጡ ይችላሉ—በተነሳሱ ሀሳቦች፣ ማስጠንቀቂያዎች፣ ግልጽ ግንዛቤ እና መንፈሳዊ ትዝታዎች። መንፈስ ቅዱስ እንደ ምቾት፣ በራስ መተማመን፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ ትህትና፣ ምስጋና እና ትዕግስት ባሉ ስሜቶች ልባችሁን ሊያነጋግር ይችላል።

ግብዣዎች

“መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።” እነዚህ ቃላት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነት ማረጋገጫህ በተደረገላችሁ ጊዜ ነው። መንፈስ ቅዱስን የምትቀበሉት እንዴት ነው? የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርቶች በመታዘዝ። እርሱ የእናንተ ጥንካሬያችሁ ነው። እርሱን መከተል መንፈስ ቅዱስን ወደ ሕይወታችሁ ይጋብዛል።

የሰማዩ አባታችሁን በጸሎት ፈልጉ። ልባችሁን ወደ እርሱ አፍስሱ። ስለሰጣችሁ ብዙ በረከቶች አመሰግኑት። ደስታችሁን፣ ጭንቀታችሁን እና ጥያቄዎቻችሁን ለእርሱ አካፍሉ። ዝም በሉ እና መልሶቹን አዳምጡ፣ ይህም እንደ ሰላም ስሜት፣ በአዕምራችሁ ውስጥ ያሉ ሀሳቦች ወይም የሆነ ነገር ለማድረግ ግንዛቤ ሊመጣ ይችላል።

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የእግዚአብሔርን ድምፅ ስሙ። ቅዱሳት መጻሕፍት ለእናንተ የእግዚአብሔር ቃል ናቸው! ድምፁን ለማግኘት እና የፍቅሩን ስሜት ለማግኘት በየቀኑ ከእነሱ ተማሩ። በምታነቡበት ጊዜ፣ ምን እያስተማራችሁ እንደሆነ አሰላስሉ፣ እና የሚመጡትን ግንዛቤዎች ጻፉ። ህሕይወታችሁን በሙሉ ቅዱሳት መጻሕፍትን በተለይም መፅሐፈ ሞርሞንን የማጥናት የዕለት ተዕለት ልማድ አድርጉ።

በምትቀበሏቸው መንፈሳዊ ግንዛቤዎች ላይ እርምጃ ውሰዱ። አንድን ሰው የሚባርክ ደግ ነገር ለማድረግ ሀሳብ ወይም ስሜት ከተሰማችሁ አድርጉ! መልካም ነገር ሁሉ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው። የሰማዩ አባታችሁን ከእርሱ የሚሰጡትን ግንዛቤዎች እንድትከተሉ ሊያምናችሁ እንደሚችል አሳዩት።

ኢየሱስ ክርስቶስ

ቃል የተገቡ በረከቶች

መንፈስ ቅዱስ ያጽናናችኋል እንዲሁም ይመራችኋል። አጽናኝ በመባል ይታወቃል። በፈተና ጊዜ ይረዳችኋል። ምን ማለት ወይም ማድረግ እንዳለባችሁ እንድታውቁ ይረዳችኋል። በእርሱ ተጽእኖ በእውነት እና በሐሰት መካከል ያለውን ልዩነት መለየት ትችላላችሁ። በሌሎች እና በራሳችሁ ውስጥ መልካሙን ነገር እንድታገኙ ሊረዳችሁ ይችላል። መንፈስ ስለ አደጋም ሊያስጠነቅቃችሁ ይችላል። ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመራችኋል እና ከኃጢአት ያርቃችኋል።

መንፈሳዊ ስጦታዎችን መቀበል ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ለልጆቹ በመንፈሱ በኩል የሚሰጣቸው ብዙ ስጦታዎች አሉ። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ መገለጥ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን፣ ማስተማር፣ ማስተዋል እና ጥበብን ያካትታሉ። የሰማይ አባት ስለሰጣችሁ መንፈሳዊ ስጦታዎች፣ እንዴት ማዳበር እንደምትችሉ እና ሌሎችን ለመባረክ እንዴት እንደምትጠቀምባቸው እንደሚፈልግ ለመጠየቅ ጸልዩ።

ጥያቄዎች እና መልሶች

ሌሎች ሰዎች ከእኔ የበለጠ መንፈሳዊ ልምዶች ያሏቸው ለምንድን ነው? ሁሉም መንፈሳዊ ልምዶች ተአምራዊ ወይም አስደናቂ አይደሉም። ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር በአዕምሯችን ወይም በልባችን ውስጥ ባለው የዋህ ስሜት ያናግረናል። እነዚህ ጸጥ ያለ እና ትንሽ ድምፅ ሹክሹክታዎች ናቸው። ምናልባት መንፈስ እየተሰማችሁ ሊሆን ይችላል እና ገና አላወቃችሁትም። መጸለያችሁን ቀጥሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናታችሁን ቀጥሉ። ከጊዜና ልምምድ ጋር መንፈስ ቅዱስን በተለያየ መንገድ መለየትን ትማራላችሁ።

1ኛ ነገሥት 19፥11–12 (እግዚአብሔር በጸጥታ በትንሽ ድምፅ ይናገራል)፤ ዮሐንስ 15፥26 (መንፈስ ስለ ክርስቶስ ይመሰክራል)፤ ሞሮኒ 10፥3–5 (እውነትን በመንፈስ እወቁ)፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥12–13 (መንፈስ መልካም ለማድረግ ይመራል)፤ 45፥57 (መንፈስን እንደ መመሪያህ ውሰድ)፤ 46፥8–26 (መንፈሳዊ ስጦታዎች) ተመልከቱ።

የቤተመቅደስ ፈቃድ ወረቀት ለማግኘት የሚጠየቅ ጥያቄ

  • በዘለአለም አባት እግዚአብሔር፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ እምነት እና ምስክርነት አለህ/አለሽ?