2025
በመጀመሪያው የጌታ ልደት ስለነበሩት እረኞች ምን እናውቃለን?
ታህሳስ 2025 ፟(እ.አ.አ) ሊያሆና


ወርሀዊ የ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ታህሳስ 2025 (እ.አ.አ)

በመጀመሪያው የጌታ ልደት ስለነበሩት እረኞች ምን እናውቃለን?

ወጣት ሴት

እረኞች፣ በብራይን ኮል

በመጀመሪያው የጌታ ልደት ስለነበሩት እረኞች ጥቂት ነገሮችን እናውቃለን።

በቤተልሄም አቅራቢያ ነበሩ። እረኞቹ ክርስቶስ በተወለደበት “ተመሳሳይ ሃገር” ውስጥ ነበሩ (ሉቃስ 2፥8)። እና እርሱ እዚያው እያለ እነርሱ ወደ ቤተልሄም በእግራቸው ለመጓዝ ችለዋል (ሉቃስ 2፥15-16)።

እነርሱ ስራቸውን እየሰሩ ነበር። እርኞችም “በሌሊት በሜዳ መንጋቸውን ሲጠብቁ ነበር፡፡” (ሉቃስ 2፡8)። እነርሱም እንደ አዳኙ መልካም እና ታማኝ እረኞች ነበሩ—መልካምእረኞች (ዮሐንስ 10፥11፣ 14)።

እነርሱ ስለመሲሁ የተነገረውን ትንቢት አውቀዋል። በእርግጥም መልአኩ ስለ “ጌታ ክርስቶስ” መወለድ የምስራቹን ሲያበስር ስለምን እየተናገረ እንደነበር አውቀዋል (ሉቃስ 2፥11)፣ ጥንት ስለመሲሁ የተነገረ ትንቢት።

ታላቅ ቅናትም አደረባቸው። መልአኩ “ህጻን …በግርግም ተኝቶ” ባዩ ጊዜ (ሉቃስ 2፥12)፣ “በፍጥነት” ሊመለከቱት ሄደዋል (ሉቃስ 2፥16)።

የምሥራቹን ለሰዎች አካፈሉ። እነርሱም “በአገሩ ሁሉ” ስለ ክርስቶስ መወለድ የመልአኩን መልእክት ያዩትን እና የሰሙትን ሁሉ አሳውቀዋል (ሉቃስ 2፥17)።

እግዚአብሔርንም አመሰገኑ እንዲሁም አወደሱ። ከዚህም ሁሉ በኋላ “ስላዩት እና ለሰሙት ነገሮች ሁሉ እግዚአብሄርን እያከበሩ እና እያወደሱ ተመልሰዋል” (ሉቃስ 2፥20)።