‘’በክህነት ስልጣን እና ሃይል የተባረከ፣’’ ሊያሆና፣ መስከረም 2025።
ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ መስከረም 2025 (እ.አ.አ)
በክህነት ስልጣን እና ሃይል የተባረከ
የቤተክርስቲያን አባላት የእግዚአብሔርን ሃይል በመጠቀም ለማገልገል እና በቤተክርስቲያን፣ በቤት፣ እና በአለም ዙሪያ ሌሎችን ለመባረክ የተመረጡ ናቸው።
ቅዱሱ የእግዚአብሔር ክህነት የእርሱን የደህንነት እና ከፍ የማድረግ ስራ ለመፈጸም አስፈላጊ በመሆኑ ክህነትን ወደ ምድር ዳግም መልሷል እናም ይህም በኋለናው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሚተዳደር መሆኑ ይህ ለዓለም ምስክርነታችን ነው።
የክህነት ስልጣን እና ሃይል አስፈላጊነት
ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያኗ ራስ ነው። ቤተክርስቲያኗ ልክ እርሱ በምድር ሲኖር እንደነበረበት ጊዜ አስፈላጊውን የሰው ልጆችን በዚህ በዘመን መጨረሻ የማዳን ስራን ለመስራት የተፈጠረች መሳሪያ ነች። በቤተክርስቲያኗ አማካይነት፦
-
በዓለም ዙሪያ ሁሉ ወንጌሉን ሊያሰራጭ ይችላል።
-
ለሰለስቲያል መንግስቱ እንኳን የቃል ኪዳን መንገድን ጨምሮ—ጥምቀትን እና ሌሎች ቃል ኪዳኖችን ሁሉ ሊያቀርብልን ይችላል።
-
ቤተሰብን ለዘለዓለም አንድ ሊያደርግ ይችላል።
-
ያለእነርሱ ለሞቱት ጨምሮ፣ የደህነትን ስጦታ ሊያቀርብ ይችላል።
ይህንን ታላቅ ዓላማ ለማሳካት፣ እና ለጌታም ምጽአት ለማዘጋጀት፣ ቤተክርስቲያኗ የእግዚአብሔር ቀጣይ ምሪት፣ ስልጣን፣ እና ሃይል ያስፈልጋታል። ቤተክርስቲያኗ “እውነተኛ እና ህያው [የሆነች] ቤተክርስቲያን” ናት (ትምህርት እና ቃል ኪዳንኖች 1፥30) ምክንያቱም በእርሱ ክህነት፣ እንዲሁም “እንደ እግዚአብሔር ልጅ ስርአት፣ ቅዱሱ ክህነት” በኩል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥3)፣ ይህችን የእርሱ መሪነት እና ሀይል ሰጥቷታል።
ነገር ግን ለዚህ ቅዱስ ክህነት ባይሆን ኖሮ፣ ቤተክርስቲያኗ በዓለም መልካምን የምታደርግ ነገር ግን በእርሱ ፊት የእግዚአብሔርን ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን ለዘለዓለም ህይወት ለማዘጋጀት ታላቁን ዓላማ ለማሳካት ሃይል የሌላት ተራ ምድራዊ ድርጅት ትሆን ትሆናለች። የክህነት ቁልፍ፣ የጌታን ሥራ በመስራት ሂደት የክህነት አጠቃቀምን ለመምራት የሚያስችል ሥልጣን ነው።
“በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ ሁሉም የክህነት ስልጣን ስራ የሚከናወነው የክህነት ስልጣን ቁልፍ ባላቸው አመራር ነው።
“ብቁ የሆኑ ወንድ የቤተክርስቲያኗ አባላት ክህነትን በመሰጠት እና በክህነት ክፍሎች በመሾም የክህነት ሥልጣንን ይቀበላሉ (አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ፣ 3.4)። ሁሉም የቤተክርስቲያኗ አባላት በተለዩ ጊዜ ወይም የእግዚአብሔርን ስራ ለመስራት ሃላፊነትን በወሰዱ ጊዜ በየተሰጥቸውን ስልጣል ለመጠቀም ይችላሉ።”
በክህነት ቁልፎች አማካይነት፣ የጌታ ተቀዳሚ ነገሮች በላይነት ይኖራቸዋል። ከእርሱ ልጆች ጋር የማይጣጣምን የግል አጀንዳ ሊያካሂድ የሚችል ማንም ሰው አይኖርም። የግል ጥቅምን በመሻት እና የግል ተከታዮችን ለማግኘት ማንም አስማተኝነት ሊሳካለት አይችልም።
ክህነት በቤተክርስቲያን አባላት ቤት ውስጥ ልዩ ሚና እንዲሁ ይጫወታል። ፕሬዚዳንት ዳለን ኤች. ኦክስ፣ በቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ፣ እንዳስተማሩት፣ “የክህነት ስልጣንን መለማመድ የሚቻለው ቁልፎችን በያዘው ግለሰብ ፍቃድ ብቻ መሆን አለበት የሚለው መርህ በቤተክርስቲያን ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው ነገር ግን ይህ መርህ በቤተሰብ ውስጥ ተግባራዊ አይሆንም።” አባቶች—ለመምከር፣ የቤተሰብ ስብሰባዎችን ለማድረግ፣ ለሌሎችም ሆነ ለቤተሰቡ አባላት የክህነት በረከት ለመስጠት፣ እናም ሌሎች ነገሮችን ለማድረግ—ማናቸውም የክህነት ቁልፍ ያላቸው አመራር ወይም ስልጣን ሳያስፈልጋቸው በቤተሰባቸው ውስጥ ለመምራት እና ክህነትን በመለማመድ ይችላሉ።
“አባት በሌለበት እና እናት የቤተሰብ መሪ በሆነችበት ሁኔታ ተመሳሳይ መሰረተ ሃሳቦች ተግባራዊ ይሆናሉ። ከቤተመቅደስ በተቀበለችው ቡራኬ እና እትመት አማካኝነት በቤቷ ውስጥ ትመራለች እናም የክህነትን ኃይል እና በረከቶች ወደ ቤቷ ውስጥ ለማምጣት ሚና ትጫወታለች።”
በእኛ ጊዜያት የክህነት ዳግም መመለስ
ግንቦት 15፣ 1829 (እ.አ.አ)
በኋለኞቹ ዘመናት የክህነት ስልጣን ዳግም መመለስ በስርዓት፣ ደረጃ በደረጃ ሂደት የቀጠለ ነው። ለዘመናችን መሰረታዊ ቅዱሳት መጻህፍት በመሆን፣ በመፅሐፈ ሞርሞን በ1829 (እ.አ.አ) እየተተረጎመ ነበር፣ ጌታም የክህነት አወቃቀሩን በስፍራው ማድረግ ጀመረ። ስለ ጥምቀት ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ በጸሎት ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ፣ ከሞት የተነሳው መጥምቁ ዮሐንስ ተገለጠ እና ለእነሱ የአሮናዊ ክህነት ስልጣን ሰጣቸው፣ ይህም ክህነት “የንስሀን ወንጌል፣ እና ለኃጢአት ስርየት በማጥለቅ የማጥመቅ አገልግሎት ቁልፎች የያዘውን” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥1) ነው። በዚያም ስልጣን፣ ቤተክርስቲያኗ በመደበኛነት ስትመሰረት ጆሴፍ እና ኦሊቨር አንዳቸው ሌላውን እንዲሁም ሌሎችን አጥምቀዋል።
ወዲያውኑም ከግንቦት 15፣ 1829 (እ.አ.አ) በኋላ
ከመጥምቁ ዮሐንስ መገለጥ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ኳድሪ “የመንግስቱን እና የዘመኑን የጊዜ ሙሉነት ቁልፎች እንደተሸከሙ” ባወጁት በጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ተሾሙ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥13)፤ እንዲሁም 128፥20 ተመልከቱ)።
ሚያዝያ 3፣ 1836 (እ.አ.አ)
ተጨማሪ አስፈልጎ የነበረው የክህነት ስልጣንም የመጣው በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥም ሶስት የጥንት ነቢያት፣ ሙሴ፣ ኢልያስ፣ እና ኤልያ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር ተገልጠው እናም የእስራኤልን የመሰብሰብ እና ለጌታ ቤተመቅደስ ስራ የሚያስፈልጉትን ቁልፎች ሲሰጧቸው ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥ 11–16 ተመልከቱ)።
በጋ 1829–ሚያዝያ 1835 (እ.አ.አ)
አሁን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ይፉ የሆነው ሰዎችን ለታላቁ የክህነት ስልጣን (መልከ ጸዴቅ) እና ለሚያዘጋጀው (የአሮናዊ) ክህነት ስለመሾም፤ ፣ እንደ ኤጲስ ቆጶስ አይነት የክህነት ባለስልጣናትን ስለመመደብ፤ እና የክህነት ቡድኖችን እና ሸንጎዎችን ስለማደራጀት ለጆሴፍ ስሚዝ መመሪዎች ተሰጥተዋል።
1835–1973 (እ.አ.አ)
የክህነት አደረጃጀትን እና በቤተክርስቲያን ያሉትን ተግባራት ለመምራት ነቢያታዊ አመራሮች ቀጥለዋል። ለምሳሌ፣ የአስራ ሁለቱን ቡድኖች ለመርዳት የሰባዎቹ ቡድኖች ተደራጅተዋል። በመራዕብ ከተደረገው ታላቅ ጉዞ በኋላ እና በተለያዩ የመልክዓ ምድር ስፍራዎች የቤተክርስቲያኗ አባላት መበተን በኋላ፣ እነዚህ ቡድኖች በቤተክርስቲያኗ ካስማዎች እንዲያገለግሉ ተሰማርተዋል።
1973 (እ.አ.አ) እስከ አሁን
በፕሬዚዳንቶቹ ስፔንሰር ደብሊው ኪምቦል [1895—1985 (እ.አ.አ)]፣ ኤዝራ ታፍት ቤንሰን [1899–1994 (እ.አ.አ)]፣ እና ጎርደን ቢ. ሂንክሊ [1910—2008 (እ.አ፣አ)] አመራር፣ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያን ደረጃ እና በቤተክርስቲያን አካባቢዎች ሰባዎቹ እና ቡድኖቻቸው በአስራ ሁለቱ ቡድን አመራር ስር መስራት ጀምረዋል። ከዚያም በካስማ ደረጃ የነበሩ ቡድኖች ተቋርጠዋል። ዛሬ የአጠቃላይ ባለስልጣናት ቡድኖች እና የአካባቢ ሰባዎች “ቤተክርስቲያኗን በመገንባት እና የእርሷን ጉዳዮች በሀገሮች ውስጥ ሁሉ በመቆጣጠር” ሃዋርያትን ይረዳሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥34)። ቤተክርስቲያኗ በሰፋች ቁጥር ተጨማሪ የሰባዎቹ ቡድኖች ሊፈጠሩ ይችላሉ።
በጋምቢያ፣ ምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ሽማግሌ ክሪስቶፈርሰን ወንድም ሳምፕሰን እና ዳንኤል አሞኮን በየካቲት 2022 (እ.አ.አ) ሰላም ሲሉ።
ክህነት፦ የመባረክ ሃይል
በአንድ አባባልም፣ ኢየሱስ ዳግም መልሶ ያመጣው የክህነት ስልጣን ዓላማ እና ሀይል ለመባረክ ነው። ይህም የቤተክርስቲያን አባላት የእግዚአብሔርን ሃይል በመጠቀም ለማገልገል እና በቤተክርስቲያን፣ በቤት፣ እና በአለም ዙሪያ ሌሎችን ለመባረክ ያስችላቸዋል። አባላት የእግዚአብሔር መንግስት ምድርን በመሙላት እንድታድግ ለመርዳት ከራሳቸው በላይ በሆነ መለኮታዊ ስጦታዎች እና ሃይሎች የጌታን የማዳን ስራ እና ዘለዓለማዊነት ለማሳካት ከጌታ ጋር አብረው ይሰራሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 65፥2፣ 5–6)።
ጌታም እንደገለጽው፣ “እናም ይህም ታላቅ ክህነት [መልከ ጼዴቅ] ወንጌሉን ያስተዳድራል እናም የመንግስቱን ሚስጥር ቁልፎች፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን እውቀት ቁልፎችን፣ ይዟል።
“ስለዚህ፣ በዚህም ስርዓት ውስጥ፣ የአምላክ አይነት ሀይል ይታያል።
“ካለዚህም ስርዓት፣ እናም ካለክህነት ስልጣን፣ የአምላክነት ሀይል ለሰዎች በስጋ አይታይም” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19–21)።
ስርዓቶች፣ በእርግጥ፣ ከጥምቀት የሚጀምሩ እና በጌታ ቤት ውስጥ በቃል ኪዳኑ በቀጣይነት የምንቀበላቸውን ጨምሮ በክህነት የሚሰሩ ስራዎች ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የምንገባባቸው ቅዱስ ቁርባኖች ናቸው። እነዚህን ቃል ኪዳኖች በመቀበል ከ”ተፈጥሮአዊ” ወንድ እና ሴት ወደ ቅዱሳንነት እንቀየራለን (ሞዛያ 3፥19) ያለነውር እና ያለነቀፋ በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ እንቀደሳለን እንዲሁም እንነጻለን ((ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥29–31፣ 3 ኔፊ 27፥16-20 ተመልከቱ)።
በቀዳሚ አመራር እና በአስራ ሁለት ሐዋሪያት ከተሰጠው “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት በዳግም መመለስ፦ የሁለት መቶኛ አመት መታሰቢያ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” የሚገኘው ይህ ጥቅስ መልካም ማጠቃለያ ይሰጣል፡፡
“በሚያዝያ 6፣ 1830 (እ.አ.አ) የተደራጀችው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን በዳግም የተመለሰች እንደሆነችም እናውጃለን። ”ይህችም ቤተክርስቲያን የማዕዘን አለቷ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ህይወት እና መፈጸሚያ በሌለው የኃጢያት ክፍያው እና በእውን ትንሳኤው ላይ የተተከለች ናት። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገናም ሐዋሪያትን ጠርቷል እናም ለእነርሱም የክህነት ስልጣንን ሰጥቷቸዋል። እርሱም መንፈስ ቅዱስንና የደህንነት ስርዓቶችን ለመቀበል፣ እና የሚጸና ደስታን ለማግኘት እንችል ዘንድ ወደ እርሱ እና ወደ ቤተክርስቲያኑ እንድንመጣ ሁላችንንም ይጋብዛል።”
© 2025 by Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ ታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፤ 6/19። የMonthly Liahona Message, September 2025 ትርጉም። Amharic. 19604 506