2025
የሰማይ አባት ሊያናግራችሁ ይፈልጋል።
መጋቢት 2025 (እ.አ.አ)


“የሰማይ አባት ሊያናግራችሁ ይፈልጋል፣” ሊያሆና፣ መጋቢት 2025 (እ.አ.አ)

ወርኃዊ ሊያሆና መልዕክት፣ መጋቢት 2025 (እ.አ.አ)

የሰማይ አባት ሊያናግራችሁ ይፈልጋል።

በሰማይ አባት እና በተወደደው ልጁ ላይ ያላችሁ እምነት መጋረጃውን እንድትለዩ እና የአብን ድምፅ እንድትቀበሉ ይርዳችሁ።

ወጣት ሴት ስትጸልይ

እኛ ከሰማያዊ ቤታችን ርቀን ምድርን በጋራ የምንጋራ፣ የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች ነን። ይህ ምድራዊ ህይወታችን ነው፣ ሰውነታችንን የምንቀበልበት፣ ከክፉ ይልቅ መልካምን የምንመርጥበት፣ ‘’የመልካሙን ነገር ሽልማት ያውቁ ዘንድ፣ መራራውንም ይቀምሳሉ።’’ (ሙሴ 6:55)፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በተቀደሰው የሀጢያት ክፍያ ላይ ያለንን እምነት ለማሳደግ፣ እና የአባታችንን የደስታ እቅድ ለመቀበል። እዚህ የመጣነው እንደ ሰማይ አባታችን ለመሆን ነው።

የቅድመ ህይወታችን ትውስታ ሳይኖረን፣ አንዳንድ ጊዜ፣ እኛ ለተውነው አለም ብቸኝነት ይሰማናል። አባታችን ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት እንድንቀጥል እና መመሪያ፣ እና መጽናናትን ከእርሱ እንድንቀበል መንፈሳዊ ስጦታ ሰጥቶናል። ይህን ስጦታ በደንብ እናውቀዋለን፤ ጸሎት ተብሎ ይጠራል።

ወደ ሰማይ አባታቹ ጸልዩ።

ለአዳምና ለሔዋን እንዲሁም ለሚከተሏቸው ሁሉ፣ መልአክ እንዳዘዘ፣ “ንስሀ ግባ እና በወልድም ስም እግዚአብሔርን ለዘለአለም ጥራ” (ሙሴ 6፡8)።

ክርስቶስ እንዳስተማረው፣ “ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል” (ማቴዎስ 7፥7)። “አንተ ግን ስትጸልይ፥…በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤…” (ማቴዎስ 6፡9)። ስለዚህ እንዲህ ብላችሁ ፀልዩ፥ በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ (ማቴዎስ 8፡9)።

ኢየሱስ ያለማቋረጥ ወደ አባቱ ይጸልይ ነበር። “በእነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።” (ሉቃስ 6፡12) “ካሰናበታቸውም በኋላ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ (ማርቆስ 6፡46)። “ጌቴሴማኒ ወደምትባልም ስፍራ መጡ፥ ደቀ መዛሙርቱንም ስጸልይ ሳለሁ፥ በዚህ ተቀመጡ አላቸው።” (ማርቆስ 14፡32) ኢየሱስ በመስቀል ላይ እያለ ስለቀሉት ወታደሮች ጸለየ፡ “አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ።” (ሉቃስ 23፡34)

ቅዱሳት መፅሀፍት “ሁልጊዜ እንድንጸልይ” ይመክሩናል። (ሉቃስ 21፥362 ኔፊ 32፥93 ኔፊ 18፥15ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥519፥3820፤3331፥12።) “በስራዎችህ ሁሉ ከጌታ ጋር ተማከር፣ እናም ለአንተ ጥቅም ይመራሃልና፤” (አልማ 37፡37) በተጨማሪም አባታችን ለእኛ የሚያደርገውን ሁሉ በመገንዘብ “ነፍሳች[ን] ያለውን ሁሉንም ምስጋና እና ውዳሴ እንሠጣለን። (ሞዛያ 2፡20)

ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል፥ “መንፈሳዊ ለራስ ጥሩ ግምት መስጠት የሚጀምረው እያንዳንዱ አዲስ ጠዋት ከአምላክ የተገኘ ስጦታ መሆኑን በመገንዘብ ነው። … ከቀን ቀን የጠበቃችሁን፣ እናም ከአንዱ ወቅት ወደ ሌለኛው እንኳን የደገፋችሁን(ሞዛያ 2፡21) ተመልከቱ።”

ሰዎችን እንዲፀልዩ የሚያስተምረውን መንፈስ ካዳመጣችሁት መፀለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ፤ እርኩስ መንፈስ ሰዎችን ፀሎት አያስተምርምና፣ ነገር ግን መፀለይ እንደሌለባቸው ያስተምራቸዋል። (2 ኔፊ 32፡8)

የተጠናቀቀ የአዳኝኙሥዕል።

ዝርዝር ከ ክርስቶስ የኢያኢሮስን ሴት ልጅ ከሞት ሲያስነሳ፣ በግሬግ ኬ ኦልሰን

በአዳኛችን ምሳሌ እና በዘመናት ሁሉ በመላእክት እና በነቢያት ምክር፣ ለበረከቶቻችን ምስጋናን ለመግለጽ፣ እና ዘወትር በልባችን ውስጥ ጸሎትን ለመጠበቅ በየቀኑ መፀለያችንን በግልጽ እናውቃለን። ከአባታችን ጋር የመነጋገር ኃላፊነት አለብን።

ነገር ግን ይበልጥ በክብር፣ በሰማይ ያለው አባታችን ለጸሎታችን ምላሽ ይሰጣል። በዚህ ምድራዊ አለም ውስጥ ያለው አሳሳቢ ጥያቄ፣ ከአባታችን የሚመጡትን መልሶች፣ መመሪያዎች፣ እና መጽናናትን እንዴት በተሻለ ሁኔታ መቀበል እና መረዳት እንችላለን? የሚለው ነው።

ከሰባት አሥርተ ዓመታት በላይ ባሳለፍኩት የሕይወት ዘመኔ አባታችን እንደሚያናግረን አውቃለሁ። ብቻችንን አይደለንም። አዳኙን ለመከተል ስንጥር የሰማይ ፍጡራን ይጠብቁናል እንዲሁም ይረዱናል።

ለጸሎታችን መልስ ማግኘት የሚጀምረው በሰማይ አባታችን እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን እምነት ነው። ኢየሱስ እንዳለ “እመኑ ብቻ እንጂ፣ አትፍሩ” (ማርቆስ 5፡36)። በእርሱ እንታመናለን፣ ትእዛዛትን ለመጠበቅ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፣ እንዲሁም በሁሉም ነገሮች እጁን እንመለከታለን። በሁሉም ነገሮች ውስጥ የእርሱ እጅ እንዳለበት ካለመመስከር እና ትእዛዙን ካለማክበር በቀር፣ በምንም መንገድ ሰው እግዚአብሔርን አያስቀይመውም፣…።” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፡21)

የእግዚአብሄር እጅ በህይወታችን ማለት በዓለማችን ላይ ያለውን ክፉ ወይም አሰቃቂ አሳዛኝ ክስተት ያመጣል ማለት አይደለም። ይህ ማለት ግን፣ በችግርና በፍትህ አልበኝነት ዘመን ከጎናችሁ ይቆማል፣ ችሎታችሁን ያጠነክራል፣ ያጽናናችኋል፣ እንዲሁም “እርሱ መከራህን ወደ ጥቅምህ ይለውጥልሃል” (2 ኔፊ 2:2)።

ድምፁን ስማ

በእርሱ ላይ እምነት ሲኖረን እና ትእዛዛቱን ስንጠብቅ፣ የእርሱን ድምፅ በተሻለ ሁኔታ መስማትን እንማራለን።

በ መስከረም 1993፣ እንደ አጠቃላይ አመራር የመጀመሪያ ዓመቴ፣ ፕሬዘደንት ጄምስ ኢ ፎስት (1920–2007)፣ በዚያን ጊዜ የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ጉባኤ አባል፣ ባለቤቴን፣ ካቲን፣ እና እኔን በብሪገም ያንግ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ከእርሱ ጋር እንድንካፈል ጋበዙን። 1993 (እ.ኤ.አ.)ዓ.ም. ስማርት ስልኮች፣ ማህበራዊ ሚዲያዎችና ኢንተርኔት በስፋት ከመገኘታቸው በፊት እንደነበር አስታውሱ።

ፕሬዝዳ`ንት ፎስት “የመንፈስ ድምፅ” በሚል ርዕስ ባወጡት ንግግራቸው እንዲህ ሲሉ አስጠነቀቁ፥ “በእናንተ ትውልድ ውስጥ እንዴት መኖር፣ ፍላጎታችሁን ማርካት፣ ሁሉንም እንዴት ማግኘት እንደሚቻል በሚነግሩአችሁ ብዙ ድምፆች ተገድባችዋል። በጣቶችዎ ጫፍ እስከ አምስት መቶ የሚደርሱ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ይኖራችዋል። ሁሉንም አይነት ሶፍትዌሮች፣ ኢንተርአክቲቭ ኮምፒዩተር ሞዴሞች፣ የመረጃ ቋቶች እና የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ይኖራሉ፤ የዴስክቶፕ ህትመት፣ የሳተላይት መቀበያ እና የመገናኛ አውታረ መረብ በመረጃ የሚይዙ ይኖራሉ። … ማዳመጥ የሚገባችሁ ድምፅ የመንፈስ ድምፅ ነው።”

ፕሬዘደንት ቦይድ ኬ. ፓከር (1924–2015)፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ጉባኤ ፕሬዘዳንት፣ ከጓደኞቻቸው ጋር በተጨናነቀ መናፈሻ ውስጥ እየሄዱ ሳለ፣ የጆን ቡሮውስ ስነ-ተፈጥሮ አቀንቃኝ የመንፈስን ትንሽ የዝምታ ድምፅ ተሞክሮ አስተማሩ። የፕሬዝዳንት ፓከር ቃላት የሚከተሉት ናቸው፦

“ከከተማ ኑሮ ድምጽ በላይ [አቶ ቡሮውስ] የወፍን ዘፈን ሰማ።

“ቆም ብሎ አዳመጠ! አብረውት የነበሩት ሰዎች አልሰሙትም ነበር። ዙሪያውን ተመለከተ። ማንም አላስተዋለውም ነበር።

“ሁሉም ሰው ይህን ያህል ውብ የሆነ ነገር ማጣቱ በጣም ረብሾት ነበር።

“አንድ ሳንቲም ከኪሱ ወስዶ አየር ላይ አዘዋወረው። ከወፏ ዝማሬ የበለጠ ድምፁን ከፍ አድርጎ መንገዱን በቀለበት መታው። ሁሉም ዞረ፤ ይህን መስማት ችለው ነበር!

የአንድን ወፍ ዝማሬ ከከተማ ድምፅ ሁሉ መለየት አስቸጋሪ ነው። አንተ ግን መስማት ትችላለህ። ለማዳመጥ ራስህን ካሠለጠንክ ድምጽን በግልጽ መስማት ትችላለህ።”

የፕሬዚደንት ፓከር በ1979 የተከናወነው የመንፈስ ቅዱስ ትምህርት፣ ህይወት በጣም ጸጥ ባለበት እና የአለም ድምጽ አሁን ካለበት በበለጠ የተሸነፈበት ጊዜ ነበር።

ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “ከመንፈስ ሹክሹክታ ይልቅ በማህበራዊ ሚዲያ ለሚሰጡ ነገሮት የበለጠ ትኩረት የምትሰጡ ከሆነ፣ እራሳችሁን ለመንፈሳዊ አደጋ እያጋለጣችሁ ነው።”

ፕሬዘደንት ፋውስት እንዲህ አሉ፣ “የመንፈስን ድምፅ ለመስማት ከፈለግን፣ እኛም ጆሯችንን መክፈት፣ የእምነትን ዓይንን ወደ ድምፁ ምንጭ ማዞር፣ እና በፅናት ወደ ሰማይ መመልከት አለብን።”

ይህ የመንፈስ ድምፅ ወደ አእምሯችን እና ወደ ስሜታችን ይመጣል። ‘’በአንተ ላይ በሚሆነው እና በልብህም በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በአዕምሮህ እና በልብህ እነግርሀለሁ። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8:2) ህሊናህን አዳምጥ— ራዕይ ብዙ ጊዜ የሚጀምረው እዚያ ነው።

ሽማግሌ አንድርሰን ከቡድኑ ጋር ሲነጋገሩ

በየካቲት 2024፣ በማርኪና ሲቲ፣ ፊሊፒንስ በሚገኘው የልጃገረዶች ’ሆም ቦይስ’ ከተማ ኮምፕሌክስ ጉብኝት ላይ ሽማግሌ አንድርሰን ለወጣቶቹ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸውን አስተምሯቸው ነበር፥ “ይወዳችኋል። እናም ልትማጸኑት ትችላላችው። ጸሎታችሁን ይሰማል።”

በእምነት በታመነ ልብ ጸልዩ

መልስና ስሜት በግፊት ሊሆን አይችልም። እንጸልያለን እና በአማኝ ልብ እንጠብቃለን። አንዳንድ መልሶች በዚህ ህይወት አይመጡም፣ ለጻድቃን ግን፣ ጌታ ሁሌም ሰላሙን ይልካል (የዩሃንስ ወንጌል 14፡27 እይ)። ብዙውን ጊዜ መልስ የምናገኘው በዙሪያችን ያሉትን ለመርዳት ስንጸልይ ነው። አንዳንድ ጊዜ “በሥርዓት ላይ ሥርዓት፣ በትእዛዝም ላይ ትእዛዝ” ይመጣሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፡12)።

የሰማይ ድምፅ ባልተጠበቁ ጊዜያት እና ባልተጠበቁ ቦታዎች ወደ እኛ ሊመጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን በጸጥታ ቦታዎች እና በቅዱስ ስፍራዎች ውስጥ በጣም ትልቅ እድሎቻችንን እናገኛለን። በማለዳ በጸሎቴ እና በማሰላሰል፣ ያልተለመዱ በረከቶችን አገኘሁ። በየቀኑ፣ የግል፣ ያልተቋረጠ ቅዱሳን መጽሃፍ ንባብ፣ በአንዳንዳንድ ጊዜ ልማድ፣ የመንፈስን ድምፅ እንደሌሎች ጊዜያት እንደ እሳት ወደ ልባችን ያመጣል።

አንዳንድ ጊዜ፣ የሚሰማን ነገር በተለየ ከምናነበው ነው፤ በሌሎች ጊዜያት ደግሞ የምናሰላስልበት ነገር ለየት ያለ ሃሳብ መልስ ያመጣልናል። ሽማግሌ ሮበርት ዲ ሄልስ የተናገራቸውን ቃላት አስታውሱ፥ “ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ስንፈልግ፣ እንጸልያለን። እናም እርሱ እንዲያነጋግረን ስንፈልግ፣ ቅዱሳን መጽሃፍትን እንመርምራለን።”

የአለም ጫጫታ እና ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች በዙሪያችን ሲዞሩ፣ ጌታ ነብይን ከጊዜ ወደ ጊዜ ብዙ ቤተመቅደሶችን እንዲገነባ መመሪያ ሰጥቷል። በነዚህ የጌታ ቅዱስ ቤቶች ውስጥ፣ ፈተናዎቻችንን ወደ ውጭ ስንተው፣ ነገር ግን በፀሎታችን እና በሚያሳስቡን ነገሮች ስንገባ፣ የዘላለምን እውነቶች ተምረናል።

ከአንድ አመት በፊት፣ ፕሬዘደንት ኔልሰን ይህን አስገራሚ ቃል ኪዳን ሰጥተውናል፥ “ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ይህ ቃል ኪዳኔ ነው። ሁኔታችሁ በሚፈቅድላችሁ መጠን በቤተመቅደሥ አዘወትራችሁ የማምለክን ያህል በበለጠ ሁኔታ የብረቱን በትር አጥብቃችሁ ለመያዝ የሚረዳችሁ ምንም ነገር የለም። የዓለም የጨለማ ጭጋግ ሲያጋጥማችሁ የበለጠ የሚጠብቃችሁ ምንም ነገር የለም። የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን እና የእርሱን የኃጢያት ክፍያ ምሥክርነት የበለጠ የሚያጠናክርላችሁ ወይም የእግዚአብሔርን ድንቅ ዕቅድ የበለጠ እንድትገነዘቡ የሚረዳችሁ ምንም ነገር የለም። በህመም ጊዜ የበለጠ መንፈሣዊ ማፅናኛን የሚሠጥ ምንም ነገር የለም። ሠማያትን ይበልጥ የሚከፍት ምንም ነገር የለም። ምንም!”

እያንዳንዱ አጠቃላይ ጉባኤ ተጨማሪ በረከቶችን ያመጣል። በመጪው ሚያዝያ ወር፣ እንደገና፣ የጌታን ድምፅ ለመስማት በአጠቃላይ ጉባኤ እንገናኛለን። ወደ አጠቃላይ ጉባኤ የምንመጣው በጸሎት እና በመዘጋጀት ነው። ለእያንዳንዳችን አጣዳፊ የሆኑ ጭንቀቶችና ከልብ የመነጨ ጥያቄዎች አሉ። የመጣነው በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት ለማደስ እና ፈተናዎችን ለመቋቋም ችሎታችንን ለማጠናከር ነው። እኛ የመጣነው ከላይ ለመማር ነው። ለአጠቃላይ ጉባኤ ስብሰባዎች ስትዘጋጁ እና በጸሎት ስትመጡ፣ ለሚያሳስቧችሁ መልስ እንደሚሰማችሁ ቃል እገባላችኋለሁ፣ እናም “የሰማይ እጅ” በእናንተ ላይ እንዳለ ታውቃላችሁ።

አባታችን ለእናንተ እቅድ እንዳለው እምነት ይኑራችሁ። እሱ ነው! በእርሱ እና በተወደደው ልጁ ላይ ያላችሁ እምነት መጋረጃውን እንድትለዩ እና የአባታችሁን ድምፅ እንድትቀበሉ ይርዳችሁ። እርሱ እንዳለ እና ከቃላት በላይ እንደሚወዳችሁ እመሰክራለሁ።

ማስታወሻዎች

  1. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “በጠዋት ደስታ መጣ፣” ኤንዛይን፣ ህዳር 1986 (እ.አ.አ)፣ 68።

  2. ጄምስ ኢ ፋውስት፣, “የመንፈስ ድምጽ’’ (የብሪገም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የአምልኮ አድራሻ, መስከረም፣ 5, 1993(እ.አ.አ)), 2,3 speeches.byu.edu።

  3. ቦይድ ኬ. ፓከር፣ “ ፟ ጸሎቶችና መልሶች፣” ኤንዛይን፣ ህዳር 1979፣19፤

  4. ራስል ኤም. ኔልሰን, “[የእስራኤል ተስፋ]” [የአለም አቀፍ የወጣቶች መንፈሳዊ ስብሰባ]፣ ሰኔ 3፣ 2018 (እ.አ.አ)]፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት።

  5. ጄምስ ኢ ፋውስት፣ “የመንፈስ ድምጽ” 4።

  6. ሮበር ዲ.ሄልስ፣ “ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ኃይል ለመዳናችን፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2006 (እ.አ.አ)፣ 26-27።

  7. [ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “በክህነት ቁልፎች ስጦታ ደስ ይበላችሁ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2024 (እ.አ.አ)]፣ 122።

  8. በኔይል ኤል. አንዴርሰን፣ “የጌታ ድምፅ፣” ሊያሆና፣ ህዳር፣ 2017(እ.አ.አ)፣ 126።