2025
“እፈውሳቸዋለው”
የካቲት 2025 (እ.አ.አ)


“እፈውሳቸዋለው” ሊያሆና፣ የካቲት 2025 (እ.አ.አ)

ወርሐዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ የካቲት 2025 (እ.አ.አ)

እፈውሳ ቸዋለው

ሽማግሌ ኡክዶርፍ እንዳስተማሩት የአዳኝ የመፈወስ አገልግሎት በትንሳኤ ለእያንዳንዳችን ስለሚመጣው ዘላቂ አካላዊና ስሜታዊ ፈውስ መለኮታዊ ማሳያ እና ቃል ኪዳን ነው።

ኢየሱስ አንዲትን ሴት ሲያጽናና የሚያሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንቀሳቃሽ ምስል

የአየር መንገድ ካፒቴን በመሆን ካደረግኳቸው ረዥም በረራዎች አንዳንዶቹን እስካሁን ድረስ በደንብ አስታውሳቸዋለሁ።

ከእነዚያም መካከል በአንዱ ከጀርመን 11:00 ረፋድ ላይ ተነስቼ በተመሳሳይ ቀን ከሠዓት በኋላ 1:00 ሠዓት ላይ ካሊፎርኒያ አርፌ ነበር። የአካባቢው የመነሻ እና የመድረሻ ሰዓት ሲነጻጸር፣ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ ሰሜን አሜሪካ አህጉር የሚደረግ በረራ የሚፈጀው ጊዜ ሁለት ሰዓት ይመስላል። ቦይንግ 747 ፈጣን ነበር፣ ነገር ግን ያን ያህል የሚፈጥን አይደለም! እንደ እውነቱ ከሆነ ፣ እንደ ንፋሱ ጸባይ የ 5,600 ማይልስ (9,00 0 ኪሎ ሜትር) ርቀት ለመጓዝ 11 ሰዓት ያህል ይወስድብናል።

ወደ ምዕራብ በኩል እየበረርን ስለነበር በበረራችን ጊዜ ፀሐይዋ አልጠለቀችም ነበር። ከጀርመን አንስቶ እስከ ካሊፎርኒያ የነበረው የቀን ብርሃን አስደስቶናል።

የጸሃይ መጥለቅ ከደመናዎች በላይ

ይሁን እንጂ ወደ ጀርመን መመለስ ፈጽሞ የተለየ ታሪክ ነበር። ገና በቀትር ስንነሳም እንኳ፣ ወደ ምሥራቅም በምንበርበት ጊዜ ከወትሮው በበለጠ ፍጥነት ጀምበር ታዘቀዝቅ ነበር፤ ሳናውቀውም በፍጥነት ምሽት ይሆንብን ነበር።

በእነዚህ ረጅም በረራዎች ውስጥ የዚህን ምድር ውበት እና የእግዚአብሔርን የፍጥረት ስርዓት ሳሰላስል ነፍሴ ብዙ ጊዜ በአክብሮታዊ ፍርሃት ትሞላ ነበር። በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እየበረርኩም እንኳን ጉዟችን ከመጠናቀቁ በፊት ፀሐይ ዳግመኛ እንደምትወጣ፣ ደማቅ ብርሃን ዳግም እንደሚመለስና ለአዲስ ቀን ሙቀትን እና ሕይወት እንደሚያመጣልን በእርግጠኝነት አውቅ ነበር። የበረርኩበት ሁኔታ ፀሐይ የምትጠልቅበትን ጊዜ ይበልጥ በዝግታ ወይም በፍጥነት የሆነ አስመስሎት ይሆናል፤ ሆኖም ግን ፀሐይ እንዳለች፣ የጸናች እንዲሁም በሰማይ ላይም በአስተማማኝ ሁኔታ እንደነበረች አውቅ ነበር።

ጨረቃ ከደመናዎች በላይ

ስለ እግዚአብሔርም የሚሰማኝ ተመሳሳይ ነው። እግዚአብሔር ለፍጥረታቱ ሁሉ ስላለው ጥበብ እና አላማ በጥልቀት ስላረጋገጥኩኝ፣ ስለ ሟች ህይወታችን ሳስብ የሚያስደስት ተስፋ እና ዘላቂ ሰላም ሊሰማኝ ይችላል። የእግዚአብሄር ልጆች ነን። እርሱ ይወደናል። ሁኔታችንን ያውቃል። እርሱ ለመርዳት ዝግጁ ነው። ምንም እንኳ በአጠገባችን ያሉ ነገሮች ያልሰከኑ እና የማይገመቱ ቢሆኑም እነዚህ እውነቶች የማይቀየሩ ናቸው።

ሁላችንም የተስፋ መቁረጥ፣ የሃዘን እና ሰላማችንን የሚረብሹ እርግጠኛ የአለመሆን ስሜቶች ይሰሙናል። አስተማማኝ እንዲሁም የእውነት እና የብርሃን ምንጭ ለሆነው እንዴት አመስጋኝ ነኝ ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6-11ተመልከቱ)። ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ብርሃንና ህይወት ነው። በእርሱ እና በእርሱ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት ምክንያት የወደፊት ተስፋ፣ በጉዟችን ያሉትን የተስፋ መቁረጥ ቀናት ብሩህ ለማድረግ መለኮታዊ ብርሃን እንዲሁም በሃጢያት እና በሞት ላይ የመጨረሻ ድል እንደምንቀዳጅ ቃል ኪዳን አለን።

“እርሱ አለምን ወደደ”

በምድር ላይ ፍጹም ሆኖ ሊመላለስ የቻለው ሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነበር። በነበረው ፍጹም የሆነ ህይወት የተነሳ፣ ፍትህ በእርሱ ላይ እዳ አልነበራትም። ለእኛ ባለው ፍቅር ምክንያት፣ ለእያንዳንዳችን በግል እና ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች አለሟችነትን እና የዘለአለማዊ ህይወት በርን ለመክፈት ህይወቱን ሰጥቷል።

ሰይጣን እንድናምንለት የሚፈልገው ነገር ቢኖረውም እንኳ፣ ማናችንም ከአዳኙ የማዳን ችሎታ በላይ አይደለንም። ማናችንም ከይቅርታው ጸጋ የተወገድን አይደለንም። ማናችንም ብንሆን፣ “በእርሱ በዘለዓለማዊው ፍቅር ክንዶች ከመከበብ” ውጭ አይደለንም(2ኔፊ 1፡15

ይህ ከሁሉም የሚበልጠው ሥጦታ የሚመጣው ከኢየሱስ ክርስቶስ የማስቻል እና የማዳን ኃይል ካለው ከሀጢያት ክፍያው ነው። አዳኙ በጌቴሴማኒ እና በጎልጎታ ባሣለፈው ስቃይ ምክንያት፣ እኛን እንዴት እንደሚያድነን እና በማናቸውም ድክመቶቻችን ሁሉ እንዴት እንደሚረዳን ያውቃል ( አልማ 7፡12ይመልከቱ)

“እርሱ ለዓለም ጥቅም ካልልሆነ በስተቀር ማንኛውንም አያደርግም፤ ምክንያቱም ሰዎችን ሁሉ ወደ እርሱ ይስብ ዘንድም ሕይወቱን አሳልፎ እስከመስጠት አአለምን ይወዳል” (2 ኔፊ 26፥24)።

ኢየሱስ ክርስቶስ ጉልበታችን ነው።

እርሱ የእርዳታ እጆቹን ይዘረጋል።

እርሱ ያድሳል።

እርሱ ያድናል።

አዳኙ ለሁሉም የሰው ልጆች [የሃጢያት ክፍያውን በሰጠ ጊዜ] እርሱን ለሚከተሉት የመፈወስ፣ የማጠንከር እና የቤዛነት ሃይሉን ማግኘት እንዲችሉ መንገዱን ከፍቷል።

እንደ ጸሃይ ያለው ያ ሀይል ሁልጊዜ በዚያ አለ። መቼም አይዝልም። የአዳኙን ፈለግ የመከተል ምርጫ፣ የእግዚአብሔርን የብርሀን፣ የደግነት እና የፍቅር በረከቶች መቀበል የምንችልበት ከጥላ ወጥቶ ወደ ፀሀይ ብርሃን እንደመራመድ ነው። አንድ ቀን፣ እኛን ከፍ ለማድረግ እና ለማጠንከር የሚጥረውን ኢየሱስ ክርስቶስን እና የእርሱን መለኮታዊ ፍቅር ለመተማመን ዘላለማዊ ውሳኔ መወሰናችንን ወደኋላ ተመልሰን እንደምንመለከት እና በምስጋና እንደምንሞላ አውቃለሁ።

“ወደ እኔ ተመለሱ”

መፅሐፈ ሞርሞን የአዳኙን ስቅለት ተከትሎ በጣም ታላቅ በሆነ ጨለማ ውስጥ ሶስት ቀናትን ስላሳለፉ ሰዎች ይናገራል። በዙሪያቸው የነበረው አካላዊ ጭለማ በኃጢአታችን ምክንያት ሁላችንንም የሚያጋጥሙንን መንፈሳዊ ጨለማዎች ያመላክታል። ከዚያም ህዝቡ የክርስቶስ ድምፅ ከጨለማ ወደ እርሡ ብርሀን እንዲመጡ ሲጋብዛቸው ሰሙ።

“እፈውሳችሁ ዘንድ ንስሃ ገብታችሁ እናም ተለውጣችሁ አሁን ወደ እኔ አትመለሱምን? (3 ኔፊ 9፥13)።

“ለእኔም መስዋእት የተሰበረ ልብና የተዋረደ መንፈስ ታቀርባላችሁ” (3 ኔፊ 9፥20)።

“ንስሐ ግቡ ፣ በሙሉ ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ”(3 Nephi 10:6)።

ተስፋ ስንቆርጥ አዳኙ እነዚያን ተመሳሳይ ግብዣዎች ዛሬ ለእኛ ያቀርብልናል። እያንዳንዱ የፀሐይ መውጣት የአዲስ ቀን መጀመሪያ እንደሚያመለክት ሁሉ፣ ንስሐ በገባን ቁጥር፣ አዲስ ጅምር ፣ ብሩህ አዲስ ጅማሮን እንቀበላለን።

ነገር ግን ይህ ቀላል ይሆናል ማለት አይደለም። ንስሐ ማለት ለውጥ ነው፣ እናም ለውጥም ደግሞ በፍጥነት አይመጣም። አስደሳች ቢሆንም፣ ንሰሃ “እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ የሆነ ሃዘንን” ያካትታል (2ቆሮንቶስ 7፡10) ኃጢአታችንን አምነን መቀበላችንንና ኃጢአታችንን መናዘዝን እንዲሁም ከእግዚአብሄር ይቅርታን መጠየቃችንንና ጉዳት ያደረስንባቸውን ሰዎች ይቅር ማለትን ይጠይቃል። ከሁሉም በላይ፣ “ሁልጊዜም መልካምን ለማድረግ እንጂ ከዚህ በኋላ ክፉ ለማድረግ ዝንባሌ እንዳይኖረን ፣ በልባችን ውስጥ ታላቅ ለውጥ” ለማግኘት “ሁሉን የሚገዛውን የጌታን መንፈስ” መሻትን ይጠይቃል (ሞዛያ 5፡2)።

ያ አይነት ለውጥ ረጅም ጉዞ ነው ፣ ነገር ግን የመጀመሪያውን እርምጃ እንደወሰዳችሁ፣ “የመዳናችሁ ቀን” ይጀመራል፣ እናም “ታላቁ የመዳን እቅድ ወዲያውኑ ወደ እናንተ ይመጣል።”አልማ 34፡31

ከልባችን በሆነው ንስሃ አማካኝነት ይቅር እንደሚለንና ሃጢያታችንን ዳግም እንደማያስታውስ እግዚአብሄር ቃል ገብቶልናል። ኃጢአታችንን መርሳት ሲቸግረን፣ ጌታ ሌሎችን እና እራሳችንን ይቅር ለማለት በሰጠው ተስፋ ላይ እምነት ለመጣል እንጣር።

ፕሬዚዳንት ቦይድ ኬ. ፓከር (1924-2015) (እ.አ.አ) “ስሕተት እና ኃጢአት ስንሠራ መንፈሳችን ይጎዳል” ብለው አስተምረዋል ። ነገር ግን እንደ ሟች አካላችን ሁኔታ ሳይሆን፣ የንስሐው ሂደት ሲጠናቀቅ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምክንያት ምንም ጠባሳ አይኖርም።

ኢየሱስ አይነ ስውርን ሲፈውስ የሚያሳይ ስእል

አይነ ስውር ሰው ሲፈወስ፣ በካርል ሄንሪክ ብሎች

“ወደዚህ ስፍራ አምጧቸው”

አዳኙ ዋና ፈዋሽ ነው። ከመፈወስ ሀይሉ በጣም ውብ ከሆኑት ማሳያዎች አንዱ፣ በጥንቷ አሜሪካ ራሱ ስለሠጠው የአገልግሎት ታሪኩ በሚያወሣው በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ይገኛል፥

“ከእናንተ መካከል በሽተኞች አሉን?” ብሎ ጠየቀ። “ወደዚህ ስፍራ አምጧቸው። ከእናንተ መካከል ድውይ ወይንም ዕውር ወይም ሽባ ወይም ለምጻም፣ ወይንም ሠውነታቸው የሠለለ፥ ወይም ደንቆሮ ወይም በተመሣሣይ የሚሠቃዩ አሉን? ወደ እዚህ ስፍራ አምጧቸው እናም ለእናንተ ርህራሄ ስላለኝ እፈውሳቸዋለሁ፤ ውስጤም በምህረት ተሞልቷል።…

እናም እንዲህ ሆነ ይህንን በተናገረ ጊዜ፣ ህዝቡ በሙሉ በአንድ ልብ ከበሽተኞቻቸው፣ እንዲሁም ከሚሰቃዩትና፣ ከሽባዎቹ፣ እናም ከዐይነ ስውሮቹና፣ ከዲዳዎቹና፣ በሁሉም ዐይነት በሽታ ከሚሰቃዩ ሰዎች ጋር ሄዱ፤ እናም ወደ እርሱም በቀረቡ ጊዜ እያንዳንዳቸውን ፈወሳቸው።(3ኔፊ 17፡ 7,9 )።

አዳኙ ከትንሳኤው በፊትም ሆነ በኋላ “በማንኛውም ሁኔታ የተጎሳቆለ” ማንንም ሰው በፈወሰ ጊዜ፣ ነፍሳችንንም ለመፈወስ ስላለው የመጨረሻ ሀይሉ ምስክር ነበር። እያንዳንዱ ተአምራዊ ፈውሶች “የጌታ ፍጹም የመፈወስ እርምጃ” በሆነው በትንሳኤው አማካኝነት ለእያንዳንዳችን ስለሚመጣው ዘላቂ የሆነ አካላዊና ስሜታዊ ፈውስ የተሰጠ ማሣያ እና ተስፋ ነበር።

እውነት ነው፣ በዚህ ሕይወት ለመፈወስ የምናቀርባቸው ጸሎቶች ሁልጊዜ ተስፋ ባደረግነው መንገድ ምላሽ አያገኙም፤ ነገር ግን በፍጹም ችላ አይባሉም። የጨለማው ምሽት —በትክክለኛው ጊዜ— አስደናቂ ለሆነው የጸሃይ ብርሃን ሥፍራውን እንደሚለቅ ሁሉ የፈውስ ቀንም እንዲሁ ይመጣል።

ፕሬዚዳንት ኔልሰን፥ “እምነታችን ምስጋና የማይቸረው አይደለም”ብለው መስክረዋል። የሰማይ አባታችን አጠቃላይ አመለካከት ከእኛ አመለካከት እጅግ የላቀ እንደሆነ አውቃለሁ። እኛ የምናውቀው ስለስጋዊ ችግሮቻችንን እና ህመማችን ሲሆን፣ እርሱ ስለማይሞተው እድገታችን እና አቅማችን ያውቃል። ፈቃዱን ለማወቅ ከጸለይን እና በትእግስት እና በድፍረት ራሳችንን ለእርሱ ካስገዛን፣ ሰማያዊ ፈውስ በራሱ መንገድ እና ጊዜ ሊከናወን ይችላል።”

በቅርቡ እኔና ባለቤቴ ሃሪየት፣ ስለምንወዳቸው ሰዎች ያለንን ልዩ ተስፋን እና ተማፅኖ በጸሎታችን ውስጥ አካተናል። የጤና ጥበቃ ቡድናቸው ሕመማቸውን የመፈወስ ልዩ ችሎታ እንዲሰጣቸው እንጸልይ ነበር። ምንም እንኳን አፋጣኝ ፈውስ ወይም ማገገም ባይከሰት እንኳን የአዳኙ የመፈወስ ሀይል መጽናናትን እና ሰላምን ሊያመጣላቸው እንደሚችል በማሰብ በማከላችን ተደንቀናል። የአዳኙ ፈዋሽ የቤዛነት ውጤት ሀይል በምድር ከምናገኘው ፈውስ በላይ በስሜታዊ፣ በመንፈሳዊ እና በአካላዊ ጤንነታችን ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል። ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ እና በዘላለማዊው ህይወት ፈዋሽ ነው።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ውድ ጓደኞቼ፣ የአዳኛችን ምህረት ቁስላችሁን ለመፈወስ፣ ከሀጢያት ለማንፃት፣ በሚመጡት ፈተናዎች ለማጠንከር እንዲሁም በተስፋ፣ በጥበብ እና በሰላም ሊባርካችሁ በቂ እንደሆነ እመሰክራለሁ። ለጊዜው ከእርሱ ፍቅር፣ ብርሃን እና ደግነት የራቅን ሆኖ ቢሰማንም እንኳ የእርሱ ሃይል ሁልጊዜ እዚህ አለ— ቋሚ እና የሚታመንም ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ላደረገልን ነገር ሁሉ የአድናቆትና ጥልቅ የሆነ የምስጋና ስሜታችንን እንዳናጣ እፀልያለሁ። እባካችሁ ሙሉ በሙሉ እንደምትወደዱ እወቁ፤ እንዲሁም ለዘላለም ቃል የተገባላችሁን አስታውሱ።

“በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደስታ አማካኝነት ሸክማችሁ ቀላል እንዲሆንላችሁ እግዚአብሔር ይፍቀድላችሁ።(አልማ 33፡23)

ማስታወሻዎች

  1. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “የመንፈሳዊ ፍጥነት ሃይል፣,” ሊያሆና፣፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ) 100።

  2. ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “አሁን ማድረግ ትችላላችሁ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 57 ተመልከቱ።

  3. ቦይድ ኬ ፓከር፣ “የደስታ እቅድ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 28።

  4. ረስል ኤም ኔልሰን “Jesus Christ—the Master Healer,” ሊያሆና፣ ህዳር2005 (እ.አ.አ)፣ 87።

  5. ረስል ኤም ኔልሰን “Jesus Christ—the Master Healer,” 86።