2013 (እ.አ.አ)
ለማዳን ያለን ሃላፊነት
ኦክተውበር 2013


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ጥቅምት 2013 (እ.ኤ.አ)

ለማዳን ያለን ሀላፊነት

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን

ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ከቤተክርስቲያን ተሳትፎዎች የጠፉትን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን የማዳን አስፈላጊነት ዘለአለማዊ ጥቅም አለው። አንድ ጊዜ ወንጌልን የተቀበሉ ሰዎችን እናውቃለን? ካወቅን፣ እነሱን ለማዳን የኛ ሃላፊነት ምንድን ነው?

ያረጁት፣ ባል አልባ የሆኑ እና ህሙማንን ከጠፉት ውስጥ አስቡ። ሁሌ በየጊዜው ብቸኝነት በሚባለው የደረቀ እና ዱራማ ምድረ በዳ ውስጥ ይገኛሉ። ወጣትነት ሲለይ፣ ጤና ሲወድቅ፣ ብርታት ሲደክም ፣ የተስፋ ብርሃን በመድከም ሲጠፋ ፣ በሚረዱ እጆች እና ርህራሄን በሚያውቅ ልብ ሊረዱ እና ሊደገፉ ይችላሉ።

በእርግጥም፣ ሌሎች እርዳታ የሚያስፈልጋቸው አሉ። ጥቂቶች ከሀጢያት ጋር ሲታገሉ ሌሎች ደግሞ በፍርሀት ወይም በሀዘን ወይም ባለማወቅ ውስጥ ይንከራተታሉ። በማንኛውም ምክንያት ይሁን፣ ከቤተክርስቲያን ተሳታፊነት እራሳቸውን ነጥለዋል። እናም በእኛ— በተሳታፊ የቤተክርስቲያን አባላት—ውስጥ የመርዳት እና የማዳን ፍላጎት ካልተነሳ በስተቀር እነርሱ በእርግጠኝነት ጠፍተው ይቀራሉ።

መንገዱን የሚያሳይ ሰው

ከጥቂት ጊዜ በፊት ከቤተክርስቲያን በራቀ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ደርሶኝ ነበር። ይህም በጣም ብዙ የሆኑ አባላቶቻችን ምሳሌ ነው። እንዴት ከተሳትፎ እንደራቀ ካብራራ በኋላ፣ እንዲህ ብሎ ጻፈ፡

“በጣም ብዙ ነበረኝ እና አሁን ትንሽ አለኝ። ደስተኛ አይደለሁም እናም በሁሉም ነገር እንደወደኩ አይነት ይሰማኛል። ከህይወቴ ቢለይም እንኳን፣ ወንጌል በፍጹም ከልቤ አልወጣም። ጸሎትዎን እጠይቃለሁ።

“እባካሆ እኛ ውጪ ጠፍተን ያለነውን የኋለኛው ቀን ቅዱሳንን አትርሱ። ቤተክርስቲያኗ የት እንዳለች አውቃለሁ፣ ግን አንዳንዴ መንገዱን የሚያሳየኝ፣ የሚያበረታታኝ፣ ፍርሀቴን የሚያስወግድ፣ እና ምስክርነት ለእኔ የሚያካፍል ሰው እነደሚያስፈልገኝ አስባልሁ።”

ይህን ደብዳቤ እያነበብኩ እያልሁ፣ በለንደን፣ እንግሊዝ ውስጥ ያለ በአለም ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ማእከል ቪክቶሪያ እና አልበርት ሙዝየም በትውስታዬ መጣ። እዚያ፣ በድንቅ ሁኔታ ፍሬም የተደረገ፣ በ1831 በጆሴፍ ማሎርድ ዊልያም ተርነር የተሳለ የጥበብ ውቴት አለ። ስእሉ ጫን ያለ ከባድ ጠቁር ዳመና እና ፍርሃትና ሞትን የሚያመለክት ያልተረጋጋ ንዴታማ ባህርን ያሳያል። ለመጓዝ የማይችል መርከብ ብርሀንም ከሩቅ ይታያል። ከበስተ ፊቱ ላይ፣ በመጪው አረፋማ ውሃ በሀይል የሚገፋ ትልቅ የአደጋ ማምለጫ ጀልባ አለ። የአደጋ ማምለጫው ጀልባ ወደ ነውጡ ሲጠጋ ሰዎች ከበስተጫፍ ላይ በጽኑ ይስባሉ። በባህሩ ዳር ላይ በዝናብ እና በንፋስ ተረጭተው የረጠቡ ሚስት እና ሁለት ልጆች ቆመዋል። በጉጉት ወደ ባህሩ ይመለከታሉ። በአይምሮዬ የስእሉን ስም በምህጻረ ቃል አደረኩት። ይህም ለእኔ ለማዳን የሚል ሆነ።

በህይወት ማእበል መካከል፣ አደጋ ያንጃብባል። ወንዶች እና ሴቶች፣ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች እራሳቸውን ሲጠመዱ እና አሳሳች ነገር ሲያጋጥማቸው ያገኛሉ። የቤትን እና የቤተሰብን ምቾትን ወደኋላ በመተው፣ እና ወደ ማዳን በመሄድ፣ የአደጋ ማምለጫ ጀልባውን ማን ይመራል?

የእኛ የስራ ድርሻ የማይቻል አይደለም። እኛ በጌታ ተግባር ላይ ነን፤ ከእርሱ እርዳታ የማግኘት መብት አለን።

በጌታ የአገልግሎት ጊዜ፣ በጋሊሌ የነበሩ አሳ አጥማጆችን መረባቸውን ትተው እንዲከተሉት “የሰዎች አጥማጅ አደርጋችኋለሁ” ብሎ በማወጅም ጠራቸው። የተቻለንን እርዳታ እናቀርብ ዘንድ፣ ወንዶችን እና ሴቶችን የማጥመድ ደረጃን እንቀላቀል።

የተሳታፊነትን ደህንነት የተለዩት ወደ ጌታ ጠረጴዛ መጥተው የእርሱን ቃል እንዲቋደሱ፣ የእርሱን መንፈስ ጓደኝነት እንዲደሰቱበት፣ እና “ ከቅዱሳን ጋር እና በእግዚያብሔር ቤት እንግዶችና መጻተኞች እንዳይሆኑ፣” የእኛ ሀላፊነት እነርሱን ለማዳን መሞከር ነው።

የፍቅር መሰረተ ሀሳብ

ወደ ተሳትፎ ለመመለስ እና ለአመለካከት፣ ልምድ፣ እና ድርጊት ለውጥ ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች በአብዛኛው እንዳሉ አግኝቻለሁ። አንደኛ፣ አንድ ሰው የዘላለማዊ ችሎታቸውን ሲያሳያቸው እና እነሱን ለማሳካት እንዲወስኑ በመርዳቱ ምክንያት ግለሰቦች ይመለሳሉ። ለምሻሻል የሚችሉበት በቅርብ እንዳለ ሲመለከቱ፣ ተሳታፊ ያልሆኑት በድክመታቸው በቀጣይነት በደስታ አይቆዩም።

ሁለተኛ፣ የሌሎች መመለስ ምክንያት የሚያፈቅሯቸው ወይም “ከቅዱሳን ጋር ነዋሪ ዜጎች” የአዳኝን ተግሳጽ በመከተላቸው፣ ጎረቤቶቻቸውን እንደራሳቸው በመውደዳቸው፣ እና ሌሎችን ህልማቸው እውን ወደመሆን እንዲመጣ እና ውጥናቸው እንዲታወቅ በመርዳታቸው ነው።

የዚህ ሂድት አቀጣጣይ የሆነው—እናም በመሆንም የሚቀጥለው—የፍቅር መሰረተ ሀሳብ ነበር።

በጣም እውን በሆነ መልኩ፣ በተርነር ስዕል ላይ በባህር ማእበል ወጀብ ውስጥ የተጠመዱት ሰዎች እንደ አብዛኞቹ የአደጋ ማምለጫ ጀልባን ከሚመራው መዳንን እንደሚጠብቁት ከተሳትፎ የደከሙ አባላት ናችው። ልቦቻቸው እርዳታ ይሻሉ። እናቶች እና አባቶች ለወንዶች እና ሴቶች ልጆቻቸው ይጸልያሉ። ባሎቻቸው ይደረስላቸው ዘንድ ሚስቶች ሰማይን ይማጸናሉ። አንዳንዴ ልጆች ለወላጆቻቸው ይጸልያሉ።

ከእኛ ጋር ሙሉ ተሳትፎ የሚያበረክተውን እንዲካፈሉ፣ በተሳትፎ የደከሙትን ለማዳን እና ወደ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ደስታ መልሶ ለማምጣት ፍላጎት ይኖረን ዘንድ ጸሎቴ ነው።

ከበውን ያሉ የጠፉትን፥ ያረጁትን፣ እመበለቶችን፣ ህሙማን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ደካማ ተሳትፎ ያላቸውን፣ እና ትእዛዛትን የማይጠብቁትን ለማዳን እንሞክር። የሚረዳ እጅ እና ርህራሄን የሚያውቅ ልብ እንዘርጋላቸው። እንደዚህ በማድረግ፣ ወደ ልባቸው ደስታ እናመጣለን፣ እና ሌላውን በዘለአለማዊ ህይወት መንገድ ላይ ስንረዳ የሚመጣውን ጥልቅ እርካታም እናገኛለን።

ማስታወሻዎች

  1. የስዕሉ ሙሉ አርእስትየህይወት ጀልባ እና የሀዘን ምልክት (ሰማዊ ብርሃን) በመስራት ከተጨቆነው ጀልባ ሰው በመሳሪያ ሲወጣ የሚል ነው።

  2. ማቴዎስ 4፥19

  3. ኤፌሶን 2፡19

  4. ማቴዎስ 22፥39

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

የምትጎበኟቸውን ሰዎች ቤተክርስቲያን ለመካፈል በመታገል ላይ የነበረ ሰው የሚያውቁ እነደሆነ ለመጠየቅ አስቡ። አንድ ሰው መምረጥ እና የቤተሰብ የቤት ምሽት እንዲካፈል ወይም እንድትካፈል እና ለምግብ እንዲመጡ በመጋበዝ ፍቅር ስለማሳየት የምትችሉበትን መንገድ ለመወያየት ትችላላችሁ።