ወጣቶች
የጄን ስጦታ
ደራሲዋ በዩታ፣ ዩኤስኤ ነው የምትኖረው።
በቀዳሚው የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት አመት ተከታታይ ትክክል ያልሆኑ ምርጫዎችን አድርጌ ነበር። እነዚያ ምርጭዎች ወደ አደገኛ ውጤቶች እና ደስተኛ ያለመሆን አመሩ፣ እና የበጋውን እረፍት ለውጥ ማምጣት ለመጀመር ለመጠቀም ወሰንኩ። ትምህርት ደግሞ ሲጀምር፣ እንኳን ድህና ምጣሽ ብሎ ለመቀበል የሚጠብቀኝን መጥፎ ግንኙነት ለማሰወገድ የመጸዳጃ ክፍል ወይም ባዶ ቦታዎች ላይ ምሳዬን በላሁ።
መቼም እንደዚህ ብቸኝነት ተሰምቶኝ አያውቅም።
ከዚያ እግዚያብሔር ስጦታ ሰጠኝ፡ ጄንን ላከልኝ። በፍጹም በጥፋቶቼ አልፈረደችብኝም ግን በዚያ ምትክ በትክክለኛው አቅጣጫ መንቀሳቀሴን እንድቀጥል አበረታታችኝ። እርሷ በትምህርት ቤት እንደምትገኝ ማወቄ ቅዱሳን መጻህፍቴን ማንበብ እንድቀጥል እና ምስክርነቴን እንድንከባከብ ረዳኝ። የምርቃት ጊዜ ሲመጣ፣ ለመለወጥ መወሰኔን ለራሴ አረጋግጬ ነበር።
ጄን ለእኔ ባትደርስልኝ ኖሮ ዛሬ የት ልሆን እንደምችል አንዳነዴ ይገርመኛል። ያለ እሷ በመርሆቼ ልዘልቅ እችል ነበር? በእድለኝነት፣ በፍጹም አላውቅም ምክንያቱም እሷ እኔን ልትረዳ ዝግጁ እና ፍቃደኛ ሆና እዚያ ከነ ሙሉ ልቧ ነበረች፣ ።