2020–2024
በክርስቶስ ደስታ መዋጥ
የሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:35

በክርስቶስ ደስታ መዋጥ

የሰማይ አባታችን እንባ የተሞላ ልመናችንን እንደሚሰማ እና ሁልጊዜ በፍጹም ጥበቡ መልስ እንደሚሰጥ እመሰክራለሁ።

እንወድሃለን፣ ሽማግሌ ኪረን። የአነጋገር ዘዬህን ለ10 ደቂቃ ልዋሰው?

የሚናፈቁ ተአምራት

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ዓይነ ስውሩ በርጤሜዎስ ተአምራትን በመፈለግ ወደ ክርስቶስ እንዳለቀሰ እንማራለን። “ኢየሱስም፣ ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው። ወዲያውም አየ።”

በሌላ ጊዜ ደግሞ ቤተሳይዳ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው ፈውስ ለማግኘት ይናፍቅ ነበር። በአንጻሩ ይህ ተዓምር በቅጽበት አልመጣም። ይልቁንም፣ ”አጥርቶ ከማየቱ” በፊት ኢየሱስ ሁለት ጊዜ ባርኮታል።

በሶስተኛ ምሳሌ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ በመከራው ጊዜ “ሦስት ጊዜ ጌታን [ለምኖት] ነበር”፣ ነገር ግን እስከምናውቀው ድረስ፣ ልባዊ ልመናው አልተመለሠለትም

ሶስት የተለያዩ ሰዎች። ሶስት ልዩ አጋጣሚዎች።

ስለዚህ፣ ጥያቄው፦ ለምንድን ነው አንዳንዶች የናፈቁትን ተዓምራት ቶሎ ሲቀበሉ ሌሎች ጌታን እየጠበቁ በትዕግስት የሚጸኑት? ለምን እንደሆነ ላናውቅ እንችላለን፣ ሆኖም በአመስጋኝነት፣ “[እኛን የሚወደንን]” እና “ለዘለዓለማዊ ደህንነታችን እና ደስታችን ሁሉንም ነገር [የሚያደርገውን] እርሱን እናውቀዋለን።”

መለኮታዊ ዓላማዎች

መጨረሻውን ከመጀመሪያው የሚያየው እግዚአብሔር፣“ጭንቀትህ እና ስቃይህ ለጥቂት ጊዜ ቢሆን ነው” ይህም “ለጥቅምህ”ይቀደሳል በማለት ያረጋጋናል።

በፈተናዎቻችን ተጨማሪ መልሶች ለማግኘት ለመርዳት፣ ሽማግሌ ኦርሰን ኤፍ. ዊትኒ፦ “የትኛውም አይነት የምንሠቃይበት ህመም፣ የትኛውም የሚያጋጥመን ፈተና በከንቱ አይቀርም። እንማርበት ዘንድ ያገለግለናል።… [በትዕግስት] የምንፀናበት ሁሉ …፣ ባህሪያችንን ይገነባል፤ ልባችንን ያጠራል፣ ነፍሳችንን ያሰፋልናል፣ እንዲሁም ይበልጥ ርኅሩኅ እና ለጋሥ እንድንሆን ያደርገናል። … እዚህ ልንማር የመጣነውን ትምህርት የምናገኘው በሐዘንና በስቃይ፣ በድካምና በመከራ ነው፣ ይህም [የሰማይ ወላጆቻችንን] እንድንመስል ያደርገናል” በማለት አስተምረውናል።

ሐዋርያው ጳውሎስ በመከራው ወቅት “የክርስቶስ ኃይል [በእርሱ] ላይ እንደሚያርፍ” በመረዳት በትሕትና፣ “ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና”በማለት ተናግሯል።

የህይወት ፈተና ያነጥረናል። አዳኙ እራሱ “በመከራ [እንዲፈጸም]”፣ “መታዘዝን ተማረ”

አንድ ቀንም በርህራሄ፣ “እነሆ፥ አንጥሬሃለሁ ነገር ግን እንደ ብር አይደለም፤ በመከራም እቶን ፈትኜሃለሁ።”ይለናል።

በእግዚአብሔር መለኮታዊ ዓላማዎች መታመን ለደከሙ ነፍሳት ተስፋን ይተነፍሳል፣ በጭንቀት እና በልብ ህመም ጊዜም ቁርጠኝነትን ያነሳሳል።

መለኮታዊ ዕይታ

ከአመታት በፊት፣ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን፣ ይህን ጠቃሚ ሃሳብ አካፍለው ነበር፥ “ሁሉንም ነገሮች በዘለአለማዊ ዕይታ ስንመለከት፣ ሸክማችንን በእጅጉ ያቀልልናል።”

ሆሊ እና ትሬይ ፖርተር።

እኔና ባለቤቴ ጂል በቅርቡ የ12 ዓመት ልጃቸው ትሬ በአሳዛኝ የእሳት አደጋ ህይወቱ በተቀጠፈ ጊዜ፣ ሆሊ እና ሪክ ፖርተር በተባሉ ታማኝ ሠዎች ህይወት ውስጥ ይህን እውነት አይተን ነበር። ሆሊ ውድ ልጇን ለማዳን ባደረገችው የጀግንነት ሙከራ እጅ እና እግሯ ክፉኛ በእሳት ከተቃጠለ በኋላ፣ በአጥቢያ ቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ፣ ቤተሰቧ ጭንቀት ውስጥ ሳለ ጌታ ስላፈሰሰው ታላቅ ሰላም እና ደስታ እንደ ተአምራዊአስደናቂ እና አስገራሚ የመሳሰሉ ቃላትን በመጠቀም ተናግራለች።

የተጣመሩ የማዳን እጆች

የዚህች ውድ እናት ሊሸከሙት የማይቻል ሀዘን በላቀ ሰላም ተተክቷል፦ “እጆቼ የሚያድኑ እጆች አይደሉም። እነዚያ እጆች የአዳኙ ናቸው! ጠባሳዬን ሣይ ማድረግ ያልቻልኩትን ነገር እንደሚያስታውሰኝ ነገር ከመመልከት ይልቅ፣ በአዳኜ ላይ ያሉትን ጠባሳዎች አስታውሳለሁ።”

የሆሊ ምሥክርነት፣ ነቢያችን “ስለ ሰለስቲያል ስታስቡ፣ ፈተናዎችን እና ተቃውሞዎችን በአዲስ መልኩ ታያላችሁ” ሲሉ የሠጡትን የተሥፋ ቃል ይፈጽማል።

ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን እንዳሉት፣ “እግዚአብሔር በቅድመ ምድራዊ ህይወት የመዳን እቅዱን ባቀረበልን ጊዜ፣ መከራን የማሸነፍ እና የማደግ ጉጉት እንደነበረን አምናለሁ።” የሰማይ አባታችን እንደሚደግፈን በማወቅ፣ አሁን ይህንን ፈተና መወጣት አለብን። ነገር ግን ወደ እርሱ መመለሣችን ወሳኝ ነው። እግዚአብሄር በሌለበት፣ የስቃይ እና የመከራ የጨለማ ተሞክሮዎች ፣ወደ መከፋት፣ ተስፋ መቁረጥ እና ምሬት ይወስዱናል።”

መለኮታዊ መርሆዎች

ያለመርካትን ጨለማ ለማስወገድ እና፣ በምትኩም ታላቅ ሰላምን፣ ተስፋን እንዲሁም በህይወት አስቸጋሪ ፈተናዎች ውስጥም እንኳን ደስታን ለማግኘት የሚያስችሉ ሶስት መለኮታዊ መመሪያዎችን አካፈላለሁ።

አንደኛ—ጠንካራ እምነት የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስን በማስቀደም ነው። “ባሰባችሁት ነገር ሁሉ ወደ እኔ ተመልከቱ፣ አትጠራጠሩ፣ አትፍሩ”ሲል ተናግሯል። ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፦

“የዘለዓለም ህይወታች[ን] [በክርስቶስ] ላይ ባ[ለን] እምነት እና በኃጢያት ክፍያው ላይ የተመሰረተ ነው።”

“በቅርብ በደረሰብኝ ጉዳት ምክንያት በሚሰማኝ ከባድ ህመም ስሠቃይ፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ከመረዳት በላይ ስለሆነው የኃጢያት ክፍያ መሥዋዕቱ ጥልቅ አድናቆት ተሰምቶኛል። አስቡት! አዳኙ ‘በመከራና በሁሉም አይነት ህመምና ፈተናዎች’ ተሰቃይቷል፣ ይህም በችግር ጊዜ እኛን ማፅናናት፣ መፈወስ እና ማዳን ይችል ዘንድ ነው።”

ቀጥለው፦ “ጉዳቴ ደጋግሜ ስለ ‘እስራኤል ቅዱስ ታላቅነት’ እንዳስብ አድርጎኛል። እያገገምኩ በነበረበት ጊዜ፣ ጌታ መለኮታዊ ኃይሉን በሰላማዊ እና በማያጠራጥሩ መንገዶች አሳይቷል።”

“በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፥ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ አለምን አሸንፌዋለሁ”በማለት አዳኛችን ያበረታታል።

ሁለተኛ—ብሩህ የሆነ ተስፋ የሚመጣው የዘለዓለም እጣ ፈንታችንን በአዕምሯችን በማየት ነው። እህት ሊንዳ ሪቭስ “የአባታችንን አስደናቂ የተስፋ በረከቶች ራዕይ… በየቀኑ በዓይኖቻችን ፊት ማቆየት” ያለውን ኃይል ስትናገር፣ “ብዙ ፈተናዎች ያሉብን ለምን እንደሆነ አላውቅም፣ ነገር ግን ሽልማቱ በጣም ትልቅ እንደሆነ በግሌ ይሰማኛል … በጣም አስደሳች እና ከማስተዋል በላይ ከመሆኑ የተነሳ በዚያ የሽልማት ቀን፣ መሐሪ፣ አፍቃሪ አባታችንን፣ ‘የሚፈለገው ያ ብቻ ነበር?’ ልንለው እንችላለን።… በስተመጨረሻ እነዚያ ፈተናዎች በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለዘለዓለም ህይወት ብቁ የሚያደርጉን ከሆነ እዚህ መከራ ቢደርስብን ምን አለበት?”በማለት አስተምረዋል።

ፕሬዚዳንት ኔልሰን ይህን አስተያየት ሰጥተዋል፦ “ጆሴፍ ስሚዝ በሊበርቲ እስር ቤት ውስጥ እፎይታ ለማግኘት ሲለምን ጌታ የሰጠውን ምላሽ አስቡ። እየተፈጸመበት የነበረው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ልምድ እንደሚሰጠው እና ለጥቅሙ እንደሚሆን ጌታ ለነብዩ አስተምሮታል። ‘በደንብ ብትፀና፣ እግዚአብሔርም ወደ ላይ ዘለአለማዊ ክብር ይሰጥሀል’ በማለት ጌታ ቃል ገብቶለታል። ጆሴፍ በጊዜው በነበረው ከባድ ችግር ላይ ከማተኮር ይልቅ ስለ ሰለስቲያል እንዲያስብ እና ዘለዓለማዊ ሽልማትን እንዲያስብ ጌታ እያስተማረው ነበር።”

ይህ የዕይታ ለውጥ፣ ጆሴፍ እንዲህ በማለት ለጓደኛው በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንደሚታየው ጥልቅ ቅድስናን አምጥቶለታል፦ “ለአምስት ወራት በእስር ቤት ግድግዳዎች ውስጥ ከታሰርኩ በኋላ ልቤ ከዚህ በፊት ከነበረው ከምንጊዜውም የበለጠ ርኅሩኅ እንደሚሆን ይታየኛል። … የደረሰብኝን በደል ባይደርስብኝ ኖሮ አሁን እንደዚህ ዓይነት ስሜት አይሰማኝም ነበር።”

ሶስተኛ—ታላቅ ሀይል የሚመጣው በደስታ ላይ በማተኮር ነው። በዘለዓለም ውስጥ እጅግ ወሳኝ፣ አስጨናቂ በነበሩት ሰዓታት፣ አዳኛችን ሳያፈገፍግ መራራውን ጽዋ ጠጥቷል። ይህን ያደረገው እንዴት ነው? “በፊቱ ስላለው ደስታ [ክርስቶስ] በመስቀል ታግሷል፣” ፈቃዱም “በአብ ፈቃድ [ተዋጠ]”የሚለውን እንማራለን።

ክርስቶስ በጌተሰማኒ

ይህ “ተዋጠ” የሚለው አባባል በጥልቅ ያነሳሳኛል። በስፓኒሽ “ተዋጠ” “ተበላ” ተብሎ እንደሚተረጎም ሳውቅ ፍላጎቴ ጨመረ። በጀርመንኛ፣ “ተበላ”፤ በቻይንኛ ደግሞ “ተጠመጠመ” ተብሎ ተተርጉሟል። ስለዚህ፣ በህይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ ከመጠን በላይ ጭንቀት ሲሰማኝ፣ “በክርስቶስ ደስታ ከመዋጥ [ከመበላት፣ ከመጠምጠም] በቀር ምንም አይነት መከራ እንዳንቀበል”ጌታ የገባውን ቃል አስታውሳለሁ።

ምንም እንኳን መራራ ጽዋዎቻችሁ ገና ያልተወገዱ ቢሆኑም “ … ከምድራዊ መረዳት በላይ፣”የሆነውን ይህን ደስታ በብዙዎቻችሁ ላይ አያለሁ። ቃል ኪዳኖቻችሁን ስለጠበቃችሁ እና ለእግዚአብሔር ምስክሮች በመሆን ስለቆማችሁ እናመሰግናለን። “[ዓይን የማያየው ሐዘን ጸጥ ባለው ልባችሁ ውስጥ ተደብቆ ሳለ]”ሁላችንን ለመባረክ ስላደረጋችሁት ጥረት እናመሰግናለን። የአዳኙን እፎይታ ለሌሎች ስታመጡ፣ ፕሬዘደንት ካሚል ጆንሰን እንዳስተማሩት ለራሳችሁ ታገኛላችሁ።

መለኮታዊ ቃል ኪዳኖች

አሁን፣ የሆሊ ፖርተር ቤተሰብ በጌታ ሲታገዝ የነበረውን ተዓምር ወደምንመለከትበት የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ከእኔ ጋር ተመለሱ። ይህን ታማኝ ቤተሰብ እና ውድ ጓደኞቻቸውን ለማጽናናት ምን ልናገር እችላለሁ ብዬ ሳሰላስል፣ “የአዳኙን ቃላት ተጠቀም” የሚል ሃሳብ መጣ። ስለዚህ፣ በዚያ ሰንበት ዕለት እንዳደረግሁት ዛሬም፣ “የቆሰለውን ነፍስ [በሚፈውሱት]” በእርሱ ቃላት እዘጋለሁ

“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።”

“እናም ደግሞ በባርነት በነበራችሁ ጊዜም ቢሆን፣ በጀርባችሁም እንኳን ሊሰማችሁ እንዳይቻላችሁ፣ በትከሻችሁ ላይ ያለውን ሸክም አቃልላችኋለሁ፤ እናም ይህንን የማደርገው ከዚህ በኋላ ለእኔ በምስክርነት እንድትቆሙ ነው፤ እናም እኔ ጌታ እግዚአብሔር በእውነት በመከራቸው ጊዜ ህዝቤን እንደምጎበኝ ታውቁ ዘንድ ነው”

“ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፥ ወደ እናንተ እመጣለሁ።”

የእኔ ምስክርነት

በደስታና ጥልቅ አክብሮት፣ አዳኛችን እንዳለ እና “ቃል ኪዳኖቹ የተረጋገጡ እንደሆኑ” እመሰክራለሁ። በተለይ ለተቸገራችሁ ወይም ደግሞ “በማንኛውም ሁኔታ ለተሰቃያችሁ” የሰማይ አባታችን በእንባ የተሞላ ልመናችሁን እንደሚሰማ እና ሁል ጊዜም በፍጹም ጥበብ ምላሽ እንደሚሰጥ እመሰክራለሁ። በከባድ ችግር ውስጥ በነበርንበት ወቅት ለእኛ ቤተሰብ እንዳደረገው፣ “በክርስቶስ ደስታ ውስጥ ከመዋጥ በስተቀር ምንም ስቃይ እንዳያገኛ[ችሁ]” “[ሸክማችሁ እንዲቀልላችሁ]” “እግዚአብሄር ይፍቀድላችሁ”። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ማርቆስ 10፥52፤ አትኩሮት ተጨምሮበታል።

  2. ማርቆስ 8:25

  3. 2 ቆሮንጦስ 12፥8፤ አትኩሮት ተጨምሮበታል።

  4. መዝሙር 130፥5 ይመልከቱ።

  5. 1 ኔፊ 11፥17

  6. ሄለማን 12፥2፣ በተጨማሪም 2 ኔፊ 26፥24 ይመልከቱ።

  7. አብርሐም 2፥8 ይመልከቱ።

  8. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥7

  9. 2 ኔፊ 2፥2

  10. ኦርሰን ኤፍ. ዊትኒ፣ የቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምቦል (Spencer W. Kimball) አስተምሮት (2006 (እ.አ.አ.))፣ 16።

  11. 2 ቆሮንቶስ 12፥9–10

  12. አብርሐም 3፥25–26 ይመልከቱ

  13. ዕብራውያን 5፥82፥10

  14. 1 ኔፊ 20:10፤ አትኩሮት ተጨምሮበታል።

  15. 2 ኔፊ 4፥19–35 ይመልከቱ።

  16. Personal conversation with Elder Russell M. Nelson, Apr. 2011.

  17. ራስል ኤ. ኔልሰን፣ “ስለ ሰለስቲያል አስቡ!፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ)፣ 118።

  18. ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “The Refining Fire of Afflictions፣” ሊያሆና፣May 2022፣ 7።

  19. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “እግዚአብሔር ያሸንፍ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 94።

  20. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥36

  21. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ስለ ሰለስቲያል አስቡ!፣” 118።

  22. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ስለ ሰለስቲያል አስቡ!፣” 117። ፕሬዘደንት ጄፍሪ አር ሆላንድ እንዳስተማሩት፡- “ስትታገሉ፣ ስትከዱ፣ ሲተፋባችሁ እና ስትባረሩ፣ መፏጫ እና መሳለኪያ ስትሆኑ፣ ያኔ ነው በዚህ አለም ከሚያውቀው ሁሉ በላይ ምርጥ እንዲሁም ንጹህ እና ፍጹም ህይወት ላይ የቆማችሁት። የሕያው እግዚአብሔር ሕያው ልጅ ስለእናንተ ሀዘን እና መከራ ሁሉ ስለሚያውቅ ለመቆም እና ለማመስገን ምክንያት አላችሁ” (“Missionary Work and the Atonement,” Ensign, Mar. 2001, 15).

  23. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ስለ ሰለስቲያል አስቡ!፣” 117፣ ደግሞም አልማ 17፥11–12 ይመልከቱ።

  24. ዮሀንስ 16፥33

  25. 2 ኔፊ 31:20; ኤተር 12:4ሞሮኒ 7:48 ይመልከቱ።

  26. ሊንዳ ኤስ ሪቭስ “Worthy of Our Promised Blessings,” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ) 11.

  27. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ስለ ሰለስቲያል አስቡ!፣” 118።

  28. ጆሴፍ ስሚዝ letter to Presendia Huntington Buell, 15 Mar. 1839, josephsmithpapers.org.

  29. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Joy and Spiritual Survival፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 81–84።

  30. ማርቆስ 14:35–41ይመልከቱ።

  31. ዕብራውያን 12፥2

  32. ሞዛያ 15፥7

  33. አልማ 31:38፤ እንዲሁም መዝሙር 30:5ዮሃነስ 15:10–111 ተሰሎንቄ 1:6፣ ጆሴፍ ስሜዝ ትርጉም, ያቆብ 1:2 (በ ያቆብ 1:2፣ የግርጌ ማስታወሻ )፣ 2 ኔፊ 2:259:18አልማ 26:6–7፣ 11፣ 27፣ 3728:833:2336:20–21ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥76ሙሴ 5:10–11.

  34. አዳኝ እንዳበረከተው ”አዕምሮን ሁሉ የሚያልፍ” [ፊልጵስዮስ 4፥7]፣ ሰላም፣ እሱም የሰውን መገንዘብ እና የምድርን መረዳት የሚቃረን የጋለ፣ ጥልቅ እንዲሁም የሰፋ ደስታን ይሰጣል። ለምሳሌ፣ ልጆቻችሁ ሊዳን በማይቻል ህመም ሲሰቃዩ፣ ወይም ስራችሁን ስታጡ ወይም ባለቤታችሁ ሲከዳችሁ ደስታ የሚሰማ አይመስልም። ሆኖም በእርግጠኝነት አዳኝ የሚሰጠው ደስታ ይሄ ነው። የእርሱ ደስታ የማያቋርጥ ነው፣ ይህም መከራችን ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንደሚሆን [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥7] እና ለጥቅማችን የተቀደሰ መሆኑን ያረጋግጣል (ራስል ኤ. ኔልሰን፣ “ደስታ እና መንፈሳዊ ደህንነት፣” Ensign ወይም Liahona፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 2016)።

  35. ሞዛያ 24፥12አልማ 33፥23 ይመልከቱ። ባለፈው ዓመት እኔና ጂል ከካንሰር ጋር በጣም የምትታገል ቆንጆዋን ጓቲማላያዊት የሆነችውን ፓውላን አገኘናት። እንዴት እንደሚሰማት ለጠየቀኝ ጥያቄ የሰጠችው ምላሽ በአእምሯችን እና በልባችን ውስጥ የማይረሳ ትዝታን ጥሎ ነበር፡- “አመሰግናለሁ” ይህ ትሑት ጎረምሳ በጸጥታ በሹክሹክታ መለሰ፡ “ጌታ የሰጠኝ እንጂ ለእህቴ አይደለም።” ከዚያም ጥሩ ስሜት ባይሰማትም እሷ; እህቷ ሳሪያ; እና አባታቸው ታላቅ የግል ፍላጎቶች እና የራሳቸው ተግዳሮቶች ላሏቸው ሁለት አረጋውያን መበለቶች ሁለት የአገልግሎት ጉብኝት ሄደች።

  36. “Lord, I Would Follow Thee,” መዝሙር፣ ቁ. 220።

  37. Camille N. Johnson, “Jesus Christ Is Relief,” Liahona, May 2023, 81; see also ሉቃስ 23:34, 43; ዮሃነስ 19:26–27። ሽማግሌ ኒል ኤ ማክስዌል ይህን ውብ መልዕክት አካፍለው ነበር፣ “ለጊዜው፣ እኛ ራሳችን በአንድ የተወሰነ መስቀል ላይ ካልተዘረጋን፣ የሌላው ሰው እግር ላይ መሆን አለብን--በርኅራኄ እና በመንፈሳዊ እረፍት ተሞልተን” በሚገባ ጽኑኢንዛይን፣ ግንቦት 1990

  38. አልማ 7፥12ተመልከቱ።

  39. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “The Teachings of Jesus Christ፣“ ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 102-5 ይመልከቱ።

  40. ያዕቆብ 2፥8፤ ደግሞም also Neil L. Andersen, “Wounded,” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2018 (እ.አ.አ) 83–86 ይመልከቱ።

  41. ማቴዎስ 11፥28፤ ደግሞም ማቴዎስ 28፥20 ይመልከቱ፦ “እነሆም እኔ እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ሁልጌዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

  42. ሞዛያ 24፥14

  43. ዮሐንስ 14፥18

  44. “I Am a Child of God,” Children’s Songbook, 3; እንዲሁም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98:3። ይመልከቱ

  45. 3 ኔፊ 17፥7፣ እንዲሁም አልማ 36:3፣ 27 ይመልከቱ።

  46. ዘፀአት 2:243፥7ሞዛያ 24፥12ን ይመልከቱ።

  47. 2 ኔፊ 2:24; ሞዛያ 4:9; ኢሳያስ 55:9ይመልከቱ። “አንዳንድ በረከቶች በቶሎ ይመጣሉ፣ አንዳንዶች ዘግይተው፣ አንዳንዶች ከመንግስተ ሰማያት በፊት አይመጡም፣ ነገር ግን የኢየሱስ ከርስቶስን ወንጌልን ተቀብለው ለሚታቀፉ በረከቶቹ ይመጣሉ።(Jeffrey R. Holland, “An High Priest of Good Things to Come,” Ensign, Nov. 1999, 38)።

  48. አልማ 33፥23

  49. አልማ 31:38፤ እንዲሁም መዝሙር 30:5; ዮሃነስ 15:10–11; 1 ተሰሎንቄ 1:6; ጆሴፍ ስሜዝ ትርጉም, ያቆብ 1:2 (በ ያቆብ 1:2, footnote a); 2 ኔፊ 2:25; 9:18; አልማ 26:6–7, 11, 27, 37; 28:8; 33:23; 36:20–21; ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥76; ሙሴ 5:10–11.