2020–2024
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት
የሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:56

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት

ቃል ኪዳኖቻችንን በማክበር፣ እግዚአብሔር ከእነዚህ ቃል ኪዳኖች ጋር የተያያዙ ብዙ ቃል የተገቡ በረከቶችን እንዲያፈስ እናደርጋለን።

የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ትንንሽ ልጆቼ እያደጉ ሲሄዱ፣ የሚያዝናኑ እና ትኩረትን የሚስቡ ሆነው በታሪኮቻቸው ውስጥ ምልክትን የሚጠቀሙ መጽሃፎች እንዳሉ ደረስኩበት። ማታ ማታ አብረን ስናነብ፣ ፀሃፊው ጥልቅ መርሆዎችን፣ በተለይም የወንጌል መርሆዎችን ለማስተማር የተጠቀመበትን ምልክት ልጆቼ እንገነዘቡ መርዳት እወድ ነበር።

አንድ ቀን ትንሹ ልጄ ገና በአሥራዎቹ ዕድሜ መጀመሪያ ላይ እያለ ይህንን እየተረዳው እንደሆነ አወቅኩ። በታሪኩ ዘና ለማለት ብቻ በመፈለግ አዲስ መጽሐፍ ማንበብ ጀምሮ ነበር ነገር ግን አዕምሮው በሚያነበው ነገር ሁሉ ጥልቅ ትርጉም ለማግኘት ይሞክር ነበር። እሱ ሲበሳጭ እኔ በውስጤ ፈገግ እያልኩ ነበር።

ኢየሱስ በታሪኮች እና በምልክቶች አስተምሯል—የእምነትን ኃይል ለማስተማር የሰናፍጭ ዘር፣ የነፍስን ዋጋ ለማስተማር የጠፋ በግ፣ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ለማስተማር ደግሞ አባካኙ ልጅ። ምሳሌዎቹ “የሚሰማ ጆሮ” ላላቸው ሰዎች ጥልቅ ትምህርት የሚያስተምርባቸው ምልክቶች ነበሩ። ልክ ለልጆቼ እንደማነባቸው ዓይነት ተመሳሳይ መጽሃፎችን የሚያነቡ ብዙ ሰዎች ጥልቅ ትርጉሞች እንዳሏቸው እና ከእነዚህ ታሪኮች ውስጥ ሊገኙ የሚችሉ ተጨማሪ ነገሮች እንዳሉ ፈጽሞ እንደማያውቁ ሁሉ ጥልቅ ትርጉሙን የማይፈልጉ አይረዱትም

እግዚአብሔር አብ አንድያ ልጁን ለእኛ መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ በሰማይ ያለው አባታችን ለእያንዳንዳችን ያለውን የማይጠፋ ፍቅር ትልቅ ምልክት ሆነ። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር በግ ሆነ።

ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ቃል ኪዳን ግንኙነት እንገባ ዘንድ የመጋበዝ እድል እና በረከት አለን፣ በዚህም የኛ ህይወት ራሱ የዚያ ቃል ኪዳን ምልክት ሊሆን ይችላል። ቃል ኪዳኖች እግዚአብሔር በጊዜ ሂደት እንዲቀርጸን እና እንዲለውጠን እንዲሁም አዳኙን እንድንመስል የሚያነሳን አይነት ግንኙነት ይፈጥራሉ፣ ወደ እርሱ እና ወደ አባታችን ይበልጥ እንድንቀርብ፣ በመጨረሻም ወደ እነርሱ መገኛ እንድንገባ ያዘጋጁናል።

በምድር ላይ ያለ እያንዳንዱም [ግለሠብ] የተወደዱ የእግዚአብሔር ሴት እና ወንድ ልጆች ናቸው። የቃል ኪዳን አካል ለመሆን በምንመርጥበት ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ያሳድጋል እንዲሁም ጥልቅ እንዲሆን ያደርጋል። ፕሬዚዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ስንመርጥ ግንኙነታችን ከቃል ኪዳኑ በፊት ከነበረው ይልቅ የቀረበ እንደሚሆን እንዲሁም በዕብራይስጥ ቋንቋ ሄሴድ ተብሎ በሚጠራው የቃል ኪዳን ፍቅር፣ በተጨማሪ ምህረት እና ፍቅር እንዲባርከን ያስችለዋል በማለት አስተምረዋል። የቃል ኪዳኑ መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት—ከእርሱ ጋር ስላለን የ ሄሴድ ግንኙነት ነው።

አባታችን ከሁሉም ወንዶች እና ሴቶች ልጆቹ ጋር ጥልቅ ግንኙነት እንዲኖረው ይፈልጋል፣ ነገር ግን እርሱ እኛን አያስገድደንም። በቃል ኪዳን ግንኙነት ወደ እርሱ ለመቅረብ በምንመርጥበት ጊዜ፣ እርሱ ወደ እኛ እንዲቀርብ ያስችለዋል እንዲሁም በኃይሉ እና ከፍ ባለ ችሎታው ይባርከናል።

እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ቅድመ ሁኔታዎች እና ሃላፊነቶችን ያስቀምጣል። ወደዚያ ግንኙነት ለመግባት በምንመርጥበት ጊዜ፣ እርሱ ባስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ለመታዘዝ ፈቃደኛ መሆናችንን በቃል ኪዳኑ ምሳሌያዊ ተግባራት እንመሰክራለን። ቃል ኪዳኖቻችንን በማክበር፣ ለመለወጥ እና ይበልጥ እንደ አዳኙ ለመሆን እየጨመረ የሚሄድ ኃይልን ጨምሮ ከቃል ኪዳኖች ጋር የተያያዙ ብዙ ቃል የተገቡ በረከቶችን እግዚአብሔር እንዲያፈስ እናስችለዋለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ለምንገባቸው ቃል ኪዳኖች ሁሉ ማዕከል ሲሆን፣ የቃል ኪዳኑን በረከቶች ያስቻለው የኃጢያት ክፍያው ነው።

ውሃ ውስጥ በመጥለቅ መጠመቅ ከእግዚአብሔር ጋር የቃል ኪዳን ግንኙነት ውስጥ የምንገባበት ምሳሌያዊ በር ነው። በውሃ ውስጥ መጥለቅ እና እንደገና መውጣት የአዳኙን ሞት እና ለአዲስ ህይወት ትንሳኤ ምልክት ነው። እኛ ስንጠመቅ፣ በምሳሌያዊ ሁኔታ ሞተን ወደ ክርስቶስ ቤተሰብ ዳግመኛ እንወለዳለን እንዲሁም ስሙን በላያችን ላይ ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆናችንን እናሳያለን። እኛ እራሳችን ያንን የቃል ኪዳን ምልክት እንይዛለን። በአዲስ ኪዳን “ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና”21 የሚለውን እናነባለን። በምሳሌያዊ ሁኔታ በጥምቀታችን ክርስቶስን እንለብሳለን።

የቅዱስ ቁርባን ሥርዓትም ወደ አዳኙ ይጠቁማል። ዳቦው እና ውኃው ለእኛ የፈሰሰው የክርስቶስ ሥጋና ደም ምልክት ነው። አዳኙን እራሱን የሚወክል የክህነት ተሸካሚ፣ ዳቦውን እና ውሃውን እንደ የኃጢያት ክፍያው ስጦታ ምሳሌነት በየሳምንቱ ይሰጠናል። የሥጋውንና የደሙን ምሳሌ የመብላትንና የመጠጣትን ተግባር ስናከናውን፣ ክርስቶስ በምሳሌያዊ ሁኔታ የእኛ አካል ይሆናል። በየሳምንቱ አዲስ ቃል ኪዳን ስንገባ እንደገና ክርስቶስን እንለብሳለን።

በጌታ ቤት ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ስንገባ፣ ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት የበለጠ ጥልቅ እናደርጋለን። አዳኙ እና የኃጢያት ክፍያው ማዕከላዊ በሆነበት በቤተመቅደስ ውስጥ የምናደርገው ነገር ሁሉ አባታችን ለእኛ ወዳለው እቅድ ይጠቁማል። ልባችንን ስንከፍት እና ጥልቅ ትርጉሞችን በጸሎት መንፈሥ ለመረዳት ስንፈልግ፣ ጌታ በሥርዓቶች እና በቃል ኪዳኖች ምልክቶች አማካኝነት በሥርዓት ላይ ሥርዓት ያስተምረናል።

እንደ ቤተመቅደስ ቡራኬ አካል፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የቅዱስ ክህነትን ልብስ እንዲለብሱ ፈቃድ ይሰጣቸዋል። ይህ የተቀደሰ ግዴታ እና መብት ነው።

በብዙ ሃይማኖታዊ ባህሎች ውስጥ፣ ልዩ ውጫዊ ልብሶች የሚለበሱት፣ እንደ አንድ ግለሠብ የእምነት እና ለእግዚአብሔር ያለ ቁርጠኝነት ምልክት ሲሆን፣ የአምልኮ ሥርዓቶችን የሚመሩ ሰዎች ብዙውን ጊዜ የክብረ በዓል ልብስ ይለብሳሉ። እነዚያ የተቀደሱ ልብሶች ለለባሾቹ ጥልቅ ትርጉም አላቸው። በጥንት ዘመን የክብረ በዓል ልብሶችም ከቤተመቅደስ ሥርዓት ጋር ተያይዘው ይለብሱ እንደነበር በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ እናነባለን።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት እንደመሆናችን፣ በጌታ ቤት ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት የመረጥን ሰዎች፣ በቤተመቅደስ አምልኮ ወቅት የተቀደሰ የሥርዓት ውጫዊ ልብስ እንለብሳለን፣ እነዚህም በጥንታዊ የቤተመቅደስ የአምልኮ ሥርዓቶች የሚለበሱ አልባሣትን የሚያመላክቱ ናቸው። የቅዱስ ክህነት ልብስን ደግሞ በቤተመቅደስ አምልኮ እና በቀን ተቀን ህይወታችን እንለብሣለን።

የቅዱስ ክህነት ልብስም ጥልቅ ምሳሌ አለው እንዲሁም ወደ አዳኙ ይጠቁማል። አዳምና ሔዋን የዛፍ ፍሬውን በልተው ከኤደን ገነት ሲወጡ፣ መሸፈኛ ይሆናቸው ዘንድ የቁርበት ልብስ ተሰቷቸው ነበር። አዳኙ ለእኛ ሲል የከፈለውን መስዋዕትነት ምሳሌ ይሆን ዘንድ የቆዳ ልብስ ለመስራት አንድ እንስሳ ሳይሰዋ አልቀረም። ካፋር የሚለው ቃል የሃጢያት ክፍያ መሰረታዊ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ከትርጉሞቹ መካከል አንዱ “መሸፈን” የሚል ነው። የቤተመቅደስ ልብሳችን አዳኙ እና የኃጢያት ክፍያው በረከቶች በህይወታችን ሁሉ እንደሚሸፍኑን ያስታውሱናል። በየቀኑ የቅዱስ ክህነት ልብስን ስንለብስ ያ ውብ ምልክት የእኛ አካል ይሆናል።

በአዲስ ኪዳን የሮሜ መጽሐፍ ውስጥ “ሌሊቱ አልፎአል ቀኑም ቀርቦአል፤ እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። … ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት።” የሚል ቃል እናነባለን።

በህይወት ዘመኔ ሁሉ አዳኙ እና ወሰን የሌለው የኃጢያት ክፍያው በረከቶች በምድራዊ ጉዞዬ ሁሉ እንደሚሸፍኑኝ ለማስታወስ፣ የቅዱስ ክህነት ልብስ እንድለብስ ስለተሰጠኝ እድል በጣም አመስጋኝ ነኝ። በጌታ ቤት ከእግዚአብሔር ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ስጠብቅ፣ እራሱ የብርሃን ጋሻ የሆነውን ክርስቶስን በምሳሌያዊ ሁኔታ እንደለበስኩትም ያስታውሰኛል። ከክፉ ይጠብቀኛል ኃይልን እና አቅምን ይጨምርልኛል፣ እናም በዚህ ዓለም ጨለማ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ብርሃን እና መመሪያዬ ይሆነኛል።

በቅዱስ ክህነት ልብስ እና ከክርስቶስ ጋር ያለው ግንኙነት ጥልቅ እና የሚያምር ምሳሌያዊ ትርጉም አለ። ቅዱሥ ልብሡን ለመልበስ ያለኝ ፈቃደኝነት ለእርሱ የማሣየው የእኔ ምልክት እንደሚሆን አምናለሁ። ይህ ለእግዚአብሔር የማሣየው የራሴ የግል ምልክት እንጂ ለሌሎች የማሣየው ምልክት አይደለም።

ስለአዳኛችን ስለኢየሱስ ክርስቶስ በጣም አመስጋኝ ነኝ። ለእኛ ያደረገው የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት እርሱ እና የሰማይ አባታችን ለእያንዳንዳችን ያላቸውን እጅግ የላቀ ፍቅር፣ የዚያ ፍቅር እና መስዋዕት ተጨባጭ ምልክቶች—በአዳኙ እጆች፣ እግሮች እና ጎን ላይ ያሉ ምልክቶች— ከትንሣኤው በኋላም እንኳን ነበሩ።

የቅዱስ ክህነት ልብስን መልበስ ጨምሮ ቃል ኪዳኖቼን እና ለእግዚአብሔር ያሉብኝን ግዴታዎች ስጠብቅ፣ የገዛ ህይወቴ ለአዳኙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝ ፍቅር እና ጥልቅ ምስጋና እንዲሁም ሁል ጊዜም ከእኔ ጋር እንዲሆን ያለኝ ፍላጎት የግል ምልክት ሊሆን ይችላል።

እስካሁን ይህን ካላደረጋችሁ፣ በጌታ ቤት ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት ከእግዚአብሔር ጋር የጠለቀ ግንኙነት መመሥረትን እንድትመርጡ እጋብዛችኋለሁ። በንግግራቸው የግርጌ ማስታወሻዎች ላይ ያሉትን አስደሣች ትምህርቶች ጨምሮ (አብዛኞቹ የጉባኤ ንግግሮች አሏቸው) የነቢያችንን ንግግሮች አጥኑ። ለዓመታት በተለይም የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ስለ ቃል ኪዳኖች ደጋግመው ተናግረዋል። ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖችን በመግባት እና በመጠበቅ የእናንተ ሊሆኑ ስለሚችሉት አስደሳች በረከቶች እንዲሁም ተጨማሪ ኃይል እና አቅም ከትምህርታቸው ተማሩ።

አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ እንደሚገልጸው፣ የቤተመቅደስን ቃል ኪዳን ለማድረግ የሚስዮን ጥሪ ማግኘት ወይም ለማግባት መታጨት አያስፈልግም። አንድ ሰው ቢያንስ 18 ዓመት ሊሞላው፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም ተመሳሳይ ትምህርት ተማሪ ያልሆነ እና ቢያንስ ለአንድ ዓመት የቤተክርስቲያኗ አባል የሆነ ሊሆን ይገባል። አስፈላጊ የሆኑ የግል ቅድስና ደረጃዎችም አሉ። በጌታ ቤት ውስጥ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን በመግባት ከሰማይ አባታችሁ እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት ካላችሁ፣ ከኤጲስ ቆጶሳችሁ ወይም ከቅርንጫፍ ፕሬዚዳንታችሁ ጋር እንድትነጋገሩ እና ፍላጎቶቻችሁን እንዲያውቁት እንድታደርጉ እጋብዛችኋለሁ። እነዚያን ቃል ኪዳኖች ለመቀበል እና ለማክበር እንዴት መዘጋጀት እንዳለባችሁ እንድታውቁ ይረዳችኋል።

ከእግዚአብሔር ጋር ባለን የቃል ኪዳን ግንኙነት አማካኘነት፣ የራሳችን ህይወት በሰማይ ላለው አባታችን ላለን ቁርጠኝነት እና ጥልቅ ፍቅር፣ ለእርሱ ያለን ሄሴድ እንዲሁም አንድ ቀን ወደመገኛቸው ለመግባት በመዘጋጀት፣ ለማደግ እና በስተመጨረሻም እንደ አዳኛችን ለመሆን ያለን ፍላጎት፣ ህያው ምልክት ሊሆን ይችላል። የዚያ የቃል ኪዳን ግንኙነት ታላቅ በረከቶች ከሚያስከፍሉት ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ እንደሆኑ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ማርቆስ 4፥33–34 ይመልከቱ።

  2. ማቴዎስ17፥20 ይመልከቱ።

  3. ሉቃስ 15፥3–7ይመልከቱ።

  4. ሉቃስ 15፥11–32ይመልከቱ።

  5. ማቴዎስ 13፥9

  6. ማቴዎስ 13፥10–13ይመልከቱ።

  7. ዮሐንስ 3፥16–17 ይመልከቱ።

  8. ዮሐንስ 1፥291 ኔፊ 11፥20–22ይመልከቱ፤ በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “The Atonement,” ሊያሆና፣ ህዳር፣ 1996 (እ.አ.አ) 34–35.

  9. “ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት፣ እግዚአብሔር እኛን ከእርሱ ጋር ማሰር ብቻ ሳይሆን፣ በጀርባው ተሸክሞን እሱ ብቻ ወደሚሄድበት ቦታ ይወስደናል” (ኬሪ ሙህሌስተን፣ God Will Prevail (2021 (እ.አ.አ)፣ 8– 8)። ትምህርት እና ቃል ኪዳን 133፥53ይመልከቱ።

  10. ‘የሰው ልጆች በሙሉ —ወንድና ሴቶች —በእግዚአብሔር አምሳል ነው የተፈጠሩት። እያንዳንዱም በሰማይ ወላጆች የተወደዱ የመንፈስ ሴት ልጅ ወይም ወንድ ልጆች ናቸው፣ እናም ይህ ስለሆነም እያንዳንዱ መለኮታዊ ተፈጥሮ እና ፍጻሜ አላቸው” (“ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ላይብረሪ)።

  11. ሄሴድ ሁለት አካላት አንዳቸው የሌላውን ቃል አክባሪ እና እርስ በርስ የሚተማመኑ እንዲሆኑ የሚጠበቅባቸውን የቃል ኪዳን ግንኙነት የሚገልጽ ልዩ ቃል ነው። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ከገቡት ጋር ሄሴድ ስላደረገ ከእነርሱ ጋር መስራቱን ይቀጥላል እንዲሁም የመለወጥ እድሎችን ይሰጣቸዋል። ከመንገድ ከሳቱም ልክ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከቃል ኪዳኑ ሕዝብ ጋር ደጋግሞ እንዳደረገው ወደ እርሱ የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። ከእግዚያብሄር ጋር ቃልኪዳን ስናደርግ ሁልጊዜ ቃሉን ከሚጠብቅ ከእርሱ ጋር ቃልኪዳን አድርገናል ማለት ነው። ነጻ ምርጫችን ሳይጥስ የራሳችንን እንድንይዝ የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል።”(ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን፣” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2022 (እ.አ.አ)፣ 6፣ 11፤ ደግሞም Muhlestein, God Will Prevail, 9–12; ዘዳግም 7፥9)።

  12. እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ግንኙነቱን ፈጽሞ አይተውም። እኛን ለመርዳት በሚያደርገው ጥረት አይታክትም እንዲሁም ለእኛ ያለውን የምሕረት ትዕግሥቱንም አንጨርሰውም (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን፣” 6)። በዘለአለማዊ ቃል ኪዳን አብረን በደስታ እንተሳሰራለን።

  13. ኤርምያስ 31፥331 ኔፊ 17፥40፤ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ እግዚአብሔር ያሸንፍ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 92።

  14. ያዕቆብ 4፥8ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥63 ይመልከቱ።

  15. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ቃል ኪዳኖች፣” Liahona, ህዳር 2011 (እ.አ.አ)፣ 86።

  16. ሞዛያ 5፥518፥8–10 ይመልከቱ።

  17. See Russell M. Nelson, “Spiritual Treasures,” Liahona, Nov. 2019, 77; Russell M. Nelson, “The Temple and Your Spiritual Foundation,” Liahona, Nov. 2021, 94; Russell M. Nelson, “Overcome the World and Find Rest,” Liahona, Nov. 2022, 96; Camille N. Johnson, “Jesus Christ Is Relief,” Liahona, May 2023, 82; Dale G. Renlund, “Accessing God’s Power through Covenants,” Liahona, May 2023, 35–37; Jean B. Bingham, “Covenants with God Strengthen, Protect, and Prepare Us for Eternal Glory,” Liahona, May 2022, 66.

  18. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን፣” 7 ይመልከቱ።

  19. ሮሜ 6፥3–4ቆላሲያስ 2፥12ይመልከቱ።

  20. 2 ኔፊ 31፥13ሞርሞን 6፥3ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77ይመልከቱ።

  21. ገላትያ 3፥27፡፡

  22. ሉቃስ 22፥19-20ይመልከቱ።

  23. ዮሐንስ 6፥56ይመልከቱ።

  24. ፕሬዘደንት ራስል ኤም.ኔልሰን “ብዙ ጊዜ ቅዱስ ቁርባን የምንካፈለው በጥምቀት ወቅት የገባነውን ቃል ኪዳን ለማደስ ነው ሲባል እሰማለሁ። ይህ እውነት ቢሆንም ከዚያ የበለጠ ነው። አዲስ ቃል ኪዳን ገብቻለሁ። አዲስ ቃል ኪዳኖችን ገብተሃል” (ዳሌ ጂ ሬንሉንድ፣ “Unwavering Commitment to Jesus Christ,” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 25፣ የግርጌ ማስታወሻ 18 ይመልከቱ)።

  25. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን፣ 10 ይመልከቱ።

  26. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ቤተመቅደስ እና መንፈሳዊ መሰረታችሁ፣” 93-94።

  27. 2 ኔፊ 28፥30 ይመልከቱ።

  28. Sacred Temple Clothing [የተቀደሰ የቤተመቅደስ ልብስ]” በChurchofJesusChrist.org. ላይ ይመልከቱ።

  29. ዘጸአት 2840፥12–13ይመልከቱ።

  30. Sacred Temple Clothing [የተቀደሰ የቤተመቅደስ ልብስ]” በChurchofJesusChrist.org. ላይ ይመልከቱ።

  31. ዘፍጥረት 3፥21ይመልከቱ።

  32. ራስል ኤም. ኔልሰን “The Atonement,” 34

  33. ሮሜ 13፥12፣ 14

  34. ኤፌሶን 6፥10–18ይመልከቱ።

  35. ሞዛያ 24፥13–15;ዴቪድ ኤ. ቤድናርን፣ “ሸክማቸውን በቀላሉ ተሸከሙ [Bear Up Their Burdens with Ease]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 88-89 ይመልከቱ።

  36. መዝሙር 119፥1051 ኔፊ 17፥13ይመልከቱ።

  37. ሽማግሌ ኒል ኤ. ማክስዌል እንዲህ አስተምረዋል፣ “የገዛ ፈቃድን አሳልፎ መስጠት በእውነት እኛ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ልናስቀምጠው የሚገባን ብቸኛ ግላዊ ነገር ነው” (“Swallowed Up in the Will of the Fatherኢንዛይን፣ ህዳር 1995 (እ.አ.አ)፣ 24)።

  38. በግል ምርጫ፣ ምቾት በማጣት ወይም ዘይቤ ሳይሆን በተወሰኑ የጤና እክሎች ምክንያት ለአንዳንድ ሰዎች ልብሱን መልበስ በጣም ከባድ ነው። ጌታ ልባችንን ያውቃል እናም ከእርሱ ጋር የገባነውን ኪዳን የማክበር ፍላጎታችንን ይረዳል። ለምሳሌ፣ ሞዛያ 4፥24–25ይመልከቱ።

  39. በሌሎች የቤተመቅደስ ልብስ አጠቃቀም ላይ መፍረድ የለብንም። አልማ 41፥14፤ ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ “The Merciful Obtain Mercy [ምህረተኛው ምህረት ያገኛል]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2012 (እ.አ.አ) 70፣ 75ን ተመልከቱ።

  40. ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “None Were with Him [ማንም ከእርሱ ጋር አልነበሩም]፣” ሊያሆና ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 86-88፤

  41. ዮሐንስ 3፥16–1715፥12–13ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 34፥3 ይመልከቱ።

  42. ኢሳይያስ 49፥14–16 ይመልከቱ።

  43. ራስል ኤም. ኔልሰን “The Everlasting Covenant [ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን፣” 4–11፤ “Spiritual Treasures [መንፈሳዊ ሀብት]፣” 76–79፤ “እግዚአብሔር ያሸንፍ፣” 92–95፤ “The Temple and Your Spiritual Foundation [ቤተመቅደስ እና መንፈሳዊ መሰረታችሁ]፣” 93–96፤ “Overcome the World and Find Rest [አለምን ማሸነፍ እና እረፍትን ማግኘት]፣” 95–98፤ “A Plea to My Sisters [ለእህቶቼ የተሰጠ ልመና]፣” Liahona፣ Nov. 2015፣ 95–97።

  44. አጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል26.5.1 እና 27.2.2 በወንጌል ቤተመጻህፍት ውስጥ ይመልከቱ።

  45. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Closing Remarks [የመዝጊያ ንግግር]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 121።

  46. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን፣” 11።