መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
35. የስብሰባ አዳራሾች አያያዝ እና አጠቃቀም


“35. የስብሰባ አዳራሾች አያያዝ እና አጠቃቀም፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“35. የስብሰባ አዳራሾች አያያዝ እና አጠቃቀም፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ሰዎች መስታወት እየወለወሉ እና በቫኪዩም እያጸዱ

35.

የስብሰባ አዳራሾች አያያዝ እና አጠቃቀም

35.1

ዓላማ

የቤተክርስቲያኗ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን የምታቀርበው የሚገቡበት ሁሉ፦

35.2

ሚናዎች እና ኃላፊነቶች

35.2.2

የቤተክርስቲያኗ ፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪ

በቤተክርስቲያኗ የተቀጠረ/ረች የፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪ እያንዳንዱ ካስማ የስብሰባ አዳራሾችን መጠቀም እንዲችል ይረዳል። እርሱ ወይም እርሷ ዋና ጥገናዎችን፣ ሙሉ ፅዳትን እና መደበኛ የህንፃ ጥገና እንዲደረግ ያመቻቻል/ታመቻቻለች።

እንደ አስፈላጊነቱ፣ የፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪው፣ የካስማ እና የአጥቢያ የሕንፃ ተወካዮች ሕንፃውን እንዴት እንደሚያፀዱ እና ሌሎች የአካባቢ ሥራዎችን እንዴት እንደሚሠሩ በማስተማር ያግዛል/ታግዛለች። እርሱ ወይም እርሷ መመሪያዎችን፣ ቁሳቁሶችን እና መሳሪያዎችን ያቀርባል/ታቀርባለች።

እርሱ ወይም እርሷ የግንባታ ወጪዎችን ከኤጲስ ቆጶሳት ጋር መገምገምም ይችላል/ትችላለች።

35.2.7

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ኤጲስ ቆጶስ አመራሩ (ወይም የአጥቢያው የሕንፃ ተወካይ) አባላት ሕንፃውን እንዴት እንደሚጠቀሙ፣ እንደሚንከባከቡ እና ደህንነቱን እንደሚጠብቁ ያስተምራቸዋል። የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የህንጻ ቁልፎችን ለአጥቢያ መሪዎች ይሰጣል።

በህንፃው እንዲሁም በግቢው ውስጥ የሚደረጉ አክቲቪቲዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ መደረጋቸውን ያረጋግጣሉ (20.7ን ይመልከቱ)።

ስለጥገና እና የአጠቃቀም ፍላጎቶች ከቤተክርስቲያኗ የፋሲቲዎች አስተዳዳሪ ጋር ይነጋገራሉ። እንዲሁም ተዛማጅ ወጪዎችን ከፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪ ጋር መገምገም ይችላሉ።

35.2.9

የአጥቢያ የህንጻ ተወካይ

የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የአጥቢያ የህንጻ ተወካይን ስለመጥራት ይወስናል። ይህንን ጥሪ ለመስጠት ከወሰኑ ኤጲስ ቆጶሱ አንድን ጎልማሳ ወንድ ወይም ሴት አባል ሊጠራ ይችላል። የአጥቢያው የሕንፃ ተወካይ ካልተጠራ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ይህንን ኃላፊነት ከአማካሪዎቹ ለአንዱ፣ ለአጥቢያ ጸሐፊው ወይም ለረዳት የአጥቢያ ጸሐፊው ወይም ለዋና ጸሐፊው ሊሰጥ ይችላል።

የአጥቢያ የሕንፃ ተወካዩ አባላት እና በጎ ፈቃደኞች ሕንፃውን እንዲያጸዱ እና እንዲጠግኑ ያደራጃቸዋል።

35.3

የስብሰባ አዳራሾችን ማቅረብ

የመሰብሰቢያ አዳራሾች እንደየአካባቢው ፍላጎቶች እና ሁኔታዎች በመጠን እና በዓይነት ይለያያሉ። የመሰብሰቢያ አዳራሸ በቤተክርስቲያን የተገነባ ወይም የተገዛ ቦታ፣ የአንድ አባል ቤት፣ የአካባቢ ትምህርት ቤት ወይም የማህበረሰብ ማዕከል፣ በኪራይ የተገኘ ቦታ ወይም ሌላ የተፈቀደ አማራጭ ሊሆን ይችላል።

የዋና አካባቢ እና የቅርብ አካባቢ መሪዎች አሁን ያሉትን የመሰብሰቢያ አዳራሾች ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ይጥራሉ እንዲሁም ተጨማሪ ቦታን በጥቆማ ለማቅረብ ጥበበኞች ይሆናሉ።

35.4

የስብሰባ አዳራሾችን መጠገን

35.4.1

የስብሰባ አዳራሾችን ማፅዳት እና መጠገን

የአካባቢ መሪዎች እና አባላት ወጣቶችን ጨምሮ፣ እያንዳንዱን ሕንፃ ፅዱ የማድረግ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዲሆን የመርዳት ኃላፊነት አለባቸው።

የፅዳት መርሃ ግብሩ በአባላት ላይ ጫና መፍጠር የለበትም። ለምሳሌ ወደ ሕንፃው የሚደረግ ጉዞ አስቸጋሪ ከሆነ፣ አባላት በህንፃው ባሉበት በዚያው ጊዜ የሳምንታዊ ዝግጅቶች ክፍል አድርገው ማፅዳት ይችላሉ።

35.4.2

ጥገና መጠየቅ

የአጥቢያ እና የካስማ ምክር ቤት አባላት የሕንፃ ጥገና ፍላጎቶችን ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ይህም Facility Issue Reporting (FIR) [የፋሲሊቲ ጉዳዮች ሪፖርት ማቅረቢያ] መሳሪያን በመጠቀም ሊደረግ ይችላል።

35.4.5

ደህንነት እና ጥበቃ

መሪዎች እና አባላት የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፦

  • ደህንነቱ የተጠበቀ መግቢያ እና መውጫ እንዲኖር መተላለፊያ መንገዶችን፣ ደረጃዎችን፣ መውጫ በሮችን እና እቃ ማስቀመጫ ክፍሎች ግልፅ ማድረግ።

  • በህንፃዎች ውስጥ አደገኛ ወይም ተቀጣጣይ ነገሮችን አለመጠቀም ወይም አለማስቀመጥ።

  • ህንጻዎችን የመቆለፍ ሂደቶችን ማዘጋጀት እና መከተል።

  • የቤተክርስቲያን ንብረት የሆኑ መሳሪያዎችን ከስርቆት መጠበቅ።

  • እንደ ውሃ፣ መብራት እና ጋዝ ወይም ነዳጅ ያሉ መገልገያዎችን እንዴት መዝጋት እንደሚቻል ማወቅ

እንዳስፈላጊነቱ የፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪው/ዋ የእሳት ማጥፊያዎች፣ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ቁሳቁሶች ያሉበትን እንዲሁም መገልገያዎች የሚዘጉበትን ቦታ የሚያሳይ ካርታ ማቅረብ ይችላል/ትችላለች። ስለደህንነት የበለጠ መረጃ ለማግኘት በ“Security and Lockup Procedures [ጥበቃ እና ቦታዎችን የመቆለፍ ሂደት” “የመሰብሰቢያ አዳራሾችን መጠገን” (Meetinghouse Facilities Guide [የመሰብሰቢያ አዳራሽ መመሪያ መፅሐፍ]) ውስጥ ይገኛል። በተጨማሪም 20.7 ይመልከቱ።

35.5

የቤተክርስቲያኗን መሰብሰቢያ አዳራሽ አጠቃቀም ፖሊሲዎች

35.5.1

የቤተክርስቲኗን መሰብሰቢያ አዳራሾችን ስለመጠቀም መሰረታዊ መርሆች እና መስፈርቶች

ሁሉም የቤተክርስቲያኗ የመሰብሰቢያ አዳራሾች አጠቃቀሞች የሚከተሉትን መሰረታዊ መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፦

  • የቤተክርስትያን የመሰብሰቢያ አዳራሾች የተቀደሰ ተፈጥሮ እና አላማን ጨምሮ ከቤተክርስቲያኗ ትምህርት፣ ፖሊሲዎች እና ተግባሮች ጋር ወጥነት ያላቸው ይሁኑ።

  • በህጉ ወሰን ውስጥ ይሁኑ።

  • ተገቢ ሆኖም፣ ከቤተክርስቲያኗ ከቀረጥ ነፃ ሁኔታ ጋር ወጥነት ያላቸው ይሁኑ።

  • ልጆችን እና ወጣቶችን የሚጠብቁ የቤተክርስቲያኗ መመሪያዎችን እና ፖሊሲዎችን ጨምሮ የደህንነት ስጋቶችን ለማስወገድ፣ ለማቃለል እና ለመቆጣጠር ተገቢው እርምጃን የሚወስዱ ይሁኑ (12.5.1 እና 20.7.1ን ይመልከቱ)።

  • በካስማ ፕሬዚዳንት ወይም በኤጲስ ቆጶስ የተሰጡ ሌሎች ሁኔታዎችን እና ገደቦችን የሚያከብሩ ይሁኑ።

35.5.2

የቤተክርስቲያኗን የመሰብሰቢያ አዳራሾች አጠቃቀም

አለመግባባት ከተፈጠረ፣ የቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች፣ ፕሮግራሞች እና ተግባራት ከሌሎች የስብሰባ አዳራሽ አገልግሎት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

አጥቢያዎች እና ካስማዎች አባላትን እና ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ሌሎች የቤተክርስቲያኗ ፕሮግራሞችን ሊያቀርቡ ይችላሉ። እነዚህ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

35.5.3

የመሰብሰቢያ አዳራሾች የአባላት አጠቃቀም—የግል እና የቤተሰብ

አባላት ለግል ወይም ለቤተሰብ ተግባሮች በካስማቸው ውስጥ ያለውን የስብሰባ አዳራሽን ለመጠቀም ሊጠይቁ ይችላሉ። ፈቃድ ለማግኘት፣ እነርሱም በዚያ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የሚገኘውን የአጥቢያ ኤጲስ ቆጶስ አመራር አባልን (ወይም እሱ የሾመውን ሰው) ያነጋግሩ። የሚከተሉት ሁኔታዎች የሚገኙበት መሆን አለባቸው፦

  • አጠቃቀሙ በስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በሚገኘው ኃላፊነት ባለው አዋቂ የአጥቢያ አባል ክትትል ሊደረግበት ይገባል።

  • ተጠቃሚዎች ከዚህ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ለሚደርስ ማንኛውም ጉዳት ወይም ኪሳራ ወይም ተጠያቂነት ሙሉ ሃላፊነት አለባቸው።

  • ተጠቃሚዎች ማጽዳት እና መገልገያዎቹን ወደ ቀደመ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ መመለስ አለባቸው።

  • ተጠቃሚዎች አጠቃቀሙን ለመከታተል በአመራሮች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ጨምሮ የአካባቢ መሪዎችን መመሪያዎችን እና ጥያቄዎችን ማክበር አለባቸው።

  • መመሪያዎችን የማያከብሩ ከሆነ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን ንብረቱን መጠቀም እንዲያቆም የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ሊጠይቁ ይችላሉ።

  • ፈቃድ ለተሰጣቸው ተግባራት፣ የአጥቢያ እና የካስማ መሪዎች የስብሰባ አዳራሹን ለመጠቀም የሚገቡበት መንገድን ማዘጋጀት አለባቸው። የህንፃው ቁልፎች መሰጠት ያለባቸው ለተመረጡት የአጥቢያ ወይም የካስማ አባላት ብቻ ነው።

ለሠርግ እና ለሠርግ ግብዣዎች የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ለመጠቀም 38.3.4ን ይመልከቱ።

ለቀብር እና ለሟች ሌሎች አገልግሎቶች የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ለመጠቀም 29.5ን ይመልከቱ።

35.5.4

የቤተክርስቲያኗ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ለትርፍ ባልተቋቋሙ ድርጅቶች ወይም በሌሎች ቡድኖች ወይም ግለሰቦች መጠቀም

የአካባቢ መሪዎች ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች፣ ማህበረሰብ እና ሌሎች ቡድኖች (እንደ የስፖርት ቡድኖች ያሉ) ወይም በ35.5.3 ውስጥ ያልተገለጹ ግለሰቦች የቤተክርስትያኗን የመሰብሰቢያ አዳራሾች ለጤናማ ተግባራት ወይም አገልግሎት እንዲጠቀሙ መፍቀድ ይችላሉ። በ35.5.3 ውስጥ የተዘረዘሩት ሁኔታዎች የሚገኙበት መሆን አለባቸው።

ለእንደዚህ አይነት አጠቃቀም የአካባቢ መሪዎችን ፈቃድ ለመፈለግ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ የንብረት አስተዳዳሪውን ያነጋግራል።

35.5.5

ድንገተኛ ሁኔታዎች

በድንገተኛ አደጋ ጊዜ የቤተክርስቲያኗ የመሰብሰቢያ አዳራሾች አስፈላጊ ለሆኑ የማህበረሰብ አገልግሎት ሊውሉ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የካስማ ፕሬዚዳንት በእሱ ካስማ ውስጥ ያሉ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን የአደጋ-እርዳታ ድርጅቶች እና ሌሎች የተያያዙ ጥረቶች እንዲጠቀሙባቸው ሊፈቅድ ይችላል (35.5.4ን ይመልከቱ)።

35.5.6

የማይፈቀዱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አጠቃቀሞች

35.5.6.1

የንግድ አጠቃቀሞች

የቤተክርስቲያን ንብረት ለንግድ ዓላማ ጥቅም ላይ አይውልም። እንዲህ ያለው አጠቃቀም ከቤተክርስቲያኗ ንብረቶች አጠቃቀም ዓላማዎች ጋር አብሮ አይሄድም። በተጨማሪም የቤተክርስቲያኗን ንብረት ከቀረጥ ነፃ ማድረግን ሊፈቅዱ ከሚችሉ የአካባቢ ወይም አገራዊ ህጎች ጋር ሊጋጭ ይችላል።

35.5.6.3

ለፖለቲካ ዓላማዎች

ቤተክርስቲያኗ ከፖለቲካዊ ጉዳዮች ገለልተኛ ነች። የቤተክርስቲያኗ ንብረት ለፖለቲካ ዓላማዎች ወይም ድጋፍ ጥቅም ላይ አይውልም። የተከለከሉ ተግባራትም የፖለቲካ ስብሰባዎች ናቸው እንዲሁም ለፖለቲካ ዘመቻዎች እና ለድጋፍ ቡድኖች መጠቀምን ያካትታሉ።

ነገር ግን ለመራጮች ምዝገባ ወይም ድምጽ ለመስጠት ንብረቶችን መጠቀም እንደ ልዩ ሁኔታ ሊፈቀድ ይችላል (38.8.30ን ይመልከቱ)። የካስማ ፕሬዚዳንቱ በንብረት አስተዳዳሪ በኩል እንዲህ ያለውን ልዩ ሁኔታ ሊያገኝ ይችላል (35.5.4ን ይመልከቱ)።