“32. ንስሀ መግባት እና የቤተክርስቲያኗ አባልነት ምክር ቤት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።
“32. ንስሀ መግባት እና የቤተክርስቲያኗ አባልነት ምክር ቤት፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ
32.
ንስሀ መግባት እና የቤተክርስቲያኗ የአባልነት ምክር ቤት
32.0
መግቢያ
አብዛኛው ንስሃ መግባት የሚፈጸመው በግለሰብ፣ በእግዚአብሔር እና ኃጢያቱን በፈጸመው ሰው ምክንያት በተጎዱት ሠዎች መካከል ነው። ሆኖም አንዳንዴ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት የቤተክርስቲያኗ አባላት ንስሃ ለመግባት የሚያደርጉትን ጥረት ማገዝ ይኖርበታል።
አባላት ንስሃ እንዲገቡ በሚረዱበት ጊዜ ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች አፍቃሪ እና ተንከባካቢ ናቸው። ግለሰቦች የተሻሉ ሰዎች እንዲሆኑ በመደገፍ ፊታቸውን ከኃጢያት ዘወር እንዲያደርጉ እና ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ የረዳቸውን የአዳኙን ምሳሌ ይከተላሉ (ማቴዎስ 9፥10–13፤ ዮሐንስ 8፥3–11 ይመልከቱ)።
32.1
ንስሃ መግባት እና ይቅርታ
የምህረት እቅዱ ይከናወን ዘንድ፣ የሰማይ አባት አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ለኃጢያታችን ክፍያ እንዲፈፅም ላከው (አልማ 42፥15 ይመልከቱ)። ኢየሱስም የፍትህ ህግ ለኃጢያታችን እንዲከፈል የሚፈልገውን ቅጣት ተቀብሏል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥15–19 ተመልከቱ፤ በተጨማሪም አልማ 42፥24–25 ተመልከቱ)። በዚህ መስዋዕት አማካኝነት አብ እና ልጁ ለእኛ ያላቸውን ማለቂያ የሌለው ፍቅራቸውን አሳይተዋል (ዮሐንስ 3፥16 ይመልከቱ)።
“በንስሃ እምነት[ን]” ስንለማመድ፣ የሰማይ አባት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ምህረትን በመስጠት ይቅር ይለናል (አልማ 34፥15፤ በተጨማሪም አልማ 42፥13 ይመልከቱ)። ንፁህ ስንደረግ እና ይቅር ስንባል፣ በመጨረሻ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ እንችላለን (ኢሳይያስ 1፥18ን፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42 ይመልከቱ)።
ንስሃ መግባት ባሕርይን ከመቀየር በላይ ነው። ኃጢያትን መተው እንዲሁም ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መመለስ ነው። ልብን እና አዕምሮን ወደመለወጥ ይመራል (ሞዛያ 5፥2፤ አልማ 5፥12–14፤ ሔላማን 15፥7 ይመልከቱ)። በንስሃ አማካኝነት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የታረቅን አዲስ ሰዎች እንሆናለን (2 ቆሮንቶስ 5፥17–18፤ ሞዛያ 27፥25–26 ይመልከቱ)።
ንስሐ የመግባት እድል የሰማይ አባት በልጁ ስጦታ አማካኝነት ከሰጠን የላቁ በረከቶች መካከል አንዱ ነው።
32.2
የቤተክርስቲያኗ አባልነትን መገደብ ወይም ከአባልነት የማስወገድ አላማዎች
አንድ አባል ከባድ ኃጢያት ከሰራ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ እርሱ ወይም እርሷ ንስሃ እንዲገባ/እንድትገባ ይረዳል። እንደሂደቱ አካል፣ ለተወሰነ ጊዜ አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶችን መገደብ ሊያስፈልገው ይችላል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ለተወሰነ ጊዜ አንድን ግለሠብ ከአባልነት ማገድ ሊያስፈልገው ይችላል።
አንድን ግለሠብ ከአባልነት ማገድ ወይም ማስወገድ ቅጣትን ያለመ አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ተግባራት አንድ ግለሠብ ንስሃ እንዲገባ እና የልብ ለውጥ እንዲያደርግ ለመርዳት አስፈላጊ ናቸው። አንድ ግለሠብ የእርሱን ወይም የእርሷን ቃል ኪዳን ለማደስ እና ለመጠበቅ በመንፈሳዊ የሚዘጋጅበት/የምትዘጋጅበትን ጊዜንም ይሰጣሉ።
የአባልነት ገደቦች ወይም ከአባልነት የማስወገድ ሶስቱ አላማዎች የሚከተሉት ናቸው።
32.2.1
የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ ለመርዳት
የመጀመሪያው አላማ የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ መርዳት ነው። አንዳንድ ጊዜ አንድ ግለሠብ አካላዊ ወይም መንፈሳዊ ስጋት ሊሆን ይችላል። ሌላን ለመጉዳት ሆን ብሎ የሚደረግ ወንጀለኛ ባሕርይ፣ አካላዊ ጉዳት፣ ወሲባዊ ጥቃት፣ የዕፅ ሱሰኝነት፣ ማጭበርበር እና ክህደት ይህ ሊከሰት ከሚችልባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ ናቸው። ግለሰቡ በእነዚህ እና በሌሎች ከባድ መንገዶች ስጋት ሲፈጥር፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በሚያገኘው መነሳሳት መሠረት የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እርምጃ ይወስዳል (አልማ 5፥59–60 ይመልከቱ)።
32.2.2
አንድን ግለሠብ በንስሃ አማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ሃይል አንዲያገኝ ለመርዳት
ሁለተኛው ዓላማ በንስሃ አማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ሃይል አንዲያገኝ አንድን ግለሰብ መርዳት ነው። በዚህ ሂደት፣ እርሱ ወይም እርሷ እንደገና ንጹህ ለመሆን እና ሁሉንም የእግዚአብሔር በረከቶች ለመቀበል ብቁ ሊሆን/ልትሆን ይችላል/ትችላለች።
32.2.3
የቤተክርስቲያኗን ሀቀኝነት ለመጠበቅ
ሶስተኛው ዓላማ የቤተክርስቲያኗን ሀቀኝነት ለመጠበቅ ነው። ምግባሩ ወይም ምግባሯ ቤተክርስቲያንን በእጅጉ የሚጎዳ ከሆነ፣ ግለሠቡን ከቤተክርስቲያኗ አባልነት መገደብ ወይም ማስወገድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል (አልማ 39፥11 ይመልከቱ)። እነዚህን በማስተካከል እንጂ፣ ከባድ ኃጢያቶችን በመደበቅ ወይም በማሳነስ የቤተክርስቲያኗ ሀቀኝነት አይጠበቅም።
32.3
የእሥራኤል ዳኞች ሚና
ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች የእስራኤል ዳኛዎች እንዲሆኑ ይጠራሉ እንዲሁም ይለያሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥72–74 ይመልከቱ)። የቤተክርስቲያኗ አባላት ንስሐ እንዲገቡ በመርዳት ረገድ ጌታን ለመወከል የክህነት ቁልፎች አሏቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥1ን፤ 107፥16–18 ይመልከቱ)።
አብዛኛውን ጊዜ ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች በግል ምክር አማካኝነት ንስሃ መግባትን ያግዛሉ። ይህ እገዛ መደበኛ ባልሆነ ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶችን መገደብን ሊያካትት ይችላል።
ለአንዳንድ ከባድ ኃጢያቶች፣ መሪዎች የአባልነት ምክር ቤት በማካሄድ ንስሃ መግባትን ይደግፋሉ (32.6ን ይመልከቱ)። ይህ እገዛ መደበኛ በሆነ ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶችን መገደብን ወይም ከቤተክርስቲያኗ አባልነት መወገድን ሊያካትት ይችላል።
ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች አባላት ንስሃ እንዲገቡ በሚረዱበት ጊዜ አፍቃሪ እና ተንከባካቢ ናቸው። አዳኙ ስታመነዝር ከተያዘችው ሴት ጋር ያደረገው ግንኙነት መመሪያ ይሆናል (ዮሐንስ 8፥3–11 ተመልከቱ)። ኃጢያትዋ እንደተሠረየላት ባይናገርም፣ አልኮነናትም። ከዚያ ይልቅ “ከአሁን ጀምሮ ደግማ ኃጢያት እንዳትሰራ”—ንስሃ አንድትገባ እና ህይወቷን እንድትቀይር—ነገራት።
እነዚህ መሪዎች “ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢያተኛ በሰማይ ደስታ [እንደሚሆን]” ያስተምራሉ (ሉቃስ 15፥7)። እነርሱ ታጋሽ፣ ደጋፊ እና አዎንታዊ ናቸው። ተስፋንም ያነሳሳሉ። በአዳኙ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕትነት ምክንያት ሁሉም ንስሃ መግባት እና ንጹህ መሆን እንደሚችሉ ያስተምራሉ እንዲሁም ይመሰክራሉ።
ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች እያንዳንዱ ሰው ንስሃ እንዲገባ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ለማወቅ ከመንፈስ መመሪያን ይሻሉ። በጣም ከባድ ለሆኑት ኃጢያቶች ብቻ ነው መሪዎቿ ምን ዓይነት እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባቸው የተቀመጠ መስፈርት ቤተክርስቲያኗ ያላት (32.6 ይመልከቱ)። ሁለት ሁኔታዎች ተመሳሳይ አይደሉም። መሪዎች የሚሰጡት ምክር እና የሚያመቻቹት ንስሃ የመግባት ሂደት በመንፈስ የተነሳሳ መሆን አለበት እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሰው የተለየ ሊሆን ይችላል።
32.4
መናዘዝ፣ ሚስጥራዊነት እና ለመንግስት ባለስልጣናት ማሳወቅ
32.4.1
መናዘዝ
ንስሃ መግባት ለሰማይ አባት ኃጢያት መናዘዝን ይጠይቃል። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሏል “በዚህም ሰው ለኃጢያቶቹ ንስሀ እንደገባ ታውቃላችሁ—እነሆ፣ ይናዘዛቸዋል እናም ይተዋቸዋልም“ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥43፤ በተጨማሪም ሞዛያ 26፥29 ይመልከቱ)።
የቤተክርስቲያኗ አባላት ከባድ ኃጢያት በሚሰሩበት ጊዜ፣ ንስሃቸው ለኤጲስ ቆጶሳት እና ለካስማ ፕሬዚዳንቶች መናዘዝን ያካትታል። ከዚያም እነርሱን በመወከል የንስሐ ወንጌልን ቁልፎች መጠቀም ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥1፤ 84፥26–27፤ 107፥18፣ 20 ይመልከቱ)። ይህም በአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ኃይል እንዲፈወሱ እና ወደ ወንጌል መንገድ እንዲመለሱ ይረዳቸዋል።
የመናዘዝ አላማ፣ አባላት ለመለወጥ እና ለመፈወስ ሙሉ በሙሉ የጌታን እርዳታ ይፈልጉ ዘንድ ሸክማቸውን ከላያቸው እንዲያወርዱ ማበረታታት ነው። “የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ“ ማዳበር በመናዘዝ ይታገዛል (2 ኔፊ 2፥7)። በፈቃደኝነት የሚደረግ ኑዛዜ ሰው ንስሃ መግባት እንደሚፈልግ ያሳያል።
አንድ አባል በሚናዘዝበት ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በ32.8 ውስጥ የተቀመጠውን ምክር የመስጠት መመሪያ ይከተላል። አባሉ ንስሐ እንዲገባ ለመርዳት ስለሚቻልበት ተስማሚ ጊዜና ቦታ መመሪያ ለማግኘት በጸሎት መንፈስ ይጠይቃል። የአባልነት ምክር ቤት በዚህ ሊረዳ ይችል እንደሆነ ከግምት ውስጥ ያስገባል። የቤተክርስቲያኗ ፖሊሲ የአባልነት ምክር ቤት መጠራት እንደሚያስፈልግ የሚያመለክት ከሆነ፣ ይህንን ያብራራል (32.6 ይመልከቱ)።
አንዳንድ ጊዜ አባል የትዳር ጓደኛን ወይም ሌላ አዋቂን ጎድቶ ሊሆን ይችላል። እንደ ንስሐው አካል፣ እርሱ ወይም እርሷ አብዛኛውን ጊዜ ለዚያ ግለሠብ መናዘዝ እና ይቅርታ መጠየቅ አለበት/አለባት። አንድ ወጣት ከባድ ኃጢያት ከሰራ/ች ከአርሱ ወይም ከእርሷ ወላጆች ጋር እንዲማከር/እንድትማከር ይበረታታል/ትበረታታለች።
32.4.4
ሚስጥራዊነት
ኤጲስ ቆጶሳት፣ የካስማ ፕሬዚዳንቶች፣ እና አማካሪዎቻቸው የተሰጧቸውን ሚስጥራዊ መረጃዎች ሁሉ የመጠበቅ የተቀደሰ ሃላፊነት አለባቸው። ይህ መረጃ ከቃለ መጠይቅ፣ ከመማከር እና ከኑዛዜዎች ውስጥ ሊገኝ ይችላል። በአባልነት ምክር ቤት ውስጥ የሚሳተፉ ሁሉ ተመሳሳይ ምስጢር የመጠበቅ ግዴታው አለባቸው። ሚስጥራዊነት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም አባላት የሚያጋሩት ነገር በሚስጥር የማይያዝ ከሆነ ኃጢያቶችን ላይናዘዙ ወይም መመሪያ ላይፈልጉ ይችላሉ። መተማመንን ማፍረስ የአባላትን እምነት ይሸረሽራል እንዲሁም በመሪዎቻቸው ላይ እምነት እንዲያጡ ያደርጋቸዋል።
ኤጲስ ቆጶሳት፣ የካስማ ፕሬዚዳንቶች ወይም አማካሪዎቻቸው እነዚህን መረጃዎች ሚስጥራዊ ኃላፊነታቸውን በጠበቀ መልኩ፣ እንደሚከተለው ብቻ ሊያጋሩ ይችላሉ፦
-
የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድን ወይም ተዛማጅ ጉዳዮችን በተመለከተ ከአባሉ የካስማ ፕሬዚዳንት፣ የሚስዮን ፕሬዚዳንት ወይም ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር መነጋገር ያስፈልጋቸዋል።
-
የአባልነት ውሳኔዎችን ወይም ሌሎች አሳሳቢ ጉዳዮችን በመጠባበቅ ላይ እያሉ ግለሰቡ ወደ አዲስ አጥቢያ ይዘዋወራል (ወይም የክህነት መሪው ከጥሪው ይለቀቃል)።
-
አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ከአጥቢያው ወይም ከካስማው ውጭ የሚኖር የቤተክርስቲያኗ አባል በከባድ ኃጢያት ውስጥ ተሳታፊ ሊሆን እንደሚችል ያወቀ ከሆነ።
-
የአባልነት ምክር ቤት በሚካሄድበት ወቅት መረጃን መግለፅ አስፈላጊ ነው።
-
አንድ አባል፣ መሪው መረጃን ለተወሰኑ ሰዎች እንዲያካፍል ፍቃድ ለመስጠት ከመረጠ።
-
የአባልነት ምክር ቤት ውሳኔን አስመልክቶ የተወሰነ መረጃን ማካፈል አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
መሪዎችን የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ህጉን ለማክበር እንዲችሉ ለመርዳት እንዲቻል ቤተክርስቲያኗ በሰለጠኑ ባለሙያዎች እርዳታ ትሰጣለች። ይህንን መመሪያ ለማግኘት፣ መሪዎች አገልግሎቱ ባለበት ቦታ የቤተክርስቲያኗን የጥቃት እርዳታ መስጫ የስልክ መስመር ወዲያውኑ ይደውላሉ (38.6.2.1 ይመልከቱ)። አገልግሎቱ የማይገኝ ከሆነ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ በዋና አካባቢው ቢሮ የሚገኘውን የአካባቢውን የህግ አማካሪ ያነጋግራል።
አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት መጀመሪያ እንደዚህ አይነት መመሪያ ሳያስፈልገው ሚስጥራዊ መረጃን መግለጽ የሚኖርበት በአንድ ሁኔታ ውስጥ ብቻ ነው ። ይህም ለህይወት አስጊ የሆኑ ጥቃቶችን ወይም ከባድ ጉዳቶችን ለመከላከል ሲባል መረጃን መግለጽ አስፈላጊ ሲሆን እና መመሪያ ለመጠየቅ ጊዜ ከሌለው ነው። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ፣ ሌሎችን የመጠበቅ ግዴታ ሚስጥራዊ ከመሆን ግዴታ የበለጠ አስፈላጊ ነው። መሪዎች የመንግሥት ባለስልጣናትን በአስቸኳይ ማነጋገር አለባቸው።
32.6
የኃጢያቱ ክብደት እና የቤተክርስቲያኗ ፖሊሲ
የኃጢያት ክብደት (1) የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና (2) አንድ ግለሠብ ንስሐ እንዲገባ የሚረዳውን ሁኔታ ለመወሰን ጠቃሚ የሆነ ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ነገር ነው። ጌታ “ኃጢያትን በዝቅተኛ ደረጃ መመልከት አይቻለኝም” ብሏል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥31፤ በተጨማሪም ሞዛያ 26፥29) ይመልከቱ)። አገልጋዮቹ የከባድ ኃጢያት ማስረጃዎችን ችላ ማለት አይገባቸውም።
ከባድ ኃጢያቶች ሆን ተብሎ በእግዚአብሔር ህግጋት ላይ የሚፈጸሙ ትልቅ ወንጀሎች ናቸው። የከባድ ኃጢያት ምድቦች ከታች ተዘርዝረዋል።
-
የጠበኝነት ድርጊቶች እና ጥቃት
-
ወሲባዊ የስነምግባር ጉድለት
-
የማጭበርበር ድርጊቶች
-
እምነትን ማጉደል
-
አንዳንድ ሌሎች ተግባራት
የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ሲሆን ወይም ምናልባት አስፈላጊ ሲሆን
|
የኃጢያት አይነት |
የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው |
የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል |
|---|---|---|
የኃጢያት አይነት የጠበኝነት ድርጊቶች እና ጥቃት | የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው
| የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል |
የኃጢያት አይነት ወሲባዊ የስነምግባር ጉድለት | የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው
| የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል
|
የኃጢያት አይነት የማጭበርበር ድርጊቶች | የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው
| የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል
|
የኃጢያት አይነት እምነትን ማጉደል | የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው
| የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል
|
የኃጢያት አይነት አንዳንድ ሌሎች ተግባራት | የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው
| የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል
|
32.6.3
የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአባልነት ምክር ቤት ወይም ሌላ እርምጃ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ ከአካባቢ አመራር ጋር የሚማከሩበት ጊዜ
አንዳንድ ጉዳዮች ተጨማሪ ጥንቃቄ እና መመሪያ ያስፈልጋቸዋል። እንዴት በተሻለ ሁኔታ መርዳት እንደሚቻል ለማወቅ የካስማ ፕሬዚዳንቱ በዚህ ክፍል ውስጥ ስላሉት ሁኔታዎች ከዋና ካባቢ አመራር ጋር መማከር ይኖርበታል።
32.6.3.2
ክህደት
የክህደት ጉዳዮች ብዙውን ጊዜ ከአጥቢያው ወይም ከካስማው ወሰን ውጪ ተፅእኖ አላቸው። የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል በአፋጣኝ መፍትሄ ማግኘት አለባቸው።
የአንድ አባል ድርጊት ክህደትን ሊያመለክት እንደሚችል ከተሰማው ኤጲስ ቆጶሱ ከካስማ ፕሬዘደንቱ ጋር ይማከራል።
እዚህ ላይ ባለው አጠቃቀም፣ ክህደት ከሚከተሉት ውስጥ በአንዱ ውስጥ የሚሳተፍ አባልን ያመለክታል፦
-
በተደጋጋሚ ቤተክርስቲያኗን፣ ትምህርቶቿን፣ ፖሊሲዎቿን ወይም መሪዎቿን በግልፅ እንዲሁም ሆን ብሎ በገሃድ መቃወም
-
በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በካስማ ፕሬዚዳንቱ እርማት ከተሰጠው በኋላ የቤተክርስቲያኗ ትምህርት ያልሆነውን እንደ ቤተክርስቲያኗ ትምህርት በማስተማር መቀጠል
-
ሆን ብሎ የቤተክርስቲያኗን አባላት እምነት እና እንቅስቃሴ የማዳከም ስራ ልምድን ማሳየት
-
በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በካስማ ፕሬዚዳንቱ እርምት ከተሰጠው በኋላ የክህደት ኑፋቄ ትምህርቶችን መከተልን መቀጠል
-
በመደበኛነት ሌላ ቤተክርስቲያንን መቀላቀል እና አስተምህሮቶቹን ማስተዋወቅ
32.6.3.3
የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ መመዝበር
አንድ አባል የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ከመዘበረ ወይም የቤተክርስቲያኗን ውድ ንብረት ከሰረቀ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአባልነት ምክር ቤት ወይም ሌላ እርምጃ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ ከዋና አካባቢ አመራር ጋር ይማከራል።