መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
26.የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ


“26. የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 እ.አ.አ)]።

“26. የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ኤጲስ ቆጶስ አንድን ሰው ቃለ መጠይቅ እያደረገ

26.

የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ

26.0

መግቢያ

ወደ ጌታ ቤት መግባት ቅዱስ እድል ነው። ቤተመቅደስ አቅራቢያቸው ባይኖርም፣ ሁሉም አባላት ብቁ እንዲሆኑ እና የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ እንዲኖራቸው የአጥቢያ እና የካስማ መሪዎች ያበረታታሉ።

የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ ወደ ጌታ ቤት የሚገቡ ሁሉ ይህን ለማድረግ ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የተቻላቸውን ጥረት ያደርጋሉ (መዝሙረ ዳዊት 24፥3–5ን ይመልከቱ)።

ቤተመቅደስ ለመግባት አባላት የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል።

አንድ ኤጲስ ቆጶስ በዚህ ምዕራፍ ያልተመለሱ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድን የተመለከቱ ጥያቄዎች ካሉት ከካስማ ፕሬዚዳንቱ ጋር ይመክራል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ ጥያቄዎቹን በመያዝ የቀዳሚ አመራርን ሊያነጋግር ይችላል።

26.1

የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ዓይነቶች

ሶስት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ዓይነቶች አሉ።

  1. የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ላልተቀበሉ አባላት የሚሰጥ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ እነዚህ ፈቃዶች የሚሰጡት ከወላጆቻቸው ጋር ለሚታተሙ ወይም የውክልና ጥምቀት እና ማረጋገጫዎችን ለመቀበል ለተፈቀደላቸው አባላት ነው። በLeader and Clerk Resources (LCR [የመሪ እና የጸሀፊ ምንጭ]) በኩል ይሰጣሉ። ለተጨማሪ መረጃ 26.4ን ይመልከቱ።

  2. በህይወት ላሉ ለሚደረጉ ሥርዓቶች የሚሰጥ የቤተመቅደስ መግቢያ ፦ እነዚህ ፈቃዶች የራሳቸውን የመንፈስ ስጦታ ለሚቀበሉ ወይም ከትዳር ጓደኛቸው ጋር ለሚታተሙ አባላት ነው። በህይወት ላሉ ለሚደረጉ ሥርዓቶች የሚሰጠው ፈቃድ የመንፈስ ስጦታ ለተቀበሉ ከሚሰጠው ከመደበኛው የቤተመቅደስ ፈቃድ (ከዚህ በታች ተብራርቷል) ጋር ይያያዛል።

  3. የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ለተቀበሉ አባላት የሚሰጥ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ እነዚህ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዶች ቀደም ብለው የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ለተቀበሉ አባላት የሚሰጥ ነው። በLCR [የመሪ እና የጸሀፊ ምንጭ] በኩል ይሰጣሉ። አንድ አባል ለሞቱ በሚደረጉ በሁሉም የቤተመቅደስ ሥርዓቶች ላይ እንዲሳተፍ ፈቃድ ይሰጣሉ። በተጨማሪም አንድ የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ የተቀበለ አባል በህይወት ካሉ ወይም ከሞቱ ወላጆች ወይም ልጆች ጋር ሲታተምም ያገለግላሉ። ለተጨማሪ መረጃ 26.3ን ይመልከቱ።

26.2

ለቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ጥበቃ ማድረግ

26.2.1

የክህነት መሪዎች ለቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ጥበቃ ሲያደርጉ

የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ መፅሃፎችን እንዲይዙ ስልጣን የተሰጣቸው የክህነት መሪዎች በጥንቃቄ ጥበቃ ሊያደርጉላቸው ይገባል።

በተጨማሪም የክህነት መሪዎች ያልተፈቀደላቸው ግለሰቦች በLCR [የመሪ እና የጸሀፊ ምንጭ] ውስጥ የሚገኘውን የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ መረጃ ማግኘት አለመቻላቸውን ያረጋግጣሉ።

26.2.2

የጠፉ ወይም የተሰረቁ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዶች

አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዳቸው ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ፣ በተቻለ ፍጥነት እንዲያሳውቁት ኤጲስ ቆጶሱ ይጠይቃቸዋል። እርሱ፣ የተመደበ አማካሪ ወይም ጸሃፊ በተቻለው ፍጥነት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድን ለመጠቀም የማይቻል ለማድረግ LCR [የመሪ እና የጸሀፊ ምንጭን] ይጠቀማሉ። ይህን የማድረጊያ ዘዴ ከሌለ የቤተመቅደስ መግቢያው ፈቃድ ይሰረዝ ዘንድ ኤጲስ ቆጶሱ የቤተመቅደሱን ቢሮ ያነጋግራል።

26.2.3

የብቁነት መስፈርቶችን የማያሟሉ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ያዦች

የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ያለው አባል የብቁነት መስፈርቶችን (26.3ን ይመልከቱ) እየኖረ እንዳልሆነ ኤጲስ ቆጶሱ ካረጋገጠ፣ አባሉ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዱን እንዲመልስ ይጠይቃል። የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዱን ለመጠቀም የማይቻል ለማድረግ LCR [የመሪ እና የጸሀፊ ምንጭን] ይጠቀማል። ይህን የማድረጊያ ዘዴ ከሌለ የቤተመቅደስ መግቢያው ፈቃድ ይሰረዝ ዘንድ ኤጲስ ቆጶሱ የቤተመቅደሱን ቢሮ ያነጋግራል።

26.3

የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዶችን የመስጠት አጠቃላይ መመሪያዎች

የክህነት መሪዎች የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ መስጠት ያለባቸው አባሉ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ከመለሰ ብቻ ነው።

በካስማ ውስጥ፣ የካስማ አመራር አባል ወይም የካስማ ፀሐፊ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ከተሰጠ በኋላ በLCR [የመሪ እና የጸሀፊ ምንጭ] ውስጥ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርገዋል። በአውራጃ ውስጥ፣ ከሚስዮን አመራር አባላት አንዱ ወይም የሚስዮን ጸሃፊ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዱ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርገዋል። የውክልና ጥምቀት እና ማረጋገጫ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዶች ተቀባይነት ያላቸው የሚሆኑት በአንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ወይም በቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት ሲታተሙ ነው።

26.3.1

የአጥቢያ እና የቅርንጫፍ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለ መጠይቅ

በአጥቢያ ውስጥ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለ መጠይቆችን ያደርጋል እንዲሁም ብቁ ለሆኑ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድን ይሰጣል። በቅርንጫፍ ውስጥ፣ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለ መጠይቅ የሚያደርገው እና የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድን የሚሰጠው የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ ብቻ ነው።

በአጥቢያ ውስጥ፣ ኤጲስ ቆጶሱ የሚከተሉትን አባላት ቃለ መጠይቅ ያደርጋል፦

  • የራሳቸውን የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ለሚቀበሉ (27.1ን እና 27.2 ን ይመልከቱ)።

  • ከትዳር አጋራቸው ጋር ለሚታተሙ (27.3ን ይመልከቱ)።

ኤጲስ ቆጶሱ በሌለበት አስቸኳይ ጉዳዮች ከገጠሙ፣ ከአማካሪዎቹ አንዱ እነዚህን ቃለ መጠይቆች እንዲያደርግ ሊፈቅድ ይችላል።

ከላይ በተዘረዘሩት ሁኔታዎች መሰረት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ከመስጠቱ በፊት፣ ኤጲስ ቆጶሱ የቤተክርስቲያን አባልነት የእገዳ ማስታወሻ አለመኖሩን ለማረጋገጥ የአባሉን መዝገብ ይመረምራል። የራሳቸውን የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ለሚቀበሉ ወይም ከትዳር ጓደኛቸው ጋር ለሚታተሙ አባላት የሚከተሉትን ያረጋግጣል፦

  • የአባሉ ጥምቀት እና ማረጋገጫ በአባልነት መዝገብ ላይ መመዝገቡን።

  • ወንድሞች የመልከ ጼዴቅ ክህነትን መቀበላቸውን።

ከኤጲስ ቆጶስ አመራር አባላት በአንዱ ወይም በቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ ቃለ መጠይቁ ከተደረገ በኋላ፣ ከካስማ አመራር አባላት አንዱ በካስማ ውስጥ የሚኖሩ አባላትን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። ከሚስዮን አመራር አባላት አንዱ በአውራጃው ውስጥ ለሚኖሩ አባለት ሁለተኛውን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። ከቀዳሚ አመራር ፈቃድ ካልተሰጠው በስተቀር፣ የአውራጃ ፕሬዚዳንት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለ መጠይቅ አያደርግም።

26.3.2

ራቅ ባሉ ቦታዎች የሚኖሩ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለ መጠይቅ

አንዳንድ አባላት ከካስማ ወይም ከሚስዮን አመራር አባል ጋር ለመገናኘት ብዙ የጉዞ ወጪ በሚጠይቁ ወይም በጣም አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ይኖራሉ። በእነዚህ ሁኔታዎች አንድ የቤተመቅደስ ፕሬዚዳንት ግለሰቡን ቃለ መጠይቅ ሊያደርገው እና በቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ላይ ሊፈርም ይችላል። ቃለ መጠይቁን ከማድረጉ በፊት ከካስማ ወይም ከሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ጋር ይወያያል። ኤጲስ ቆጶሱ፣ ፈቃድ የተሰጠው አማካሪ ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ አስቀድመው አባሉን ቃለ መጠይቅ ያደረጉት እና በቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ላይ የፈረሙለት መሆን አለበት።

26.3.3

የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ለመስጠት ቃለ መጠይቅ ማከናወን

መሪዎች ማንኛቸውንም መስፈርቶች መጨመር ወይም መቀነስ አይገባቸውም።

የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለ መጠይቆች በችኮላ የሚደረጉ መሆን የለባቸውም። በሚስጥር የሚደረጉ መሆን አለባቸው። ሆኖም፣ ቃለ መጠይቅ የሚደረግለት ግለሰብ ከፈለገ ባለቤቱን፣ ወላጅን ወይም ሌላ አዋቂ ሰው እንዲገኝ ሊጋብዝ ይችላል።

26.4

የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ላልተቀበሉ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ መስጠት

26.4.1

አጠቃላይ መመሪያዎች

የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ላልተቀበሉ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ በሚከተለው ሁኔታ ይሰጣል፦

  • ዕድሜያቸው 11 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ፣ ለሞቱ ለመጠመቅ እና ማረጋገጫ ለመቀበል። (ወጣት ሴቶች እና የተሾሙ ወጣት ወንዶች 12 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት ውስጥ ካለው ጥር ጀምሮ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ለማግኘት ይችላሉ)።

  • ዕድሜያቸው ከ8 ዓመት እስከ 20 ዓመት ለሆኑ፣ ከወላጆቻቸው ጋር ለመታተም። ዕድሜያቸው ከ8 ዓመት በታች የሆኑ ከወላጆቻቸው ጋር ለመታተም የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ አያስፈልጋቸውም (26.4.4ን ይመልከቱ)።

  • ዕድሜያቸው ከ8 ዓመት እስከ 20 ዓመት ለሆኑ፣ በህይወት ያሉ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው፣ ከእንጀራ እናት ወይም አባት የተገኙ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው፣ ወይም በግማሽ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው የሆኑ ሲታተሙ ለመመልከት።

ከዚህ ቀደም የቤተመቅደስ ስጦታ የተቀበሉ አባላት በዚህ ክፍል ውስጥ ከተገለጹት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዶች ማንኛቸውም ውስጥ አንዳቸውም አይሰጧቸውም።

የክህነት ስልጣንን ለመሸከም እድሜው የደረሰ ወንድ አባል የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ከመቀበሉ በፊት ወደ ክህነት ክፍል መሾም ይኖርበታል።

26.4.2

የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድን አዲስ ለተጠመቁ አባላት መስጠት

ተገቢ ዕድሜ ላይ የደረሱ አዳዲስ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ በማግኘት የውክልና ጥምቀቶችን ማድረግ እና ማረጋገጫዎችን መቀበል ብቻ እንዲችሉ ኤጲስ ቆጶሱ ቃለ መጠይቅ ያደርጋቸዋል። አባላቱ ማረጋገጫ ከተቀበሉ በኋላ ወዲያውኑ፣ በተለምዶ በሳምንት ውስጥ፣ ይህንን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል (26.4.1ን ይመልከቱ)። ለወንድሞች፣ ይህ ቃለ መጠይቅ የአሮናዊ ክህነትን ለመቀበል የሚደረገው ቃለ መጠይቁ አካል ሊሆን ይችላል።

26.4.3

በውክልና ለመጠመቅ እና ማረጋገጫ ለማግኘት ብቻ የሚሆን የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ

በውክልና ለመጠመቅ እና ማረጋገጫ ለማግኘት የተሰጡ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዶች ለዚያ ዓላማ ብቻ መዋል ይኖርባቸዋል።

26.4.4

በህይወት ያሉ ልጆችን ከወላጆቻቸው ጋር ለማተም የሚሆን የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ

ዕድሜያቸው 21 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ አባላት ከወላጆቸቻቸው ጋር ሊታተሙ ወይም መታተምን መመልከት የሚችሉት (1) የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ የተቀበሉ ከሆኑ እና (2) የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ካላቸው ብቻ ነው።

26.5

የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዶችን በልዩ ሁኔታዎች ውስጥ መስጠት

26.5.1

የራሳቸውን የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ የሚቀበሉ አባላት

የራሳቸውን የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ለመቀበል የሚፈልጉ ብቁ አባላት የሚከተሉትን ሁኔታዎች ካሟሉ መቀበል ይችላሉ፦

  • ቢያንስ 18 ዓመት ሲሞላቸው።

  • የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ ወይም ተመጣጣኝ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወይም በአሁኑ ሰዓት እየተማሩ ያልሆኑ።

  • ማረጋገጫቸውን ከተቀበሉ አንድ ድፍን ዓመት ያለፋቸው።

  • በመላ ሕይወታቸው የተቀደሱ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን የመቀበል እና የማክበር ፍላጎት የሚሰማቸው።

በተጨማሪም፣ አንድ ሰው የራሱን የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ከመቀበሉ በፊት የመልከ ጼዴቅ ክህነት ሊኖረው ይገባል። የራሳቸውን የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ለመቀበል ስለሚዘጋጁ አባላት መረጃ ለማግኘት 25.2.8ን ይመልከቱ። የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታን ማን መቀበል እንደሚችል መረጃ ለማግኘት 27.2.1ን ይመልከቱ።

26.5.3

ከአገር ርቆ ከሚሰጥ አገልግሎት የሚመለሱ ወጣት ሚስዮናውያን

የሚሲዮን ፕሬዚዳንቱ፣ ሚስዮናዊው ወደ አገሩ ከሚመለስበት ቀን ጀምሮ በሶስት ወራት አገልግሎቱ እንዲያበቃ አድርጎ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዱ ላይ ቀኑን በመሙላት መሥራት እንዲጀምር ያደርገዋል።

በአገልግሎት ማብቂያው የመጨረሻ ሶስት ወር አካባቢ አዲስ የቤተመቅደስ መግቢያ ለመስጠት ኤጲስ ቆጶሱ ተመላሽ ሚስዮናውያንን ቃለ መጠይቅ ያደርጋቸዋል።

26.5.4

ራሳቸውን በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገልጹ ግለሰቦች

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበ አማካሪ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለ መጠይቅ ከማድረጉ በፊት ከቀድሞው ኤጲስ ቆጰስ ጋር ግንኙነት ያደርጋል።

26.5.7

ራሳቸውን በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገለጹ ግለሰቦች

የካስማ ፕሬዚዳንቱ እያንዳንዱን ሁኔታዎች በጥንቃቄ እና በክርስቶስ መሰል ፍቅር ለማየት ከዋና አካባቢው አመራር ጋር መምከር አለበት (38.6.23ን ይመልከቱ)።

26.5.8

ከባድ ኃጢያት የፈጸሙ አባላት

ከባድ ኃጢያት የፈጸመ/ች አባል ንስሃ እስኪገባ/ክትገባ ድረስ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ አያገኝም/አታገኝም (32.6ን ይመልከቱ)።

26.5.9

ከቤተክርስቲያን ከመወገድ ወይም በገዛ ፈቃድ ከቤተክርስቲያን ከመውጣት በኋላ ወደ ቤተክርስቲያኗ በድጋሚ የተቀላቀሉ አባላት

26.5.9.1

ከዚህ በፊት የቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ ያልተቀበሉ አባላት

እነዚህ አባላት በጥምቀት እና ማረጋገጫ እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ከተመለሱበት ቀን ጀምሮ እስከ አንድ ሙሉ አመት ድረስ የራሳቸውን የቤተመቅደስ ስጦታ መቀበል እንዲችሉ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዶች ሊሰጣቸው አይችሉም።

26.5.9.2

ከዚህ በፊት የቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ የተቀበሉ አባላት

ከዚህ በፊት የቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ ተቀብለው የነበሩ አባላት የበፊቱ የቤተመቅደስ በረከቶቻቸው በበረከቶች ዳግም መመለስ ስርዓት በኩል እስኪመለሱ ድረስ ማንኛውንም የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ለመቀበል አይችሉም።