ኑ፣ ተከተሉኝ
አባሪ ሐ፦ ለህፃናት ክፍል—የመዝሙር ጊዜ እና የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ፕሮግራም የማቅረብ መመሪያዎች


“አባሪ ሐ፦ ለህፃናት ክፍል—የመዝሙር ጊዜ እና የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ፕሮግራም የማቅረብ መመሪያዎች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን ፦ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 ( እ.አ.አ)]

“አባሪ ሐ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ)

ልጆች እየዘመሩ

አባሪ ሐ

ለመጀመሪያ ክፍል—የመዝሙር ጊዜ እና የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ዝግጅት የማቅረብ መመሪያዎች

የተቀደሰ መዝሙር ልጆቻችሁ ስለሰማይ አባት የደስታ እቅድ እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መሰረታዊ እውነቶችን እንዲማሩ ለመርዳት ሃይለኛ መሳሪያ ነው። ልጆች ስለወንጌል መርሆዎች ሲዘምሩ፣ መንፈስ ቅዱስ ስለ እውነትነታቸው ይመሰክራል። ቃላቱ እና መዝሙር በልጆቹ ልብ እና አዕምሮ ውስጥ በመላ ህይወታቸው ይቀመጣል።

ወንጌልን በመዝሙር አማካኝነት ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ የመንፈስን መርነት እሹ። ስለምትዘምሯቸው እውነቶች ያላችሁን ምስክርነት አካፍሉ። ልጆቹ፣ ስለመዝሙሩ በቤት እና በህፃናት ክፍሎች ውስጥ ከሚማሩት እና ከሚያጋጥሟቸው ነገሮች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እንዲመለከቱ እርዷቸው።

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ዝግጅት የማቅርብ መመሪያዎች

በኤጲስ ቆጶሱ አመራር፣ የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ዝግጅት የሚቀርበው በተለምዶ በአራተኛው ሩብ አመት ነው። እንደ የህፃናት ክፍል አመራር እና የመዝሙር መሪ፣ ዝግጅቱን ለማቀድ የህፃናት ክፍልን በበላይነት ከሚቆጣጠረው የኤጲስ ቆጶስ አማካሪ ጋር አብራችሁ ስሩ።

ፕሮግራሙ፣ ልጆቹ በዓመቱ ውስጥ የዘመሯቸውን የህፃናት ክፍል መዝሙሮች ጨምሮ፣ ልጆቹ እና ቤተሰቦቻቸው ከብሉይ ኪዳን በቤት እና በህፃናት ክፍል ውስጥ የተማሩትን እንዲያቀርቡ የሚፈቅድ መሆን ይገባዋል። ፕሮግራሙን ስታቅዱ ተሰብሳቢዎቹ በአዳኙ እና በትምህርቶቹ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ሊረዳ ስለሚችልባቸው መንገዶች አስቡ።

አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ልጆችን የያዙ የቤተክርስቲያኗ ክፍሎች፣ የቤተሰብ አባላት ከልጆቻቸው ጋር መሳተፍ የሚችሉባቸውን መንገዶች ሊያስቡ ይችላሉ። አንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ስብሰባውን አጠር ባለ ንግግር ሊዘጋ ይችላል።

ፕሮግራሙን ለማቅረብ ስትዘጋጁ፣ የሚከተሉትን መመሪያዎች አስታውሱ፦

  • በልምምዶች ጊዜ ከህፃናት ክፍል ወይም ከቤተሰባቸው እንዲለዩ የሚያደርግ አላስፈላጊ ጊዜ መኖር የለበትም።

  • የእይታ ማስተማሪያዎችን፣ አልባሳትን፣ እና ሚዲያዎችን በቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች ላይ መጠቀም ትክክል አይደለም።

አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል፣ 12.2.1.2፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ልጆች እየዘመሩ

የመዝሙር ጊዜ መመሪያዎች

5 ደቂቃ (የህፃናት ክፍል አመራር)፦ መክፈቻ ፀሎት፣ የቅዱሳት መጻህፍት ወይም የእምነት አንቀጾች፣ እና አንድ ንግግር

20 ደቂቃ (የመዝሙር መሪ)፦ የመዝሙር ጊዜ

የመጀመሪያ ክፍል አመራር እና የመዝሙር መሪ፣ ልጆች በትምህርት ክፍሎች እና በቤት እየተማሯቸው ያሉትን መርሆዎች ለማጠናከር የሚረዱ ለእያንዳንዱ ወር የሚሆኑ መዝሙሮችን ይመርጣሉ። እነዚህን መርሆዎች የሚያጠናክሩ መዝሙሮች ዝርዝር በዚህ መመሪያ ውስጥ ተካተዋል።

መዝሙሮችን ለልጆቹ በምታስተምሩበት ጊዜ፣ መዝሙሮቹ ስለሚያስተምሯቸው ታሪኮች እና ትምህርታዊ መርሆዎች አስቀድመው የተማሩትን እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። በመዝሙሮቹ ውስጥ ስለሚገኙት እውነቶች ያላቸውን ሃሳቦች እና ስሜቶች እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው።

በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ መዝሙርን በተመለከተ መሰረታዊ ግብአት የሚሆነው የልጆች መዝሙር መጽሃፍ ነው። በመዝሙር መጽሃፍ ውስጥ ያሉ መዝሙሮች እና በጓደኛ ውስጥ ያሉ መዝሙሮች ተገቢ ናቸው። እንዲሁም Hymns—For Home and Churchመጠቀም ትችላላችሁ። ማንኛውንም ሌላ መዝሙር በህፃናት ክፍል ውስጥ ለመጠቀም፣ ከኤጲስ ቆጶስ አመራር ፈቃድ መገኘት አለበት (አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ፣ 12.3.4)።

መዝሙር ለመዘመሪያ ግዜ

ጥር

  • My Heavenly Father Loves Me [የሰማዩ አባቴ ይወደኛል],” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 228–29

  • I Will Follow God’s Plan [የእግዚአብሔርን እቅድ እከተላለሁ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 164-65

የካቲት

  • Follow the Prophet [ነቢዩን ተከተሉ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 110፟–11

  • A Child’s Prayer [የልጅ ጸሎት]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 12–13

መጋቢት

  • Kindness Begins with Me[ደግነት ከኔ ይጀምራል]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 145

  • I Need Thee Every Hour [በየሰአቱ ታስፈልገኛለህ]፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 98

ሚያዝያ

  • ጌቴሴማኒ፣” የወንጌል ላይብረሪ

  • Keep the Commandments [ትዕዛዛቱን ጠብቁ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 146

ግንቦት

  • “Holy Places [የተቀደሰ ቦታ]” የወንጌል ላይብረሪ

  • As I Search the Holy Scriptures [ቅዱሳት መጻሕፍትን ስመረምር]፣” መዝሙር፣ ቁ. 277

ሰኔ

  • I Will Be Valiant [ጀግና እሆናለሁ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 162

  • Love One Another [እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 136

ሐምሌ

  • Search, Ponder, and Pray [ፈልጉ፣ አሰላስሉ እና ጸልዩ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 109

  • I Pray in Faith [በእምነት እፀልያለሁ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 14

ነሐሴ

  • Dare to Do Right [ትክክለኛውን ለማድረግ ድፈሩ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 158

  • I Feel My Savior’s Love [የአዳኜ ፍቅር ይሰማኛል]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 74–75

መስከረም

  • Teach Me to Walk in the Light [በብርሃኑ እንድጓዝ አስተምሩኝ]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 177

  • Love Is Spoken Here [እዚህ ፍቅር ይወራል]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 190–91

ጥቅምት

  • Seek the Lord Early [ቀድማችሁ ጌታን ፈልጉ]፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 108

  • I Lived in Heaven [በስማይ ኖራያለሁ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 4

ህዳር

  • Families Can Be Together Forever [ቤተሰቦች ለዘላለም አብረው ሊሆኑ ይችላሉ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 188

  • Choose the Right [ትክክለኛውን ምረጡ]፣” መዝሙር፣ ቁ. 239

ታህሳስ

  • We’ll Bring the World His Truth [ዓለምን ወደ እርሱ እውነት እናመጣለን]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 172–73

  • The Hearts of the Children [የልጆች ልብ]፣” የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 92፟-93

ትምህርትን ለማስተማር መዝሙርን መጠቀም

የመዝሙር ጊዜ ልጆች የወንጌልን እውነት እንዲማሩ ለመርዳት የታሰበ ነው። በመዝሙሮች እና በህፃናት ክፍል መዝሙሮች ውስጥ የሚገኙትን የወንጌል መርሆዎች ለማስተማር የሚያስችሉ መንገዶችን ስታቅዱ የሚከተሉት ሀሳቦች ሊያነሳሷችሁ ይችላሉ።

ተያያዥ ቅዱሳት መጻህፍትን አንብቡ።የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ እና በመዝሙር መጽሃፍ ውስጥ ለሚገኙ ለአብዛኞቹ መዝሙሮች ተያያዥ የሆኑ የቅዱሳት መጻህፍት ማጣቀሻዎች ተዘርዝረዋል። እነዚህን አንዳንድ ምዕራፎች እንዲያነቡ እርዷቸው እንዲሁም ቅዱሳት መጻህፍቱ ከመዝሙሮቹ ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ተናገሩ። ጥቂት የቅዱሳት መጻህፍት ማጣቀሻዎችን በሰሌዳው ላይ ልትዘረዝሩ እና ልጆቹ እያንዳንዱን ማጣቀሻ ከአንድ መዝሙር ወይም ከመዝሙሩ አንድ ሥንኝ ጋር እንዲያዛምዱ መጋበዝ ትችላላችሁ።

ባዶውን ቦታ ሙሉ። ብዙ ቁልፍ ቃላት የጎደሉትን የመዝሙሩን አንድ ሥንኝ በሰሌዳው ላይ ጻፉ። ከዚያም ልጆቹን፣ በባዶው ቦታ ውስጥ የሚሞሉትን ቃላት እያዳመጡ መዝሙሩን እንዲዘምሩ ጠይቋቸው። እያንዳንዱን ባዶ ቦታ በሚሞሉበት ጊዜ ከጎደሉት ቃላት ምን ዓይነት የወንጌል መርሆዎችን እንደምትማሩ ተወያዩ።

ልጆች እየዘመሩ

መስክሩ። በመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮች ውስጥ ስለሚገኙ የወንጌል እውነቶች ለልጆቹ አጭር ምስክርነት ስጡ። መዘመር ምስክርነት ሊሰጡ የሚችሉበት እና መንፈሱ እንዲሰማቸው የሚያደርግ አንድ መንገድ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ልጆቹን እርዷቸው።

ምስክር ሆናችሁ ቁሙ። ልጆች በየተራ በመቆም እየዘመሩት ካለው መዝሙር ምን እንደተማሩ ወይም መዝሙሩ ስለሚያስተምረው እውነት እንዴት እንደሚሰማቸው እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። መዝሙሩን በሚዘምሩበት ጊዜ እንዴት እንደሚሰማቸው ጠይቋቸው እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስን ተፅዕኖ እንዲለዩ እርዷቸው ።

ሥዕሎችን ተጠቀሙ። በመዝሙሩ ውስጥ ካሉ ጠቃሚ ቃላት ወይም ሀረጎች ጋር የሚሄዱ ምስሎችን በመፈለግ ወይም በመፍጠር እንዲረዷችሁ ልጆቹን ጠይቋቸው። ሥዕሎቹ ከመዝሙሩ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ እና መዝሙሩ ምን እንደሚያስተምር እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። ለምሳሌ “When He Comes Again [እንደገና ሲመጣ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ ቁጥር 82–83) የሚለውን መዝሙር እያስተማራችሁ ከሆነ (እንደ መላዕክትበረዶ፣ እና ኮከብየመሳሰሉ) በመዝሙሩ ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ቃላትን የሚያሳዩ ሥዕሎችን በክፍሉ የተለያዩ ቦታዎች ማስቀመጥ ትችላላችሁ። መዝሙሩን አብራችሁ በምትዘምሩበት ጊዜ፣ ልጆቹ ሥዕሎቹን እንዲሰበስቡ እና በትክክለኛው ቅደም ተከተል ከፍ አድርገው እንዲይዟቸው ጠይቋቸው።

ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮችን አካፍሉ። ስለመዝሙሩ ውይይት ለማነሳሳት ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገር መጠቀም ትችላላችሁ። ለምሳሌ “My Heavenly Father Loves Me [የሰማይ አባቴ ይወደኛል]” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 228–29) የሚለውን መዝሙር ስትዘምሩ፣ ወፍ፣ ዝናብ እና አበቦች ያሉ ነገሮችን ምሥሎች ለልጆቹ ልታሳዩአቸው ትችላላችሁ። ይህ የሰማይ አባት ፍቅር በዙሪያችን እንዴት ማግኘት እንደምንችል ወደ ውይይት ይመራናል።

የግል ተሞክሮዎችን ማካፈልን ጋብዙ። ልጆቹ መዝሙሩ የሚያስተምራቸውን መርሆዎች በእነዚህ መርሆዎች ላይ ካላቸው ተሞክሮዎች ጋር እንዲያዛምዱ እርዷቸው። ለምሳሌ “I Love to See the Temple [ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ]” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 95) የሚለውን መዝሙር ከመዘመራችሁ በፊት፣ ልጆቹ ቤተመቅደስ አይተው የሚያውቁ ከሆነ እጃቸውን እንዲያወጡ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። በሚዘምሩበት ጊዜ ቤተመቅደስን ሲያዩ ምን እንደሚሰማቸው እንዲያስቡ ጋብዟቸው።

ጥያቄዎችን ጠይቁ። መዝሙሮችን በምትዘምሩበት ጊዜ ልትጠይቋቸው የምትችሏቸው ብዙ ጥያቄዎች አሉ። ለምሳሌ ልጆቹ በመዝሙሩ ውስጥ ካሉ ከእያንዳንዱ ሥንኞች ምን እንደተማሩ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። መዝሙሩ የሚመልሳቸውን ጥያቄዎች እንዲያስቡ ልትጠይቋቸውም ትችላላችሁ። ይህም መዝሙሩ ስለሚያስተምራቸው እውነታዎች ውይይት ወደ ማድረግ ሊያመራ ይችላል።

ቀላል የእጅ እንቅስቃሴዎችን ተጠቀሙ። ልጆቹ የአንድን መዝሙር ቃል እና መልዕክት ለማስታወስ እንዲረዳቸው ቀላል የእጅ እንቅስቃሴዎችን እንዲያስቡ ጋብዟቸው። ለምሣሌ፣“Search, Ponder, and Pray [ፈልጉ፣ አሰላስሉ እና ጸልዩ]” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 109)፣ የሚለውን መዝሙር በምትዘምሩበት ጊዜ፣ በቅዱሣት መፃህፍት ውስጥ ስለመፈለግ በሚዘምሩበት ጊዜ ወደ ዓይኖቻቸው እንዲጠቁሙ፣ ስለማሰላሠል በሚዘምሩበት ጊዜ ወደ ጭንቅላታቸው እንዲጠቁሙ እንዲሁም ስለፀሎት በሚዘምሩበት ጊዜ እጆቻቸውን እንዲያጣጥፉ መጋበዝ ትችላለህ።