“የኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን አጠቃቀም፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ብሉይ ኪዳን 2026 (እ.አ.አ) [2026 ( እ.አ.አ)]
የኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን አጠቃቀም
ይህ ጽሁፍ ለማን ነው?
ኑ፣ ተከተሉኝ በግለሰብ ደረጃ፣ እንደ ቤተሰብ እንዲሁም በቤተክርስቲያን ክፍሎች ውስጥ መማር ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው ይሆናል። ከዚህ በፊት ቅዱሳት መጻህፍትን ዘወትር የማታጠኑ ከነበረ፣ ይህ ጽሁፍ እንድትጀምሩ ይረዳችኋል። ቀድሞውኑ በቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ጥሩ ልምድ ካላችሁ፣ ይህ ጽሁፍ የበለጠ ትርጉም ያለው ተሞክሮ እንዲኖራችሁ ይረዳል።
ግለሰቦች እና ቤተሰቦች በቤት
ከሁሉም የተሻለው ወንጌልን የመማሪያ ስፍራ ቤት ነው። በቤተክርስቲያን ያሉ አስተማሪዎቻችሁ ሊረዷችሁ ይችላሉ እንዲሁም ከሌሎች የአጥቢያ አባላት ማበረታቻ ልታገኙ ትችላላችሁ። ሆኖም በመንፈሳዊነት ለመጽናት እናንተ እና ቤተሰባችሁ እለት ተእለት “የእግዚአብሄርን መልካም ቃል” መመገብ (ሞሮኒ 6:4 ይኖርባቸኋል፤ እንዲሁም ራስል ኤም. ኔልሰን“Opening Remarks፣” ሊያሆና፣ ሕዳር 2018 [እ.አ፣አ] 6–8) ይመልከቱ።
ይህንን ጽሁፍ ለእናንተ በሚረዳ በማንኛውም መንገድ ተጠቀሙበት። መዘርዝሮቹ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙትን አንዳንድ ዘለአለማዊ እውነቶች ያጎላሉ። በተጨማሪም በግለሰብ ደረጃ፣ ከቤተሰባችሁ ወይም ከጓደኞቻችሁ ጋር ቅዱሳት መጻህፍትን ለማጥናት የሚረዱ ሃሳቦችን እና አክቲቪቲዎችን ይጠቁማሉ። በምታጠኑበት ጊዜ፣ ለእናንተ ትርጉም ያላቸውን ዘለአለማዊ እውነቶች እንድታገኙ የመንፈስን ምሪት ተከተሉ። እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን መልዕክት ፈልጉ እንዲሁም የምትቀበሏቸውን መነሳሳቶች ተከተሉ።
አስተማሪዎች እና ተማሪዎች በቤተክርስቲያን
ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ቤተክርስቲያን የልጆች ክፍል፣ የወጣቶች እና የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ቤት፣ የወጣት ሴቶች ክፍሎች እና የአሮናዊ ክህነት ቡድን የሰንበት ትምህርት ስርአተ ትምህርት ነው። ከእነዚህ በአንዱ ላይ የምታስተምሩ ከሆነ፣ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ያሉትን ማብራሪያዎች ለግል ጥናታችሁ እንዲሁም ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ እንድትጠቀሙ ትበረታታላችሁ። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የራሳችሁን ልምዶች በማግኘት ጀምሩ። እጀግ አስፈላጊው ዝግጅታችሁ የሚከናወነው ቅዱሳት ጽሁፎችን ስትመረምሩ እና የመንፈስ ቅዱስን መነሳሳትን ስትሹ ነው። ይበልጥ እንደ ሰማይ አባት እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትሆኑ የሚረዷችሁን ዘላለማዊ እውነቶች ፈልጉ። ኑ፣ ተከተሉኝ እነዚህን አንዳንድ እውነቶች እንድትለዩ እና የቅዱሳት ጽሁፎችን አንደምታ እንድትገነዘቡ ሊረዳችሁ ይቸላል።
ወንጌልን ለመማር ከሁሉም የተሻለው ቤትን ማዕከል ያደረገ እና በቤተክርስቲያን የተደገፈ ሲሆን እንደሆነ አስታውሱ፡፡ በሌላ አነጋገር የእናንተ ዋና ኃላፊነት የምታስተምሯቸው ሰዎች ወንጌልን በቤት ውስጥ ለመማር እና ለመኖር የሚያደርጉትን ጥረት መደገፍ ነው። በክፍል ውስጥ ለእነርሱ ስለምታቀርቡት የተለየ ይዘት አታስቡ። ከዚያ ይልቅ ልምዶቻቸውን፣ ሃሳቦቻቸውን እና በቤታቸው በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ስላነበቧቸው ምንባቦች ያሏቸውን ጥያቄዎች እንዲያካፍሉ እድሎችን ስጧቸው። ያገኟቸውን ዘለአለማዊ እውነቶች እንዲያጋሩ ጋብዟቸው። ይህ፣ የጽሁፍን የተወሰነ ክፍል ከመሸፈን የበለጠ አስፈላጊ ነው።
የወጣቶች እና የጎልማሶች የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍሎች
በሰንበት ትምህርት ቤት ክፍሎች የምንሰበሰብበት አንዱ ዋና ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል በምናደርገው ጥረት እርስ በርስ ለመደጋገፍ እና ለመበረታታት ነው። ይህንን ማድረግ የሚቻልበት ቀላሉ መንገድ “በዚህ ሳምንት ኑ፣ ተከተሉኝን በመጠቀም ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠኑ መንፈስ ቅዱስ ምን አስተማራችሁ?” የሚል ጥያቄን መጠየቅ ነው። የዚህ ጥያቄ መልሶች በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ ላይ ያለን እምነት ወደሚገነባ ትርጉም ያለው ውይይት ሊያመራ ይችላል።
ከዚያም በኑ፣ ተከተሉኝ ውስጥ ባሉት የጥናት ሐሳቦች ላይ በመመርኮዝ ውይይት እንዲደረግ መጋበዝ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ አንድ የጥናት ሃሳብ ኢሳይያስ 53ን በመመርመር የአዳኙን ተልእኮ የሚገልጹ ቃላትን መፈለግን ሊጠቁም ይችላል። የክፍል አባላት እነዚህ ቃላት ያነሳሷቸውን ሃሳቦች ወይም ስሜቶች እንዲያካፍሉ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። የክፍል አባላት ያገኟቸውን ቃላት እንዲያካፍሉ እና እንዲናገሩ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ወይም ጊዜ ወስዳችሁ እነዚህን ጥቅሶች በክፍል ደረጃ በጋራ ልታጠኗቸው ትችላላችሁ።
የአሮናዊ ክህነት ቡድኖች እና የወጣት ሴቶች ክፍሎች
የአሮናዊ ክህነት ቡድኖች እና የወጣት ሴቶች ክፍሎች በየእሁዱ በሚገናኙበት ጊዜ፣ ዓላማቸው በተወሰነ መልኩ ከሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል የተለየ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመማር ረገድ እርስ በርስ ከመረዳዳት በተጨማሪ እነዚህ ቡድኖች የመዳን እና በዘላለም ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግ ስራን ስለማከናወን በጋራ ለመምከር ይገናኛሉ (አጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ፣ 1.2 ተመልከቱ)። ይህንን በክፍል እና በቡድን አመራሮች መመሪያ ያደርጋሉ።
በዚህ ምክንያት፣ እያንዳንዱ የቡድን ወይም የክፍል አመራር አባል ለምሳሌ ወንጌልን በመኖር፣ የተቸገሩ ሰዎችን በማገልገል፣ ወንጌልን በማካፈል ወይም በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ሥራ በመሳተፍ ረገድ ስለሚደረጉ ጥረቶች የተመለከተ ውይይትን በመምራት መጀመር አለበት።
ከዚህ በጋራ ክሚመካከሩበት ጊዜ በኋላ አንድ አስተማሪ ወንጌልን በአንድ ላይ በመማር ረገድ ክፍሉን ወይም ቡድኑን ይመራል። ጎልማሳ መሪዎች ወይንም የክፍል ወይንም የቡድን አባላት እንዲያስተምሩ ሊመደቡ ይችላሉ። የክፍል ወይንም የቡድን አመራር ከጎልማሳ መሪዎች ጋር በመመካከር እነዚህን ምደባዎች ያከናውናሉ።
እንዲያስተምሩ የሚመደቡ ሰዎች በኑ፣ ተከተሉኝ ሳምንታዊ መዘርዝር ውስጥ ባሉት የመማር ሃሳቦች በመጠቀም መዘጋጀት አለባቸው። በያንዳንዱ መዘርዝር ውስጥ ያለው ይህ ምልክት በተለይ ለወጣቶች የሚሆን አክቲቪቲን ያሳያል። ሆኖም በመዘርዝሩ ውስጥ ያሉት ማንኛቸውም ሃሳቦች ለወጣቶች እንደትምህርት እክቲቪቲ በመሆን ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።
ለቡድን ወይም ለክፍል ስብሰባዎች ናሙና አጀንዳ ለማግኘት አባሪ መን ተመልከቱ።
የመጀመሪያ ክፍል
የመጀመሪያ ክፍልን ለማስተማር የምታደርጉት ዝግጅት የሚጀምረው በግል እንዲሁም ከቤተሰባችሁ ጋር መጽሐፈ ሞርሞንን በምታጠኑበት ጊዜ ነው። ይህንን ስታደርጉ፣ በመጀመሪያ ክፍላችሁ ውስጥ ያሉትን ልጆች አስመልክቶ ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጡ መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን እና ሃሳቦችን ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ። ጸልዩ፤ ከዚያም መንፈስ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲማሩ እንድትረዷቸው በሃሳቦች ሊያነሳሳችሁ ይችላል።
ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ፣ በኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን የማስተማሪያ ሃሳቦች በማገላበጥ ተጨማሪ መነሳሳትን ልታገኙ ትችላላችሁ። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ መዘርዘር “ልጆችን ለማስተማር የሚጠቅሙ ሃሳቦች” የሚል ክፍል አለው። እነዚህን ሀሳቦች መነሳሳት እንዲሰማችሁ እንደሚያደርጉ ጥቆማዎች ውሰዷቸው። በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ያሉትን ልጆች ታውቋችዋላችሁ—እንዲሁም ከእነርሱ ጋር በክፍል ውስጥ በምትገናኙበት ጊዜ የበለጠ ታውቋችዋላችሁ። እግዚአብሄርም ያውቃቸዋል፤ ስለዚህም እነሱን ለማስተማር እና ለመባረክ በምትችሉባቸው ከሁሉም የተሻሉ መንገዶች ያነሳሳችኋል።
በክፍላችሁ ያሉ ልጆች በኑ፣ ተከተሉኝ ውስጥ ያሉትን አንዳንድ መልመጃዎች አስቀድመው ሰርተው ሊሆን ይችላል። ያ መልካም ነው። መደጋገም ጥሩ ነው። ልጆቹ በቤት የተማሯቸውን ነገሮች አንዳቸው ለሌላቸው እንዲያካፍሉ መጋበዝን ግምት ውስጥ አስገቡ—ሆኖም፣ ልጆች በቤት ውስጥ ባይማሩም እንኳን ሊሳተፉ የሚችሉባቸውን መንገዶች ማቀድም አለባችሁ። ልጆች እነዚህን እውነቶች በተለያዩ አክቲቪቲዎች በተደጋጋሚ ሲማሩ የወንጌልን እውነቶች በላቀ ብቃት ይማራሉ። አንድ የመማር አክቲቪቲ ለልጆቹ ውጤታማ ሆኖ ካገኛችሁት በተለይ ትንንሽ ልጆችን እያስተማራችሁ ከሆነ ድገሙት። ባለፈው ትምህርት ጥቅም ላይ የዋለ አክቲቪቲን መከለስም ትችላላችሁ።
አምስት እሁዶች ባሏቸው ወራት ውስጥ፣ የልጆች ክፍል አስተማሪዎች በአምስተኛው እሁድ መርሐ ግብር የተያዘለትን ኑ፣ ተከተሉኝ መዘርዝር በ“አባሪ ለ፦ ለልጆች ክፍል—ልጆችን ለእድሜልክ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ እንዲሆኑ ማዘጋጀ” ውስጥ ባሉት አንድ ወይም ከአንድ በላይ የትምህርት አክቲቪቲዎች እንዲተኳቸው ይበረታታሉ።