ሊያሆና
የምድር ቤተሰቦችን በሙሉ መባረክ
መጋቢት 2026 (እ.አ.አ) ሊያሆና


“የምድር ቤተሰቦችን በሙሉ መባረክ፣” ሊያሆና፣ መጋቢት 2026 (እ.አ.አ)።

ወርኃዊ የሊያሆና መልዕክት፣ መጋቢት 2026 (እ.አ.አ)

የምድር ቤተሰቦችን በሙሉ መባረክ

የሰማዩ አባታችን ለቤተሰቦች ያለውን እቅድ ብንከተል እና ለሌሎች ብናካፍል፣ እርሱ ከእኛ ጋር ይሆናል፣ ይደግፈናል እንዲሁም ወደ እርሱ ዳግም ለመመለስ በምናደርገው ጉዞ አብሮን ይሆናል።

ያዕቆብ ራእይን ሲቀበል የሚያሳይ ምሥል

የያዕቆብ ህልም በቤቴል፣፣ በ ጄ. ኬን ስፔንሰር

በቅርቡ፣ እህት ኡክዶርፍ እና እኔ የልጅ ልጆቻችን ከሆኑት በአንዱ ጥምቀት ላይ ተገኝተን ነበር። ብዛት ያላቸው ትውልዶች በደስታ ይህንን ክስተት ሲያከብሩ ባየን ጊዜ፣ የሰማዩ አባታችን ለልጆቹ ስላለው የደህንነት እቅድ ጥልቅ የሆነ ምስጋና ተሰማን። ከጅምሩ ቤተሰብ እና የተቀደሱ ስርዓቶች ምን ያህል ለእርሱ አስፈላጊ እንደሆኑ ተሰምቶናል።

ያም አስፈላጊነት ሚስት ለማግኘት ረዥም እና አድካሚ ጉዞ በተጓዘው፣ በቃል ኪዳን ውስጥ ጋብቻን በፈፀመው እና ቤተሰብ በመሰረተው ታማኝ በሆነው የብሉይ ኪዳን ዘገባ ውስጥ ባለው በያዕቆብ ሊታይ ይችላል። በአንድ ምሽት፣ ያዕቆብ ሌሊቱን ያርፍ ዘንድ ቆም አለ ነገር ግን ያገኘው የድንጋይ ትራስ ብቻ ነበር። እጅግ ተዳክሞ ስለነበር እንቅልፍ ወሰደው—እንዲሁም ህልም አየ።

ያዕቆብ ብቁ የሆኑትን የቃልኪዳን ጋብቻ ግቦች እና ቤተሰብ እያሰበ “በምድር ላይ የተዘረጋ እና ጫፉም ወደ ሰማይ የደረሰ መሰላል፤ እናም እነሆ የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡ እና ሲወርዱ ተመለከተ።

“እና፣ እነሆ፣ ጌታም በላዩ ቆሞ ነበር፣ እናም አለ፣ እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ እና የይስሃቅ አምላክ ነኝ” (ዘፍጥረት 28፥12-13)።

ጌታም ለያዕቆብ አንዳንድ የቃልኪዳን የተስፋ ቃሎችን አደረገ--ይህንንም ቃልኪዳን ከያዕቆብ አባት ከይስሃቅ፣ እና ከአያቱ ከአብርሃም ጋር እንዲሁ አድርጓል፤

  • የተስፋ ቃሎቹም ያእቆብ “የብዙ ህዝብ” አባት እንደሚሆንም የሚያጠቃልል ነበር (ዘፍጥረት 28፥3፤ በተጨማሪም ቁጥር 14ተመልከቱ)።

  • ለያዕቆብ ዘር ቃል የተገባ መሬት ( ዘፍጥረት 28፥4፣ 13ተመልከቱ)።

  • በያዕቆብ እና ‘’በዘሩ የምድር ቤተሰቦች ሁሉ ይባረካሉ” (ዘፍጥረት 28፥14የሚል ተስፋ (ማብራሪያ ተታከለበት)።

የያዕቆብም ልምምድ እጅግ የተቀደሰ ከመሆኑ የተነሳ እንዲህ አለ፤ ”በእውነት እግዚአብሄር በዚህ ስፍራ ነው”… ይህ ሌላ አይደለም ነገር ግን የእግዚአብሔር ቤት ነው፣ እናም የመንግስተ ሰማያት በር ነው”(ዘፍጥረት 28፥ 16-17)። እና በመሆኑም ቤቴ-ል፣ ‘’የእግዚአብሔር ቤት’’ ማለት ነው (ዘፍጥረት 28፥19፣ የግርጌ ማስታወሻ )።

በያእቆብ ህልም ውስጥ የተሰጡት ተስፋ የተደረጉ በረከቶች ያዕቆብ በእውነተኛው ህይወት መሰል የሽቅብ ጉዞዎችን እንደሚያደርግ ነበር። እንደኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ በጌታ ቃልኪዳን እና በጌታ ቤት መካከል ያለውን ግንኙነት በያእቆብ ህልም ውስጥ ለማየት የሚከብድ አይደለም። ቤተመቅደስ ማለት ያ ያዕቆብ እንዳየው መሰላል ነው። የጌታ ቤት ትምህርቶች፣ ስርዓቶች፣ እና ቃልኪዳኖች መንግስተ ሰማያትን እና ምድርን የሚያገናኙ ናቸው። ቃልኪዳኖቹ ወደ ጌታ በሚያቀርቡን የመሰላሉ ደረጃዎች ሊመሰሉ ይችላሉ። እናም በተቀደሱ ቤተመቅደሶች ውስጥ በምናቀርባቸው አገልግሎቶች አማካይነት—ያለፉትን፣ አሁን ያሉትን፣ እና የወደፊቶቹን ‘’የምድር ቤተሰቦች ሁሉ’’ እየባረክናቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው።

“እንዴት ያለ ግኝት ነው!”

ሽማግሌ ብሩስ ሲ. ሃፈን፣ የተከበሩ የሰባዎቹ አባል፣ በአንድ ወቅት ከብሄራዊ ዜና መጽሔት አዘጋጅ የስልክ ጥሪ ደረሳቸው። አዘጋጁም በተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ ስለ መንግስተ ሰማያት ያሉ እምነቶችን ስለሚዳስሰው መጽሀፍ ለመነጋገር ፈልጎ ነበር።

‘’ደራሲዎቹም ህዝቡ ለመንግስተ ሰማይ--እና በሰማይ ስለሚሆኑ ቤተሰቦች እጅግ የበዛ ረሃብ ያደረበት መሆኑን፣’’ ሽማግሌ ሃፈን ጽፈዋል። ነገር ግን ብዙ ሰዎች አሁንም ከሞት በኋላ ህይወት መኖሩን፣ የዘለዓለም ህይወት፣ እና በሰማይ የቤተሰብን በአንድ ላይ መሆን አምነዋል፣ ከአንድ፤ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በቀር-- ‘’ብዙ የክርስቲያን ቤተክርስቲያናት ለዚህ ውስጣዊ ረሃብ ጥቂት ምላሽ ነው የሚሰጡት።

በአዳኙ ዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀደሱ መቅደሶች አሉን። ከአካላዊው ሞት በኋላ ከሚባርክ የመጣመር ስልጣን ጋር ዘለዓለማዊ ጋብቻ አለን። በአብ እና በወልድ ፊት ከምንወዳቸው ጋር ዘለዓለማዊ የተስፋ ቃል አለን። ከዚህ ሁሉ ጋር፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መንግስተ ሰማይ እጅግ የተሟላ ነው በማለት ደራሲው ያጣቃልላል--እንዲሁም ፍጹም ደስታ ያለበት በማለት አክልበታለሁ።

“እንዴት ያለ ግኝት ነው!” ሽማግሌ ሃፈን በማስተዋልም፣ “ብዙ ሰዎች ዛሬ ዘለዓለማዊ ቤተሰብን ይጓጓሉ፣ እናም [ዳግም የተመለሰው የክርስቶስ ወንጌል] ከየትኛውም ከታወቀ የሃሳብ ስብስብ [ወይም ሃይማኖት] በተሻለ ሁኔታ ያንን ጉጉት የሚያሳካ ነው። ልጆቻችን ‘ቤተሰቦች ለዘለዓለም በአንድነት መሆን ይችላሉ’ ብለው የዘመሩትን መላው ዓለም ሊሰማው ቢችል እመኛለሁ።’’

ቤተሰቦች እንዲሁ ብቻ አመቺ ማህበራዊ ቅንጅቶች አይደሉም። የመንግስተ ሰማያት ዘለዓለማዊ ንድፍ ናቸው። እነርሱ ‘’የፈጣሪ የልጆቹ ዘለዓለማዊ ዕጣ ፈንታ ማእከላዊ እቅድ ናቸው።’’ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን (1924–2025 [እ.አ.አ]) እንዳስተማሩን፣ ‘’[ጌታ] ምድርን የፈጠረው አካላዊ ሰውነትን እንድናገኝ እና ቤተሰብን እንድንመሰርት ነው። ቤተሰቦችን ከፍ ለማድረግ ቤተክርስቲያኑን መሰረተ። ቤተሰቦችም ለዘለዓለም በአንድነት ይሆኑ ዘንድ ቤተመቅደሶችን አዘጋጀ።’’

ነገር ግን የእኛ ጠንካራ ቤተሰብን መሻት ለዘለዓለም እጣፈንታ ብቻ አይደለም። ቤተሰብ በምድራዊ ደስታችንም ውስጥ እንዲሁ ጉልህ ሚናን ይጫወታል። አሁን እና በዘለዓለም ውስጥ ደስታን የሚያመጣው ምን እንደሆነ የሚያውቀው የሰማዩ አባታችን፣ ልጆቹን--ፍጹም የሆኑ ባይመስሉም--ወደ ቤተሰብ ይልካል እና ጠንካራ ቤተሰብን እንድንገነባ እና እንድንኮተኩት ይጋብዘናል። በርግጥ የአካል ጉዳት፣ ሞት፣ ወይም ሌሎች ሁኔታዎች የግል ልምምዶችን አስፈላጊ ያደርጓቸዋል።” ነገር ግን ምንም ነገር አስፈላጊውን፣ የባል እና የሚስትን፣ የአባት እና የእናትን በመለኮታዊነት የተሰጡ ሃላፊነቶች ሊቀይር አይችልም።

‘’በስነፍጥረት፣ የተጣመሩ፣ የሁለት ወላጆች ቤተሰቦች’’ ቤተሰብ ‘’የጠለቀ የፍቅር እና የመተሳሰብ ቁርኝትን’’ ለማቆየት አስፈላጊነቱ የሚቀጥል መሆኑን ጥናቶችም ያሳያሉ። ‘’የተረጋጋ፣ በአግባቡ የተስተካከለ፣ እና በማህበራዊነት ንቁ የሆነ ግለሰብን ለመፍጠር ቀዳሚው መፈልፈያ’’ ነው።

ትጉህ የሆኑ የቤተሰብ ተከላካዮች

በርግጥ፣ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ተቃርኖ የሚገጥመው መሆኑ ሊያስገርመን አይገባም። ሰይጣን ለቤተሰብ የተመቸ ሆኖ አያውቅም፣ እናም ‘’ጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳለው የሚያውቅ በመሆኑ ምክንያት’’ ጥረቶቹ በችኮላ እየሆኑ መጥተዋል (ዮሐንስ ራእይ 12፥12)። ፕሬዘዳንት ኤም ራሰል ባላርድ (1928-2023)፣ የአስራ ሁለቱ ሃዋርያት ቡድን ተጠባባቂ ፕሬዘዳንት ሲናገሩ፣ “ሰይጣን የጌታን ስራ ለማወክ እርግጠኛው እና ይበልጥ ውጤታማው መንገድ የቤተሰብን ውጤታማነት እና ቤትን ቅድስና ማኮሰስ እንደሆነ ያውቃል።”

ስለ እግዚአብሄር ዘለዓለማዊ ቤተሰብ፣ እርሱ ለልጆቹ ያለውን እቅድ፣ እና የቤተሰብን ግንኙነት ዘለዓለማዊ አስፈላጊነት የምናውቀውን በማወቃችን፣ በዓለም ላይ ካሉ ዋናዎቹ የቤተሰብ ተከላካዮች መካከል ልንሆን ይገባል።

ይህን ልናደርግ የምንችለው እንዴት ነው?

ፕሬዘዳንት ዳሊን ኤች. ኦክስ ይህንን ምክር ለግሰዋል፤ “የቤተሰብ አዋጅ… በቤተሰብ ላይ በአሁን ጊዜ እየመጡ ካሉት ተግዳሮቶች ልንጠበቅ የምንችልበት የጌታ የወንጌል እውነት ማሳሰቢያ ነው።”

በግል ህይወታችን ውስጥ፣ የቤተሰብን ግንኙነት ሊያጠናክሩ የሚችሉ “ትንሽ እና ቀላል ነገሮችን” ልናደርግ እንችላለን (አልማ 37፥6)። ይህ በአዋጁ ውስጥ የተጠቀሱትን የሚከተሉትን የስኬታማ ቤተሰብ መርሆችን፣ “እምነት፣ ጸሎት፣ ንስሀ መግባት፣ ምህረት፣ ክብር፣ ፍቅር፣ ርህራሄ፣ ስራ እና ጤናማ የሆኑ የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች” ያጠቃልላል። አሁን ያለው የቤሰባችን ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣ በድርጊቶቻችን የቤተሰብ ግንኙነት በዘለዓለማዊነት ለእኛ አስፈላጊ መሆኑን ልናሳይ እንችላለን።

“ሃላፊነት እንደሚሰማው ዜጋ” በማህበረሰባችን ውስጥ፣ “ቤተሰብን ለመጠበቅና ለማጠናከር የተነደፉትን እርምጃዎች ለማስተዋወቅ” መጀመር እንችላለን።

እኛ የጌታ የኋለኞቹ ቀናት የቃል ኪዳን ህዝቦች ነን። እኛ ቤተሰብን በሚመለከት በሁሉም ነገር ግንኙነት ያላቸውን የተስፋ ቃሎች--ለአብርሃም፣ ለይስሃቅ፣ እና ለያእቆብ የተሰጡትን የተስፋ ቃሎች ወራሽ ነን። እነዚህ የተስፋ ቃሎች “የምድርን ቤተሰቦች ሁሉ” ለመባረክ ከተቀደሰ ጥሪ ጋር የመጡ ናቸው። እና ያንን ለማድረግ አንድ አስፈላጊው መንገድ “ቤተሰብ በእግዚአብሄር የተመሰረተ” እና ‘’በቅዱስ ቤተ መቅደሶች የሚገኙትም ቅዱስ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖችም ግለሰቦች ወደ እግዚአብሔር ፊት እንዲመለሱ እና ቤተሰቦችም ለዘላለም እንዲጣመሩ ያስችላቸዋል” የሚለውን ዘለዓለማዊ እውነት በመኖር፣ በመከላከል እና ይህንንም እውነት ለሌሎች በማካፈል ነው።

“እኔ ከአንተ ጋር ነኝ”

እህት ኡክዶርፍ እና እኔ ቤተሰባችን ከተወደደው የሰማይ አባት ጋር የተቀደሱ ስርዓቶችን ሲያደርጉ ባየን ጊዜ ልባችን በሃሴት እና በምስጋና ተሞላ። በልጆቻችን እና በልጆቻቸው ብቻ ሳይሆን በወላጆቻችችን እና በወላጆቻቸው ጭምር ሃሴት እናደርጋለን። የወንጌል ቃልኪዳኖች ምን ያህል ከትውልድ ባሻገር አንድ እንደሚያደርገን ከጠለቀ ፍቅር ጋር እናሰላስለዋለን። ይህ “በምድር ላይ የተዘረጋ እና ጫፉም ወደ ሰማይ የደረሰ መሰላል፤ እናም እነሆ የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡ እና ሲወርዱ” ከነበረበት ልምድ የተለየ አይደለም። (ዘፍጥረት 28፥12)።

ጌታ ለያእቆብ በህልሙ ተስፋ የገባቸው በረከቶች እኔ እና እናንተን ጨምሮ—ለቃል ኪዳን ልጆቹ በሙሉ የሚተላለፉ ናቸው። ጌታ ለያእቆብ እንዳደረገው እኛም ከመረጥነው “በጭንቀት ቀኖቻችን” ይመልስልናል።(ዘፍጥረት 35፥3)

“እነሆ፣” ጌታም ሲናገር፣ “እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፣ በሄድክበት በሁሉም እጠብቅሃለሁ፣… አልተውህም” (ዘፍጥረት 28፥15)።

እንደ ያእቆብ ሁሉ፣ ሁላችንም የምንሻገረው ምድረ በዳ አለን። አንዳንድ ጊዜ ቃል የተገቡልን በረከቶች ሩቅ ይመስላሉ። ከባድ የሆኑ ችግሮች እና ተግዳሮቶች ሲመጡ፣ የጌታን ፍቅር ጥያቄ ውስጥ እናስገባ ይሆናል። ምናልባትም እግዚአብሄር ትቶናል በማለት እናስብ ይሆናል። በደቀመዝሙርነታችን ከሚገጥሙን መልካም ጥረቶች በተቃራኒ፣ ተስፋ ያደረግናቸውን በረከቶች እየተቀበልን እንዳልሆነ ይሰማናል።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ውድ ጓደኞች፣ ምናልባት አንዳንድ ጊዜ በእንባ የራሰ ቢመስልም የቃልኪዳኑ መንገድ የደስታ መንገድ ነው። ምናልባት ያ የደስታ እቅድ አሁን በህይወታችሁ የተፈጸመ መስሎ የማይሰማችሁ እንኳ ቢሆን እባካችሁ ጌታ እንደሚያስታውሳችሁ እና በእርሱ ጥበብ መሰረት በራሱ ጊዜ እንደሚባርካችሁ እመኑ።

በኢየሱስ ክርስቶስ እና በእርሱ የተስፋ ቃል ያለ እምነት ወደ ፊት እንድናይ ያነሳሳናል እንጂ ወደ ኋላ እንድናይ አያደርገንም። በእርሱ ምክንያት ቀድሞ በተከሰቱ ማናቸውም ነገሮች በእስራት ውስጥ በመጋረድ የወደፊት ህይወታችንን ወይም አሁን ያለንን እይታ እንዲጋርግብን ልንፈቅድ አይገባም። አዎን፣ ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ልንቆስል እንችላለን። ነገር ግን በታላቁ ፈዋሽ እናምናለን። በርግጥ “ምንም እንኳ የራቁ ቢሆኑም እንኳ” የእርሱን የተስፋ ቃሎች ሙሉ ለሙሉ “በመታመን” እርሱን እናምነዋለን (ዕብራውያን 11፥13)።

ፕሬዘደንት ኔልሰን እንደተናገሩት፣ “በጌታ በራሱ መንገድ እና ጊዜ፣ ምንም አይነት በረከት ለታማኝ ቅዱሳኑ እንደማይከለከል ልናስታውስ ይገባል።’’ “ጌታ ለእያንዳንዱ ግለሰብ እንደ ልቡ ፍላጎት እና ተግባሩ ይፈርዳል እናም ይሸልማል።”

የሰማይ አባታችንን ለቤተሰቦች እቅድ ስንከተል እና ስናካፍል ከእኛ ጋር እንደሚሆን ፣ እንደሚደግፈን እና በጉዟችን ውስጥ አብሮን እንደሚሆን ቃል እገባለሁ ። በተለይም ፈተና በእኛ ላይም ሆነ በምንወዳቸው ላይ ሲመጣ እርሱ በጭራሽ ብቻችንን አይተወንም። እርሱ ይሸከመናል፣ ያነሳናል፣ እና ከእርሱ ጋር፣ ከልጁ ጋር እና ለዘለዓለም ከቤተሰቦቻችን ጋር ወደ ተስፋይቱ ምድር የደስታው ሙላት ያመጣናል።

ማስታወሻዎች

  1. ሜሪየን ጂ. ሮምኒ፣ “Temples--The Gates to Heaven፣” ኤንዛይን፣ መጋቢት 1971 (እ.አ.አ)፣ 16 ተመልከቱ።

  2. ብሩስ ሲ. ሃፈን፣ Covenant Hearts: Marriage and the Joy of Human Love (2005)፣ 58-59።

  3. ብሩስ ሲ. ሃፈን፣ Covenant Hearts፣ 59፤ እንዲሁምFamilies Can Be Together Forever, መዝሙሮች፣ ቁ. 300 ተመልከቱ።

  4. ቤተሰብ፦ ለአለም አዋጅ፣” የወንጌል ላይብረሪ።

  5. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Set in Order Thy House፣” ሊያሆና፣ ጥር 2002 (እ.አ.አ)፣ 80።

  6. ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ።”

  7. ስኮት ኤል. ቡችናን፣ ‘’The Nuclear Family Is Indispensable,’’ የአደባባይ ንግግር፣ ሰኔ 4፣ 2020 (እ.አ.አ)thepublicdiscourse.com.

  8. ኤም ራሰል ባላርድ፣ ‘’The Sacred Responsibilities of Parenthood(የብሪግሃም ያንግ ዩኒቨርሲቲ መንፈሳዊ መርሃግብር፣ ነሐሴ 19፣ 2003 (እ.አ.አ)፣ 3 speeches.byu.edu; በተጨማሪ ኤንዛይን፣ መጋቢት 2006 (እ.አ.አ)፣ 28-29 ተመልከቱ።

  9. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “The Plan and the Proclamation፣’’ ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 30።

  10. ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ።”

  11. ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ።”

  12. ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ።”

  13. ራስል ኤ. ኔልሰን፣ “Celestial Marriage፣ሊያሆናህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 94።