የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ጥር 2017 (እ.አ.አ)
የሴቶች መረዳጃ ማህበር አላማ
በፀሎት ይህንን የማስተማሪያ ወረቀት አጥኑ እናም ምን ማካፈል እንዳለባችሁ ለማወቅ ምሬትን እሹ።
እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ
አጠቀላይ የሴቶች መረደጃ ፕሬዘደንት፣ ሊንዳ ኬ. በርተን እንዳሉት፣ የሴቶች መረደጃ ማህበር አላማ “ሴቶችን ለዘላለም ህይወት በረከቶች ማዘጋጀት ነው።”1 “በወሳኝ የስራው ድርሻችን ውስጥ” በእምነት፣ በቤተሰብ፣ እና በእርዳታ አማካኝነት ነው የምንሳተፈው።2
የሴቶች መረዳጃ ማህበር “የምድራዊ እና መንፈሳዊ ስራ ነው፣” ሲሉ በአጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ አመራር የመጀምሪ አማካሪ ካሮል ኤም. ስቲቨንስ ተናገሩ። “በክርስቶስ ዘመን ጊዜ ያንን ነው ሴቶቹ ሲያደርጉ የነበሩት፣ እናም እኛም ያንኑ በማድረግ ነው የምንቀጥለው።”3
የውሀ እንስራዋን ትታ ኢየሱስ ነቢይ እንደነበር ለሌሎች ሰዎች ለመንገር ስለ ሮጠችው ጉድጓድ ውሃ ጋር ስለነበረችው ሳምራዊት ሴት (ዮሀንስ 4፥6–42 ተመልከቱ)፣ ወይም በህይወቷ ሙሉ ሌሎች ሰዎችን በደስታ ስላገለገለችው ወደ ፌቤ ስንመለከት ( ሮሜ 16፥1–2 ተመልከቱ)፣ በአዳኝ ዘመን ወደ ክርስቶስ በመምጣት ንቁ የሆነ የተሳትፎ ድርሻ ስላደረጉ ሴቶች ምሳሌዎች እንመለከታለን። እርሱ ነው የዘላለማዊ ህይወት መንገዳችንን የሚከፍትልን ( ዮሀንስ 3፥16 ተመልከቱ)።
በ1842 (እ.አ.አ) በናቩ፣ ኢሊኖስ፣ በሳራ ኪምባል ቤት የራሳቸውን አወቃቀር ለማቋቋም ተሰባስበው ወደ ነበሩት መስራች እህቶቻችን ስንመለከት፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበርን ወደ መፈጠር እና ከክህነት ጋር አንድ ወደ መሆን እንዲመጣ ያደረገውን የእግዚአብሔርን እቅድ እንመለከታለን። ኤሊዛ አር. ስኖው መተዳደሪያ ደንብ ከፃፉ በኋላ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ገመገመው። ሴቶች እስካልተደራጁ ድረስ ቤተክርስቲያኗ ሙሉ ለሙሉ ተደራጅታ እንዳልነበረች ተገነዘበ። ጌታ ያቀረቡትን እንደተቀበለ ነገር ግን የተሻለ ነገር እንደነበር ተናገረ። እንዲህም አለ፣ “ሴቶችን በክህነት አሰራር መሰረት በክህነት ስር አደራጃቸዋለሁ”4
“የሴቶች መረዳጃ ማህበር ልክ በአለም ውስጥ መልካምን ለማድረግ እየሞከሩ እንዳሉ ቡድን ብቻ አልነበረም። የተለየ ነበር። ‘የተሻለ ነገር’ ነበር ምክንያቱም በክህነት ስልጣን ስር ተደራጅቶ ስለነበር። በምድር ላይ ያለን የእግዚአብሔርን ስራ በማሳወቅ ውስጥ አደረጃጀቱ ጠቃሚ ደረጃ ነበር።”5
ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍትና መረጃዎች፡፡
© 2017 Intellectual Reserve, Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/16 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/16 (እ.አ.አ)። Visiting Teaching Message. January 2017 (እ.አ.አ) ትርጉም። Amharic 97921 506
ይህንን አስቡ
የሴቶች መረዳጃ ማህበር የሰማይ አባት ለእነርሱ ያለውን መለኮታዊ ሚና ለማሟላት እና ወደ ዘላለም ህይወት ለመምራት ሴቶችን እንዴት መርዳት ይችላል?