ለወጣቶች ጥንካሬ
ፋሲካችን--ቅዱስ ቁርባን
ለወጣቶች ጥንካሬ መጋቢት 2026 (እ.አ.አ)


ወርኃዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልእክት፣ መጋቢት 2026 (እ.አ.አ)

ዘፀአት 12

ፋሲካችን--ቅዱስ ቁርባን

በጥንቱ ፋሲካ እና በሳምንታዊው ቅዱስ ቁርባናችን መካከል የጋራ የሆነ ትስስር አለ።

ወጣት ሴት

ምሥል በአሊሳ ታለንት

የጥንቶቹ እስራኤላውያን በግብጽ ከባርነት ከመውጣታቸው በፊት የሞት መልአክ ያተርፋቸው ወይም አልፏቸው ይሄድ ዘንድ ከጌታ የተሰጧቸውን ዝርዝር ትእዛዛት እንዲያከብሩ ተጠይቀው ነበር። ( ዘጸአት 12ተመልከቱ)። ግብጽንም ትተው ከሄዱ በኋላ እስራኤላውያን ጌታ የቃልኪዳን ህዝቡን እንዴት እንደታደገ እንዲያስታውሱ ፋሲካ የተባለውን በዓል በየዓመቱ ያከብሩ ነበር።

በምድራዊ አገልግሎቱ መጨረሻ ላይ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በፋሲካ በዓል ተገኝቶ ነበር። ያንንም ምግብ የጌታ እራት ብለን እንጠራዋለን። አዳኙም ያንን አጋጣሚ አሁን በየሳምንቱ የምንወስደውን ቅዱስ ቁርባንን ለማስተዋወቅ ተጠቅሞበታል። ( ማቴዎስ 26፥26-28ሉቃስ 22፥19-20ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77፣ 79ይመልከቱ)።

በጌታ አማካይነት ነጻ የወጣንበትን ለማስታወስ የሚረዱን በቀደመው ፋሲካ፣ በጌታ እራት፣ እና በዛሬው ቅዱስ ቁርባን መካከል ያሉት ሁለት የጋራ ትስስሮች እነዚህ ናቸው።

በፋሲካ ወቅት የነበረው መቃን
የጌታ እራት
የቅዱስ ቁርባን ዳቦ እና ውሃ

ዳቦው

ፋሲካ፤ ለሰባት ቀናት እስራኤላውያን እርሾ የሌለውን ዳቦ ይበላሉ (ይህም ለመስራት ፈጣን የሆነ እና ለሻጋታ እና ለመበላሸት በቀላሉ የማይጋለጥ ነው)።

የጌታ እራት ኢየሱስ ክርስቶስ እርሾ የሌሌውን የፋሲካ ዳቦ ባርኮ እና ቆርሶ ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው። በቅርቡ እንደሚቆረስ እና እንደሚሞት ነገር ግን ከሞትም እንደሚነሳ ያውቅ ስለነበር አካሉን ለማስታወስ እንዲበሉት ነገራቸው።

ቅዱስ ቁርባን፤ ዳቦውን የምንበላው የኢየሱስ ክርስቶስን አካል ለማስታወስ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ የህይወት ዳቦ ነው። በእርሱ ትንሳኤ ምክንያት፣ ከሞትን በኋላ ሁላችንም ፍጹም፣ የማይበሰብስ፣ ህያው የሆነ አካል ለብሰን እንነሳለን። እርሱ ከሞት ይታደገናል።

የበጉ ደም

ፋሲካ፤ የፋሲካው በግ እንከን አልባ፣ የአንድ ዓመት ጠቦት ነበር። ይገደል እና ደሙም በጎድጓዳ ሳህን ይቀመጥ ነበር። ሂሶጵ (ቅጠል) በደሙ ውስጥ ይነከር እና በቤቱ የውጪኛው የመቃኑ ክፍል ላይ ለመርጨት ጥቅም ላይ ይውል ነበር። ይህም የቃልኪዳኑ ህዝብ ከአጥፊው የሞት መልአክ ከግብጽ ባርነት ነጻ መውጣት ይችሉ ዘንድ ከጌታ ለመለያነት የተሰጠ ውጫዊ ምልክት ነው።

የጌታ እራት፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን እንዲወክል ወይንን ተጠቅሟል። ለደቀ መዛሙርቱም ለሃጢያት ስርየት እንደሚፈስ እና የአዲስ ኪዳን አካል እንዲሆን ድእሙን ለማስታወስ እንዲጠጡት ነገራቸው።

ቅዱስ ቁርባን፤ ውሃውን የምንጠጣው የኢየሱስ ክርስቶስን ደም ለማስታወስ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር በግ ነው። ለሃጢያታችን እና ለህመማችን በተሰቃየ ጊዜ ደሙ ፈሷል። ደሙ—የእርሱ መስዋእትነት—ያነጻናል። እርሱ ከሃጢያት ይታደገናል።