ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሰኔ 2025 (እ.አ.አ)
በእውነት ንሰሃ መግባቴን እና ይቅር መባሌን እንዴት ላውቅ እችላለሁ?
በተሟላ ክብ መምጣት፣ በጄነዲ ፔጅ
ጌታ እንዲህ ብሏል፦ “ለኃጢያቶቹ ንስሀ የሚገባም፣ ይቅርታን ይቀበላል፣ እናም እኔ ጌታ ደግሜ አላስታውሳቸውም።
“በዚህም ሰው ለኃጢአቶቹ ንስሀ እንደገባ ታውቃላችሁ—እነሆ፣ ይናዘዛቸዋል እናም ይተዋቸዋልም’’ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42–43)።
ልባዊ በሆነ ንሰሃ፣ ይቅርታን ልንቀበል እንችላለን። ‘’ከመንፈስ መጽናናትን ስታገኙ፣ የጌታ የሃጢያት ክፍያ ሃይል በህይወታችሁ እየሰራ እንደሆነ ታውቃላችሁ።’’ እና ዳግም ሲያዳልጠን፣ እንደገና ንሰሃ ልንገባ እንችላለን፣ እና በሙከራው እንቀጥላለን።
በተጨማሪም፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል የሆኑት ሽማግሌ ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዳስተማሩት፦ ‘’ሰይጣን ሃጢያቶቻችን ይቅር እንዳልተባሉ አድርገን እንድናምን ይጥራል ምክንያቱም እኛ ልናስታውሳቸው ስለምንችል። ሰይጣን ሃሰተኛ ነው። … እግዚአብሔር እኛ ሃጢያታችንን እንደማናስታውስ ቃል አልገባልንም። ማስታወሱ ተመሳሳይ ጥፋቶችን ዳግም መስራትን እንድናስወግድ ይረዳናል። ነገር ግን እኛ እውነተኛ እና ታማኞች ሆነን ብንቆይ፣ የሃጢያታችን ትውስታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደበዘዘ ይሄዳል።
© 2025 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፤ 6/19። Monthly For the Strength of Youth Message, June 2025 ትርጉም። Amharic. 19629 506